2022-07-08 14:50:16
የእርጅና ቅናሽ ስሌት ዘዴዎች
ግብር ከፋይ ለግብር አከፋፈልና ለሌላ አላማ ለሚያዘጋጃቸው የሂሣብ ሪፖርቶች በፋይናንስ ሪፖርት አቀራረብ ደረጃዎች መሠረት አንድ ዓይነት የእርጅና ቅናሽ ዘዴ መጠቀም አለበትዋጋቸው ለሚቀንስ ሀብቶች ሁሉ መጠቀም ያለበት አንድ ዓይነት የእርጅና ቅናሽ ዘዴ ነው፡፡
ሁለት አይነት የእርጅና ቅናሽ ዘዴዎች ያሉ ሲሆን
ቀጥተኛ የእርጅና ቅናሽ እና
ዋጋው እየቀነሰ የሚሄድ የእርጅና ቅናሽ ዘዴ በመባል ይታወቃሉ፡፡
ታክስ ከፋዮች የሚፈቀድላቸውን የእርጅና ቅናሽ በቀጥተኛ ወይም ዋጋው እየቀነሰ በሚሄድ የእርጅና ቅናሽ ዘዴ መሠረት ሊወስኑ ይችላሉ፡፡
ቀጥተኛ የእርጅና ቅናሽ ዘዴ
የሚከተሉት ሀብቶች የእርጅና ቅናሽ መሰላት ያለበት በቀጥተኛ የእርጅና ቅናሽ ዘዴ ብቻ ይሆናል፡፡
• ግዙፋዊ ሀልዎት የሌላቸው የንግድ ሥራ ሀብቶች፣
• በማይንቀሳቀስ ሀብት ላይ የሚደረግ ማሻሻያ፤
በማይንቀሳቀስ ሀብት ላይ የሚደረግ ማሻሻያ የእርጅና ቅናሽ ሲሰላ በማይንቀሳቀስ ሀብት ላይ የሚደረግ ማሻሻያ ወጪ ማሻሻያው ያረፈበትን መሬት ወጪ መጨመር የለበትም፡፡
ማንኛውም ግብር ከፋይ “አስተላላፊ” ተብሎ ከሚጠራ ግንኙነት ያለው ሰው ላገኘው እና በአስተላላፊው ሙሉ የእርጅና ቅናሽ ላገኘበት ዋጋው የሚቀንስ ሀብት ወይም ግዙፋዊ ሀልዎት የሌለው የንግድ ሥራ ሀብት የእርጅና ቅናሽ ማግኘት አይችልም ፡፡
ለአንድ ግብር ከፋይ በአንድ የግብር ዓመት ዋጋው ለሚቀንስ ሀብት ወይም ግዙፋዊ ሀልዎት ለሌለው የንግድ ሥራ ሀብት የተፈቀደው በቀጥተኛ የእርጅና ቅናሽ ዘዴ መሠረት የሚወሰን የእርጅና ቅናሽ መጣኔ በሀብቱ ወጪ ላይ ተፈጻሚ በማድረግ ይሰላል፡፡
ዋጋው እየቀነስ የሚሄድ የእርጅና ቅናሽ ዘዴ
• ለአንድ ግብር ከፋይ በአንድ የግብር ዓመት ዋጋው ለሚቀንስ ሀብት የተፈቀደው ዋጋው እየቀነሰ በሚሄድ የእርጅና ቅናሽ ዘዴ መሠረት የሚወሰን የእርጅና ቅናሽ መጣኔ በዓመቱ መጀመሪያ ባለው የሀብቱ የተጣራ የመዝገብ ዋጋ ላይ ተፈጻሚ በማድረግ ይሰላል፡፡
• በአንድ የግብር ዓመት ዋጋው በሚቀንስ ሀብት ላይ ተፈጻሚ ከሆነ፣የሀብቱ የተጣራ የመዝገብ ዋጋ ሀብቱ በግብር ዓመቱ የንግድ ሥራ ገቢን ለማግኘት ብቻ ጥቅም ላይ እንደዋለ በመውሰድ ይሰላል፡፡
• የግብር ከፋዩ ዋጋው የሚቀንስ ሀብት ቀሪ ዋጋ ከብር ሁለት ሺህ በታች ከሆነ በአንድ ጊዜ በወጪነት ይያዛል፡፡
• ዋጋው እየቀነሰ የሚሄድ የእርጅና ቅናሽ መጠን የሚሰላው በግብር ዓመቱ መጀመሪያ በነበረው የተጣራ የመዝገብ ዋጋ ላይ የእርጅና ተቀናሽ መጣኔውን በማስላት ይሆናል፡፡
በግብር ዓመቱ መጀመሪያ የነበረው የተጣራ የመዝገብ ዋጋ ማለት፡- ከመጀመሪያው የመዝገብ ዋጋ በየጊዜው የተቀነሱ የእርጅና ተቀናሾች ከተቀነሰ በኋላ የሚገኝ ዋጋ ነው፡፡
1.2K viewsMOR EAST, 11:50