Get Mystery Box with random crypto!

Obadiah Apologetics

የቴሌግራም ቻናል አርማ ovadiah — Obadiah Apologetics O
የቴሌግራም ቻናል አርማ ovadiah — Obadiah Apologetics
የሰርጥ አድራሻ: @ovadiah
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 567
የሰርጥ መግለጫ

✟ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ✟
"የሰውንም አሳብ በእግዚአብሔርም እውቀት ላይ የሚነሣውን ከፍ ያለውን ነገር ሁሉ እናፈርሳለን ለክርስቶስም ለመታዘዝ አእምሮን ሁሉ እንማርካለን፥"
(2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 10:5)
📌 ዋናው ቻናላችን፦ @TheTriune

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-12-10 18:18:36 ➣ ልክ እንደ ሌሎቹ ክፍሎች ሁሉ፥ ኢሳያስ 61 እና ሚክያስ 4-5 አንድ አይነት መልእክት አላቸው። በሁለቱም ስፍራ የመሲሁ አምላክነት ተገልጿል። በሚክ 5:2 መሲሁ አወጣጡ ከጥንት ጀምሮ የሆነው መሆኑ ተነግሯል። ይህ መሲሁ በስጋ ከመምጣቱ በፊትም የነበረና፥ ከጥንትም ጀምሮ ሕያው የሆነ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው። በሚክ 5:2 ላይ "አወጣጡ ከጥንት" የሚለው አገላለፅ፥ በዕንባቆም 1:12 ላይ ለእግዚአብሔር የዋለ አገላለፅ ነው። እግዚአብሔር ነው አወጣጡ ከጥንት የሆነው። ስለዚህ መሲሁ በዚህ አገላለፅ መገለፁ አምላክ መሆኑን ያረጋግጣል። በኢሳይያስ 61:8 ላይም ደግሞ፥ ተናጋሪው ቃል "እኔ እግዚአብሔር" በማለት አምላክነቱን ገልጿል። ስለዚህ ሁለቱም ክፍሎች ስግው መለኮት (incarnate deity) ስለሆነው መሲህ ነው የሚናገሩት ማለት ነው። ይህ በኢሳ 61:8 እና በሚክ 4 እና 5 ላይ ፈራጅነቱና አምላክነቱ የተገለጸው አካል፥ መሲሁ መሆኑን በሚገባ ያረጋግጣል።

6) ዘላለማዊ ቃል ኪዳን ከሕዝቡ ጋር ይገባል

"እኔ እግዚአብሔር ፍርድን የምወድድ ስርቆትንና በደልን የምጠላ ነኝ፤ ፍዳቸውንም በእውነት እሰጣቸዋለሁ፥ ከእነርሱም ጋር #የዘላለም #ቃል #ኪዳን #አደርጋለሁ።"
(ትንቢተ ኢሳይያስ 61:8)

ለሰዎች ሁሉ ፍዳቸውን እንደሚሰጥ ከተናገረ በኋላ፥ በኢሳይያስ 61 ላይ ያለው ተናጋሪ ከሕዝቡ ጋር የዘላለም ቃል ኪዳን እንደሚያደርግ ሲናገር እንመለከታለን። ይህ ማለት ዘላለማዊና የማይሻር ቃል ኪዳን ይመሰረታል ማለት ነው። ዘላለማዊ ቃል ኪዳንን እንደሚያደርግ መናገሩ፥ ተናጋሪው መሲሁ ለመሆኑ ማስረጃ ነው።

ምክንያቱም በመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ መሰረት ይመሰረታል ተብሎ የሚጠበቀው ዘላለማዊ ቃል ኪዳን፥ የመሲሁ ነውና፦

"ጆሮአችሁን አዘንብሉ ወደ እኔም ቅረቡ፤ ስሙ ሰውነታችሁም በሕይወት ትኖራለች፤ የታመነችይቱን #የዳዊትን ምሕረት፥ #የዘላለምን #ቃል #ኪዳን ከእናንተ ጋር አደርጋለሁ።"
(ትንቢተ ኢሳይያስ 55:3)

በዚህ ክፍል ላይ፥ እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር የታመነችውን የዳዊትን ምሕረትና የዘላለምን ቃል ኪዳን እንደሚያደርግ ሲናገር እንመለከታለን። በመጪው ዘመን የማይሻርና የማይቀር ቃል ኪዳን እንደሚኖር ይህ ክፍል ግልፅ ያደርጋል። ይህም ቃል ኪዳን ከታመነችው ከዳዊት ምህረት ጋር የሚሄድ ቃል ኪዳን ነው። በዚህ ስፍራ "ዳዊት" ተብሎ እየተጠራ ያለው በታሪክ የነበረው ንጉሥ ዳዊት ሳይሆን፥ መሲሁ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ መሲሁ በብዙ ስሞች የተጠራ ሲሆን ከነዚህም ስሞች አንዱ "ዳዊት" ነው። መሲሁ "ዳዊት" ተብሎ የተጠራበት ምክንያት፥ እግዚአብሔር በ2 ሳሙ 7:12-16 ላይ ለዳዊት ከሆዱ ፍሬ በዙፋኑ ላይ ለዘላለም እንደሚያስቀምጥ ቃል ስለገባለት ነው።

ስለዚህ ከዳዊት የስጋ ልጆች አንዱ ለዘላለም በዳዊት ዙፋን ላይ ይቀመጣል ማለት ነው። ያም የስጋ ልጁ መሲሁ ነው። ስለዚህ እግዚአብሔር ለዳዊት ይህን ቃል ኪዳን ስለገባለት፥ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ መሲሁ "ዳዊት" ተብሎ ተጠርቷል (ሆሴ 3:5 ኤር 30:9 ሕዝ 34:23-24 ሕዝ 37:24-25) ስለዚህ እግዚአብሔር፥ የታመነችውን የዳዊትን ምህረትና የዘላለምን ቃል ኪዳን አደርጋለሁ ሲል፥ በመሲሁ አማካኝነት ስለሚያደርገው የዘላለም ኪዳን እየተናገረ ነው። በንጉሥ ዳዊት አማካኝነት የተደረገ ዘላለማዊ ቃል ኪዳን የለም። ስለዚህ ይህ ክፍል የሚናገረው ስለ ዳዊት አይደለም ማለት ነው። በመሲሁ ስለሚመሰረተው ዘላለማዊ ቃል ኪዳን ይናገራል እንጂ። ይህ በኢሳ 61:8 ላይ የዘላለምን ቃል ኪዳን እንደሚያደርግ የተናገረው አካል፥ መሲሁ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው

"6፤7፤ እኔ እግዚአብሔር በጽድቅ ጠርቼሃለሁ፥ እጅህንም እይዛለሁ እጠብቅህማለሁ፥ የዕውሩንም ዓይን ትከፍት ዘንድ የተጋዘውንም ከግዞት ቤት በጨለማም የተቀመጡትን ከወህኒ ቤት ታወጣ ዘንድ #ለሕዝብ #ቃል #ኪዳን ለአሕዛብም ብርሃን አድርጌ #እሰጥሃለሁ።"
(ትንቢተ ኢሳይያስ 42:6-7)

በዚሁ ስፍራም፥ መሲሁ ለሕዝቡ ቃል ኪዳን እንደሚሆን ተነግሮ እንመለከታለን። በኢሳ 42:1 ላይ መንፈሱ በእርሱ ላይ የሆነውን አገልጋዩን ለሕዝቡ ቃል ኪዳን እንዲሆን አድርጎ እንደሚሰጠው እግዚአብሔር ይናገራል። ይህ ማለት፥ መሲሁ ከኛ ጋር ቃል ኪዳን እንዲመሰርት ከእግዚአብሔር የተሰጠን ነው ማለት ነው። በእርሱ አማካኝነት ነው አዲሱ ኪዳን የሚመሰረተው። ይህ በኢሳ 61:8 ላይ ዘላለማዊ ቃል ኪዳን አደርጋለሁ በማለት የተናገረው ተናጋሪ መሲሁ መሆኑን ያሳያል። ኢሳያስ 42 ዝነኛ መሲሃዊ ትንቢት ሲሆን በዚያ ክፍል ላይ ስለ መሲሁ ይህ መባሉ፥ በእርግጥም በኢሳይያስ 61:8 ላይ "እኔ እግዚአብሔር" በማለት አምላክነቱን የገለፀውና፥ የዘላለም ኪዳንን እንደሚመሰርት የተናገረው መሲሁ መሆኑን ያረጋግጣል።

