Get Mystery Box with random crypto!

Natinael Mekonnen

የቴሌግራም ቻናል አርማ natinaelmekonnen21 — Natinael Mekonnen N
የቴሌግራም ቻናል አርማ natinaelmekonnen21 — Natinael Mekonnen
የሰርጥ አድራሻ: @natinaelmekonnen21
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 9.15K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ቻናል ቴሌግራሜ hacked በተደረገበት ሳት ለግዝያዊነት የከፈትኩት ቻናል ነው ለችግር ጊዜ ይጠቅማል ተቀላቀሉ
በቀጥታ መረጃዎችን ለመስጠት ከፈለጉ @NatnaelMekonnen7 በማለት መረጃዎችን ይላኩልን
Facebook.com/natnaelmekonnen.et
Instagram.com/natnaelmekonnen21
Telegram https://t.me/NatinaelMekonnen21

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-08-30 15:40:14
ወልዲያ አደርን ጠላት በከበባ ውስጥ አድርጎ ሊበትነን ቢመኝም እስከ ቀኑ 5: :00 ሠዓት ድረስ በጀኔራል ሀሠን ከረሙ በአዋጊው ሻለቃ ሞገስ ከበደ, በደምሌ አራጋው , በወርቄ ጀግኖች እየተመራ በአማራ የወሎ ፋኖ ጦር ከመከላከያ ከልዩሀይል ጋር በመሆን ወልዲያን አላሥደፈራትም ።

በአሁኑ ሠአት በወርቄ ቂልጡ ,በአላ ውሀ, በጎብየ , በሶስት ግንባሮች ተሠልፎ እየተፋለመ ይገኛል ።
ህዝባችን በተረጋጋ መንፈስ ይጠብቅ ጦርነት የብዙ ነገሮች ውጤት ነውና !!!

አማራነት ይለምልም በምስጋን ደስዬ ከስፍራው የተጻፈ
1.5K views12:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 15:40:14 ከዳባት ከተማ አስተዳደር የፀጥታው ምክር ቤት በወቅታዊ ዙሪያ የሚከተሉትን ውሳኔዎች አሳልፏል!

1ኛ. በከተማዉ ዉስጥ ማንኛዉም ሰዉ ከምሽቱ 2:00 ስዓት በኃላ እንቅስቃሴ የተገደበ ነው።

2ኛ. ማንኛዉም መጠጥ ቤቶችና ምግብ ቤቶች ከምሽቱ 2:00 በኃላ አገልግሎት መስጠት የተከለከለ ነው

3ኛ. በከተማችን ማንኛውም ተሽከርካሪ ባጃጅን ጨምሮ ከምሽቱ 12:00በ በኋላ እና ጧት ከ12:00 ስዓት በፊት ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንዳያደርጉ ተከልክሏል።

4ኛ. የከተማችን ማህበረሰብ በአደረጃጀቶቹ አካባቢውን የመጠበቅና ከፀጉረ ልውጦች እና ስርጓ ገቦች በንቃት እንዲጠብቅ ።ይህ ሁኔታ ሲያጋጥም ለህግ አካል ጥቆማ መስጠትና በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውል የመተባበር ግዴታዎች አስቀምጧል።

5ኛ. በከተማችን የምትገኙ አልጋ ቤቶች ፣ቤት አከራዮች እና ሆቴሎች ማንነቱ ያልታወቀ ማንነቱን በመለየት በመረጃ ፎርም ሞልቷ ማከራየት እና አጠራጣሪ ሁኔታ ሲያጋጥም ለህግ አካላት እንድታሳውቁ።

6ኛ. የባጃጅ አሽከርካሪዎች ከዳባት ዳራ እና ከዳባት ወቅን ብቻ እንድታሽከረክሩ የተወሰነ ሲሆን ከዳባት ወደ አጅሬ መስመርና ከዳራ ገደብየ ማሽከርከር የተከለከለ ነው።

