Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ National Election Board of Ethiopia

የቴሌግራም ቻናል አርማ nationalelectionboardnebe — የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ National Election Board of Ethiopia
የሰርጥ አድራሻ: @nationalelectionboardnebe
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 23.27K
የሰርጥ መግለጫ

NEBE

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 19

2022-08-24 10:07:10
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ-ጉባዔ ለቦርዱ ያቀረበው የሕዝበ ውሣኔ ማደራጀት ጥያቄ ላይ ውሣኔ አሳለፈ
ውሣኔው የተላለፈበት ደብዳቤ ከላይ ተያይዟል
4.1K views07:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 18:04:26
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ኢ.ሠ.ፓ በሚል ስያሜ የቀረበ የሀገር ዐቀፍ ፓርቲነት የምዝገባ ፍቃድ ላይ ያሳለፈው ውሳኔ ከላይ ተያይዟል
4.8K views15:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 14:34:54 Announcement

The National Election Board of Ethiopia (NEBE) has been given the responsibility of registering political parties in Ethiopia based on the National Election Board Establishment Proclamation No.1133/2019 and the Ethiopian Electoral, Political Parties Registration, and Election’s Code of Conduct Proclamation 1162/2019.

Accordingly, in Article 66 of Proclamation No. 1162/2019, it is stipulated that any political party can act as a political party in Ethiopia only when it is registered by the Board and obtains a certificate of legal personality in accordance with the law.
It is known that political parties that have obtained a temporary registration license from the Board can only use the temporary license to perform the activities required to register the party according to the proclamation. Therefore, the Board would like to inform that these parties are not allowed to engage in other activities with only a temporary registration certificate and without being given a certificate of legal identity.

Click on the following link to read the full details of the notification.
https://nebe.org.et/en/node/767
4.6K views11:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 19:15:26 ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያ ዐዋጅ ቁጥር 1133/2011 ዓ.ም. እና በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ-ምግባር ዐዋጅ ቁጥር 1162/2011 ዓ.ም. መሠረት የፖለቲካ ፓርቲዎችን የመመዝገብ ኃላፊነት ተሰጥቶታል፡፡
በዚህም መሠረት በዐዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 66 ንዑስ አንቀጽ አንድ ላይ ማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ በኢትዮጵያ ውስጥ በፖለቲካ ፓርቲነት ለመንቀሳቀስ የሚችለው በሕጉ መሠረት በቦርዱ ተመዝግቦ የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ሲያገኝ ብቻ እንደሆነ ተደንግጓል፡፡
ከቦርዱ ጊዜያዊ የምዝገባ ፈቃድ ያገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጊዜያዊ ፈቃዱን መጠቀም የሚችሉት በዐዋጁ መሠረት ፓርቲውን ለማስመዝገብ የሚያስፈልጉ ተግባራትን ለማከናወን ብቻ እንደሆነ ይታወቃል። ስለሆነም የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ሳይሰጣቸው በጊዜያዊ የምዝገባ ፈቃድ ብቻ ወደተለያዩ እንቅስቃሴዎች መግባት የማይችሉ መሆኑን ቦርዱ ያሳውቃል፡፡

የማሳሰቢያውን ሙሉ ዝርዝር ለማንበብ ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ
https://nebe.org.et/am/node/766
4.8K views16:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 12:55:23 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለክልል ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊዎችና ሠራተኞች የሕግ ማዕቀፍ ሥልጠና ሰጠ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሕግ ማዕቀፍ ላይ በማተኮር ለቦርዱ የክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎችና ሠራተኞች ሥልጠና የሰጠው ነሐሴ 10 እና 11 ቀን 2014 ዓ.ም ነው። ሥልጠናው በቦርዱ አመራር አባል የሆኑት ፍቅሬ ገ/ሕይወት ንግግር ተከፍቷል። አመራሩ በንግግራቸው የቦርዱ የክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎችና ሠራተኞች እንዲሁም የምርጫ አስፈጻሚዎች በ6ተኛው ሀገራዊ ምርጫ የነበራቸውን አስተዋፅዖ በማንሳት ምሥጋና አቅርበዋል።
አያይዘውም ቦርዱ እንደ አዲስ የተቋቋመ በመሆኑ በጊዜው በርካታ እቅዶች ቢኖሩም ከጊዜና ከሁኔታዎች አንጻር የታቀደውን ሁሉ በሚፈለገው መጠን መፈፀም እንዳልተቻለ የጠቆሙ ሲሆን፣ አሁን ግን እነዚህን ጉዳዮች ለመተግበር አመቺ ሁኔታ ስለተፈጠረ በተለይ በቀጣይ ለሚደረገው ትልቅ ዐቅም ለሚጠይቀው የአካባቢ ምርጫ ይህ ሥልጠና የሚኖረውን አስተዋፅዖ አብራርተዋል።

ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችን ባካተተ መልኩ የምርጫ ጽንሰ ሐሳቦችና ተሞክሮዎችን እንዲሁም ቴክኒካዊ ክሕሎት ለማስጨበጥ ታስቦ የተዘጋጀው ሥልጠና፣ የቦርዱን ተልዕኮና ኃላፊነት ጨምሮ አጠቃላይ የምርጫ ዑደትን የዳሰሰ ነው። ሥልጠናው ቦርዱ ከዚህ ቀደም ሚያዝያ 20 እና 21 ቀን 2014 ዓ.ም የ6ተኛውን ሀገራዊ የምርጫ ሂደት አስመልክቶ ለባለ ድርሻ አካላት ባዘጋጀው ዐውደ-ጥናት ላይ የተገኙ ትምህርቶችንና ቢሻሻሉ ተብለው የተያዙ የሥራ እንቅስቃሴዎች ላይ ትኩረት አድርጓል። ከቅ/ጽ/ቤት የተወከሉት ኃላፊዎችና ባልደረቦች በሥራው ሂደት አጋጠሙን ያሏቸውን ተግዳሮቶች ባነሱበት መድረክ፣ እነዚህን ተግዳሮቶች መፍቻ መንገድ በባለሞያዎች ማብራሪያ ተሰጥቷል።

ለሁለት ቀናት በቆየው ሥልጠና የመዝጊያውን ንግግር ያደረጉት የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ናቸው። ዋና ሰብሳቢዋ በንግግራቸው እንደ ተቋም ባለን ጥንካሬ ላይ ሣይሆን አሉብን በምንላቸው ክፍተቶች ላይ ትኩረት ማድረግ ተቀዳሚ ተግባር ነው ብለዋል። ብርቱካን ሚደቅሳ ሥልጠናው የክልል ቅ/ጽ/ቤቶች ያሉባቸውን ክፍተቶች ለመሙላት የሚደረገው ጥረት አንዱ አካል መሆኑን ገልጸው፤ ሥራዎች በተዋረድ ወደ ቅ/ጽ/ቤት የመሄዳቸው ጉዳይ አይቀሬ መሆኑንም በመጠቆም፤ ከአተገባበር ጋር ችግሮች ሊፈጠሩ ስለሚችሉ የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራውን አስፈላጊነት አስረድተዋል። የሕግ ማዕቀፍ ላይ የሚሰጠው ሥልጠና የክልል ቅ/ጽ/ቤቶችን በተሻለ ለማዋቀርም ከፍተኛ አስተዋፅዖ እንደሚኖረው በንግግራቸው አመልክተዋል።
7.3K viewsedited  09:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 20:47:20 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የአካባቢ ምርጫ የሕግ ማዕቀፍ እና አፈጻጸምን የተመለከተ ያስጠናው ጥናት ላይ ባለድርሻ አካላትን አወያየ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ነሐሴ 9 ቀን 2014 ዓ.ም. የአካባቢ ምርጫ የሕግ ማዕቀፍ እና አፈጻጸምን የተመለከተ ያስጠናው ጥናት ላይ ባለድርሻ አካላትን አወያየ። የውይይቱ ዋና ዐላማ በኢትዮጵያ ለ5ኛው ጊዜ የሚካሄደውን የአካባቢ ምርጫ ለማከናወን በሚደረገው ዝግጅት ላይ የአካባቢ ምርጫን አጠቃላይ ባህሪና አሠራር አስመልክቶ ምርጫ ቦርዱ ባስጠናው ጥናት ላይ ጥናቱ የተከናወነባቸውን ሳይንሳዊ ዘዴዎች፣ በጥናቱ የተገኙ ልምዶችን ፣ ተግዳሮቶችን፣ እንዲሁም ምክረ ሃሳቦችን ጥናቱን ባካሄዱት በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የፈደራሊዝም እና አስተዳድር ጥናት/ ትምህርት ክፍል (Centre for Federalism and Governance Studies Addis Ababa University) በሚሠሩ ከፍተኛ የዘርፉ ተመራማሪዎች በማቅረብ አፈጻጸሙን አስመልክቶ ባለድርሻ አካላትን በማወያየት ሃሳብ ለመሰብሰብ ያለመ ነው።
በውይይቱ ላይ የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳን ጨምሮ ሁሉም የቦርድ አመራር አባላትና የቦርዱ የማዕከልና የክልል መሥሪያ ቤት ባልደረቦች የተገኙ ሲሆን፤ ከባለድርሻ አካላትም እንዲሁ ከፖለቲካ ፓርቲ፣ ከሲቪል ማኅበራት፣ ከተወካዮች ምክር ቤት፣ ከፌደራልና ከክልል መንግሥታት፣ እንዲሁም ከፀጥታ አካላትና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ተወካዮች ተገኝተውበታል።