በኢሳ 42:6-7 ላይ የምንመለከተውን ይህን ሀሳብ በኢሳ 49:9 ላይ ተደግሞ እናየዋለን፦

"የተጋዙትንም። ውጡ በጨለማም የተቀመጡትን። ተገለጡ ትል ዘንድ #ቃል #ኪዳን #አድርጌ ለሕዝቡ #ሰጥቼሃለሁ። በመንገድም ላይ ይሰማራሉ፥ ማሰማርያቸውም በወና ኮረብታ ሁሉ ላይ ይሆናል።"
(ትንቢተ ኢሳይያስ 49:9)

በኢሳያስ 42 ላይ የምንመለከተው ሀሳብ በኢሳያስ 49 ላይ ተደግሞ እናገኘዋለን። ሁለቱም ክፍሎች መሲሃዊ ክፍሎች ሲሆኑ በኢሳይያስ 42 ላይ ለአገልጋዩ የተባሉት ነገሮች በሙሉ በኢሳ 49 ላይ ላለው አገልጋይ ተብለዋል። የእግዚአብሔር አገልጋይ እንደሆነ (ኢሳ 42:1 ኢሳ 49:3) ለአሕዛብ ብርሃን እንደሚሆን (ኢሳ 42:6 ኢሳ 49:6) የታሰሩትን ነጻ እንደሚያወጣ (ኢሳ 42:7 ኢሳ 49:9) ለሕዝቡም ቃል ኪዳን እንደሆነ (ኢሳ 49:9 ኢሳ 42:6) ተነግሯል። ስለዚህ በሁለቱም ስፍራ እየተነገረለት ያለው አገልጋይ መሲሁ ነው ማለት ነው። ሁለቱም ክፍሎች መሲሃዊ ክፍሎች ናቸው። መሲሁ ለሕዝቡ ቃል ኪዳን እንደሚሆን የተነገረለት በዚህ ክፍል ላይ ነው። ይህ በኢሳ 61:8 ላይ የዘላለምን ቃል ኪዳን እንደሚገባ የተናገረው አካል መሲሁ ለመሆኑ የማይታበል ማስረጃ ነው። በኢሳይያስ 61:8 ላይ "እኔ እግዚአብሔር" በማለት አምላክነቱን ገልፆ፥ የዘላለምን ቃል ኪዳን ከሕዝቡ ጋር እንደሚያደርግ ቃል የገባው መሲሁ ነው።

➣ ሌላው አስገራሚ ነገር፥ መሲሁ በመሲሁ አማካኝነት የዘላለም ቃል ኪዳን እንደሚመሰረት የሚናገሩት ክፍሎች በሙሉ (ኢሳ 42:6-7 ኢሳ 49:9 እና ኢሳ 55:3) የኢሳ 61:8 ትንቢት ተዘግቦ ባለበት በዚያው የትንቢት መጽሐፍ መገኘታቸው ነው። መሲሁ የዘላለም ኪዳን እንደሚመሰርት በሚናገረው በዚያው መጽሐፍ ውስጥ የኢሳያስ 61 ተናጋሪ የዘላለምን ቃል ኪዳን እንደሚመሰርት መናገሩ፥ ተናጋሪው መሲሁ መሆኑን ከማሳየት አልፎ የጸሐፊውን መረዳትና እምነት ግልፅ ያደርጋል። ጸሐፊውም በኢሳ 61:8 ላይ አምላክነቱን በመግለፅ የዘላለም ቃል ኪዳንን እንደሚያደርግ የተናገረው ተናጋሪ፥ መሲሁ መሆኑን ያምናል ማለት ነው።

ይቀጥላል
183 views15:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-10 18:18:36 እኔ እግዚአብሔር (ክፍል 5)

" #እኔ #እግዚአብሔር ፍርድን የምወድድ ስርቆትንና በደልን የምጠላ ነኝ፤ ፍዳቸውንም በእውነት እሰጣቸዋለሁ፥ ከእነርሱም ጋር የዘላለም ቃል ኪዳን አደርጋለሁ።"
(ትንቢተ ኢሳይያስ 61:8)

ባለፉት ተከታታይ ክፍሎች፥ መሲሁ ክርስቶስ ኢየሱስ አንድም ቦታ በራሱ አንደበት "እኔ እግዚአብሔር ነኝ" ብሎ ተናግሮ አያውቅም ለሚለው የሀሰት ሙግት መልስ ለመስጠት ሞክረን ነበር። እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ቀጥተኛ አስተምህሮ መሰረት፥ መሲሁ በራሱ አንደበት እግዚአብሔር መሆኑን ተናግሯል። ለዚህም ማስረጃው ኢሳ 61:8 ነው

በብዙ ማስረጃዎች ለመመልከት እንደሞከርነው፥ በዚህ ክፍል ላይ እየተናገረ ያለው መሲሁ ነው። በክፍሉ ስለተናጋሪው የተባሉት ነገሮች በሙሉ፥ በሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ለመሲሁ ብቻ የተባሉ ነገሮች ናቸው። ስለዚህ ክፍሉ መሲሃዊ አይደለም ብሎ መከራከሪያ አይቻልም። በተጨማሪም ከቁ.1 ጀምሮ እስከ መጨረሻው አንድ ተናጋሪ ነው ያለው። ሁለተኛ ተናጋሪ የለም። ስለዚህ በቁ.8 ላይ የተናጋሪ ለውጥ አለ ማለት አይቻልም። ስለዚህ እግዚአብሔር ነኝ ያለው መሲሁ ነው ማለት ነው።

ዛሬም ከባለፈው ክፍል በመቀጠል፥ በኢሳይያስ 61 ላይ እኔ እግዚአብሔር በማለት አምላክነቱን የገለፀው መሲሁ መሆኑን በተጨማሪ ማስረጃዎች ለማሳየት እንሞክራለን፦

"ሕዝብህን በጽድቅ፥ ችግረኞችህንም #በፍርድ #ይዳኝ ዘንድ።"
(መዝሙረ ዳዊት 72:2)

በዚህ ስፍራ የመሲሁ ፈራጅነት ተገልጾ እንመለከታለን። መሲሁ አለምን ሁሉ ሊገዛ ወደ ምድር ከተመለሰ በኋላ ከሚሆኑት ነገሮች አንዱ ሕዝቡን በፍርድ መዳኘቱ ነው። ሕዝቡን በፍርድ እንደሚዳኝ መነገሩ፥ መሲሁ በእርግጥም ለሰዎች የስራቸውን ዋጋ የሚሰጣቸው ፈራጅ መሆኑን ያረጋግጣል። መዝሙር 72 ታዋቂ መሲሃዊ መዝሙር ነው። ቀዳማዊ ትንቢቱ የተነገረው ለሰለሞን ቢሆንም፥ የትንቢቱ ትክክለኛ ፍጻሜ ክርስቶስ ነው። ሰለሞን የክርስቶስ ጥላ በመሆኑ፥ መሲሃዊ ትንቢቶች እርሱን በማስመልከት ሊነገሩ ይችላሉ። ፍጻሜው ግን ኢየሱስ ነው። በዚህ መዝሙር ላይ በሰለሞን ሕይወት ያልተከናወኑ ነገሮች ተብሎ እንመለከታለን። እነዚህ በእርሱ ዘመን ያልሆኑ ነገሮች፥ በመሲሁ የሚከናወኑ ነገሮች መሆናቸው በሌላው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ተነግሯል። መላውን አለም ከባህር እስከ ባህር ይገዛል ይላል (መዝ 72:8) ይህ በሰለሞን ሕይወት ያልተፈጸመ ሲሆን፥ ተፈጻሚነቱን የሚያገኘው በመሲሁ ነው (ዘካ 9:10 ሚክ 5:4) አሕዛብ ሁሉ እንደሚገዙለትና እንደሚሰግዱለት ተነግሯል (መዝ 72:9-11) ይህ በሰለሞን ሕይወት አልተከናወነም። ይልቁኑም በመሲሁ የሚፈፀም ነገር ነው (ዳን 7:13-14 ዘካ 14:16) ስለዚህ ይህ መዝሙር መሲሃዊ ነው ማለት ነው። በዚህ መሲሃዊ መዝሙር የመሲሁ ፈራጅነት መገለፁ መሲሁ ዳኛ መሆኑን ከማሳየት ባሻገር፥ በኢሳ 61:8 ላይ ለሰዎች ሁሉ ፍዳቸውን እንደሚሰጣቸው የተናገረው ተናጋሪ እርሱ መሆኑን ያረጋግጣል።

