Get Mystery Box with random crypto!

Christ and Him Crucified

የቴሌግራም ቻናል አርማ christisallsufficient — Christ and Him Crucified C
የቴሌግራም ቻናል አርማ christisallsufficient — Christ and Him Crucified
የሰርጥ አድራሻ: @christisallsufficient
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.44K
የሰርጥ መግለጫ

This channel is created to talk about nothing except Christ & Him Crucified.
We talk things in a reformed way.
Any comment & suggestion, please click on the link below.
👇👇👇👇👇👇
@reformed_1517

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-02 07:46:13 እንደ ክርስቲያን አንዳንድ መጠንቀቅና ማስተዋል ያለብን ነገሮች...

እኔን ለረጅም ዘመን ከቆጠርኩት ፊደልና ትምህርት ይልቅ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ እግዚአብሔርን ማወቄ ብዙ አስተውሎትን እና ጥበብን እንድጎናጸፍ አድርጎኛል። በዚህ ምድር ከየትኛውም ነገር በቀዳሚነት ለደስታችን ምክንያት ሊሆን የሚገባው እግዚአብሔርን ማወቃችን ነው። ሌላው ሁሉ ኮተት ነው። ዛሬ ዛሬ ሰዎች ከእግዚአብሔር ይልቅ በእግዚአብሔር "by product" በሆኑ ነገሮች ይደሰታሉ።

ለጊዜው በአጸደ ሥጋ የምንኖር እኛ ከዚህ ሟች ሥጋችን እስከምንለይ ድረስ እንደማንኛውም የሰው ልጅ ኑሯቸን እዚሁ ምድር ነው ሚሆነው። ሰርቶ ማደግና መለወጥ፤ አግብቶ መውለድ፤ ታሞ መታከም ድኖም ማመስገን ለሁሉም የሰው ልጅ የተተወ ጉዳይ ነው። እግዚአብሔርን ስላወቅን በምድር ላይ እግዚአብሔር ከሌሎች ሰዎች በተሻለ የገባልን ተስፋ የለም። በአዲስ ኪዳን የምንመለከታቸው ተስፋዎች በሙሉ መንፈሳዊ ናቸው ብል የተሳሳትኩ አይመስለኝም።

አማኝ ሥራ ቢያጣ፤ ፈተና ቢበዛበት፤ ታሞ ቢቸገር ምን መሆን አለበት?

እንግዲህ በሕይወት ዘመናችን የሚገጥሙን መልካም ነገሮች ሁሉ ከእግዚአብሔር ዘንድ ናቸው። እግዚአብሔር የተሻለ ሥራ(እንጀራ) ይሰጠኛል ብሎ ማመን አንድ ነገር ነው። ይኽ ማለት ደ'ሞ እጃችን ከሥራ ለጉመን አጣጥፈን እንድንቀመጥ ልያደርገን አይገባም። ኃጢአት የሌለበትን የትኛውንም ዓይነት ሥራ እየሰራን የእግዚአብሔርን ጊዜ መጠበቅ ብልጠት ነው። ይኽ በእግዚአብሔር አለማመን ማለት አይደለም። እግዚአብሔር ያልለፋንበትን እንጀራ አይሰጥምና።

ሌላው አማኝ እንደ ማንኛውም ሰው ይታመማል። ካልታከመ ይሞታል። ለበሽታ(ለሕመም) ሁሉም ሰው እኩል ነው። ነጭ ሆንክ ጥቁር፤ አማኝ ሆንክ ኢአማኒ፤ ሕጻን ሆንክ አዋቂ...። አማኝ ሲታመም ከሁሉ በላይ በእግዚአብሔር መታመን አለበት። ምድር ላይ ሊወስደው ካለው ከየትኛውም ሜዲከሼን በላይ እምነቱ በአምላኩ ላይ መሆን አለበት። እግዚአብሔር ይፈውሰኛል ብሎ ማመን አንድና ትልቁ ነገር ነው። መታከመም ሌላ ጉዳይ ነው። በእግዚአብሔር መታመናችን ወደ ሕክምና ተቋም ከመሄድ ሊያግደን አይገባም። ጸልዮ ቶሎ ሄዶ ሕክምና መውሰድ ብልጠት ነው። በርግጥ "ክርስቲያን አይታመምም" ብሎ ሚያምን መጋቢ ባለበት ዘመን እንዲህ ማለት ሊያሰድብ ሁላ ይችላል። መጋቢዎች ለራሳቸው ለተለያዩ chronic ሕመሞች ሕክምና እየወሰዱ ምዕምናን ያሰንፋሉ። በርግጥ ይጠየቁበታል።

