Get Mystery Box with random crypto!

Murad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ muradtadesse — Murad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹 M
የቴሌግራም ቻናል አርማ muradtadesse — Murad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @muradtadesse
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 86.01K
የሰርጥ መግለጫ

ትክክለኛው ኢስላማዊ አስተምህሮ፦
1) ከቁርኣን፣
2) ከሐዲሥ፣ [በሰለፎች አረዳድ]
3) ከታማኝ ዑለማዎችና
4) ከትክክለኛ ቂያስ ተጠናቅሮ ይቀርብበታል።
√ አዳዲስና ወቅታዊ ኢስላማዊ የሆኑ ጉዳዮችም ይዳሰሳሉ።
√ አላማዬ በዲኔ ላይ ያለውን የመረጃ ክፍተት መሙላት ነው።
ማንኛውም አስተያዬት ሲኖራችሁ @Murad_Tadesse ላይ አስፍሩት።
ስህተትም ባያችሁ ጊዜ አርሙኝ።
ጀዛኩሙል`ሏህ ኸይራ!

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2024-05-31 21:48:59 ይሄ የአሜሪካው አሳ'ማ ሰበር ዜና ብሎ ብቅ ብሏል።
በጋ'ዛ ላይ አሜሪካና አጋሮቿ በወ'ራ'ሪዋ እስራ'ኤል በኩል እየተፈጸመ ያለው የዘር ማፅ'ዳት ጭፈ'ጨፋና የጦ'ር ወን'ጀል እንዲቆም አዟል። የጦርነት ማቆም ስምምነቱ 3 ዑደቶች የሚኖሩት ሲሆን፤ የመጀመሪያው ወራ'ሪዋ ከጋ'ዛ ጦ'ሯን ማውጣት፣ ሁለተኛው ሐ'ማስ ያገታቸውን መልቀቅና ወራ'ሪዋም ፈለስጢናዊ እስረ'ኞችን መልቀቅ፣ ሦስተኛው የጋ'ዛ መልሶ ግንባታ ይሆናል። ይህ ሃሳብ የመጣው ከእስራኤል ሲሆን ዓለም አቀፋዊ ጫናውን ስላልቻለችና በቅርቡ በራፋህ የመጠለያ ካምፕ ላይ በፈፀ'መችው ወን'ጀል ወዳጆቿ እነ ፈረንሳይ ጭምር በጥብቅ ያወገዟት መሆኗ ነው።

በሃገረ አሜሪካ ሃርቫርድ ዩኒቨርስቲን ጨምሮ በርካታ ተማሪዎች ድግሪያችንን ቀቅላችሁ ብሉት ብለው በየቀኑ ተቃውሟቸውን ቀጥለው ነበር። በዛ ላይ የትራንምፕን ምላስ አልቻለውም። የራሱ ዙፋንም ከቀጣይ ምርጫ ጋር ተያይዞ ያሰጋው ይሄ በቁሙ የሞ'ተ ባይደን የሚባል አሮ'ጊት፤ የእስራኤል ቃል አቀ'ባይ መሆኑን ዛሬ አስመስክሯል።

ያሻቸውን ያክል ፈለስጢናዊ ህፃንና ሴት ከጨ'ፈጨፉ በኋላ መውጫ ቀዳዳው ሲጠ'ፋቸው ልክ አፍጋ'ኒስታን ላይ እንደሆኑት ከጋ'ዛም ሊወጡ ጫፍ ደርሰዋል። አላህ ከዱንያም ያውጣቸውና! ያ ሲደሰኩርለት የነበረው ሐማ'ስን ከምድረ ገፅ በማጥፋት ታጋ'ቾችን እንቀበለዋለን ሲሉት የነበረው ጉ'ራ መና ሊቀር ጫፍ ደርሷል። ስንትና ስንት የዓለም ኃያላን ተሰባስቦ፣ ስንትና ስንት ትሪሊዮን ዶላሮች ፈሰውበት፣ አለ የተባለ ዘመኑ ያፈራው ጨፍ'ጫፊ መሳሪያ ተለግሶ… የአዲስ አበባን ⅓ኛ በማታክል ምድር ላይ ለተከታታይ 8 ወራት ከዘ'ነበ በኋላ አንዳችም ምኞታቸውን ሳያሳኩ ተስፋ ቆር'ጠው ሊወጡ ነው። አላህ በሁለቱም ዓለም ያክስ'ራቸው።