በመዝ 72:2 ላይ የተገለፀው ሃሳብ በቁ.4 ላይ ተደግሞ እንመለከታለን፦

"ለችግረኞች ሕዝብ በጽድቅ #ትፈርዳለህ የድሆችንም ልጆች ታድናለህ፤ ክፉውንም ታዋርደዋለህ።"
(መዝሙረ ዳዊት 72:4)

የመዝሙር 72 ጸሐፊ ንጉሥ ዳዊት፥ በልጁ በሰለሞን ጥላነት (foreshadowing) የመሲሁን ፈራጅነት አጽንዖት ሰጥቶ ሲናገር እንመለከታለን። በቁ.4 ላይ ለችግሮች በጽድቅ እንደሚፈርድ ይናገራል። ይህ በትክክል የመሲሁን ፈራጅነት የሚያረጋግጥ ማስረጃ ነው። ባለፉት ተከታታይ ክፍሎች በብዙ ማስረጃዎች እንዳየነው፥ በምድር ላይ በጽድቅ የሚፈርደው መሲሁ ነው (ኤር 33:15-16 ኤር 23:5-6 ኢሳ 9:6-7) በዚህ መሲሃዊ መዝሙር ላይም የመሲሁ ጻድቅ ፈራጅነት በድጋሚ ተነገሮ እናያለን። ይህ በእርግጥም መሲሁ ኢየሱስ ወደ ምድር ሲመለስ በአለም ሁሉ ላይ የሚፈርደው ፈራጅ መሆኑን ከማረጋገጥ አልፎ፥ በኢሳ 61:8 ላይ በሰዎች ሁሉ ላይ እንደሚፈርድ የተናገረው ተናጋሪ እርሱ መሆኑን ያረጋግጣል። ስለዚህ በዚያ ክፍል ላይ "እኔ እግዚአብሔር" በማለት አምላክነቱን የገለፀው መሲሁ ነው ማለት ነው።

"በአሕዛብም መካከል #ይፈርዳል፥ በብዙ አሕዛብም ላይ #ይበይናል፤ ሰይፋቸውንም ማረሻ ጦራቸውንም ማጭድ ለማድረግ ይቀጠቅጣሉ፤ ሕዝብም በሕዝብ ላይ ሰይፍ አያነሣም፥ ሰልፍም ከእንግዲህ ወዲህ አይማሩም።"
(ትንቢተ ኢሳይያስ 2:4)

በዚህ ክፍል ላይም፥ መጽሐፍ ቅዱስ የመሲሁን ፈራጅነት ሲናገር እንመለከታለን። መሲሁ በብዙ አሕዛብ መካከል እንደሚፈርድና እንደሚበይን እግዚአብሔር ይናገራል። ይህ የመሲሁን ፈራጅነት በትክክል የሚያሳይ ነው። ኢሳያስ 2 ዝነኛ መሲሃዊ ትንቢት ሲሆን፥ መሲሁ ምድርን ሁሉ በሚገዛበት ሰአት የሚሆነውን ነገር ይገልፃል። ለዚያ ነው "..በዘመኑ ፍጻሜ" በማለት የሚጀምረው (ኢሳ 2:2) በመጨረሻው ዘመን የሚሆነውን ነገር እየተነበየ ነውና። መሲሁ አለምን ሁሉ በሚገዛበት በዚያ ዘመን በአሕዛብ ሁሉ ላይ ይፈርዳል፥ በብዙ አሕዛብ ላይም ይበይናል። ፈራጅ ነውና። ይህ በኢሳ 61:8 ላይ በሰዎች ሁሉ ላይ እንደሚፈርድ የተናገረው ተናጋሪ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው። ነገሩን በይበልጥ አስገራሚ የሚያደርገው፥ የኢሳ 2:4 እና የኢሳ 61:8 ትንቢቶች በአንድ መጽሐፍ መገኘታቸው ነው። መሲሁ በአሕዛብ ሁሉ ላይ እንደሚፈርድ የሚናገረው ያው የኢሳያስ የትንቢት መጽሐፍ ነው፤ በኢሳ 61:8 ላይ ያለውን የመሲሁን ንግግር መዝግቦ የያዘው። ይህ የጸሐፊውን እምነትና አቋም ግልፅ ያደርግልናል።

"በብዙዎችም አሕዛብ መካከል #ይፈርዳል፥ በሩቅም ባሉ በብርቱዎች አሕዛብ ላይ #ይበይናል፤ ሰይፋቸውንም ማረሻ፥ ጦራቸውንም ማጭድ ለማድረግ ይቀጠቅጣሉ፤ ሕዝብም በሕዝብ ላይ ሰይፍ አያነሣም ከእንግዲህም ወዲህ ሰልፍ አይማሩም።"
(ትንቢተ ሚክያስ 4:3)

በኢሳይያስ 2 ላይ ያለው ትንቢት፥ በሚክያስ 4 ላይ ተደግሞ እንመለከታለን። በዚሁ ስፍራም መሲሁ በብዙ አሕዛብ ላይ እንደሚፈርድና እንደሚበይን ተተንብይዋል። ይህ ለመሲሁ ፈራጅነት የማይታበል ማስረጃ ነው። ሚክያስ 4 ልክ እንደ ኢሳያስ 2 "...በመጨረሻው ዘመን" በማለት ነው የሚጀምረው (ሚክ 4:1) ስለዚህ በመሲሃዊው ዘመን ስለሚሆነው ነገር የሚያስረዳ ትንቢት ነው ማለት ነው። መሲሁ መላውን አለም ሊገዛ በሚመለስበት ጊዜ የሚሆነው ይህ ነው። በአሕዛብ ላይ ይፈርዳል፥ ይበይንማል። ፈራጅ ነውና። ሚክያስ 4 መሲሃዊ ትንቢት በመሆኑ ነው፥ በቀጣዩ ምዕራፍ ላይ መሲሁ አወጣጡ ከጥንት እንደሆነ (ሚክ 5:2) ለሕዝቡ እረኛ እንደሆነ (ሚክ 5:4) የተነገረው። ሀሳቡ ተያያዥ ነውና። በኢሳይያስ 61:8 ላይ የምንመለከተው ሀሳብ ይህ ነው። ተናጋሪው ለሰዎች ሁሉ ፍዳቸውን እንደሚሰጣቸው ተናግሯል። ስለዚህ በሚክ 4:3 ላይ የተተነበየለት መሲህ ነው ማለት ነው።
194 views15:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-30 12:36:50 በዚያ ክፍል ላይ ተናጋሪው ለሰዎች ፍዳቸውን እንደሚሰጥ ተናግሯል። ይህ ለዘላለም በፍርድ ይጸናል የተባለለት ሕጻን (መሲሁ) መሆኑን ከምንም በላይ ያረጋግጣል። ፈራጅነቱ ተገልጿልና። ስለዚህ በኢሳ 61:8 ላይ "እኔ እግዚአብሔር" በማለት አምላክነቱን የገለፀው መሲሁ ነው ማለት ነው።

