Get Mystery Box with random crypto!

Hussein Ali (Durus & Fewa'id)

የቴሌግራም ቻናል አርማ husseinali210 — Hussein Ali (Durus & Fewa'id) H
የቴሌግራም ቻናል አርማ husseinali210 — Hussein Ali (Durus & Fewa'id)
የሰርጥ አድራሻ: @husseinali210
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.16K
የሰርጥ መግለጫ

ሑሴን ዐሊ (ደርሶችና መልእክቶች)

Ratings & Reviews

1.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 12:00:03 የዛሬ  ሀሙሰረሶፈር 5/1444 የ القواعد المثلى ደርስ
ደርስ ቁጥር= 036
የእለቱ ደርስ=   የተእዊል ባለቤቶች በሚያነሷቸው ሹብሃዎች (ማምታቻዎች) ምላሽ መስጠትን በተመለከተ  ሰባተኛ ደርስ
Hussein Ali (Durus & Fewa'd)
https://t.me/husseinali210
277 viewsedited  09:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 06:24:02 ጥቂት ነጥቦች ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ
~
1. ወገኔ ሆይ! አገርህን አትልቀቅ።

ባለፈው ተፈናቃዮች ላይ የደረሰውን አስታውስ። ደብረ ብርሃንና ባህርዳር ለተፈናቃዮች ከማጎሪያ ካምፕ የማይለዩ እንደነበሩ ሲወራ ነበር። አሁን ደግሞ ነገሮች ከቀድሞው ቢብሱ እንጂ የተሻሉ አይደሉም። ፖለቲከኛውን ተወው። ህዝብ እራሱ ኑሮ ስለከበደው ሊጨካከን፣ ሊሰላች ይችላል። ሩቅ አትሂድ። ደሴ ወልዲያን፣ ወልዲያ ቆቦን ሊሰለች ይችላል። የጎደለበት ደግሞ በትንሽ በትልቁ ይከፋዋል። ስለዚህ በተለየ እፈለጋለሁ ብሎ የሚሰጋ ካልሆነ በስተቀር ጦርነቱ ቀጥታ ከሚካሄድባቸው ቀጠናዎች ለጊዜው ዞር ከማለት ውጭ ካገር ርቆ መሄድ ስቃዩን የከፋ ያደርገዋል።

2. ወገኔ ሆይ! ንብረትህን ጠብቅ።

ሩቅ ብቻ አትመልከት። እዚያው በዙሪያህ ለዘረፋ ተደራጅተው ከግለሰብ ንብረት እስከ ተቋም ሲዘርፉ የነበሩ እንደነበሩ ይታወቃል። ዛሬም ይኖራሉ። ፍሪጅና ቴሌቪዥን ሳይቀር በግመል እየጫኑ የወሰዱ የገጠር ሰዎች እንዳሉ ሰምቻለሁ። “መብራት የላችሁ ምን ያደርግላችኋል?” ሲባሉ “እንሸጠዋለን” ሲሉ ነበር። ስለዚህ ቅድሚያ ለህይወት ጥንቃቄ ካደረግክ በኋላ በቅርብህ ሆነህ በተቻለህ መጠን ንብረትህን ተደራጅተህ ጠብቅ።

3. ወገኔ ሆይ! ለፈተና እራስህን አዘጋጅ!

ወደድንም ጠላንም ፈተና ላይ ነው ያለነው። መጠኑ ከህዝብ ህዝብ በእጅጉ እንደሚለያይ ግልፅ ነው። ፈተናው ምን ያህል እንደሚዘልቅም አናውቅም። የሆነች ያክል የምንዘጋጅባት ሰበብ ካለችን ባለችን መጠን ለሚመጣው ሁሉ ራሳችንን እናዘጋጅ። ምግቡ፣ ወፍጮው፣ ባንኩ፣ መብራቱ፣ ቴሌው፣ መድሃኒቱ፣ ... ብዙ ነገር ይቸግራል። እስካሁንም ብዙ የተፈተነ አለ። ልዩነቱ ብዙ ባይሆን እንኳ የተዘጋጁበትና የተዘናጉበት ፈተና አንድ አይደለም። አላህ ለሁሉም ፈረጃውን ያቅርብልን።

4. ወገኔ ሆይ! ጊዜ አይተህ አትለወጥ!

