Get Mystery Box with random crypto!

M.O.R East Addis Ababa Branch

የቴሌግራም ቻናል አርማ moreastaddisabababranch — M.O.R East Addis Ababa Branch M
የቴሌግራም ቻናል አርማ moreastaddisabababranch — M.O.R East Addis Ababa Branch
የሰርጥ አድራሻ: @moreastaddisabababranch
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 5.57K
የሰርጥ መግለጫ

Ministry Of Revenues (MOR) is the body responsible for collecting
revenue from customs duties and domestic taxes.

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 17:43:18 ከሽያጭ ታክስ/ Turn over tax/ ክፍያ ነፃ ግብይቶች

የሽያጭ ታክስ/ Turn over tax/ ቀጥተኛ ካልሆኑ ታክስ አይነቶች የሚመደብ የታክስ አይነት ሲሆን ለተጨማሪ እሴት ታክስ ያልተመዘገቡ ግብር ከፋዮች በአገር ውስጥ በሚከናውኑት ግብይት ወይም አገልግሎት ነጻ ከተደረጉት በስተቀር የዕቃ ወይም የአገልግሎት ሽያጭ ወቅት በየደረጃው የሚጣል የታክስ አይነት ነው፡፡

ከሽያጭ ታክስ/ Turn over tax/ ክፍያ ነፃ ግብይቶች፡-

• ቢያንስ ሁለት ዓመት ያገለገለ የመኖርያ ቤት ሽያጭ እና የመኖርያ ቤት ኪራይ
• የፋይናንስ አገልግሎቶች
• ለሳንቲሞችና መዳልያዎች ጥናት አገልግሎት ከሚውሉት በስተቀር የአገር ውስጥና የውጭ አገር ገንዘቦች እና የዋስትና ሰነዶች ማሰራጨት
• በሃይማኖት ድርጅቶች የሚሰጡ የእምነት ወይም ከአምልኮ ጋር የሚገናኙ አገልግሎቶች
• የሕክምና አገልግሎቶች እና አግባብ ባለው የመንግስት መሥርያ ቤት በሚወጣ መመርያ መሠረት ነፃ የተደረጉ አገልግሎቶች
• በትምህርት ተቁዋማት የሚሰጡ የማስተማር አገልግሎቶች እንዲሁም ለሕፃናት ጥበቃ በመዋእለ ሕፃናት የሚሰጡ አገልግሎቶች
• ለሰብአዊ ዕርዳታ የሚውሉ ዕቃዎችና አገልግሎቶች፣ የኤሌክትሪክ፤የኬሮሲን እና የውሃ አቅርቦት፣ የትራንስፖርት አገልግሎቶች
• ማንኛውም የስራ እንቅስቃሴ ለማከናወን ለሚስጥ ፈቃድ ለመንግስት የሚሰጥ ክፍያ
• ከ60% በላይ ሠራተኞቹ አካል ጉዳተኞች የሆኑበት አካል ጉዳተኞችን ቀጥሮ የሚያሰራ ድርጅት የሚቀርባቸው ዕቃዎችና አገልግሎቶች
• መፃሕፍት( ወደ ሀገር የሚገቡ፣ በሀገር ውስጥ የሚሸጡ እና መጻህፍትን ወቅታዊ ለማድረግ የሚወጡ እትሞች )
• የምግብ እህል (ጤፍ፤ ስንዴ፣ ገብስ፣ በቆሎ፣ ማሽላ፣ ዘንጋዳ ፣ዳጉሳ ፣ አጃ፣ እንዲሁም የነዚህ ዱቄት ከጥራጥሬ አተር ፣ባቄላ፣ምስር ፣አኩሪ አተር፣ሽንብራ ፣ግብጦ ፣ጓያ )
• የቅባት እህሎችም ሆኑ ፕሮሰስ የተደረጉ ምግቦች፣ ፉርሽካም ጭምር የታክስ መነሳት አይመለከታቸውም ፡፡
1.1K viewsMOR EAST, 14:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 17:43:02
1.0K viewsMOR EAST, 14:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 16:07:28