➣ ኢሳ 61:8 እና ኢሳ 9:6-7 የማይታበል የመልእክት አንድነት ያላቸው ክፍሎች ናቸው። ምክንያቱም በሁለቱም ቦታዎች ላይ የመሲሁ አምላክነት ተገልጿል። በኢሳ 9:6-7 ላይ መሲሁ፥ ኀያል አምላክ ተብሎ ተጠርቷል። ይህ ስያሜ በቀጣዩ ምዕራፍ ላይ እግዚአብሔር የተጠራበት ስያሜ ነው (ኢሳ 10:21) ስለዚህ አምላክነትን የሚያሳይ ነው ማለት ነው። እንዲሁም፥ የዘላለም አባት ተብሎ ተጠርቷል። የዘላለም አባት ማለት የዘላለማዊነት ባለቤት ወይንም ዘላለማዊ ማለት ነው። ይህም በዚያው በኢሳይያስ መጽሐፍ እግዚአብሔር የተገለፀበት አገላለጽ ነው (ኢሳ 57፥15) ስለዚህ መገለጫው አምላክነትን የሚገልጽ ነው ማለት ነው። በኢሳ 9:6-7 የመሲሁን አምላክነት የሚገልጽ ክፍል ነው። ልክ እንዲሁ ደግሞ፥ በኢሳ 61:8 መሲሁ "እኔ እግዚአብሔር" በማለት አምላክነቱን ገልጿል። ስለዚህ ኢሳ 61:8 የመሲሁ አምላክነት የተነገረበት ክፍል ነው። በኢሳ 9:6-7 እና በኢሳ 61:8 የመሲሁ ፈራጅነትና አምላክነት ተነግሯል። ይህ ሁለቱ ክፍሎች ቀጥተኛ ግንኙነትና የመልእክት አንድነት እንዳላቸው ያሳያል

"5፤ እነሆ፥ ለዳዊት ጻድቅ #ቍጥቋጥ የማስነሣበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር፥ እርሱም እንደ ንጉሥ ይነግሣል፥ ይከናወንለታልም፥ በምድርም #ፍርድንና ጽድቅን ያደርጋል። 6፤ በዘመኑም ይሁዳ ይድናል እስራኤልም ተዘልሎ ይቀመጣል፥ የሚጠራበትም #ስም። #እግዚአብሔር ጽድቃችን ተብሎ ነው።"
(ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ 23:5-6)

በዚህ ስፍራም እንዲሁ መሲሁ በምድር ላይ ፍርድን እንደሚያደርግ ተገልጾ እንመለከታለን። እግዚአብሔር በነቢዮ ኤርምያስ አማካኝነት፥ ለዳዊት ጻድቅ ቁጥቋጥን እንደሚያስነሣ ይናገራል። ከዚህ በፊት ለማለት እንደሞከርነው ቁጥቀጥ መሲሁ በመጽሐፍ ቅዱስ ከተጠራባቸው ስያሜዎች መካከል አንዱ ነው (ዘካ 3:8 ዘካ 6:11-12 ኤር 33:15-16 መዝ 132:17 ኢሳ 4:2) ስለዚህ በዚህ ቦታ ላይ እግዚአብሔር እንደሚያስነሳው ቃል የገባው መሲሁን ነው ማለት ነው። እግዚአብሔር መሲሁን ማስነሳቱ ከኢሳ 61:1 ጋር ቀጥተኛ ቁርኝት አለው። በዚያ ክፍል ላይ ተናጋሪው በእግዚአብሔር እንደተላከ ተናግሯልና። እግዚአብሔር ያስነሳዋል ማለት ይልከዋል ማለት ነው። የእርሱን ስራ እንዲሰራ ያሰማራዋል ማለት ነው። ይህ በሁለቱ ክፍሎች መካከል ያለውን የመልእክት አንድነት ያሳያል።

ከዚህ ቀጥሎ፥ ይህ የሚያስነሳው መሲህ በምድር ላይ ፍርድን እንደሚያደርግ እግዚአብሔር ይናገራል። ይህ ማለት መሲሁ ፈራጅ ነው ማለት ነው። በምድር ላይ ፍርድንና ብይንን የሚያደርገው እርሱ ነው ማለት ነው። ስለዚህ ለሰዎች እንደ ስራቸው መጠን የሚፈርድባቸው እርሱ ነው ማለት ነው። በኢሳ 61:8 ላይ የምንመለከተው ይህንኑ ነው። በዚያ ክፍል ላይ የሚናገረው አካል ለሰዎች ሁሉ ፍዳቸውን እንደሚሰጣቸው ይናገራል። ስለዚህ ሰዎች ሁሉ የስራቸውን ዋጋ የሚቀበሉት ከእርሱ ነው ማለት ነው። ይህ በኤር 23:5-6 ላይ የተነገረለት መሲሁ መሆኑ በማያሻማ ሁኔታ ያረጋግጣል። በሁለቱም ቦታ ላይ ፈራጅነቱ ተብራርቷልና። ስለዚህ በኢሳ 61:8 ላይ "እኔ እግዚአብሔር" ያለው በምድር ሁሉ ላይ ፍርድን የሚያደርገው መሲሁ ነው ማለት ነው።

➣ ልክ እንደ ሌሎቹ ክፍሎች፥ ኢሳ 61:8 እና ኤር 23:5-6 አንድ አይነት መልእክት አላቸው። ሁለቱም የመሲሁን አምላክነት የሚገልፁ ክፍሎች ናቸው። በኤር 23:5-6 የመሲሁ ስም "እግዚአብሔር ጽድቃችን" ነው ተብሏል። በመጽሐፍ ቅዱስ ስም ባህርይን ወይንም ሕላዌን ይገልጻል። ስለዚህ የመሲሁ ስም "እግዚአብሔር ጽድቃችን" መባሉ በባህሪው መለኮት መሆኑ የሚያሳይ ነው። ከዚያ ባሻገር፥ ስሙ "እግዚአብሔር/ያህዌ" የሆነው እግዚአብሔር ብቻ ነው (ዘጽ 15:3 ኤር 10:16 ኤር 33:2) ስለዚህ መሲሁ ስሙ እግዚአብሔር/ያህዌ መሆኑ በትክክልም አምላክ መሆኑን የሚያሳይ ነው። በኢሳይያስ 61:8 ላይም እንዲሁ መሲሁ ቃል በቃል "እኔ እግዚአብሔር" በማለት አምላክነቱን ገልጿል። ስለዚህ ሁለቱም ክፍሎች አንድ አይነት መልእክት አላቸው ማለት ነው። በሁለቱም ቦታዎች ላይ የመሲሁ አምላክነትና ፈራጅነት ተገልጿል። ይህ ሁለቱም ክፍሎች ተያያዥ ሃሳብ እንዳላቸው የሚያሳይ ነው።

"15፤ በዚያም ዘመን በዚያም ጊዜ ለዳዊት የጽድቅን #ቍጥቋጥ አበቅልለታለሁ፤ እርሱም #ፍርድንና ጽድቅን በምድር ያደርጋል። 16፤ በዚያም ዘመን ይሁዳ ይድናል ኢየሩሳሌምም ተዘልላ ትቀመጣለች፤ የምትጠራበትም ስም። #እግዚአብሔር ጽድቃችን ተብሎ ነው።"
(ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ 33:15-16)

በኤር 23:5-6 ተገልጾ የምንመለከተው እውነት በኤር 33:15-16 ላይም ተደግሞ እንመለከታለን። በዚህም ስፍራ እግዚአብሔር ለዳዊት የጽድቅን ቁጥቋጦ እንደሚያበቀል ቃል ይገባል። ከላይ በብዙ ማስረጃ ለማየት እንደሞከርነው፥ እግዚአብሔር እንደሚያስነሳው ቃል የገባው ቁጥቋጥ መሲሁ ነው። በተደጋጋሚ ለመግለፅ እንደሞከርነው፥ እግዚአብሔር መሲሁን ማስነሳቱ ከኢሳ 61:1 ጋር ተያያዥነት አለው። በዚያ ክፍል ላይ ተናጋሪው በእግዚአብሔር እንደተላከ ተናግሯል። እግዚአብሔር ያስነሳዋል ማለት ይልከዋል ማለት ነው። የእርሱን ስራ እንዲሰራ ያሰማራዋል። ይህ የሁለቱን ክፍሎች የይዘት አንድነት ያሳያል።

ከዚህ በመቀጠልም ይህ እግዚአብሔር የሚያስነሳው መሲህ በምድር ላይ ፍርድን እንደሚያደርግ በድጋሚ ተገልፆ እንመለከታለን። ይህ ማለት መሲሁ ፈራጅ ነው ማለት ነው። በምድር ላይ ለሰዎች ሁሉ የሚገባቸውን ፍርድ የሚሰጣቸው እርሱ ነው ማለት ነው። በኢሳ 61:8 ላይም የምንመለከተው ይህንኑ ነው። በዚያ ክፍል ላይ የሚናገረው አካል ለሰዎች ሁሉ ፍዳቸውን እንደሚሰጣቸው ይናገራል። ስለዚህ ሰዎች ሁሉ የእጃቸውን ዋጋ በሙሉ የሚቀበሉት ከእርሱ ነው ማለት ነው። ይህ አሁንም በኤር 33:15-16 ላይ የተነገረለት መሲሁ መሆኑን የሚያሳይ ነው። በሁለቱም ስፍራዎች ፈራጅነቱ ተነግሯል። ስለዚህ በኢሳ 61:8 ላይ "እኔ እግዚአብሔር" በማለት አምላክነቱን የገለፀው፥ በምድር ሁሉ ላይ ፍርድን የሚያደርገው መሲሁ ነው ማለት ነው።