BREAKING: President Joe Biden outlines a new three-phase proposal designed to end fighting between Israel and Hamas, including a total cease-fire, return of hostages and rebuilding of Gaza.

||
t.me/MuradTadesse
5.5K views18:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-31 21:17:24 December 23, 2021 የጻፍኩት ፖስት ነው። 3ኛ አመቱን ይዟል። ያኔ የኮሚሽነሩ መሪ የሚሆኑ ሰዎችን ጠቁሙ ሲባል እየለፈለፍኩ ነበር። ስንቶቻችሁ ነበራችሁ የተገበራችሁት? ዛሬ አንዳንዱ ሲገባው ጥያቄ ያነሳል። አንዱን እድል ያኔ አሳልፈኸዋል፣ ለሴራቸው አመቻችተህላቸዋል። ልክ የተወሰኑ ሰዎች ዛሬ ላይ እንደባነኑት፤ ነገ ደግሞ ውጤቱን ስታይ ታለቃቅሳለህ።

ግን አብዛሃኛዎቻችሁ ያኔም እንቅልፍ ላይ ነበራችሁና ነገሩን እንደ ተራ ነገር ቆጥራችሁ በንቃት ሳትሳተፉ ቀራችሁ። ዛሬም እንቅልፍ ላይ ናችሁ። ነገም እስከምትወጉ ድረስ ከተኛችሁበት የምትነቁ አይመስለኝም። ነገሮችን በቀላሉ በጊዜ በተገቢው መልክ ማስሄድ እየተቻለ፤ ለምን በዓይናችን ካላየን አናምንም እንደምንልና ራሳችንን ላላስፈላጊ መስዋዕትነት እንደምናጋልጥ አይገባኝም። ይህን ያክል ንቃተ ህሊናችን ደክሟል ማለት ነው? መቼ ነው የምንነቃው?

ከላይ የጻፍኩትን እንኳ ጨርሶ ታግሶ ያነበበ ስንት ነው? ሐቂቃ እንዲህ አይነቱ የሚያመጣው መዘዝ እንዲህ ቢነግሩት የማይገባውን ኳስ፣ ፊልም፣ ድራማ፣ ሙዚቃ፣ ጫት… ያደነዘዘውን ብቻ የሚጎዳ በነበር ደስ ይለኛል።

እንደው አላህ በጥበቡ እያከሸፈልን እንጂ እኛማ ጥልቅ እንቅልፍ ውስጥ ነን።

የያኔዎቹን ጽሑፎች በዚህ ሊንክ ታገኟቸዋላችሁ፦

https://t.me/MuradTadesse/15402
https://t.me/MuradTadesse/15513
7.2K viewsedited  18:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-31 20:48:48
በቀላል ለማይገባችሁ…

ለምሳሌ እዚህ በምትመለከቱት ላይ ከ25ቱ ተሳታፊዎች መካከል ወደ ክልል ተለይተው የሚላኩት 2ት ብቻ ናቸው ብያችሁ ነበር አይደል? (ግን ያነበባችሁትም አይመስለኝም። ምክንያቱም ቀልድና ዛዛታ ላይ እንጂ ቁም ነገሩ ላይ አብዛሃኛው ቁብ የለውም።)

ለማንኛውም ለስሙ ከ25ቱ መካከል 5 ሙስሊሞች አሉበት። ይሄውም ጥሩ የሚባል ነው። ግን ምን ዋጋ አለው? 5 ከ20 ጋር አይመጣጠንምና ነፃነትና አሰፋሽ ወልደ ገብርኤል ተመርጠዋል። 5ቱ ሙስሊሞች ከጀርባቸው ከናለው ህዝብ እንዲሁ ቀሩ ማለት ነው። እነ አሰፋሽ የሚላኩት የነዚህንም አጀንዳ ይዘው ነው literally. ግን እንኳን የነ ዘሃራን አጀንዳ የሚያቀርቡበት የራሳቸውን ከጨረሱ ደግ ነው።

