Get Mystery Box with random crypto!

Natinael Mekonnen

የቴሌግራም ቻናል አርማ natinaelmekonnen21 — Natinael Mekonnen N
የቴሌግራም ቻናል አርማ natinaelmekonnen21 — Natinael Mekonnen
የሰርጥ አድራሻ: @natinaelmekonnen21
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 9.15K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ቻናል ቴሌግራሜ hacked በተደረገበት ሳት ለግዝያዊነት የከፈትኩት ቻናል ነው ለችግር ጊዜ ይጠቅማል ተቀላቀሉ
በቀጥታ መረጃዎችን ለመስጠት ከፈለጉ @NatnaelMekonnen7 በማለት መረጃዎችን ይላኩልን
Facebook.com/natnaelmekonnen.et
Instagram.com/natnaelmekonnen21
Telegram https://t.me/NatinaelMekonnen21

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2022-07-14 17:33:51
አሸባሪው ኦነግ ሸኔ በጎረቤት አገራት መደበቁን መንግሥት ገለጸ

የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እየወሰዱ ባለው እርምጃ አሸባሪው ኦነግ ሸኔ ከመዳከም አልፎ ወደ ጎረቤት አገራት በመሸሽ መደበቁን መንግሥት አስታወቀ፡፡

በአሸባሪው ሸኔ ላይ እየተወሰደ ያለውን እርምጃ በተመለከተ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ከበደ ዴሲሳ ዛሬ በሰጡት መግለጫ አሸበሪ ቡድኑን ማዳከም መቻሉን አስታውቀዋል፡፡

ቡድኑ እየተወሰደበት ባለው እርምጃ እየተዳከመ ቢሆንም የውሸት መረጃዎችን በማሰራጨት ለጥፋት ሀይሉ ሽፋን የሚሰጡ ግለሰቦች መኖራቸውን የጠቆሙ ሲሆን ሁኔታው በሕዝብ ዘንድ መጠራጠርን ለመፍጠር ታስቦ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በወለጋ አሸባሪው ቡድን ጥቃት ላደረሰባቸው ዜጎች መንግሥት አስፈላጊውን ደጋፍ እያደረገ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ የአሸባሪዎቹ አላማ ከውጭ ባንዳዎች ጋር በመተባበር ሕዝቡ በመንግሥት ላይ ተስፋ እንዲቆርጥ ማድረግ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው ህብረተሰቡ ከመንግስት ጋር በመቆም የህግ ማስከበር ዘመቻውን እንዲያግዝ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
659 views14:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 12:44:11
12 ሺህ ዜጎችን ከተለያዩ የአፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ ሀገራት የመመለስ ስራ በዛሬው እለት ተጀመረ

መንግስት ለዜጎች ትኩረት በሰጠበት ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ እስካሁን በርካታ ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቄ አቀባይ አምባሳደር መለሰ አለም በዛሬው እለት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።

ከሳውዲ አረቢያ ውጭ በተለያዩ የአፍሪካ እና የመካከለኛው ምሳራቅ ሀጋራት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚኖሩ ዜጎችን ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ ለማድረግ ራሱን የቻለ ኮሚቴ ተቋቁሞ ሲንቀሳቅስ መቆየቱን ገልፀዋል።

በዚህም በዛሬው እለት 12 ሺህ ዜጎችን ከተለያዩ የአፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ ሀገራት የመመለስ ስራ በይፋ መጀመሩን ተናግረዋል።

ከታንዛኒያ፣ከማላዊ፣ ዛምቢያ፣ ዚምባብዌ ፣ ጁቡቲ ሱዳን፣ የመን እና ኦማን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የሚመለሱት ከአለም የፍልሰት ድርጅት አይ ኦ ኤም  ጋር በተደርገ የጋራ ስራ እንደሆነም አምባሳደር መለሰ መናገራቸውን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል።