➣ ልክ እንደ ሌሎቹ ክፍሎችም በኤር 33:15-16 የመሲሁ አምላክነት ተገልጿል። በቁ.16 ላይ ኢየሩሳሌም "እግዚአብሔር ጽድቃችን" ትባላለች ይላል። ይህ ሊሆን የቻለው ከተማይቱ በገዢዋ በመሲሁ ስም ስለምትጠራ ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ መሰረት ከተማ በገዢዋ ስም ልትጠራ ትችላለች (ዘፍ 4:17 1 ነገ 16:24) መሲሁም በዳዊት ዙፋን ተቀምጦ ኢየሩሳሌምን ሲገዛ በእርሱ ስም "እግዚአብሔር ጽድቃችን" ተብላ ትጠራለች። ብዙ ጻድቅ ነገስታት በኢየሩሳሌም ነግሰዋል፥ ነገር ግን በማናቸውም ዘመን በዚህ ስም አልተጠራችም። መሲሁ እግዚአብሔር ስለሆነ፥ እርሱ ከተማይቱን በነገሠበት ዘመን በዚህ ስም ትጠራለች። በኢሳ 61:8 ላይ ደግሞ መሲሁ በቀጥታ "እኔ እግዚአብሔር" በማለት አምላክነቱን ሲገልፅ እንመለከታለን። ስለዚህ ሁለቱም ክፍሎች አንድ አይነት መልእክት አላቸው ማለት ነው። በሁለቱም ስፍራ የመሲሁ ፈራጅነትና አምላክነት ተገልጿል። ይህ ኢሳ 61:8 እና ኤር 33:15-16 መሲሃዊ ትንቢቶች መሆናቸውን በይበልጥ ያሳያል።

ይቀጥላል
440 viewsedited  09:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-30 12:36:50 እኔ እግዚአብሔር (ክፍል 4)

" #እኔ #እግዚአብሔር ፍርድን የምወድድ ስርቆትንና በደልን የምጠላ #ነኝ፤ ፍዳቸውንም በእውነት እሰጣቸዋለሁ፥ ከእነርሱም ጋር የዘላለም ቃል ኪዳን አደርጋለሁ።"
(ትንቢተ ኢሳይያስ 61:8)

ባለፉት ተከታታይ ክፍሎች "ኢየሱስ ክርስቶስ አንድም ቦታ በራሱ አንደበት እግዚአብሔር ነኝ ብሎ አያውቅም" ለሚለው የክርስቶስ ተቃዋሚዎች የሀሰት ተቃውሞና ሙግት መልስ መስጠት ጀምረን ነበር። መሲሁ ኢየሱስ ክርስቶስ በራሱ አንደበት እግዚአብሔር መሆኑን ተናግሯል። ለዚህም ኢሳያስ 61 ዋነኛው ማሳያ ነው።

ይህን ክፍል በጥንቃቄ ስናጠና፥ በመሉ ምዕራፉ አንድ ተናጋሪ ብቻ እንዳለ እንረዳለን። ከቁ.1 ጀምሮ እስከ መጨረሻው ቁጥር ድረስ የሚናገረው አንድ አካል ብቻ ነው። ሁለተኛ ተናጋሪ የለም። ስለዚህ የተናጋሪ ለውጥ አለ ብሎ መከራከር አይቻልም። ከአንድ በላይ ተናጋሪ ሳይኖር፥ የተናጋሪ ለውጥ ሊኖር አይችልምና። በቁ.1 ላይ መላኩን የተናገረው አካል ነው በቁ.8 ላይ እግዚአብሔር መሆኑን የተናገረው። ይህ በይበልጥ የክርስቶስ ተቃዋሚዎችን መከራከሪያ ያፈርሰዋል

ዛሬ በዚህ ክፍል፥ እግዚአብሔር ቢፈቅድ በኢሳይያስ 61 ላይ እግዚአብሔር ነኝ በማለት አምላክነቱን የገለፀው መሲሁ መሆኑን በማስረጃ ማሳየቱን እንቀጥላለን

5) ለሰዎች ፍዳቸውን ይሰጣል

"እኔ እግዚአብሔር ፍርድን የምወድድ ስርቆትንና በደልን የምጠላ ነኝ፤ #ፍዳቸውንም #በእውነት #እሰጣቸዋለሁ፥ ከእነርሱም ጋር የዘላለም ቃል ኪዳን አደርጋለሁ።"
(ትንቢተ ኢሳይያስ 61:8)

በኢሳይያስ 61 ላይ ያለው ተናጋሪ እኔ እግዚአብሔር በማለት አምላክነቱን ከገለፀ በኋላ፥ ለሰዎች ፍዳቸውን እንደሚሰጣቸው ይናገራል። ፍዳቸውን ይሰጣቸዋል ማለት እንደ ስራቸው ይከፍላቸዋል፥ መጠን ዋጋቸውን ይሰጣቸዋል ማለት ነው። "ፍዳ" ተብሎ የተተረጎመው የዕብራይስጥ ቃል "פְּעֻלָּה/ፔኡላህ" ሲሆን "ስራ፥ ተግባር" የሚለውን ሀሳብ ያመለክታል። ይህ ማለት፥ በዚህ ክፍል ላይ እየተናገረ ያለው አካል ለሰዎች እንደ ስራቸው መጠን ይፈርድባቸዋል፥ የሚገባቸውን ይሰጣቸዋል ማለት ነው።

ይህ ተናጋሪው መሲሁ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው። ምክንያቱም እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ መሰረት፥ ለሰዎች እንደ ስራቸው መጠን የሚሰጣቸው፥ የሚገባቸውን ፍርድ የሚሰጣቸው እርሱ ነውና፦

"ነገር ግን ለድሆች #በጽድቅ #ይፈርዳል፥ ለምድርም የዋሆች #በቅንነት #ይበይናል፤ በአፉም በትር ምድርን ይመታል፥ በከንፈሩም እስትንፋስ ክፉዎችን ይገድላል።"
(ትንቢተ ኢሳይያስ 11:4)

በዚህ ስፍራ ተተንብዮ እንደምንመለከተው፤ መሲሁ በጽድቅ ይፈርዳል፥ በቅንነትም ይበይናል። ይህ ማለት ሰዎች ለሚሰሯቸው ስራዎች በሙሉ የሚገባውን ፍርድና ብይን ይሰጣል ማለት ነው። ይህ ቃል ግልፅ እንደሚያደርገው፥ መሲሁ ወደ ምድር ከተመለሰ በኋላ ከሚያከናውናቸው ነገሮች መካከል አንዱ ቅንና ጻድቅ የሆነን ፍርድ መስጠት ነው። በኢሳ 61:8 ላይ የምናየው ይህንኑ ነው። በቁ.1 ላይ በእግዚአብሔር እንደተቀባና እንደተላከ የተናገረው አካል፥ በቁ.8 ላይ ለሰዎች ፍዳቸውን እንደሚሰጣቸው ይናገራል። ይህ በዚህ ክፍል ላይ እየተናገረ ያለው አካል፥ መሲሁ መሆኑን በማያሻማ ሁኔታ ያረጋግጣል። ስለዚህ በቁ.8 ላይ "እኔ እግዚአብሔር" በማለት አምላክነቱን የገለፀው ራሱ መሲሁ ነው ማለት ነው።

"እነሆ ደግፌ የያዝሁት ባሪያዬ፤ ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት ምርጤ፤ በእርሱ ላይ መንፈሴን አድርጌአለሁ፥ እርሱም #ለአሕዛብ #ፍርድን ያወጣል።"
(ትንቢተ ኢሳይያስ 42:1)