ለለውጥ መትጋት፣ ጤንነትን ለመጠበቅ መወትወት፣ ነገን የተሻለ ለማድረግ መሯሯጥ በእግዚአብሔር አለማመን ማለት አይደለም። ይልቅ በእግዚአብሔር መታመን ማለት ነው። እግዚአብሔር ማስተዋሉን ያድለን!!

ይበቃናል...!

Join us
@Christisallsufficient
35 viewsFantahun Beyene, 04:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 13:58:28 "...ሔዋን የእግዚአብሔርን ክብር ለማንፀባረቅ ብቻ ሳይሆን፣ ክብሩን ሙሉ በሙሉ ለራሷ ፈለገች። ይህም ዛሬ ዋናው የሰዎች ኀጢአት ነው፤ ሰው ለራሱ ክብር እንጂ ለእግዚአብሔር ክብር መኖር አይፈልግምና። እግዚአብሔር እስኪያድነው ድረስ ሰው እግዚአብሔርን ማክበር የማይፈልግና የማይችል ኀጢአተኛ ነው።"
~ቄስ ኮሊን ማንሰል

Join us
@Christisallsufficient
100 viewsAbenezer Mesfin, edited  10:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 21:59:12 አንድ ቀን የሠላም አለቃ ጌታ ኢየሱስ ለሰሜኑ የአገራችን ክፍል (አማራ | ትግራይ) ሠላምን ይመልሳል። እኔ በግሌ በጥሞና ጊዜዬ ይኽን አከባቢ በጸሎት አስባለሁ። እግዚአብሔር ሠላም ይስጠን። ለመሪዎችም ማስተዋል ይብዛላቸው።

Join us
@Christisallsufficient
141 viewsFantahun Beyene, 18:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 08:34:04 “እግዚአብሔርን ከማያስከብር ከንቱ ልፍለፋ ራቅ፤ በዚህ ነገር የተጠመዱ ሰዎች ከእግዚአብሔር እየራቁ ይሄዳሉና።”
— 2ኛ ጢሞቴዎስ 2፥16

Join us
@Christisallsufficient
58 viewsAbenezer Mesfin, 05:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 10:38:30 ካህኑ እያሱ ቢቆሽሽም ልብሱ
ቢጠፋው ውበቱ ቢደክም ጉልበቱ
አምላኩ አልተወውም አልቆበት ምህረቱ
.
.
.
የእግዚአብሔር ምሕረት


Join us
@Christisallsufficient
127 viewsFantahun Beyene, 07:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 10:22:46 A flood of false doctrine has lately broken in upon us. Men are beginning to tell us “that God is too merciful to punish souls for ever…that all mankind, however wicked and ungodly…will sooner or later be saved.” We are to embrace what is called “kinder theology,” and treat hell as a pagan fable… This question lies at the very foundation of the whole Gospel. The moral attributes of God, His justice, His holiness, His purity, are all involved in it. The Scripture has spoken plainly and fully on the subject of hell… If words mean anything, there is such a place as hell. If texts are to be interpreted fairly, there are those who will be cast into it… The same Bible which teaches that God in mercy and compassion sent Christ to die for sinners, does also teach that God hates sin, and must from His very nature punish all who cleave to sin or refuse the salvation He has provided.
– Source: J.C. Ryle (1816-1900), Holiness