መንግስት ከሳውዲ አረቢያ ከመጋቢት 21 ጀምሮ በተደረጉ 126 በረራዎች 102 ሺህ የሚሆኑ ዜጎችንም መመለሱንም አንስተዋል ። እነዚህ ዜጎች በሶስት ወራት ውስጥ ከሪያድ እና ከጅዳ የተመለሱ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
1.2K views09:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 12:44:10 የስሪላንካ ፕሬዝዳንት ወደ ሲንጋፑር ሊሰደዱ ነው

ፕሬዝዳንቱ ወደ ማልዴቪስ ሸሽተው ነበር። ፕሬዝዳንት ጎታብያ ራጃፓክሳ ሀገሪቱን ለ20 ዓመታት መርተዋል።
https://am.al-ain.com/article/sri-lanka-president-heads-to-singapore
1.1K views09:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 12:44:10
ከ1 ሺህ በላይ የሽጉጥ ጥይት ከጤፍ ጋር በመቀላቀል ወደ አዲስ አበባ ያስገቡ 3 ተጠርጣሪዎችን ከእነ ጥይቱ በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።

ሦስቱ ተጠርጣሪዎች እና ጥይቱ በቁጥጥር ስር የዋለው ሐምሌ 4 ቀን 2014 ዓ.ም በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 በተለምዶ አባ ጅፋር መስጊድ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ከሚገኝ አንድ ቁርስ ቤት ውስጥ መሆኑ ተገልጿል።

መነሻውን ምሥራቅ ጎጃም ደብረወርቅ ከተማ ያደረገ የሠሌዳ ቁጥር ኮድ 3- 92916 አ/አ ኤፍ.ኤስ.አር የጭነት መኪና አሽከርካሪ እና ተባባሪዎቹ ጥይቱን ከጤፍ ጭነት ጋር በመቀላቀል ወደ አዲስ አበባ ካስገቡ በኋላ ከአንድ የግለሰብ ቁርስ ቤት ውስጥ ተጠርጣሪዎቹን ከ1 ሺህ 100 የሽጉጥ ጥይቶች ጋር የአዲስ አበባ ፖሊስ ከኅብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን አስታውቋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ፀረ-ሰላም ኃይሎች የከተማዋን ሰላም እና ፀጥታ ለማደፍረስ የሚያሴሩትን ሴራ ከኅብረተሰቡ እና ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት እና የተለያዩ መረጃዎችን በማሰባሰብ ሙከራቸውን እያከሸፈ እንደሚገኝም ገልጿል።

በመሆኑም ኅብረተሰቡ ለፀጥታ አካላት እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪውን አስተላልፏል።
1.0K views09:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 12:44:10 ከምዕራብ ጉጂ በተነሱ ታጣቂዎች ሶስት የቡርጂ አርሶአደሮች መገደላቸዉ ተነገረ።

በደቡብ ክልል በቡርጂ ልዩ ወረዳ በትላንትናው ዕለት ከምዕራብ ጉጂ የመጡ ናቸዉ በተባሉ የታጠቁ ኃይሎች በወሰዱት እርምጃ ሶስት አርሶ አደሮች መገደላቸዉን እና በርካታ ከብቶች መዘረፋቸዉን ምንጮች ተናግረዋል።

ሐምሌ 6 ቀን 2014 ዓ.ም ከረፋዱ 4:00 ገደማ በዋሌያ ተብሎ በሚጠራው ቀበሌ የእርሻ ስራ እና ጤፍ በማጨድ ላይ የነበሩ ሶስት አርሶ አደሮች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን እና ከ50 በላይ ከብቶች መዘረፋቸዉን የቡርጂ ልዩ ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ገብረወልድ ሂዶ ተናግረዋል። ለጥቃቱ ተጠያቂ የሚሆነዉ መንግስት "ኦነግ ሸኔ" በማለት የሚጠራቸዉ ቡድኖች ናቸዉ የሚሉት ኃላፊዉ የጉጂ ማህበረሰብ ግን በዚህ ዉስጥ አይካተትም ሲሉ በተለይ ለአዲስ ዘይቤ ተናግረዋል።