ውይይቱን በንግግር የከፈቱት የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ሲሆኑ፤ በንግግራቸውም በዚህ በአስፈላጊነቱ እጅግ ጉልህ በሆነው የአካባቢ ምርጫን አስመልክቶ በተደረገ ጥናት ላይ ሃሳብና አስተያየታቸውን ለመስጠት ለተገኙት ባለድርሻ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የአካባቢ ምርጫን ማስፈፀም እንደየአካባቢው የራሱ ተግዳሮት እንደሚኖረው የገለጹት ሰብሳቢዋ ስኬቱን ለማረጋገጥ ጥናቶችን ማሰጠናቱ አስፈላጊ እንደሆነ በቦርዱ ታምኖበት ከባለሞያዎች ጋር በመነጋገር እንደተከናወነ አስረድተዋል። በጥናቱም ዓለም ዐቀፍ ተሞክሮዎችንና እንደ ኢትዮጵያ ያሉ አዳጊ ሀገራትን ተሞክሮዎች ለማካተት እንደተሞከረና የአካባቢ አስተዳደር ሊኖረው የሚገባውን ቅርፅና ማዕቀፍ እንዲሁም የሥልጣን ወሠን ባካተተ መልኩ እንደተከናወነ ገልጸዋል። የአካባቢ ምርጫን አስፈላጊነት በገለጹበት ንግግራቸውም በወካዩንና ተወካዩ መኻል የሚኖረውን ርቀት የሚያጠብና ሥልጣንን ለዜጎች ለመቆጣጠር መሠረት እንደሆነ አጽንዖት ሰጥተው ተናግረዋል።

ጥናቱን ዘመላክ አየለ (ፒ.ኤች.ዲ) እና ክርስቶፍ ቫንደር (ፒ.ኤች.ዲ) ለተሣታፊዎች ያቀረቡት ሲሆን፤ የጥናቱ ጭብጥ ዓለም ዐቀፍ የአካባቢ ምርጫ ሕጎችን እና ተሞክሮዎችን ገምግሞ፣ ቦርዱ ከዚህ በኋላ ለሚያከናወነው የአካባቢ ምርጫ እንደ’መመሪያ ሊያገለግሉ የሚችሉ የማሻሻያ ሃሳቦችን ማዘጋጀት/ማቅረብ ሲሆን ከዚህ በፊት የተካሄዱ የአካባቢ ምርጫዎችን ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች በመለየት ለቀጣይ የአካባቢ ምርጫ ጠቃሚ ሠነድ ማዘጋጀት፣ የየክልሎችን የአካባቢ ምርጫ የምክር ቤት ቁጥር ለመወሰን የወጡ ዐዋጆች እና የዐዋጅ ማሻሻያዎችን መመርመር ከዐዋጆቹ በመነሣት ማሻሻያ ሀሳቦችን ማቅረብን እንደ ዝርዝር ዐላማ ይዞ የተነሣ ነው።