Join us
@Christisallsufficient
127 viewsAbenezer Mesfin, 07:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 14:10:28 Philosophy-Psychiatry-Psycho-Babbles... Jesus Is Better Than All These

Philosophy and Vain Deceit:

“Beware lest any man spoil you through philosophy and vain deceit, after the tradition of men, after the rudiments of the world, and not after Christ.” (Colossians 2:8)
It is bound to be significant that, in the only place where the Scriptures even mention philosophy, we are warned to beware of it! Likewise, the only philosophers mentioned were evolutionary humanists who called the apostle Paul a “babbler . . . because he preached unto them Jesus, and the resurrection” (Acts 17:18).
The word “philosophy” literally means “love of wisdom,” and every philosophy—ancient or modern—is essentially a humanistic devotion to man’s wisdom for its own sake.
But such wisdom is false wisdom. It derives in type from “the tree of knowledge,” through the “vain deceit” of Satan, who tries to persuade us that partaking of it would “make one wise” and that “your eyes shall be opened, and ye shall be as gods” (Genesis 2:17; 3:5-6). It has “indeed a shew of wisdom” (Colossians 2:23), but “the wisdom of this world is foolishness with God” (1 Corinthians 3:19), and eventually all “the wisdom of this world, . . . [and] of the princes of this world, . . . [will] come to nought” (1 Corinthians 2:6).
Genuine wisdom, on the other hand, is as this study reminds us, “after Christ. For in him dwelleth all the fullness of the Godhead bodily. And ye are complete in him, which is the head of all principality and power” (Colossians 2:8-10). For in Him “are hid [literally ‘stored up’] all the treasures of wisdom and knowledge” (Colossians 2:3).
The Lord Jesus Christ is “the truth” (John 14:6), and is both “the power of God, and the wisdom of God” (1 Corinthians 1:24). This true wisdom is freely available to all who desire it. “If any of you lack wisdom, let him ask of God . . . and it shall be given him” (James 1:5).
Therefore, we need never waste our God-given time on human philosophy.
Turn to God and His word.
He is the Great I AM !
God Bless.

Join us
@Christisallsufficient
163 viewsAbenezer Mesfin, 11:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 10:01:46 ጨለማዬን በብርሃኑ አብርቷል። የኃጢአት ቀንበርን ከላዬ ላይ አራግፎታል። የማይገባኝም ጽድቅና ቅድስና አልብሶኛል። ሕይወቱን ሰ'ቶ ለዘለዓለም በቤቱ እንደኖር ወዷ'ል። እኔም ጌታዬን አዳኜን እወደዋለሁ!!