ለሚያልፍ ቀን ትዝብት ላይ አትውደቅ። የትኛውም ቡድን አጠቃኝ በሚል ማመሃኛ ማንንም ብሄር ለይተህ እንዳታጠቃ። የአማራ ህዝብ ሆይ! ህወሓትን መነሻ አድርገህ ለፍቶ አዳሪ ትግሬን አታጥቃ። “ያው ናቸው” ከሚል ስሜት ወለድ ሂሳብ ራቅ። “ህወኃት እከሌን አካባቢ የተቆጣጠረው ተፈናቃይ ትግሬዎችን ተጠቅሞ ነው” እየተባለ የሚናፈሰው ብታምንም ባታምንም ከንቱ ውሸት ነው። እንዲህ አይነት አሉባልታ ይዘህ ደካሞችን እንዳትጎዳ።
ትግሬው ሆይ! ህወኃት ሲገባ ጠብቀህ አደባባይ ለጭፈራ አትውጣ። ጠቋሚ፣ አፋኝ፣ አሳፋኝ ለመሆን አትሞክር። ሃይማኖት ወይም ሞራል እንኳ ባይገታህ ቢያንስ ለራስህ ፍራ! ነገሮች የተቀያየሩ እለት መግቢያ ታጣለህ። በባለፈው ግጭት አማራውም፣ ትግሬውም፣ ኦሮሞውም፣ አፋሩም ዘንድ ብዙ ደስ የማይሉ ነገሮች ሲወሩ ነበርና አላህን ልንፈራ ይገባል።

5. ወገኔ ሆይ! ለመጣ ለሄደው አታጨብጭብ።

አንድ ኃይል አንድን አካባቢ ሲቆጣጠር ሆ ብሎ መውጣት፤ ሌላው በግሩ ሲተካ አሁንም ሆ ብሎ መነሳት ይሄ ግልብነት ነው። የሃገራችን ፖለቲካ ቂመኛና ተበቃይ ነው። እንኳን የገባበትን፣ የሌለበትንም ጊዜ ተጠግቶ ያጠቃል። ደግሞም በጣም ተገለባባጭ ነው። እዚች አገር ውስጥ ስንት አይሆንም የተባለ ነገር ሆኗል! መንግስት ትግራይን ሲቆጣጠር ህወኃት ዳግም ያንሰራራል ብሎ የገመተ አልነበረም። ህወኃት ሰሜን ሸዋ ከደረሰ በኋላ በዚያ አሰቃቂ ሁኔታ ይመለሳል ብሎ የገመተም አልነበረም። ስለሆነም ጥንቁቅ መሆን ያስፈልጋል። በሁለቱም አይንህ ዛሬ ላይ ብቻ አታፍጥጥ። በአንድ አይንህ ነገን ተመልከት።

6. ወገኔ ሆይ! ህይወት አትርፍ።

አጋጣሚዎችን ተጠቅመው የሚጠሉትን ለማጥቃት የማያመነቱ እርኩስ ፍጡሮች ይኖራሉና ቢቻልህ ያለ ጥፋታቸው የበደለኞች ሰለባ ሊሆኑ የሚችሉ ወገኖችን አትርፍ። ከጎናቸው ቁም። በባለፈው ግጭት ህወኃት ሲገባ ጠብቀው ደካሞችን ያጠቁ ሰዎች አሉ። ከነሱ አንፃር ሲታይ ህወኃት በጣም የተሻለ ነበር። መረጃ ያለው ሰው የምለው ይገባዋል። ህወኃት ከወጣ በኋላም እንዲሁ ከየትኛውም ኃይል ጋር ምንም አይነት ንክኪ የሌላቸው ምስኪኖች ተጎድተዋል። ከተቻለን ጊዜ አይተው ከሚያጠቁ ነውረኞች አንድ ነፍስ እንኳ ብናተርፍ ዋጋው የትና የት ነው!! በቅርቡ ኦሮሚያ ውስጥ በነበረውን ግጭት የራሳቸውን ህይወት አደጋ ላይ ጥለው አማራዎችን ያተረፉ ስንት ኦሮሞዎች አሉ። ግን አላወራንላቸውም። አማራ ውስጥ የራሳቸውን ህይወት አደጋ ላይ ጥለው ትግሬዎችን ያተረፉ ስንት አማራዎች አሉ። ግን አላወራንላቸውም። የራሳቸውን ህይወት አደጋ ላይ ጥለው አማራዎችን ያተረፉ ስንት ትግሬዎች አሉ። ግን አላወራንላቸውም። ሰው ማለት፣ ሰው የሚሆን ነው ሰው የጠፋለት!

