2022-07-01 10:46:52
ከተጨማሪ ዕሴት ጋር የተያያዙ አስተዳደራዊ ቅጣቶች
• በጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ መሰረት ለጨማሪ እሴት ታክስ መመዝገብ ያለበት ሰው ሳይመዘገብ የቀረ እንደሆነ፤ መመዝገብ ከነበረበት ቀን ጀምሮ ለመመዝገብ እስካመለከተበት ወይም በባለስልጣኑ አነሳሽነት እስከተመዘገበበት ቀን ድረስ ላለው ለእያንዳንዱ ወር ወይም ከወሩ ከፊል ለሆነው ጊዜ ብር 2 ሽህ (ሁለት ሽህ ብር) ቅጣት ይከፍላል፡፡
• በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 1 መሰረት ከሚጣለው ቅጣት በተጨማሪ፤ ንዑስ አንቀፁ ተፈፃሚ የሚሆንበት ሰው መመዝገብ ከነበረበት ቀን ጀምሮ ለመመዝገብ እስካመለከተበት ወይም በባለስልጣኑ አነሳሽነት እስከተመዘገበበት ቀን ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ በፈፀመው የተጨማሪ እሴት ታክስ የሚከፈልበት ግብይት ላይ ሊከፈል ይገባ የነበረውን የተጨማሪ እሴት ታክስ 100 % (መቶ በመቶ) ቅጣት ይከፍላል፡፡
• በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 2 መሰረት የሚጣለው ቅጣት በንዑስ አንቀፁ በተገለፀው ጊዜ ውስጥ ታከስ ከፋዩ በፈፀመው የተጨማሪ እሴት ታክስ የሚከፈልበት ግብይት ላይ ሊከፈል ይገባ የነበረውን የተጨማሪ እሴት ታክስ አያስቀርም፡፡ ሆኖም ታክስ ከፋዩ በዚህ ጊዜ ውስጥ ባከናወነው ግብይት ላይ የከፈለው የተርን ኦቨር ታክስ ካለ ተቀናሸ ይደረግለታል፡፡
• ማንኛውም ሰው ሆን ብሎ ሊከፈል የሚገባውን የተጨማሪ እሴት ታክስ ለማሳነስ ወይም በግብቱ ላይ ተመላሽ የሚደረገውን የታክስ መጠን ለመጨመር በማሰብ ትክክለኛ ያልሆነ የታክስ ደረሰኝ የሰጠ እንደሆነ ብር 50 ሽህ (ሃምሳሽህ ብር) ቅጣት ይከፍላል፡፡
• ደረሰኝ መስጠት ሲገባው ያልሰጠ ማንኛውም ታክስ ከፋይ ለገዥ ባልሰጠው ለእያንዳንዱ ደረሰኝ ብር 50 ሽህ (ሃምሳ ሽህ) ቅጣት ይከፍላል፡፡
• በታክስ ማስታወቂያ የተገለጸው የታክስ መጠን ታክስከፋዩ ሊከፍል ከሚገባው ትክክለኛ የታክስ መጠን ያነሰ እንደሆነ ( “የታክስ ጉድለት” ልዩነት እና የልዩነቱን መጠን በ10% ይቀጣል፡፡ይህንኑ ከደጋገመ ልዩነቱን ከ30-50% ይከፍላል፡፡
3.0K viewsMOR EAST, 07:46