#Join us
@Christisallsufficient
152 viewsFantahun Beyene, 07:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 07:32:35 "ያቆስላል
እጆቹም ይፈውሳሉ" (ኢዮ.5፥18)
መጽሐፍ ቅዱስ በኢዮብ ሕይወት የሚያስተምረን አንዱ ነገር ሰዎች በጽድቅና በቅድስና እየኖሩ መከራ ሊገጥማቸው እንደሚችል ነው፡፡ በዚህ ረገድ የኢዮብ አጽናኞች ስሕተት ነበሩ፡፡
መቼም ኢዮብ ባለፈበት መጠን ባይሆንም በብዙ ስቃይና ፈተና የሚያልፉ ክርስቲያኖች ሞልተዋል፡፡ ለመሆኑ የምናልፍባቸውን ኣንዳንድ ኣስቸጋሪ ክስተቶች “ይህ ነገር የእግዚአብሔር እጅ ይኖርበት ይሆንን?” ብለን የምናስብ ስንቶቻችን እንሆን?
ብዙዎቻችን ችግሮች ሲገጥሙን በክስተቱ ውስጥ የእግዚአብሔር ፈቃድ ይኖራል ብለን ኣናስብም፤ እንዳውም ሌሎች ትንተናዎችን ማድረግን እንመርጣለን፡፡ ብዙ ጊዜ ዕይታችን የተንሽዋረረ ስለሚሆን፣ በመከራ የሚያልፉት ወገኖችን ከመፈረጅ ወደ ኋላ ኣንልም፡፡ አንዳንዶቻችንም በችግር የሚያልፉ ሰዎች ካሉበት ሁኔታ ፈጥነው የሚወጡበትን የትኛውንም አቋራጭ ለማሳየት ወደ ኋላ የምንል አይመስለኝም፡፡ ብዙ ጊዜ ሰዎች ከፍታ ስኬትና ድል ሲገጥማቸው ብቻ ነው "እግዚአብሔር ከእዚህ ሰው ጋር ነው ብለን" በሙሉ ልብ የምንናገረው የምንቀበለውም፡፡ ስለ ሁኔታውም ፈጥነን በኣደባባይ እንመሰክርም ይሆናል!
ኢዮብ ግን መንፈሳዊ ዓይኑ የተከፈተለት ሰው ስለ ነበር የእግዚአብሔር አጅ በመንገዱ ላይ እንዳለ ገብቶት ነበር፡፡ ምዕራፍ 19 እንዲህ ይላልና፡-
•“እንግዲህ እግዚአብሔር እንደ ገለበጠኝ፥ በመረቡም እንደ ከበበኝ እወቁ።” (ቁ.6)፤
•“እንዳላልፍ መንገዴን ዘግቶታል፥ በጎዳናዬም ጨለማ አኑሮበታል።” (ቁ.፤
•“እናንተ ወዳጆቼ ሆይ፥ ማሩኝ፤ የእግዚአብሔር እጅ መትታኛለችና ማሩኝ።” (ቁ.21)፡፡
ኢዮብ ጥቂት ምዕራፎች አልፍ ብሎ “የምሄድበትን መንገድ ያውቃል፤ ከፈተነኝም በኋላ እንደ ወርቅ እወጣለሁ። እግሬ ወደ እርምጃው ተጣብቆአል፤ መንገዱንም ጠብቄአለሁ፥ ፈቀቅም አላልሁም። ከከንፈሩ ትእዛዝ አልተመለስሁም፤ የአፉን ቃል በልቤ ሰውሬአለሁ። እርሱ ግን ብቻውን ነው፤ እርሱንስ የሚመስለው ማን ነው? ነፍሱም የወደደችውን ያደርጋል። በእኔ ላይ የተወሰነውን ይፈጽማል፤ እንደዚህም ያለ ብዙ ነገር በእርሱ ዘንድ አለ።” (ኢዮ.23፥10-14) በማለት በሚያልፍበት ሁኔታ ላይ ያለውን ኣተያይና አቋም በቅንነት ተናግሯል፡፡ እምነቱ እንደ ወርቅ እየተፈተነ እንደ ሆነም ኣስረድቷል! ጌታ ሆይ እንዲህ ዓይነቱን ማስተዋል ስጠን!
“ቅጣት ሁሉ ለጊዜው የሚያሳዝን እንጂ ደስ የሚያሰኝ አይመስልም፥ ዳሩ ግን በኋላ ለለመዱት የሰላምን ፍሬ እርሱም ጽድቅን ያፈራላቸዋል።” (ዕብ.12፥11)
ጌታ ሆይ እንደ ኢዮብ ዓይኖቻችን ክፈትልን!
መልካም ቀን ተባረኩልኝ!

Bekele Berhanu

Join us
@Christisallsufficient
189 viewsAbenezer Mesfin, 04:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 11:49:47 And the more bold the reprobate are to oppress the truth, the more courage ought we to take to ourselves. For the servants of God must be armed with invincible constancy of the Spirit, that they may never give place to the devil, nor to his ministers; as the Lord commandeth Jeremiah to encounter the reprobate with a face of iron.

John Calvin

Join us
@Christisallsufficient
65 viewsAbenezer Mesfin, edited  08:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