በባለሞያዎቹ የቀረበውን የመጀመሪያ ደረጃ የጥናት ውጤት ተከትሎ ጥናቱን ይበልጥ ለማዳበር የሚያስችለውን ሃሳብና አስተያየት ከባላድርሻ አካላቱ የተሰበሰበ ሲሆን፤ ባለድርሻ አካላቱም ቦርዱ ይህን ጥናት አስጠንቶ የባለድርሻ አካላቱን አስተያየት ለመሰብሰብ መድረኩን ማዘጋጀቱን አድንቀው፤ በማስከተልም አስተያየታቸውን አጋርተዋል። ከተሰጡ አስተያየቶች ውስጥም ቀደም ሲል ሀገራዊ ምርጫውን ለማካሄድ ጥቅም ላይ የዋለው ሕግ ለአካባቢ ምርጫው የሚኖረው ፋይዳ፣ የአካባቢ ተመራጮች ከክልልና ከባለድርሻ አካላት ጋር የሚኖራቸው በጀትን የተመለከተ ግንኙነት፣ ማኅበረሰቡና ባለድርሻ አካላቱ ስለአካባቢ ምርጫ ሊኖራቸው የሚገባው ግንዛቤና ይህንኑ ግንዛቤ ለማስጨበጥ መከተል ስለሚገባው አማራጮች በባለድርሻ አካላቱ ከተነሰት አስተያየቶች ውስጥ ይጠቀሳሉ።

በተሣታፊዎቹ ለተነሡት አስተያየቶች ባለሞያዎቹ መልስ የሰጡበት ሲሆን፤ በምርጫ ቦርዱ ከፍተኛ ቁጥጥር የሚደረግበት በክልል መንግሥታት ደረጃ የሚዘጋጅ የቀበሌ ምርጫ አስተዳደር፤ በግልጽ ገደብ የተበጀለት ኃላፊነት ለክልልና ለአካባቢ የምርጫ ቢሮዎች መስጠትና የነዚህን ቢሮዎችን ሥልጣንና ኃላፊነት በዝርዝር የያዘው መመሪያው አካባቢዎቹ የሚኖራቸውን የመፈጸም ነፃነትና ለበላይ አካል የሚኖራቸውን ተጠያቂነት በበቂ ማቻቻል የሚያስገኝ ሆኖ መዘጋጀት እንዳለበት ምክር ሃሳብ አቅርበዋል። የቦርዱ ዋና ሰብሳቢም የተሰሡ አስተያየቶችን ባካተተ መልኩ ቦርዱ አዳብሮት ውሣኔ እንደሚሰጥበትና ዝርዝር አፈጻጸሙም ይህን ተከትሎ እንደሚሆን አሳውቀዋል።
7.2K viewsedited  17:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 11:22:58
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አ.ብ.ን በድጋሜ የሚያካሂደው ጠቅላላ ጉባዔን አስመልክቶ ውሣኔ አሣለፈ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) እስከ ሰኔ 18 ቀን 2014 ዓ.ም. ድረስ ጠቅላላ ጉባዔ እንዲያደርግ መወሠኑ ይታወቃል። ይሁንና ፓርቲው በቦርዱ ውሣኔ መሠረት ጉባዔውን ሳያካሂድ የተሰጠው የጊዜ ገደብ አልፏል፡፡ በመሆኑም ቦርዱ ፓርቲው ጠቅላላ ጉባዔውን መቼ ለማድረግ እንደወሠነ ለቦርዱ በአስቸኳይ እንዲያሳውቅ፣ ጠቅላላ ጉባዔው እንዲነጋገርበት የሚቀርቡ አጀንዳዎችን አስቀድሞ ለቦርዱ እንዲያሳውቅ፣ የፓርቲው የጠቅላላ ጉባዔ አባላት የሚጠሩበትን ሁኔታ በተመለከተ በፓርቲው የተሰጡ የፓርቲው ውሣኔዎችን እንዲያቀርብ እና እስካሁን ያለውን ክዋኔያቸውን እንዲያብራራ፣ በተጨማሪም ሌሎች የጠቅላላ ጉባዔ ቅድመ ጉባዔ ዝግጅቶችን ለቦርዱ እንዲገልጽ ቦርዱ የወሠነ መሆኑን እናሳውቃለን።