2.1K viewsMOR EAST, 13:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 18:38:39 የነገ አገር ተረካቢ ህጻናት ላይ መስራት አገርን መገንባት ነው - አቶ ገዛኸኝ ታምሩ

ማክሰኞ ነሐሴ 24 ቀን 2014 ዓ.ም (ምስራቅ ገቢዎች)በገቢዎች ሚኒስቴር የምስራቅ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በህፃናት ማቆያ ማዕከሉ ከየካቴት 2012 ዓ.ም ጀምሮ ሲንከባከባቸው የነበሩ ህፃናትን እድሜያቸው ለትምህርት በመድረሱ ምክንያት የአሸኛኘት መርኃግብር አካሄዷል፡፡

የህፃናት ማቆያ ማዕከሉ በቅ/ጽ/ቤት ደረጃ መገንባቱ የሚያጠቡ እናቶች ልጆቻቸውን በቅርበት እንዲከታተሉ፣ የሴት ሠራተኞችን ጫና በመቀነስ ሙሉ ጊዜቸውን በሥራ ላይ በማዋል ለገቢ አሰባሰቡ አወንታዊ ድጋፍ እንዲያደርጉ ማስቻሉን የቅ/ጽ/ቤቱ ሥራ አስኪያጅ አቶ ገዛኸኝ ታምሩ በንግግራቸው አመላክተዋል፡፡

ህጻናት አስፈላጊውን እንክብካቤ እንዲያገኙና ንቁ ሆነው እንዲያድጉ የህጻናት ማቆያ ማዕከሉ ሚናው ከፍተኛ መሆኑን የገለፁት ሥራ አስኪያጁ የነገ አገር ተረካቢ ህጻናት ላይ መስራት አገርን እንደመገንባት ይቆጠራል ሲሉ ገልፀዋል፡፡

ልጆቻቸውን በማዕከሉ የሚያውሉ ሰራተኞች በሽኝት ሥነ ሥርዓቱ ወቅት በሰጡት አስተያየት ማዕከሉ በሚሰጠው አገልግሎት ደስተኛ እንደሆኑና የልጆቻቸው በእንክብካቤ መቆየት ስራቸውን በተረጋጋ መንፈስ እንዲሰሩ እንዳስቻላቸው ገልጸዋል፡፡

ለሰራተኞች ውጤታማነት እና ለልጆች ጤንነት ማዕከሉ ከፍተኛ እገዛ እያደረገ መሆኑን የገለፁት ደግሞ በቅ/ጽ/ቤቱ የሴቶች ህፃናት እና ወጣቶች ጉዳይ ድጋፍና ክትትል ቡድን አስተባባሪ ወ/ሮ ኑሪያ አሊ ናቸው፡፡