በአጭሩ በየቦታው እየሆነ ያለው፤ «እንዳያማህ ጥራው እንዳይበላ ግፋው!» እንዲሉ ነው አበው።

አልተሳተፉም እንዳንባል የተወሰነ ሰው ያካትታሉ። ግን ውጤት እንዳይኖረን ከግማሽ በታች ያደርጉትና ያስቀሩታል።

ህዝበ ሙስሊሙ በሃገሪቱ ከግማሽ በላይ ስለሆነ፤ ከ25ቱ በትንሹ 13ቱ ሙስሊሞች መሆን ነበረባቸው። ዋና የኮሚሽኑ አባላትም ከ11ዱ በትንሹ 6ቱ ሙስሊም መሆን ነበረባቸው። በዚህ አካሄዳቸው ኢ-ተጋማሽ ቁጥር ባያደርጉት ራሱ ስለማንቀራረብ በነፃነት ያሻቸውን መሥራት ይችላሉ።


እየነቃን ወገን! በርግጥ ጥልቅ እንቅልፍ ውስጥ ነን! አንዳንዶች በምን መርፌ ብትወጉ እንደምትባንኑ ባላውቅም!

||
t.me/MuradTadesse
8.2K views17:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-31 18:14:07
በአጠቃላይ፦ ሃገራዊ ምክክር ሃገራት ብዙ ጊዜ አለመግባባትና ግጭት ውስጥ ሲገቡ፤ ምንድን ናቸው የሚለያዩን አጀንዳዎች ብለው ቁጭ ብለው ተወያይተው መፍትሄ የሚያበጁበት ነው። በዚህ ሂደት ጦር አንግቦ ገዢውን መንግስት የሚዋጋ ሁሉ ይሳተፋል። ከማያግባቡ አጀንዳዎች መካከል አንዱ ህገ መንግስቱ ከሆነ እነዚያ የማያግባቡ አንቀፆች እንዲወገዱና እንዲሻሻሉ እስከማድረግ ደረጃ ይደርሳል። ስለሆነም እንደ ሙስሊም…
10.7K views15:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-31 18:13:44 በአጠቃላይ፦ ሃገራዊ ምክክር ሃገራት ብዙ ጊዜ አለመግባባትና ግጭት ውስጥ ሲገቡ፤ ምንድን ናቸው የሚለያዩን አጀንዳዎች ብለው ቁጭ ብለው ተወያይተው መፍትሄ የሚያበጁበት ነው። በዚህ ሂደት ጦር አንግቦ ገዢውን መንግስት የሚዋጋ ሁሉ ይሳተፋል። ከማያግባቡ አጀንዳዎች መካከል አንዱ ህገ መንግስቱ ከሆነ እነዚያ የማያግባቡ አንቀፆች እንዲወገዱና እንዲሻሻሉ እስከማድረግ ደረጃ ይደርሳል።

ስለሆነም እንደ ሙስሊም በዚህች ሃገር ላይ ያሉን አጀንዳዎች በዋናነት ይታወቃሉ። እነዚያ አጀንዳዎቻችን መቅረብ አለባቸው። የራሳችንን አጀንዳ እንደምናቀርበው ሁሉ ሌሎች የሚያቀርቡትም አጀንዳ የኛን እምነት የማይነካ መሆኑን ማረጋገጥ አለብን። የሚነካ ከሆነ እነርሱ አጀንዳ ስላሉት ብቻ ተቀባይነት እንዳያገኝ የመቃወም መብት አለን።
በአጭሩ ሚናችን ሁለት ነው፥ አንድ፦ የራሳችንን አጀንዳዎች ማቅረብ፣ ሁለት፦ ሌሎች የሚያቀርቡት አጀንዳ ድናችንን አለመንካቱን ማወቅ።
ለምሳሌ፦ አንዱ ሒጃብና ኒቃብ መለበስ የለበትም ቢል መቃወም ግድ ነው።