በዚሁ ክፍል ላይም መሲሁ ለአሕዛብ ፍርድን እንደሚያወጣ ተተንብዮ እንመለከታለን። ኢሳያስ 42 እጅግ ታዋቂ ትንቢት ሲሆን፥ መሲሁ ምድርን ሁሉ ለመግዛት ሲመለስ የሚያደርጋቸውን ነገሮች ይዘረዝራል። ከእነዚህም ነገሮች አንዱ ፍርድን ማውጣት ነው። መሲሁ በሚገዛበት ዘመን፥ በአሕዛብ ሁሉ ላይ ይፈርዳል። ይህ ማለት፥ እንደ ስራቸው መጠን የሚገባቸውን ፍርድ ይሰጣቸዋል ማለት ነው። የስራቸውን ዋጋ የሚቀበሉት ከእርሱ ነው። ይህ በኢሳ 61:8 ላይ የስራቸውን ፍዳ እንደሚሰጥ የተናገረው እርሱ መሆኑን ያሳያል።

ባለፉት ክፍሎች ለማየት እንደሞከርነው በኢሳ 42:1 ላይ ለመሲሁ የተባለው ነገር፥ በኢሳ 61:1 ላይ የተባለው ነገር ነው። በሁለቱም ቦታዎች ላይ የእግዚአብሔር መንፈስ በአገልጋዩ ላይ እንዳለ ተነግሯል። አሁን ደግሞ በዚያ በሁለቱም ምዕራፎች ላይ ይህ አገልጋይ ፈራጅ መሆኑ መገለጹ፥ የሁለቱን ክፍሎች ቁርኝትና የመልእክት አንድነት ያሳያል። ሁለቱም መሲሃዊ ምዕራፎች ናቸው በራሱ በኢሳይያስ መጽሐፍ የሚገኙ እንዲህ አይነት የመልእክት አንድነት ያላቸው ክፍሎች ናቸው።

➣ በኢሳ 42:1 ላይ የተገለጸው የመሲሁ ፈራጅነት፥ በቁ.3-4 ላይም ተደግሞ እናገኘዋለን፦

"3፤ የተቀጠቀጠን ሸምበቆ አይሰብርም፥ የሚጤስንም ክር አያጠፋም፤ #በእውነት #ፍርድን #ያወጣል። 4፤ #በምድርም #ፍርድን #እስኪያደርግ ድረስ ይበራል እንጂ አይጠፋም፤ አሕዛብም በስሙ ይታመናሉ።"
(ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ 42:3-4)

በዚህ ስፍራም መሲሁ በእውነት ፍርድን እንደሚያወጣ ተነግሮ እንመለከታለን። ይህ አሁንም የሚረጋገጠው፥ መሲሁ በሰዎች ሁሉ ላይ የሚፈርድ መሆኑን ነው። መሲሁ በሰዎች ሁሉ ላይ ፍርድን በእውነት ያወጣል። በኢሳ 61:8 ላይ የምንመለከተው ይህንኑ ነው። በዚያ ክፍል ላይ የሚናገረው ተናጋሪ፥ ለሰዎች ፍዳቸውን በእውነት እንደሚሰጥ ይናገራል። ስለዚህ በኢሳ 42:3 ላይ በእውነት ፍርድን እንደሚያወጣ የተነገረለት መሲሁ ነው ማለት ነው። ኢሳ 42:3-4 እና ኢሳ 61:8 የማይካድ textual ግንኙነት አላቸው። በሁለቱም ቦታዎች መሲሁ #በእውነት ፍርድን እንደሚያወጣ ተነግሯል። ይህ በማያሻማ መልኩ ኢሳያስ 61 መሲሃዊ ምዕራፍ መሆኑንና፥ በኢሳ 61:8 ላይ እኔ እግዚአብሔር በማለት አምላክነቱን የገለፀው መሲሁ መሆኑን ነው። ክፍሎቹ ሊታበል የማይችል የቃላትና የመልእክት አንድነት አላቸውና።

"6፤ ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል። 7፤ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም ድረስ #በፍርድና በጽድቅ ያጸናውና ይደግፈው ዘንድ በዳዊት ዙፋንና በመንግሥቱ ላይ አለቅነቱ ይበዛል፥ ለሰላሙም ፍፃሜ የለውም። የእግዚአብሔር ቅንዓት ይህን ያደርጋል።"
(ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ 9:6-7)

በዚህ ቦታ ላይም እንደምናየው መሲሁ ፈራጅ መሆኑ ተገልጿል። ልክ እንደ ሌሎቹ መሲሃዊ ትንቢቶች፥ ኢሳ 9:6-7ም ሌላኛዋ ዝነኛ መሲሃዊ ትንቢት ነው። መሲሁ ዘላለማዊ ዙፋን እንደሚኖረው (መዝ 45:6 ሕዝ 37:25 ዳን 7:13-14) በዳዊት ዙፋን ላይ እንደሚቀመጥ (መዝ 132:11 2 ሳሙ 7:12-16 1ዜና 17:11-14) አምላክ እንደሆነ (መዝ 45:6 መዝ 110:1 ዘካ 9:14-17 ሚክ 4:7) የሚናገር መሲሃዊ ትንቢት ነው። ይህ ክፍል፥ መሲሁ በዳዊት ዙፋን ለዘላለም ሊነግስ ወደ ምድር ከመጣ በኋላ የሚሆነውን ነገር ያትታል። እርሱም ፈራጅነቱ ነው። ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም ድረስ በጽድቅና በፍርድ ያጸናዋል። ይህ መሲሁ ዘላለማዊ ፈራጅነት እንዳለው የሚያሳይ ነው። ለዘላለም የፈራጅነት ስልጣን አለው። ይህ መሲሁ ክርስቶስ ኢየሱስ በእርግጥም በሰዎች ሁሉ ላይ የሚፈርደው ፈራጅ መሆኑን ያረጋግጣል። በኢሳይያስ 61:8 ላይም የምንመለከተው ይህንኑ ነው።
383 viewsedited  09:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-26 00:05:21 ረብል አለሚን፦ ሌላኛው እስላማዊ ኩረጃ

በቁርአን ውስጥ የሙስሊሞች አምላክ አላህ ከተጠራባቸው መጠሪያዎች መካከል አንዱ "ረብል አለሚን" የሚለው መጠሪያ ነው። ረብል አለሚን ማለት በአረብኛ "የአለማቱ ጌታ" ማለት ነው። ይህ ስያሜ በቁርአን ብቻ ሳይሆን፥ በሀዲሳትም እንዲሁ ጥቅም ላይ ውሏል። በሀዲሳትም ላይ አላህ በዚህ ስያሜ ሲጠራ እንመለከታለን።

በቁርአን ላይ አላህ በዚህ መጠሪያ የተጠራባቸውን ቦታዎች እንመልከት፦

"ምስጋና ለአላህ ይገባው #የዓለማት_ጌታ ለኾነው" (ሱራ 1:2)

" #ከዓለማት_ጌታ የተወረደ ነው፡፡" (ሱራ 56:80)

" #የዓለማት_ጌታ አላህ ካልሻም አትሹም፡፡" (ሱራ 81:29)

"በእርሱም ላይ ምንም ዋጋ አልለምናችሁም፡፡ ዋጋዬ #በዓለማት_ጌታ ላይ እንጅ በሌላ ላይ አይደለም" (ሱራ 26:145)

በሀዲሳትም ላይ አላህ በዚህ መጠሪያ የተጠራባቸውን ቦታዎች እንመልከት፦

"Ibn Abbas narrated: The Prophet went from Al-Madinah to Makkah, not fearing anyone except Allah #the_Lord_of_the_worlds, and he prayed two Rak'ah" (Jami at-Tirmidhi 547)

"It was narrated that Ali bin Abi Talib (رضي الله عنه) said: The Messenger of Allah (ﷺ) taught me to say, if calamity befell me: “There is no god but Allah, the Forbearing the Most Generous; glory be to Allah, blessed be Allah, the Lord of the mighty Throne; praise be to Allah, #the_Lord_of_the_Worlds” (Musnad Ahmad 701)

"Ibn 'Abbas said, "When one of you sneezes and says, 'Praise be to Allah,' the angel says, 'The Lord of the Worlds.' When you say, #The_Lord_of_the_Worlds, the angel says, 'May Allah have mercy on you" (Al-Adab Al-Mufrad 920)

ነገር ግን ይህ መጠሪያ ከአይሁዳውያን ታልሙድ የተኮረጀ መሆኑን ያውቁ ኖሯል?