ማዕከሉ ከስድስት ወር እስከ አራት ዓመት ያሉ 13 ህፃናትን ተቀብሎ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ የገለፁት ወ/ሮ ኑሪያ ከእነዚህ መካከል እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ሦሥት ህፃናት መሸኘታቸውን አክለዋል፡፡
የህፃናት ማቆያው የካቲት 20 ቀን 2012 ዓ.ም በይፋ ተመርቆ ለ5 ህፃናት አገልግሎት መስጠት የጀመረ ሲሆን ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ ከ20 በላይ ለሆኑ ህፃናት አገልግሎት ለመስጠት ቅድመ ዝግጅት እያደረገ ይገኛል፡፡
2.4K viewsMOR EAST, 15:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 18:38:32
2.3K viewsMOR EAST, 15:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 16:49:47 ለተመራቂ የሞጁላር ሰልጣኞች
ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ሲሰጠው የነበረውን የሞጁላር ስልጠና አጠናቃችሁ ለምርቃት እየተጠባበቃችሁ መሆኑ ይታወቃል፡፡ የምርቃት ሥነ ሥርዓቱ በነሐሴ ውስጥ ለማካሄድ መረሃ ግብር ተይዞ የነበረ ቢሆንም በአንዳንድ ምክንያቶች ምርቃቱ ወደ መስከረም 2015 ዓ.ም ተዛውሯል፡፡
ስለሆነም የተሰጠውን ትምህርት በብቃት ማጠናቀቃችሁን በሚያረጋግጠው ሰርተፍኬት ላይ የሚፃፈውን ትክክለኛ ስም እና አድራሻ በእንግሊዘኛ ጽፋችሁ እንድትልኩልን በትህትና እንጠይቃለን፡፡
መላክ የሚጠበቅባችሁ፡-
• የሰልጣኝ ሙሉ ስም
• የድርጅት ሥም
• የድርጅቱ የግብር መለያ ቁጥር እንዲሁም
• የሰልጣኙ እና የድርጅቱን ስልክ ቁጥር በእንግሊዘኛ እንድትልኩልን እናሳስባለን፡፡
2.6K viewsMOR EAST, edited  13:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 10:19:39 በድጋሜ የተላለፈ ማስታወቂያ ለምስራቅ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች በሙሉ

ከፌዴራል ገቢ በተጨማሪ የሥራ ግብር እና የጡረታ ታክሶችን በኦን ላይን መክፈል መጀመራቸውን ስለማሳወቅ

ታክስን በኤሌክትሮኒክስ ለመሰብሰብ በተደረገው የአገልግሎት አሰጣጥ ስምምነት መሰረት ከዚህ በታች በተጠቀሱት የመንግስትና የግል ባንኮች ማለትም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ዳሽን ባንክ፣ ብርሃን ባንክ፣ ህብረት ባንክ፣ አቢሲኒያ ባንክ፣ አዋሽ ባንክ፣ ወጋገን ባንክ፣ ኦሮሚያ ባንክ፣ ዘመን ባንክ፣ ቡና ባንክ፣ እናት ባንክ እና ደቡብ ግሎባል ባንክ የአገልግሎት አሰጣጥ ስምምነት ፈርመው መስተንግዶ በመስጠት ላይ መሆናቸው ይታወቃል፡፡
ስለሆነም፡-

1. በፌዴራል የሚሰበሰቡ ታክሶችና ወጪ መጋራትን ጨምሮ ብሄራዊ ባንክ በሚገኘው የኤሌክትሮኒክስ የገቢዎች ሚኒስቴር የቀጥታ ታክስ የሒሳብ ቁጥር

2. የአዲስ አበባ የደመወዝ ገቢ ግብርና የኪራይ ገቢ ግብር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሚገኘው የኤሌክትሮኒክስ መክፈያ ሂሳብ ቁጥር እንዲሁም


3. የግል ድርጅቶች ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጄንሲ የጡረታ ክፍያ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሚገኘው የኤሌክትሮኒክስ መክፈያ የባንክ ሂሳብ ቁጥር መፈፀም የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን ለሁሉም ክፍያዎች ትክክለኛውን የባንክ የሒሳብ ቁጥር; በዋናነት የሰነድ ቁጥር በመጠቀም ይህ ማስታወቂያ ከተላለፈበት ቀን ጀምሮ ግብራችሁን በባንክ እንድትከፍሉ እናሳስባለን፡፡

ማሳሰቢያ፡- ክፍያዎን ከላይ በተገለፁት ባንኮች ብቻ እንዲፈፅሙ እያሳሰብን፤ ከላይ ከተዘረዘሩ ባንኮች ውጪ ክፍያ ብትፈፅሙ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን አውቃችሁ ቅ/ጽ/ቤቱም ኃላፊነት የማይወስድ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
2.5K viewsMOR EAST, 07:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 07:12:23 የተጠናቀቀው በጀት ዓመት በታክስ ኦዲት ስራ ጥሩ ውጤት የተገኘበት ነው
- አቶ ተስፋዬ ቱሉ የታክስ ስርዓት ዘርፍ ሚኒስትር