7ኛ. የዳባት ከተማ ፈቃድ የሌለዉ ባጃጅ ከዳባት ወደ ሌላና ከሌላ ቦታ ወደ ዳባት ማሽከርከር ተከልክሏል።

8ኛ. ለፀጥታ ስራ ከተሰማሩት ዉጭ ማንኛዉም ግለሰብ የጦር መሳሪያ ይዞ በከተማ መንቀሳቀስና በመጠጥ ቤትም ሆነ ምግብ ቤቶች ይዞ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው።

9ኛ. ወራሪና አሸባሪዉ የህዉሓት ቡድን ከሚያሰራጨው የሀሰት ፕሮፖጋንዳና ለህዝባችን ስነ ልቦና የማይነጥኑና ለጠላት ጉልበት የሚሆኑ ወሬዎችን ከማሰራጨት ሁሉም ህዝብ እንዲቆጠብ

10ኛ. በከተማችን ተከራይተዉ የሚኖሩ ኤርትራዊያን ስደተኞች ጋር ተያይዞ ወደ ካፕ የሚመለሱበት ምቹ ሁኔታ እንዲመቻች ከሚመለከታቸዉ አካለት ጋር ስራ እየተሰራ መሆኑን የከተማችን ህዝብ እንዲገነዘብ እያሳሰብን ከዚህ ጎን ለጎን ስራዎች ስለሚያስፈልጉ

ሰርጎ ገቦች ሊኖሩ ስለሚችሉ ጉዳዩ በጥንቃቄ በፀጥታ ሀይሉ እየተገመገመ የሚመራና የሚከወን ይሆናል ይህ ተግባር በጥንቃቄ ካልተመራ ለከተማችን የሚኖረዉ አሉታዊ ተጽኖ ከፍ ያለ በመሆኑ ህዝባችን ጉዳዩን በእያለበት ክትትል እንዲያደርግ።

ሁሉም አከራይ ተክክለኛ ኤርትራዊ ስደተኛ መሆኑን ማረጋገጥና እንቅስቃሴዉን መከታተል የተለየ ነገር ሲመለከት ለፀጥታ መዋቅሩ እንዲጠቁም።
1.4K views12:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 15:40:14
"በዚህ ሰዓት የወገን ጥምር ሀይል በወልድያ ዙሪያ ባሉ ቀበሌዎች እየተፋለመ ነው። እስካሁኗ ሰዓት ወልድያ ነፃነቷን አላስነካችም። የመጡብን እንደ ህዝብ ነው። እንደ ህዝብ ልንመክታቸው ይገባል። ቤቱን ዘግቶ ወደ ሌላ ከተማ በመሸሽ ነፃነት አይገኝም። በዱላ፣ በቢላዋ፣ በቆንጨራ ሳይቀር መፋለም አለብን።"

ሻለቃ ምሬ ወዳጆ - የምስራቅ አማራ ፋኖ አዛዥ
1.4K views12:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 15:40:14 የተከበሩ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ዲያቆን ተስፋው ባታበል ወልዲያ በወገን ጦር እንጅ  በጠላት አልተያዘችም !!

አሸባሪው የትግራይ ወራሪ  ኃይል  በዞናችን በድጋሜ   ወረራ ለመፈፀም ያለ የሌለ ኃይሉን አሰባስቦ   ለሁለተኛ ጊዜ ጦርነት  አውጆብናል።

ከትናንት ስህተቱ የማይማረው የትግራይ ወራሪ ኃይል መንግስት ያቀረበለትን የሰላም አማራጭ ወደ ጎን በመተው  ለትግራይ ህዝብ ግድ የሌለው መሆኑን በተግባር አረጋግጧል።