በቡርጂ ልዩ ወረዳ በተደጋጋሚ ከምዕራብ ጉጂ በሚነሱ ታጣቂዎች ግጭት እንደሚነሳ የሚያስታውሱት የመንግስት ኮሙኒኬሽን ኃላፊው አቶ ገብረወልድ በሰኔ ወር 2014 ዓ.ም ብቻ አምስት አርሶአደሮች ሲገደሉ ከ 60 በላይ ከብቶች ተዘርፈዋል ብለዋል።

ለግጭቱ መነሻ ምክንያት እንደ ከዚህ ቀደሙ "የድንበር ይገባኛል" የሚል ሳይሆን ሌላ አላማ ያለው ነው የሚሉት የልዩ ወረዳዉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ገብረወልድ ሂዶ መንግስት በሌሎች አከባቢዎች እያደረገ የሚገኘዉን የህግ ማስከበር ዘመቻ በቡርጂ እና በጉጂ ኦሮሚያ አከባቢዎች ላይም መዉሰድ እንደሚገባዉ ተናግረዋል።
984 views09:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 12:44:10 የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ስድስተኛ የፓርላማ ዘመን 1ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ 2ኛ መደበኛ ስብሰባውን በምክር ቤቱ የጉባኤ አዳራሽ ማካሄድ ጀመሯል፡፡

ምክር ቤቱ ስድስተኛ የፓርላማ ዘመን 1ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ በግፍ ለተጨፈጨፉ ንጹሀን ዜጎች የህሊና ጸሎት በማድረግ ጉባኤውን የጀመረ ሲሆን 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባ ቃለ ጉባኤን መርምሮ በማጽደቅ ውይይቱን ቀጥሏል።

በመቀጠልም የአራቱን ቋሚ ኮሚቴዎችን እና የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤን የ2014 ዓ.ም. የአፈጻጸም ሪፖርቶች፣ ከሕገ መንግሥት አጣሪ ጉባኤ የሕገ መንግሥት ትርጉም ያስፈልጋቸዋል በተባሉ የውሳኔ ሐሳቦች፣ የሕገ መንግሥት ትርጉም አያስፈልጋቸውም በሚል ውሳኔ በተሰጣቸው እና ለምክር ቤቱ በይግባኝ በቀረቡ አቤቱታዎች ላይ በመወያየት ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በተጨማሪም የኢፌዲሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አዋጅ ቁጥር 1261/ 2013 ለማስፈጸም የተዘጋጀ ረቂቅ ደንብ፣ ውስን ዓላማ ያላቸው የድጎማ በጀትና የፌዴራል መሠረተ ልማት ስርጭት ፍትሐዊነት የክትትል ሥርዓትን ለማስፈጸም የተዘጋጀ ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ እንደሚያጸድቅ የሚጠበቅ ሲሆን የተለያየዩ ሹመቶችንም ያጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከምክር ቤቱ ያገኘነዉ መረጃ ያመለክታል፡፡
1.1K views09:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 12:44:10
በሰልጣን መፎካከር የሚቻለው ሀገር ሲትኖር ነው !!

የሶማሌ ክልል ኘሬዝዳንት ሙስጠፌ ሙሁመድ ዑመር

Good Night #Ethiopiaዬ
1.1K views09:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 21:29:43 የባለ ስልጣን ሌቦች እስር ማምሻውን ተጠናክሮ ቀጥሏል!
1.7K views18:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 21:29:43
የነዚህ ወጣቶችን ፍዳና ግፍ ሀላፊነቱን የሚወስደው የህወሓት ወያኔ ነው:: በመቀሌ ጎዳናዎች እየታዩ ያሉ በጦርነቱ የቆሰሉ አካላቸው የጎደለ ወጣቶች:: ግልባጭ አውሮፓና አሜሪካ ቁጭ ብለው ጦርነት ባህላዊ ጫዎታችን ነው ሲሉ ለነበሩት ለነ አሉላ ሰልሞን እና መንጋዎቹ ይድረስልኝ!

ጦርነት ይብቃን!
1.7K views18:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 20:10:53
1.7K views17:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