የውሣኔውን ዝርዝር ለማንበብ ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ
https://nebe.org.et/am/node/759
9.8K views08:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 14:54:08
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሐምሌ 26 ቀን 2014 ዓ.ም. ለፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የሥራ እንቅስቃሴ የሚረዳ የመኪና ድጋፍ አደረገ። የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ ውብሸት አየለ በተገኙበት የተፈጸመው ርክክብ ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ዋና ሰብሳቢ መብራቱ አለሙ (ፒ.ኤች.ዲ) ጨምሮ የምክር ቤቱ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ተገኝተዋል።
8.4K views11:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-01 15:35:54 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለአገው ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ የፖለቲካ ፓርቲ የምዝገባና ሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ሰጠ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያ ዐዋጅ ቁጥር 1133/2011 እና በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ-ምግባር ዐዋጅ ቁጥር 1162/2011 በተሰጠው የፖለቲካ ፓርቲዎችን የመመዝገብ ኃላፊነት መሠረት «አገው ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ (ፍትህ)»ን የክልል የፖለቲካ ፓርቲ የምዝገባና ሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ሐምሌ 19 ቀን 2014 ዓ.ም. ሰጥቶቷል።

https://nebe.org.et/am/node/757
8.9K viewsedited  12:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-28 14:11:15
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተለያዩ ፓርቲዎች ያካሄዱት ጠቅላላ ጉባዔን ተከትሎ ውሣኔዎች አሣለፈ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሐምሌ 15 ቀን 2014 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ የሞቻ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ሞዴፓ) መጋቢት 3 ቀን 2014 ዓ.ም.፣ የአርጎባ ብሔረሰብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (አብዴን) መጋቢት 08 ቀን 2014 ዓ.ም.፣ የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ሚያዚያ 1 እና 2 ቀን 2014 ዓ.ም. ያካሄዱትን ጠቅላላ ጉባዔ አስመልክቶ ፓርቲዎቹ ከሪፖርታቸው ጋር አያይዘው ያቀረቧቸውን ሠነዶች ከሕጉ፣ ከፓርቲዎቹ መተዳደሪያ ደንብ እና የቦርዱ ታዛቢዎች ካቀረቡት ሪፖርት አንጻር መርምሯል። በዚህም መሠረት ቦርዱ ፓርቲዎቹ መተዳደሪያ ደንባቸው ላይ ማሻሻያዎችን ሲያደርጉ የሕግ አፈጻጸም መሠረታዊ ጉድለቶች ያገኘ ሲሆን፤ ፓርቲዎቹ መተዳደሪያ ደንባቸውን ሲያሻሽሉ ዐዋጁ ላይ ከተቀመጡት አንቀጾች ጋር በማይቃረንና እና በመተዳደሪያ ደንባቸው ላይ የተቀመጡት ድንጋጌዎች አንዳቸው ከሌላኛቸው ጋር በማይጣረሱበት አግባብ ተስተካክለው እንዲሁም የተጓደሉ ድንጋጌዎች ተማልተው ተገቢውን ማስተካከያዎች በሙሉ በማድረግ ለቦርዱ እንዲያቀርቡ ሲል ወሥኗል፡፡

የውሣኔውን ዝርዝር ለማንበብ ተከታዩን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ
https://nebe.org.et/am/node/754
11.1K views11:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