ጦርነትን እንደ ዋነኛ ግብ ቆጥሮ፣ በሰው ደም ላይ የሚረማመደው  የትህነግ አሸባሪ ቡድን  ዛሬም ከትናንት ስህተቱ  ሳይማር የጦር ነጋሪት ሲጎስም ከከረመ በኋላ  ሀገር የማፍረስ አጀንዳ  አንግቦ ወደ ጦርነት  ገብቷል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ በየዘመናቱ ከውስጥም ሆነ ከውጭ ጠላቶች ሲገጥሟት ኑሯል  ። 
ከጥንት ጀምሮ የገጠማትን  የውሰጥና የውጭ ጠላቶችን አሸንፋ በድል እየተረማመደች የመጣች የጥቁር አፍሪካ  ህዝቦች የነፃነት ፈርጥ መሆኗን የታሪክ ድርሳናት አስረግጠው ይመሰክራሉ።

ወራሪው የትግራይ ኃይል በመንግስት በኩል የቀረበለትን የሰላም አማራጭ  አልቀበልም ብሎ ጦርነትን አማራጭ ያደረገው ለትግራይ ህዝብ አስቦ ሳይሆን የውጭ ኃይሎችን ጣልቃ ገብነት፣ የባንዳነት  ተልዕኮውን ለማስፈፀም አበክሮ እየሰራ ስለመሆኑ  አንዱ ማሳያ ነው።

ኢትዮጵያውያን  በሀገራቸው  ሉኣላዊነትና አንድነት ላይ  የማይደራደሩ፣ በደምና በአጥንታቸው አፅንተው  ያቆሟትና  ሀገር  የመሠረቱ  ያነፁ የእንቁ ልጆች ባለቤት  ናት ። ዛሬም ቢሆን  ከዚህ ከፍታዋና  ክብሯ ማንም ዝቅ ሊያደርጋት  አይችልም።

የሀገራችን ትናንት  በደምና በአጥንት የቋሟት  ጀግኖች ልጆች እንደነበሯት ሁሉ ዛሬም  የሀገራቸውን ሉአላዊነትና አንድነት  በደምና በአጥንታቸው የሚያፀኑ  ጀግኖች ልጆች አሏት።

ወራሪው ኃይል በዞናችን  ወረራ ሲፈፀም  ትናንት ይጠቀምባቸው የነበሩ የሀሰት ቅስቀሳና ፕሮፖጋንዳዎች   አሁንም ተጠናክሮ  ህዝብን ለማደናገር  በስፋት  እየተሰራጨ ይገኛል።

ይህ የሽብር ቡዱኑ ፕሮፖጋንዳ  በማህበራዊ ሚዲያ ተከፋይ  አክቲቪስቶች  ብቻ የሚተገበር ሳይሆን የፈጠራ ወሬዎችን በሚያራግቡ  እና  የጥላት ፕሮፖጋንዳ  ከውሰጥ ሁነው  በሚደግፉ ስዎች  ጭምር  የሚተገበር  በመሆኑ   ዛሬም እንደለመደው ወልዲያን ተቆጣጠርኩ እያለ ያራግባል ።

ስለዚህ ህብረተሰቡ ከእንደዚህ ዓይነት  የሀሰተኛ መረጃዎች ራሱን ሊጠብቅና አጠራጣሪ መረጃዎችን ሲመለከት ለመንግስት የፀጥታ መዋቅር ጥቆማ መስጠት ይጠበቅበታል።

የዞናችን ህዝብ በወራሪው ኃይል  የደረሰበት የሰብዓዊ፣ ስነ ልበናዊና ቁሳዊ ውድመት መንገር ለቀባሪ እንደማርዳት ይቆጠራ፤ የችግሩ ቀጥተኛ ተጠቂና  ገፈት ቀማሽ ነው።  ሰለሆነም  ወራሪው ኃይል እንደ ሀገር ወረራ ሲፈፀም ዞናችን  ቀጥተኛ የትግሉ ቦታ ላይ የሚገኝ በመሆኑ  ከትናንት ችግሮች ትምህርት በመውሰድ ያለ የሌለ አቅማችን አሟጠን ከሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ ከአማራ ልዪ ኃይልና ፋኖ ጋር ደጀን በመሆን አጋርነታችን እንደ ወትሮው አጠናክረን ልንቀጥል ይገባል።