7. ወገኔ ሆይ! ወቅታዊ ግጭቶችንና ተያያዥ ጉዳዮችን ከሃይማኖት ጋር እንዳታጠላልፍ።

የየትኛውም ቡድን ደጋፊ ልትሆን ትችላለህ። የኔ የምትለው ወገን ከሌሎች በተለየ እንደተገፋ ሊሰማህ ይችላል። ግን እወቅ! ሌሎችም መሰል ህመም አላቸው። ቢቻል በፖለቲካውም ሞራል ግብረ ገብነት ቢኖርህ እሰየው። ያለበለዚያ ግን የሃይማኖት ተቋማትም፣ አስተማሪዎች እና የደዕዋ መድረኮችም አንተ በምትፈልገው መልክና መጠን እንዲያወሩ፣ የፖለቲካ ፍጭቶች ማራገፊያ እንዲሆኑ አትፈልግ። ማህበራዊ ሚዲያዎችም ላይ ሆነ መሬት ላይ እየተከተልክ በአክቲቪስት ቋንቋ እንዲያወሩ አጉል አትወትውት። ልትረዳ ቢያቅትህ ቢያንስ አደብ ይኑርህ። ከፖለቲከኛ ጋር የለመድከውን እሰጥ አገባ በየደረስክበት አትድፋ።

8. የሃይማኖት አስተማሪ ሆይ! ከመንጋው ተለይ!

ብሄርህን ተከትለህ ቅስቀሳ ውስጥ አትግባ። ሌላው አካል ለጦር ቢቀሰቅስ አንድ ሁለት ነገር ተመልክቶ ነው። አንተ ተጨማሪ አርቀህ የምትመለከትበት አላህን መፍራቱ ሊኖርህ ይገባል። ያለበለዚያ በምንህ ነው ከሌሎች የምትለየው? ኢን ሻአላህ ነገ ሰላም ይመጣል። እሱን ታሳቢ አድርግ። መንጋው ሊያግባባህ፣ ሊገፋፋህ፣ አልሆን ሲለው ሊያወግዝህ ይችላል። የፈለገውን ይበል እሱ በቀደደው አትፍሰስ። የሃይማኖት አስተማሪ ሆነው በቀጥታ የግጭት ተሳታፊ፣ ወይም ቀስቃሽ፣ ወይም ደጋፊ፣ ወይም የዘር ጥላቻ ጠማቂ የሆኑ መርዘኛ ሰባኪዎች ሁሉም ብሄር ጋር አሉ። እነዚህ አካላት ነገ ችግሩ ቢያልፍ እንኳ የማያልፍ ጠባሳ እየጣሉ ነው። ጦሳቸውም ከራሳቸው አልፎ ለህዝብ ይተርፋል። ከሃይማኖትህ ተማር። እስካሁን ካለፈው ተማር። ከሌሎች ድክመት ተማር። የትኛውንም ውሳኔ ብትመርጥ ከትችት ላታመልጥ ነገር የሰው ስሜት ተከትለህ እንዳትወስን። አላህን አስብ።
በመጨረሻም አደራ የምለው እንተዛዘን፣ እንተሳሰብ፣ ዱዓእ እናድርግ፣ ወደ ጌታችን እንመለስ። አላህ ከገባንበት መከራ አውጥቶ የሰላም አየር የምንተነፍስ ያድርገን። ኣሚን።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
185 views03:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 10:12:05 የዛሬ ማክሰኞ ሶፈር 3/1444 የ القواعد المثلى ደርስ
ደርስ ቁጥር= 035
የእለቱ ደርስ=   የተእዊል ባለቤቶች በሚያነሷቸው ሹብሃዎች (ማምታቻዎች) ምላሽ መስጠትን በተመለከተ  ስድስተኛ ደርስ
Hussein Ali (Durus & Fewa'd)
https://t.me/husseinali210
300 viewsedited  07:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 13:20:28 የዛሬ እሁድ ሶፈር 1/1444 የ القواعد المثلى ደርስ
ደርስ ቁጥር= 034
የእለቱ ደርስ=   የተእዊል ባለቤቶች በሚያነሷቸው ሹብሃዎች (ማምታቻዎች) ምላሽ መስጠትን በተመለከተ አምስተኛ ደርስ
Hussein Ali (Durus & Fewa'd)
https://t.me/husseinali210
519 viewsedited  10:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 09:29:00 የዛሬ ሀሙስ ሙሃረም 27/1444 የ القواعد المثلى ደርስ
ደርስ ቁጥር= 033
የእለቱ ደርስ= የተእዊል ባለቤቶች በሚያነሷቸው ሹብሃዎች (ማምታቻዎች) ምላሽ መስጠትን በተመለከተ አራተኛ ደርስ
Hussein Ali (Durus & Fewa'd)
https://t.me/husseinali210
863 viewsedited  06:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 10:43:20 የዛሬ ማክሰኞ ሙሃረም 25/1444 የ القواعد المثلى ደርስ
ደርስ ቁጥር= 032
የእለቱ ደርስ= የተእዊል ባለቤቶች በሚያነሷቸው ሹብሃዎች (ማምታቻዎች) ምላሽ መስጠትን በተመለከተ ሶስተኛ ደርስ
Hussein Ali (Durus & Fewa'd)
https://t.me/husseinali210
937 viewsedited  07:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 09:05:47 የዛሬ እሁድ ሙሃረም 23/1444 የ القواعد المثلى ደርስ
ደርስ ቁጥር= 031
የእለቱ ደርስ= የተእዊል ባለቤቶች በሚያነሷቸው ሹብሃዎች (ማምታቻዎች) ምላሽ መስጠትን በተመለከተ ሁለተኛ ደርስ
Hussein Ali (Durus & Fewa'd)
https://t.me/husseinali210
1.0K viewsedited  06:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 20:48:52 የሙስሊም ወንድሙ ጭንቀት ለሚያሳስበው ሁሉ የእርዳታ ጥሪ

አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ

ውድ ሙስሊም ወንድምና እህቶች እነሆ "በዚህች ምድር የወንድሙን ጭንቀት ያስወገደ አላህ በመጪው አለም/በአኺራ/ የሱን ጭንቀት ያስወግድለታል" ሲሉ አዛኙ ነብይ ﷺ ነግረውናል ።

የሱና ወንድማችን አብዱ ሰይድ ይባላል። በልጅነቱ በሆነ አጋጣሚ በተፈጠረ አደጋ አንድ አይኑን አጥቶ ሲኖር የነበረና በችግርና በመከራ ውስጥም ቢሆን አግብቶ ሁለት ልጆችን ወልዷል።አላህ አግርቶሎት በቀረችው በአንድ አይኑ #ቁረአንም_ሀፍዟል እስካሁን በቆየበትም ጊዜ ለሱና ባለው ጉጉትና ፍላጎት የተነሳ ከቤተሰቦቹ ተገሎና ርቆ ምንም እገዛ እንኳን የማያደርጉለትና ዘወር ብለው የማያዩት ሲሆን ስራም ትንሽም ቢሆን የቀን ስራ እየሰራ ቤተሰቦችን ያስተዳድር ነበር ። አሁን ግን መስጊድ ቁጭ ብሎ ቁረአን ሲቀራ ነው የሚውለው ።

ሆኖም አሁን ደግሞ የአሏህ ውሳኔ ሆነና በሚኖርበት ግቢ በተፈጠረ የእሳት አደጋ ምክንያት እሳቱን ለመከላከል ጥረት በሚያደርግበት ወቅት የኤሌክትሪክ መብራት ይዞት ጭንቅላቱን ክፉኛ የተመታ ሲሆን ይህ አደጋም የቀረችው አንድኛው አይኑ ላይም ተፅእኖ በመፍጠሩ ከፍተኛ ህመም ሲፈጥርበት ዶክተሮችም በፍጥነት አድስ አበባ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በመሄድ ህክምና ካልወሰድክ የአይንህ ነርቭ በመነካቱ ሁለተኛውንም አይንህን ልታጣው ትችላለህ ብለውታል።