ግን የራሳችንን አጀንዳ እንድናቀርብም ሆነ የሚጎዳንን እንድንቃወም እድሉን አላገኘንም።
ዝርዝሩን ዶክመንታቸው ላይ ካያችሁት፤ ከወረዳ ጀምሮ እስከ ፌዴራል ድረስ የኃይማኖት ተቋማት እንደ አንድ ተሳታፊ ናቸው። ሌሎች ተቋማትም አሉ። እኛ ደግሞ እንኳን እነዛ  ተቋማት ላይ ላይ የኃይማኖት ተቋማት ተብየው ላይም ቁጥራችንን የሚመጥን ውክልና የለንም።


ስለዚህ ምን እየሆነ ነው? ከወረዳ ጀምሮ የህዝቡን አጀንዳ አቅራቢ የሆኑ የስብሰባ ተሳታፊዎች ሲለዩ፤ በተለያዩ ዘዴዎችና መስፈርቶች ህዝበ ሙስሊሙ ቁጥሩን በማይመጥን መልኩ ተወክሏል። እነዚያኑም እያጣሩና ቁጥራቸውን እየቀነሱ ሲመጡ፤ በድምፅ ብልጫ በሚል አብዛሃኛዎቹን ከወረዳ እንዳያልፉ አድርገዋቸዋል።

መጨረሻ ላይ እጅግ በጣም ወሳኝ የሚባሉት መሠረታዊ አጀንዳዎች የትኞቹ ናቸው? ተብሎ ከወረዳ ጀምሮ ከአራቱም አቅጣጫ የተሰባሰበው አጀንዳ ሁሉ ፌዴራል ላይ ሲጣራ፤ ምናልባት በሆነ መልኩ እየተንገዳገደ ፌዴራል ድረስ የደረሰ የኛ አጀንዳ ካለ፤ በእጅ ብልጫ "ይህ ለጊዜው አንገብጋቢና መሠረታዊ አይደለም!" በሚል ይቀራል።


በአጭሩ፤ ከወረዳ ጀምሮ እስከ ፌዴራል ድረስ ከዚህ የምክክር ኮሚሽን አንድም ነገር አትርፈን የማንወጣበት ተጨባጭ ላይ እንገኛለን።

ምናልባት፤ በኃይማኖት ተቋማት በኩል ከመጅሊስ በኩል የተወሰኑ ሰዎችን ወክሎ ይልካል። የነርሱም ድምፅ በአብላጫ ድምፅ ይባልና ይቀበራል።

ከተፅዕኖ ፈጣሪ፣ ከታዋቂ ግለሰቦች፣ ከንግዱ ማኅበረሰብ፣ ከአክቲቪስቶች፣ ከሚዲያ አካላት… ይባልና የምናውቃቸው ታዋቂ ሰዎች በየዘርፉ በተሳታፊነት ይገቡ ይሆናል። ግን ያነሱት አጀንዳ እዛ ከተሰበሰቡበት አዳራሽ አያልፍም። ምክንያቱም ሌሎችን በቁጥር አብልጠው ስለሚያሳትፏቸው አጀንዳ ሲጣራ የነርሱ ይወድቃል።


በመጨረሻም፦ አንዳንዶች በዚህ ተሳታፊነት በሆነ መልኩ ሲመረጡ ስልጣን የተሰጣቸው መስሏቸው የኡማው ወኪል እንደሆኑ አስበው ሊያወሩ ይችላሉ። ግን ድምፃቸው እንደሚደመሰስ የዘነጉ ይመስላል።