አዎ፥ ልክ ከዚህ በፊት እንዳየናቸው ኩረጃዎች ሁሉ ይህኛውም መጠሪያ ከአይሁዳውያን ታልሙድ የተኮረጀ መጠሪያ ነው። የአይሁድ ረበናት በታልሙዳቸው ላይ አምላክን ለመጥራት ከሚጠቀሟቸው መጠሪያዎች አንዱ "ሪቦና ሼል ኦላም" ወይንም "የአለማት ጌታ" የሚለው መጠሪያ ነው። መሐመድም እነርሱ አምላክን በዚህ ስያሜ ሲጠሩ ሰምቶ የእስልምና አካል ያደረገው ኩረጃ ነው። ማስረጃው እነሆ፦

"Based on these concepts, I will explain important principles regarding the deeds of the #Master_of_the_worlds to provide a foothold for a person of understanding to develop love for God" (Mishneh Torah, foundations of the Torah 2:2)

[ https://www.sefaria.org/Mishneh_Torah%2C_Foundations_of_the_Torah.2.2?ven=Mishneh_Torah,_trans._by_Eliyahu_Touger._Jerusalem,_Moznaim_Pub._c1986-c2007&with=all&lang=bi ]

"He began and said #Master_of_the_worlds, redeem and save, rescue and deliver Your people, Israel, from the pestilence and from the sword, and from spoil, and from the blight, and from the mildew, and from all types of afflictions that suddenly erupt and come to the world" (Ketubot 8b:11)

[ https://www.sefaria.org/Ketubot.8b.11?ven=William_Davidson_Edition_-_English&lang=bi&with=all&lang2=en ]

"Abraham said before the Holy One, praise to Him #Master_of_the_worlds it is open and known before You that when You said to me to sacrifice my son Isaac I could have answered and said before You yesterday You said to me for in Isaac will your descendants be named and now You are saying sacrifice him as elevation offering" (Jerusalem Talmud Taanit 2:4)

[ https://www.sefaria.org/Jerusalem_Talmud_Taanit.2.4.2?ven=The_Jerusalem_Talmud,_translation_and_commentary_by_Heinrich_W._Guggenheimer._Berlin,_De_Gruyter,_1999-2015&with=all&lang=bi ]

"May it please You to make Zion prosper rebuild the walls of Jerusalem (Psalms 51:20) For we have trusted only in You, King; high and elevated God, #Master_of_the_worlds" (Siddur Sefard, Simchat Torah, Hakafot 5)

[ https://www.sefaria.org/Siddur_Sefard%2C_Simchat_Torah%2C_Hakafot.5?ven=Sefaria_Community_Translation&with=all&lang=bi ]

"Through these apertures which are in the east the sun goes forth and opposite to them in the west the sun sets. The Shekhinah is always in the west. The sun sets and worships before the King of Kings, the Holy One, blessed be He, saying: #Lord_of_all_worlds! I have done according to all that Thou hast commanded me" (Pirkei DeRabbi Eliezer 6:11)

[ https://www.sefaria.org/Pirkei_DeRabbi_Eliezer.6.11?ven=Pirke_de_Rabbi_Eliezer,_trans._Rabbi_Gerald_Friedlander,_London,_1916&lang=bi ]

ይህ መጠሪያ አይሁዳውያን በታልሙድ አምላክን የሚጠሩበት መጠሪያ እንደሆነ ከዚህም በላይ ማስረጃ ማምጣት እንችላለን። ይህ ስም የአይሁድ ረበናት በታልሙድ ውስጥ ለአምላክ የሰጡት ስያሜ ነው። መሐመድም ይህን ስያሜ ለአምላክ ሲሰጡ ሰምቶ በመኮረጅ እስልምና ውስጥ አካተተው

ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ለማለት እንደሞከርነው፥ ኮራጆቹ አይሁዳውያኑ ናቸው ሊባል አይችልም። ምክንያቱም የአይሁድ ረቢዎቹም ሆነ፥ ታልሙዱ ከመሐመድና ከቁርአን በፊት ነበሩ። ስለዚህ የኩረጃ ክስ ቢነሳ ተጠያቂ የሚሆነው ማን እንደሆነ ግልፅ ነው። ይህ እስልምና ከተለያዩ ምንጮች የተኮረጀ የውሸት ሃይማኖት መሆኑን በግልፅ ያሳያል።
259 views21:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-21 14:10:42 " #አምላክ ሆይ፥ ዙፋንህ ለዘላለም ነው፤ የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ነው።"
(መዝሙረ ዳዊት 45:6)

በዚህ ስፍራ፥ መሲሁ አምላክ ሆይ ተብል ሲጠራ እንመልከታለን። መዝሙር 45 ታዋቂ መሲሃዊ መዝሙር ሲሆን፥ መሲሁ አምላክ መሆኑ የተነገረበት አንዱ ክፍል ነው። እንደ ኦሪትና እንደ ራሱ እንደ መዝሙረ ዳዊት አስተምህሮ መሰረት፥ ዘላለማዊ ዙፋን ያለው አምላክ እግዚአብሔር ብቻ ነው (ዘጽ 15:18 መዝ 29:10 መዝ 146:10) ይህ አምላክነቱ እውነተኛ አምላክነት እንደሆነ ያረጋግጣል። ስለዚህ መሲሁ አምላክ የተባለበት አውድ፥ ትክክለኛ መለኮትነትን የሚያመለክት አውድ ነው ማለት ነው። በተጨማሪም በዚሁ በመዝሙር 45 ላይ፥ መሲሁን የቀባው እግዚአብሔር መሆኑን እንረዳለን (ቁ.7) ይህ ክፍሉ ከኢሳያስ 61 ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት እንዳለው ያሳያል።

ምክንያቱም በዚያም ስፍራ ተናጋሪው በእግዚአብሔር መቀባቱን ይናገራል። ይህ በሁለቱም ስፍራ ላይ የተነገረለት አካል አንድ አካል መሆኑን በማያሻማ መልኩ ያሳያል። ሁለቱም ክፍሎች የሚናገሩት ስለ መሲሁ ነው። መዝ 45:7 መሲሁ በእግዚአብሔር መቀባቱን ከማሳየት ባሻገር፥ እግዚአብሔር የመሲሁ አምላክ መሆኑን ".. አምላክህ" በማለት ግልፅ ያደርጋል። ይህ አሁም በኢሳይያስ 61 ላይ ያለው ተናጋሪ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው። ምክንያቱም በኢሳ 61:10 ላይ ተናጋሪው እግዚአብሔርን "አምላኬ" በማለት ይጠራዋል። ስለዚህ በዚህ ክፍላ ላይ ያለው ተናጋሪ በመዝሙር 45 ላይ የተነገረለት መሲሁ ነው ማለት ነው። በኢሳ 61:8 ላይ እግዚአብሔር ነኝ ያለው፥ በመዝሙር 45:6 ላይ የተዘመረለት ዘላለማዊ ዙፋን ያለው አምላክ በመሆኑ ነው

"ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ #ኃያል_አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።"
(ትንቢተ ኢሳይያስ 9:6)

በዚሁ ስፍራም እንዲሁ፥ መሲሁ አምላክ መሆኑ ተገልጾ እናገኛለን። በኢሳይያስ 9:6 ላይ የሚወለደው ሕጻን (መሲሁ) ኀያል አምላክ መሆኑ ተነግሯል። ኀያል አምላክ የሚለው ስም፥ በቀጣዩ ምዕራፍ ላይ ለእግዚአብሔር የዋለ ስም በመሆኑ (ኢሳ 10:21) ትክክለኛ አምላክነትን እንደሚያመለክት እርግጠኛ መሆም እንችላለን። ኢሳያስ 9:6-7 ታዋቂ መሲሃዊ ትንቢት ሲሆን፥ መወለዱ የተተነበየለት ሕጻን በዳዊት ዙፋን ላይ ለዘላለም እንደሚቀመጥ ተነግሯል።