ሰላማችን የሚረጋገጠው በአንድ ወገን ፍላጎት ብቻ አይደለም። መንግስት ለሰላም ያለውን ቁርጠኝነትና አማራጭ አሟጦ  ተጠቅሟል። ለሰላም ሲባል ረጅም ርቀት በመንግስት በኩል የተወሰዱ አዎንታዊ እርምጃዎች የሚደነቁ ናቸው። ያም ሆኖ  በጥላት  የቀረበለትን የሰላም አማራጭ ወደ ጎን ብሎ በኩል  ጦርነትን እንደ ብቸኛ አማራጭ ተጠቅሞ  ዳግም ወረራ ከፍቷል።

ሰለሆነም የዞናችን ህዝብ የተቃጣብንን ወረራ የህልውና ጉዳይ  በመሆኑ  አያጠያይቅም። ትናንት ብዙ ትምህርት ወሰደናል፤ ዛሬ ለነፃነታችንና ለአንድነታችን  ዘብ በመቆም ይጠበቅብናል።

የሰሜን ወሎ ዞን ኮሙኒኬሽን፣
ነሃሴ 24/2014 ዓ.ም
1.4K views12:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 15:40:14
ወያኔ ዛሬ ያወጣው መግለጫ ነው።

መግለጫው ለኢትዮጵያና ለኤርትራ ህዝብ የተላለፈ ጥሪ ሲሆን የመግለጫው አንኳር ይዘት ባጭሩ .......
"የኢትዮጵያና የኤርትራ ጦሮች በጋራ ትግራይን ለመውረር ዝግጅት መጨረሳቸውን ተረድቻለሁ ፤ በመሆኑም እኛ ከኢትዮጵያና ከኤርትራ ህዝብ ጋር ጠብ የለንም፤ጠባችን ከአቢይ እና ከአማራ ጋር ብቻ መሆኑን ተረድታችሁ ይሄንን እኩይ የጥፋት ድግስ እንድታወግዙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን" ይላል ።

ትርጉም በአስፋው አብርሃ
1.6K views12:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 17:33:52
750 views14:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 17:33:52 አቶ ምትኩ ካሳ ከልጃቸው ከእያሱ ምትኩ ጋር በተጠረጠሩበት የሙስና እና በህገወጥ መንገድ የተገኘ ገንዘብን ህጋዊ አስመስሎ መጠቀም ወንጀል ፍርድ ቤት ቀረቡ።

ተጠርጣሪዎችን በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ያቀረበው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን መርማሪዎች አቶ ምትኩ የብሔራዊ አደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ሲሰሩ ከኤልሻዳይ የበጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በመመሳጠር የተረጂዎችን ቁጥር ከፍ በማድረግና የሌሉ ተረጂዎችን እንዳሉ በማስመሰል ሀገሪቱ በከፍተኛ በውጭ ምንዛሬ ያስገባችውን የገንዘብ ግምቱ በሚሊዮኖች የሚገመት ከ700 ሺህ 200 ኩንታል በላይ የስንዴና ቦቆሎ እህል እንዲሁም 208 ሺህ ሊትር የዘይት እና ጥሬ ገንዘብ ከሚመሩት ተቋም በሳቸው ፍቃድ ወጪ ተደርጎ ለኤልሻዳይ ድርጅት መሰጠቱን ጠቁሟል።