ስለዚህ ይህ የሱና ወንድማችን የቀረችውን አንድ አይኑን ለማትረፍ ህክምናውን ለመጀመር በትንሹ 70,000ሺ ብር( ሰባ ሺ ብር) እንደሚያስፈልገው በዶክተሮች ተነግሮታል ።ይሄንን ብር ደግሞ አይደለም በአንድ ጊዜ በአንድ አመትም ማገኘት ስለማይችል የኛ የወንድምና የእህቶቹ እገዛና እርዳታ ያስፈልገዋል

ያ አሏህ... ተመልኩቱ አንዷንም የተረፈችዋንም አይኑን ሊያጣት ነው ሲደመር ችግር ፣ ድህነት ፣ ልጆች ማሳደግ ፣ ስራ ማጣት ፣ ከቤተሰብ መገለል እያሰቃየው ነው።

እኛ ደግሞ ሁለቱም አይኖች አሉን። #አልሀምዱሊላህ ፣ አሏህም በቁረአኑ እንዲህ ብሎናል (أَلَمْ نَجْعَل لَّهُۥ عَيْنَيْنِ) "ለእርሱ(ለሰው ልጅ) ሁለት አይኖችን አላደረግንለትምን?"( ሱረቱል በለድ ፣ 8) ይላል። ታዲያ አሏህ እንዲህ አይነት ፀጋ ሲውልልን ምስጋናችን ከምንገልፅባቸው መንገዶች መካከል አንዱ እንዲህ በአይናቸው የተፈተኑ ሰዎችን በማገዝና በመርዳት አሏህ የኛንም አይኖች እንዲጠብቅልን ዱዓ በማድረግ ነው።

ውድ ኸይር ፈላጊ ወንድምና እህቶች ፣ ለዚህ ለተጨነቀ ወንድማችን ትንሽ ትልቅ ሳንል የህክምና ወጪውን በመሸፈን ካለበት ጭንቀት ወጥቶ ለቤተሰቡም ለድኑም የሚያገለግል ወንድማችን እንዲሆን የአቅማቹህን እንድታበረክቱ ስንል ለሁሉም ኸይር ፈላጊ ወንድምና እህቶች የእርዳታ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

በገንዘብ መርዳት ባትችሉ share በማድረግ ተባበሩት።

ወንድማችንን ለመርዳት የተቋቋመ የባንክ አካውንት ቁጥር :- የኢትዮ ንግድ ባንክ
#1000034096008
#የአካውንቱ ስም :- አብዱ ሰይድ መሀመድ

ለበለጠ መረጃ የወንድማችን ስልክ
ስልክ: #0914324157

"በዚህች ምድር የወንድሙን ጭንቀት ያስወገደ አላህ በመጪው አለም/በአኺራ/ የሱን ጭንቀት ያስወግድለታል" ሲሉ አዛኙ ነብይ ﷺ ነግረውናል ።

ይሄንን ፅሁፍ ያነበባችሁ ሁሉ በአላህ ስም እጠይቃችኋለሁ በተለያዩ ቻናሎች ግሩፖች ሸር እንዲታደርጉልን ።
2.0K views17:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 20:48:31
774 views17:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 12:16:03 በወንድማችን
ኡስታዝ አብዱሰላም ሀሰን (አቡ ዓብዲላህ)
እና
ሁሴን ዓሊ ( አቡ አመቲረህማን)

" ኪታብ አዱሩሱል-ሙሂማህ ሊዓመቲል
ኡማህ"
የታላቁ ዓሊም ኢብኑ ባዝ
ኪታብ

ከ ሙሃረም 21_1444 ዓመተ ሂጅራ

(ከነሀሴ 13-2014E.C)


እለተ ጁሙዓ ጀምሮ
10:00 ሰአት ከአስር ሶላት ቡሃላ


በዓፋር ክልል አዋሽ 7 ኪሎ ከተማ
በአቢ-አዩበል አንሷሪ መስጅድ

ጀምሮ ለተከታታይ ቀናት መሰጠት በሚጀምረው ኮርሥ ላይ ማንኛውም ወንድም ሆነ ሴት ሙስሊም እንድትሳተፉ የተጋበዛችሁ እና ለኮርሱ የተዘጋጀውን ኪታብ እዛው ደውራ ቦታ ላይ የሚገኝ ሲሆን ደውራው ላይ ብንገኝ በአላህ ፈቃድ ተጠቃሚ እንሆናለን።
https://t.me/awash7kilosalafis
2.6K viewsedited  09:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