ቅዳሜ ነሐሴ 21 ቀን 2014 ዓ.ም (ምስራቅ ገቢዎች) በገቢዎች ሚኒስቴር የታክስ ኦዲት ስርዓቱን ግልፅ እና ተዓማኒ ከማድረግ እንዲሁም ሊታጣ የነበረ የመንግስት ገቢ ከማስቀረት አንፃር የተከናወኑ ስራዎች ውጤት የተመዘገበባቸው መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ይህ የተገለፀው የገቢዎች ሚኒስቴር የታክስ ኦዲት ዳይሬክቶሬት በአዳማ ከተማ እያካሄደ በሚገኘው የ2014 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም እና የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ ውይይት ላይ ነው፡፡

በውይይቱ መክፈቻ ላይ የገቢዎች ሚኒስቴር የታክስ ስርዓት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተስፋዬ ቱሉ እንደገለፁት ሚኒስቴር መ/ቤቱ የለውጥ ሂደቱን ተከትሎ ግልፅ ራዕይ እና ተልዕኮ አስቀምጦ ለተግባራዊነቱ ሰፊ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፡፡ በዋነኛነትም ለታክስ ከፋዩ ቀልጣፋና ፍትሃዊ አገልግሎት መስጠት፣ የታክስ ህግ ተገዢነት ስርዓትን ማስፈን እና ገቢን በአስተማማኝ ደረጃ ማሳደግ ላይ ትኩረት አድርጎ በመስራት ላይ ይገኛል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ከዚህ አንፃር የታክስ ኦዲት ውሳኔ ጥራትና ፍትሃዊነት ከማረጋገጥ አንፃር በርካታ ተግባራት ተከናውነዋል ብለዋል፡፡ በተገባደደው በጀት ዓመት ከታክስ ኦዲት ጋር የተያያዙ ተግባራት አፈፃፀም እጅግ አበረታችና አመርቂ መሆናቸውንም ጠቁመዋል፡፡ ለዚህም መላው የዳይሬክቶሬቱ እና የቅ/ፅ/ቤቶች አመራርና ስራተኞችን አመስግነው በቀጣይም ለተሻለ ውጤት መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

የታክስ ኦዲት ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ አበበ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ወደ ለውጥ እንቅስቃሴ ከገባችበት ጊዜ ጀምሮ ለውጡን እየዘወሩ ከሚገኙ ተቋማት የገቢዎች ሚኒስቴር አንዱና ዋነኛው ነው ብለዋል፡፡ ሚኒስቴር መ/ቤቱ የታክስ ኦዲት ፖሊሲዎችን ከመፈተሽ ጀምሮ በርካታ የማሻሻያ ስራዎች መስራቱን ተናግረዋል፡፡ በ2010 የበጀት ዓመት 8 ቢሊየን ብር ብቻ የነበረውን የኦዲት ተደራሽነት ወደ 52 ቢሊየን ብር ማሳደግ መቻሉንም ገልፀዋል፡፡ ተገቢ ያልሆነ ተመላሽና ኪሳራ እንዲሁም ከደረሰኝ ጋር የተያያዙ ወንጀሎችን ከመከላከል አንፃር ዳይሬክቶሬቱ ሰፋፊ ተግባራት ማከናወኑንም ጠቁመው በቀጣይም የታክስ ኦዲት ስራዉን ጥራቱን የጠበቀ ፍትሃዊና ተዓማኒ ለማድረግ እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡

በውይይቱ ከሁሉም ቅ/ፅ/ቤቶች የተውጣጡ አመራሮችና የታክስ ኦዲት ባለሙያዎች ተገኝተዋል፡፡

ምንጭ፦ የገቢዎች ሚኒስቴር
2.9K viewsMOR EAST, 04:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 07:11:51
2.5K viewsMOR EAST, 04:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