√ መሳተፋችን እንደ ኡማ ያሉብንን አጀንዳዎች እናቀርባለን፣ ተከታትለን እናስፈፅማለን።

√ ካልተሳተፍን የኛ አጀንዳዎች ተቀብረው የሌሎች አጀንዳ ተፈፃሚ ሆኖ በነርሱ ህግ እንመራለን። እንኳን ሌላ አጀንዳ ተይዞላቸው የበፊቱንም አልቻልነውም። ምናልባት እነዚህን ህገ መንግስቱን እስከማስቀየር ደረጃ የሚደርሱ አጀንዳዎች ማን ያስፈፅማቸዋል ካላችሁ ራሱ መንግስት ነው። በተለይ የኛ ጉዳዮች በብዛት ከሌሉና የነርሱ ከበዙ እንደማያስፈፅማቸው ምን ያጠራጥራል?  ለምን ይህ ይሆናል ብትል እንኳ ሰሚ የለህም። ምክንያቱም ይህን የማስፈልመው ሃገራዊ ኮሚሽኑ አንተን ጭምር ተሳተፍ ብሎ እድሉን ሰጥቶህ የተዋጣውን አጀንዳ ነው፣ ከተቃወምክ ያኔውኑ በተቃወምክ፣ ይሄ አጀንዳዬ ቀረ ካልክ ያኔውኑ ባልክ… እያለ አፍህን ያሲዝሃል። ስለዚህ ወይ ከወዲሁ የለሁበትም በል፣ አሊያ ደግሞ አለሁበት ትል ዘንድ በበቂ ሁኔታ በንቃት ተሳተፍና አጀንዳህን እስከ ላይ ድረስ አስጨብጥ።



መፍትሄው አንድና አንድ ብቻ ነው፦ የምክክር ኮሚሽኑ ከወረዳ እስከ ፌዴራል ድረስ ተሳታፊን የሚለይበትን መስፈርት ይቀይር፣ ህዝበ ሙስሊሙ ቁጥሩን የሚመጥን የተሳታፊ ውክልና ኮታ ይሰጠው። ይህ ካልሆነ ታዋቂ ሰዎቻችንም ቢሳተፉ ዋጋ የለውም። ምክንያቱም ሃሳባቸው ውድቅ ስሚደረግ።




ይህን ጉዳይ መጅሊስ በደንብ ያስብበትና ሚዲያዎችን በሙሉ ጠርቶ መግለጫ ያውጣ። ቀነ ገደብ ያስቀምጥና ኮሚሸኑ እስከዛ ቀን ድረስ አሠራሩን ህዝበ ሙስሊሙን ባማከለ መልኩ ካላስተካከለ፤ ከዚህ የምክክር መድረክ ራሱን ማግለሉን ያሳውቅ። ጊዜ የለንም! ምንም እንኳ ሊያራዝሙለት ቢችሉኝ 3ኛ አመቱ ላይ ስለሆነ እየተጣደፈ ነው። እንፍጠን!

ጨረስኩ!


√ የሚጠቅሟችሁ ፋይሎች፦
1) ተሳታፊዎችን ለመለየት እና አጀንዳ ለማሰባሰብ የተዘጋጀ አሰራር ስርዓት፦ የሶፍት ኮፒ መገኛ፦https://t.me/MuradTadesse/35996?single