በሁለተኛ ተጠርጣሪ በአቶ ምልኩ ልጅ እያሱ ምትኩ ስም ከኤልሻዳይ ድርጅት የተገዙለት ሁለት መኪኖች መኖራቸውን የገለጸው ፖሊስ በተጨማሪ ኤልሻዳይ ከ2013 ዓ/ም ጀምሮ ለልጃቸው በወር 15 ሺህ ብር የቤት ክራይ ተከራይቶለት እንደሚኖር ፖሊስ ጠቁሟል።

እንዳጠቃላይ በጎዳና ያሉ ዜጎችን ለማሰልጠን በሚል ለኤልሻዳይ ከ2006 አስከ 2012 ዓ/ም ባሉት ጊዜያት 472 ሚሊዮን 886 ሺህ 304.33 ብር ወጪ ተደርጎ ድርጅቱ ተከፋይ መሆኑን ፖሊስ ለችሎቱ አስረድቷል።

ያልተገባ ጥቅም በማግኘት ቤትና የተለያዩ ንብረት ማፍራታቸውን ጠቅሶ ምንጩ ያልታወቀ የውጭ ሀገር ገንዘብ መገኘቱንም አመላክቷል።

ሀገሪቱ የውጭ ምንዛሬ እጥረት ላይ መሆኗ እየታወቀ የተለያዩ የውጭ ሀገር ገንዘብ አከማችተው መገኘቱን ተከትሎ ምንጩን እያጣራን ነው ብሏል ፖሊስ በሪፖርቱ።

15 ምስክር ቃልና በርካታ አስረጂ የሰነድ ማስረጃ መሰብሰቡን ገልጾ ለቀሪ 10 ምስክር ቃል ለመቀበል እና ግብረ አበር ለመያዝ ቀሪ ማስረጃ ለማሰባሰብ የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቋል።

የተጠርጣሪ ጠበቆች ፈትሉ ኑሬና እና ሀብተማርያም ፀጋዬ በበኩላቸው ከፍትህ ሚኒስቴር ጋር ፖሊስ ምርመራ አጠናቆ ኦዲት ተደርጎ በቂ ማስረጃ መሰብሰቡን በመግለጫ በሚዳያ ባሳወቀበት ሁኔታ ዛሬ ደግሞ ማስረጃ ለመሰብሰብ 14 ቀን
ይሰጠኝ ማለቱ አሳማኝ ያልሆነና ተገቢነት የሌለው ጥያቄ ነው ሲሉ ተከራክረዋል።

በሌላ በኩል አቶ ምትኩ የተረጂዎችን ቁጥር መጨመርና የሌሉትን እንዳሉ በማድረግ የመመዝገብና የማሳወቅ ሀላፊነት የለባቸውም ሲሉ አሰረድተዋል።

እርዳታውንም በተመለከተ ገንዘብ ሚኒስቴር ሲፈቅድ እንጂ በሳቸው ሀላፊነት ፍቃድ የሚሰጥ እንዳልሆነ ገልጸዋል።

ከመንግስት ተቋም የሚሰበሰብ ማስረጃን ማጥፋት ስለማይችሉ በዋስ ወተው ምርመራው እንዲቀጥል ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል።

ዋስትና ጥያቄውን ፖሊስ ተቃውሟል።ጉዳዩን የተከታተለው ፍርድ ቤቱ የዋስትና ጥያቄውን ውድቅ በማድረግ ከጉዳዩ ውስብስብነት አንጻር ተጨማሪ ምርመራ ማድረግ አስፈላጊነቱን ከግምን ውስጥ በማስገባት ለፖሊስ የ 14 ቀን ጊዜ ፈቅዷል።

በታሪክ አዱኛ
755 views14:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 17:33:52
ልዩ መረጃ

በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበረ 129 ሽጉጥ ተያዘ።

መነሻውን ከሰሜን ጎንደር በማድረግ ሲጓጓዝ የነበረ 129 ሽጉጥ የደቡብ ወሎ ዞን ጸጥታ ተቋማትና የብሔራዊ መረጃ ደህንነት አገልግሎት በጋራ ባደረጉት ክትትል በቁጥጥር ስር ውሏል።