2) የኮሚሽኑ የሦስት ዓመት ስትራቴጂያዊ ዕቅድ 2015-2017፦https://t.me/MuradTadesse/35996?single

3) የኮሚሽኑ ማቋቋሚያ አዋጅ፦ አማርኛና እንግሊዝኛ፦ https://t.me/MuradTadesse/35996?single
10.2K viewsedited  15:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-31 18:13:44 ስለ ሃገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ምንነትና አላማ
===============================
(ኮሚሽኑ ማነው? በማንና በምን ምክንያት ተቋቋመ? አላማውስ ምንድን ነው? አላማውን የማስፈጸም አቅሙስ እስከ ምን ደረጃ ድረስ ነው?…)
°
[ሁሉም ሙስሊም ስለ ጉዳዩ ግንዛቤ ይኖረው ዘንድ በጥሞና ታግሶ ያንብበው፣ ከዚያም ቢያንስ ለ10 ሰው በተለያዬ መልኩ እናሰራጭ!]
||
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት በአዋጅ ቁጥር 1265/2014 E.C. የተቋቋመ ተቋም ነው። ተቋሙ እንደአስፈላጊነቱ የሚራዘም የሦስት ዓመት ዕድሜ እንደሚኖረው በአዋጁ ተጠቅሷል። ኮሚሽኑ ለሀገራዊ መግባባት ወሳኝ በሆኑ ጭብጦች ላይ ቁልፍ በሆኑ ባለድርሻ አካላት መካከል ውጤታማ ውይይት እንዲደረግ ሁኔታዎችን እንዲያሳልጥ ነበር የተቋቋመው። ኮሚሽኑ በምክክር ከሚያገኛቸው ምክረ ሃሳቦች በመነሳት የሀገሪቱን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ የሚያስችልና ሀገራዊ መግባባት ለመፍጠር የሚያግዙ ምክረ ሃሳቦችን ለሚመለከተው አካል ያቀርባል።

•
√ አላማ፦
በኮሚሽኑ ማቋቋሚያ አዋጅ አንቀፅ 6 ላይ እንደሰፈረው ከሆነ አላማው፦
«በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች መካከል እንዲሁም በመንግሥት እና በሕዝብ መካከል ያለውን ግንኙነት የማሻሻል፣ መተማመን የሰፈነበትና አዲስ የፖለቲካ ሥርዓት የመፍጠር ፣ ለዘመናት ሲንከባለሉ የመጡ ውስጣዊ ችግሮችን በውይይት ለመፍታት የሚያስችል የፖለቲካ ባህል ለማዳበር እና ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ምቹ መደላድል ለመፍጠር፣ ወቅታዊ ችግሮች ዘላቂ በሆነ መንገድ ተፈተው አስተማማኝ ሰላም የሚረጋገጥበትን የፖለቲካ እና የማህበራዊ መደላድል ለማመቻቸት እንዲሁም ለአገራዊ መግባባት እና ጠንካራ ቅቡልነት ያለው ሀገረ መንግሥት ለመገንባት ጽኑ መሠረት ለመጣል እንዲሁም ወቅታዊ ችግሮች ዘላቂ በሆነ መንገድ ተፈተው አስተማማኝ ሰላም የሚረጋገጥበትን የፖለቲካ እና የማኅበራዊ መደላደል ለማመቻቸት» የሚል ነው።
አላማው ጥሩ ነበር። ግን መሬት ላይ ያለው ትግበራው ከወረቀቱ በተቃራኒ ነው።

•
√ የኮሚሽኑን ምክር ቤት አባላት በተመለከተ፦
በአዋጅ ቁጥር 1265/ 2014 E.C. የተቋቋመው ይህ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን በሕዝብ ከተጠቆሙ ተብሎ 632 ሰዎች መካከል 11 ሰዎችን በኮሚሽነርነት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሁለተኛ አስቸኳይ ጉባዔ  ሹሟል። ዋና ኮሚሽነሩና ስብሳቢው ፕ/ር  መስፍን አርአያ ይባላል። ማን እንደሆነ አልነግራችሁም። በቅርበት የሚያውቁትን የትግራይ ወንድሞችን ጠይቋቸው ሙስሊሞች ላይ ስላለው አቋም። ም/ዋና ኮሚሽነር ሂሩት ገ/ሥላሴ ትባላለች። ሌሎች በአባልነት ደረጃ ያሉት፦ ዶ/ር አምባዬ ኡጋቶ፣ ዶ/ር አይሮሪት ሙሐመድ፣ ብሌን ገ/መድህን፣ መላኩ ወ/ማርያም፣ አምባሳደር ሙሐመድ ድሪር፣ ሙሉጌታ አጎ፣  ዶ/ር ተገኘ ወርቅ ጌቱ፣ ዶ/ር ዮናስ አዳዬ እና ዘገየ አስፋው ናቸው።