የደቡብ ወሎ ዞን ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር እርገጤ ጌታሁን እንዳስታወቁት መነሻውን ሰሜን ጎንደር ያደረገው አይሱዙ ተሽከርካሪ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያውን ይዞ ሲንቀሳቀስ በቁጥጥር የዋለው ትላንት ሐምሌ 6/2014 ከቀኑ 5:30 ሰዓት በተሁለደሬ ወረዳ ልዩ ስሙ ፓሶ ሚሌ እየተባለ በሚጠራ አካባቢ ነው።

የኀብረተሰቡን ጥቆማ መነሻ በማድረግ በተደረገ ክትትል በተደረገ የኬላ ፍተሻ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3 አአ 00175 በሆነ ተሽከርካሪ ተጭኖ ወደ ሐይቅ ከተማ ሲያመራ በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውል መደረጉን አስታውቀዋል።

ተሽከርካሪው ተደራቢ የነዳጅ ቋት በማዘጋጀትና የጦር መሳሪያዎቹን ቋቱ ውስጥ አስገብቶ በማስበየድ በቁጥጥር ስር ከዋለው 129 ቱርክ ሰራሽ ሽጉጥ ጋር አንድ ተጠርጣሪ በህግ ቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተጣራበት እንደሚገኝ መምሪያ ኃላፊው ገልጸዋል።

መረጃው የደቡብ ወሎ መንግስት ኮሚኒዩኬሽን
661 views14:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 17:33:51
ጎበዝ ይህ ፕራንክ እሚባል የምዕራብያዊያን ጫዎታ ለኛ ሃገር አይሆንም እንዲህ ያለ ለኛ ሃገር ባልተለመደ ህዝቡም የማያውቀውና ባልተገነዘበው ነገር የሰው ህይወት እንዳይጠፋ ፍራቻ አለኝ:: ለ YouTube ብላችሁ አጉል ቅጥ ያጣ ፕራንክ እምታደርጉ ወጣቶች ጥንቃቄ አድርጉ::
620 views14:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 17:33:51
‹‹ትናንትና የተለያየ መዋቅራዊ አሰራርን ተጠቅመው የድሃውን ቤት ለመንጠቅ ብዙ የጣሩ ዘራፊዎችን አሳፍረን ፤ ለሚገባው ለማድረስ ውሳኔ ላይ የደረስንበት ቀን ነበር፡፡ ዛሬ ደግሞ ለድሃና አቅመ ደካሞች ድጋፍ ለሚገባቸው ቤት ሰርተን ቤት ለምቦሳ በማለታችን ፤ የከተማ አስተዳደራችንን ያለውን የህዝብ ወገንተኝነት የሚያሳይ ስለሆነ ፤ እንደ ህዝብ የሰጣችሁንን አደራ መቼም ቢሆን እንደማንበላው ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ!

በብዙ ስራዎቻችን ውስጥ ብዙ ትንቅንቅ አለ፤ ነገር ግን የሚጥለን ትንቅንቁ ሳይሆን ተስፋ መቁረጥ ነው፡፡ አይቻልም ያልን እለት ነው የምንወድቀው፤ ይቻላል ብለን ከተነሳን ከተባበርን ፤ሌላው ቢቀር በመታገስ እንኳን ከተባበርን ብዙ ርቀት መሄድ እንችላለን!!

ተባብረን እንስራ ፤ለጊዜው የሚገጥሙንን አንዳንድ እንቅፋቶችን ከልክ በላይ አጉልተን እንደማይቻል፤እንቅፋቱን ከበላያችን ገዥ አድርገን እኛ ከስሩ ስብር ብለን መነጋገር ለብንም፤ ከእንቅፋቱ በላይ ከፍ ብለን መነጋገር ይኖርብናል፡፡
ተባብረንና ተጋግዝን እንስራ!››

ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ
613 views14:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