ስለዚህ ከ11ዶቹ መካከል ስማቸው እንደሚያሳየው ከሆነ 2ቱ ሙስሊም ናቸው። ይህ ማለት ገና ከኮሚሽኑ አወቃቀር ስንነሳ 50+% ህዝበ ሙስሊም 18% ውክልና ብቻ ነው ያለው። እነዚሁስ ሁለቱ እነማን ናቸው? የእውነት የኡማውን አጀንዳዎች ጠንቅቀው አውቀው የሚያስሄዱ ናቸው ወይ? የሚለው እንዳለ ሆኖ፤ የተለመደው ዲሞክራሲያዊ አሠራር የሚሉት ሐቅ መደፍጠጫ "የእጅ ብልጫ" የሚባል ነገር ስላለ፤ የነዚህ የ2 ሰዎች መኖር ለስም እንጂ ምንም አይነት ውሳኔ ማስፈጸም አይችሉም። ምክንያቱም በየትኛውም ታዕምር 2 እና 9 ስለማይቀራረቡ።

•


√ አሠራሩን በተመለከተ፦
```````````
የመጀመሪያ ሥራው የተሳታፊ አካላትን መለየት ነው። ተሳታፊ አካላት ማለት የሆነን አካባቢ ማኅበረሰብ ወክለው የዚያ ማኅበረሰብ አጀንዳ ይህ ነው ብለው የሚያቀርቡ ሰዎችን መመልመል ነው። እነዚህን ሰዎች ለመለየት ቀጥታ ማኅበረሰቡን ከራሳችሁ የሆነ ሃሳባችንን ይገልፅልናል የምትሉትን ታማኝ ሰዋችሁን ስጡኝ ብሎ አይደለም የለየው።

ይልቁንም በተሳታፊ ልየታ ሥራ ላይ እገዛን ያደርጉልኛል ብሎ ያመነባቸውን የሚከተሉትን ሰባት ተባባሪ አካላት ለይቷል፡፡
 
– የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበራት ምክር ቤት
– የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት
– የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር
– የኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ የእድሮች ማህበራት ጥምረት
– የኢትዮጵያ ሀይማኖት ተቋሟት ጉባኤ
– የወረዳ ፍርድ ቤት ዳኞች
– የወረዳ (ልዩ ወረዳ) አስተዳደር ተወካዮች

አንዱና ዋነኛው ችግር ከዚህ ይጀምራል። ሲጀመር እነዚህ ተሳታፊን በመለየቱ ረገድ ያግዙኛል ያላቸው አካላት የኃይማኖትን ተቋማት ጉባዔን ጨምሮ ሁሉም የሙስሊሙን ቁጥር ያላማከሉ ቀድሞውንም አነስተኛ ሙስሊም ያለባቸው ተቋማት ናቸው። ስለዚህ እነርሱ የጠቆሙት ሁሉ ሙስሊሙን አይወክልም።

ከነዚህ ተባባሪ አካላት ባሻገር ኮሚሽኑ በራሱ የመረጣቸውም አሉ። ግልፅ ባልሆነ መስፈርትና አካሄድ። ልክ ባለፈ አንድ ወንድም መራጯን ስለምንተዋወቅ ብቻ ስጠይቃት አንተ ትገባለህ አለችኝ እንዳለው በራሳቸውኝ ተሳታፊን ይለያሉ።

√ ከዚያስ? የመጀመሪያው ሥራቸው ያኔ መጋቢት 2014 ላይ በይፋ ሥራ ሲጀምሩ ከወረዳዎች በተለያዩ አካባቢዎች እየዞሩ ተሳታፊን መለየት ጀመሩ። በምን መልኩ? ከላይ ባልኳችሁ መሠረት። ወረዳን እንደ አነስተኛ መነሻ መዋቅር የተጠቀሙት ከብዙ ምክንያት አንፃር ነው።
በኢትዮጵያ ክፍለ ከተሞችንና የከተማ አስተዳደሮችን ጨምሮ ከ 1ሺ 300 የሚሆኑ ወረዳዎች አሉ፡፡ እያንዳንዱ ወረዳ በአማካይ 10 ቀበሌዎች አሉት ቢባል ከ13ሺ የማያንሱ ቀበሌዎች ይኖራሉ እንደማለት ነው፡፡ አንድ ቀበሌ በአማካይ 7 ጎጦች ቢኖሩት ከ91ሺ በላይ ጎጦች ይኖራሉ እንደማለት ነው፡፡ ስለዚህ ከጎጥና ከቀበሌ ከሚነሱ ከወረዳ መነሳቱ የተሻለ ያፈጥናል፣ ወጪም ይቀንሳል።


በእያንዳንዱ ወረዳ በአማካይ ቁጥራቸው ከ 7-9 የሚደርስ ሰዎች በሂደቱ ይሳተፋሉ፡፡ በአብዛኞቹ ወረዳዎች በተባባሪነት የሚሳተፉ አካላት በዋናነት 7 ናቸው፡፡ እንደየ አከባቢው ሁኔታ ለሂደቱ ስኬት ጠቄማታቸው የተማነባቸው አካላት ሊካተቱ ይችላሉ፡፡ እነዚህ እነማን እንደሆኑ አልነግራችሁም።

በመጀመሪያው ደረጃ በተባባሪ አካላቱ እገዛ ከየማህበረሰብ ክፍሉ የተለዩት 10 ተሳታፊዎች አመቺ ወደ ሆኑ የዞን ከተሞች እንዲሰባሰቡ ይደረጋል፡፡ የመጀመሪያ ደረጃ ተሳታፊዎች በቀጣይ የሚያከናውኑት ተግባር ኮሚሽኑ በክልል ደረጃ በሚያዘጋጃቸው መድረኮች ላይ ወረዳቸውን በመወከል የአጀንዳ ሀሳቦችን የሚሰጡ ተወካዮችን መምረጥ ነው፡፡ እዚህ ላይ ምን ቁማር ይሠራል መሰላችሁ፦ መጀመሪያ በተባባሪ አካላት በተባሉትና በራሳቸው ወረዳ ላይ ተሳታፊዎችን ሲመርጡ በጣት የሚቆጠሩ ሙስሊሞችን ያስገቡ ይሆናል። ግን ከነዚህ ወረዳ ላይ ከተመረጡት መካከል ወደ ዞንና ክልል 2 ሰው ተመርጦ ሲላክ አሁንም በእጅ ብልጫ ይባልና እነዚያ ወረዳ ላይ የተወከሉት ሙስሊሞች ከወረዳው ሳያልፉ ይቀራሉ። ታዲያ ሌላኛው ሙስሊም ያልሆነው በምን እዳው ነው አንተን ወክሎ ዞንና ክልል ላይ የአንተን አጀንዳ የሚያቀርብልህ? ውሃ በላው ማለት ነው የአንተ አጀንዳ።


*
√ የኮሚሽኑ አራት የትኩረት ቦታዎች፡-
1) ክልሎች 2) ከተማ መስተዳደሮች 3) በፌደራል ደረጃ  4) በዲያስፖራ ነው። በነዚህ በአራቱም ላይ እነማን በምን ያልክ የተወካይ መጠን ይወከላሉ የሚለው ራሳቸው ዲክመንት ላይ ስላለ ከዚያ አንብቡ።
10.0K views15:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-31 18:13:00 ተሳታፊዎችን-ለመለየት-እና-አጀንዳ-ለማሰባሰብ-የተዘጋጀ-አሰራር-ስርዓት.pdf
9.4K views15:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-27 14:40:16
ግብፅና እስራኤል እየተፈታተሹ ይሆን እንደ¿
6.4K views11:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-27 10:38:40
At least 35 displaced Palestinians were killed and dozens were injured by Israeli bombardment targeting a camp for displaced civilians in Rafah, Gaza, on May 26.

A paramedic reported a large number of dead children were retrieved from the Israeli bombardment, including a child without a head and children whose bodies had been shredded to pieces
10.8K views07:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