ይህ ኢሳያስ 9:6-7 መሲሃዊ ለመሆኑ ግልፅ ማሳያ ነው። በዳዊት ዙፋን ላይ ለዘላለም የሚቀመጠው መሲሁ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምራል (መዝ 132:11 ሕዝ 37:25 መዝ 132:17) በተጨማሪም ይህ የሚወለደው ሕጻን ለሰላሙ ፍጻሜ እንደሌለ ተነግሯል። ይህ መሲሁ ለመሆኑ ሌላ ማሳያ ነው፥ ምክንያቱም እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ መሲሁ ምድርን በሚገዛበት ዘመን ፍጹም ሰላም ይሆናል (መዝ 72:7 ሚክ 4:3 ኢሳ 2:4 ኢሳ 11:6-8 ዘካ 9:10) ስለዚህ መሲሁ ኀያል አምላክ ተብሎ መጠራቱ፥ ትክክለኛ መለኮት መሆኑን ያረጋግጣል

ሌላው ሊስተዋል የሚገባው ነገር፥ የዚህ ሕጻን ውልደት የእግዚአብሔር ቅንዓት ያደረገው ነገር መሆኑ ነው። ይህ ማለት ይህ ሕፃን የተወለደው በእግዚአብሔር ላኪነትና ፍቃድ ነው ማለት ነው። ስለዚህ ሕፃኑ በእግዚአብሔር ላኪነትና ፈቃድ ቢወለድም፥ ኀያል አምላክ ነው። በኢሳይያስ 61 ላይም የምንመለከተው ይህንኑ ነው። ተናጋሪው በእግዚአብሔር ቢላክም (ቁ.1) እግዚአብሔር ነኝ አለ። ስለዚህ በኢሳ 61:8 ላይ እኔ እግዚአብሔር ነኝ ያለው ተናጋሪ፥ በኢሳ 9:6-7 የተተነበየለት ኀያል አምላክ የሆነው መሲሁ ነው ማለት ነው። በራሱ በኢሳይያስ መጽሐፍ መጽሐፍ ላይ እግዚአብሔር አስነስቶት/ልኮት ነገር ግን እግዚአብሔር መሆኑ የተነገረለት እርሱ ነውና።

የመሲሁ አምላክነት በብሉይ ኪዳን በብዙ ቦታ ተገልጿል (መዝ 110:1 ሚክ 5:2 ዳን 7:13-14 ኢሳ 53:1) የመሲሁ አምላክነት በብሉይ ኪዳን መብራራቱ በኢሳይያስ 61:8 ላይ በእግዚአብሔር የተቀባ ሆኖም እንኳ፥ እግዚአብሔር ነኝ ያለው መሲሁ መሆኑን በሚገባ ያሳያል።

5) ፍርድን ይወዳል፥ ስርቆትንና በደልን ይጠላል

"እኔ እግዚአብሔር #ፍርድን_የምወድድ #ስርቆትንና_በደልን #የምጠላ ነኝ፤ ፍዳቸውንም በእውነት እሰጣቸዋለሁ፥ ከእነርሱም ጋር የዘላለም ቃል ኪዳን አደርጋለሁ።"
(ትንቢተ ኢሳይያስ 61:8)

በኢሳይያስ 61 ላይ ያለው ተናጋሪ ስለ ራሱ ከተናገራቸው ሌሎች ነገሮች መካከል፥ ፍርድን እንደሚወድና አመጻን እንደሚጠላ ነው። ስለዚህ ተናጋሪው ትክክለኛ ፍርድን የሚወደድ፥ ስርቆትና በደልን የሚጸየፍ ነው ማለት ነው። አሁንም ይህ ተናጋሪው መሲሁ መሆኑን የሚያሳይ ነው።

ምክንያቱም ጽድቅን የሚወድደው፥ አመጽንም የሚጠላው መሲሁ ነውና፦

" #ጽድቅን #ወደድህ #ዓመፃንም #ጠላህ፤ ስለዚህ ከባልንጀሮችህ ይልቅ እግዚአብሔር አምላክ የደስታ ዘይትን ቀባህ።"
(መዝሙረ ዳዊት 45:7)

በዚሁ ስፍራ፥ መሲሁ ጽድቅን እንደሚወድ ዓመፃንም እንደሚጠላ ተነግሮ እንመለከታለን። ይህ ማለት መሲሁ መልካም የሆኑ ነገሮችን የሚወድድ፥ ክፉ የሆኑ ነገሮችን ደግሞ የሚጠላ መሆኑን ያረጋግጣል። በኢሳይያስ 61 ላይም የምንመለከተው ይህንን ነው። ነቢዩ ኢሳያስ በኢሳይያስ 61 ላይ ያለውን ትንቢታዊ መልእክት ሲጽፍ፥ መዝሙር 45ን ታሳቢ በማድረግ ነው። በመሉ በመዝሙር 45 ላይ ለመሲሁ የተነገሩት ነገሮች በኢሳይያስ 61 ላይ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ተደግመዋል። ይህ በእርግጥም ኢሳያስ 61 መሲሃዊ መልእክት መሆኑንና፥ በኢሳይያስ 61:8 ላይ እኔ እግዚአብሔር ነኝ ያለው መሲሁ መሆኑን ያረጋግጣል። በሁለቱም ቦታ ጽድቅን የሚወድደው፥ አመጻንም የሚጠላ መሆኑ ተገልጿልና። በእግዚአብሔር መቀባቱና አምላክነቱ በተነገረበት በዚያው አውድ ስለ እርሱ እንዲህ መባሉ፥ የትንቢቱ ብቸኛው ፍጻሜ እርሱ መሆኑን ያረጋግጣል

ይቀጥላል
567 views11:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-21 14:10:41 እኔ እግዚአብሔር (ክፍል 3)

" #እኔ #እግዚአብሔር ፍርድን የምወድድ ስርቆትንና በደልን የምጠላ #ነኝ፤ ፍዳቸውንም በእውነት እሰጣቸዋለሁ፥ ከእነርሱም ጋር የዘላለም ቃል ኪዳን አደርጋለሁ።"
(ትንቢተ ኢሳይያስ 61:8)

ባለፉት ተከታታይ ክፍሎች መሲሁ ክርስቶስ ኢየሱስ አንድም ቦታ በራሱ አንደበት "እኔ እግዚአብሔር ነኝ" ያለበት ቦታ የለም ለሚለው የሙስሊሞች የሀሰት ተቃውሞ መልስ መስጠት ጀምረን ነበር። ኢየሱስ ክርስቶስ በራሱ አንደበት እግዚአብሔር መሆኑን ተናግሯልና። ለዚህም ኢሳያስ 61 ዋነኛው ማስረጃ ነው

ከዚህ በፊት ለመናገር እንደሞከርነው፥ አምላክነት "እግዚአብሔር ነኝ" በማለት ብቻ አይደለም የሚገለፀው። አምላክነት መለኮታዊ ተግባርን በመስራት፥ የመለኮታዊ ባህሪያት ባለቤት መሆንን በማሳወቅ ነው የሚገለፀው። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ መለኮታዊ ባህርይ እንዳለው፥ መለኮታዊ ስራዎችን እንደሚሰራ በቃልም በተግባርም ገልጿል። ይህ በሥጋ የመጣው አምላክ መሆኑን ያሳያል። ነገር ግን ከዚያም በተጨማሪ፥ ቃል በቃል "እግዚአብሔር ነኝ" ብሎም ተናግሯል። ይህ የክርስቶስ ተቃዋሚዎችን ሙግት ከስር መሰረቱ ይነቅለዋል

ዛሬ በዚህ ክፍል፥ ጌታ ቢፈቅድ በኢሳይያስ 61 ላይ እግዚአብሔር ነኝ በማለት አምላክነቱን የገለፀው፥ መሲሁ መሆኑን በማስረጃ ማሳየት እንቀጥላለን

4) እግዚአብሔር ነኝ ብሏል

" #እኔ #እግዚአብሔር ፍርድን የምወድድ ስርቆትንና በደልን የምጠላ ነኝ፤ ፍዳቸውንም በእውነት እሰጣቸዋለሁ፥ ከእነርሱም ጋር የዘላለም ቃል ኪዳን አደርጋለሁ።"
(ትንቢተ ኢሳይያስ 61:8)

በዚህ ሥፍራ ላይ በኢሳይያስ 61 ላይ የምንመለከተው ተናጋሪ፥ በቀጥታ እኔ እግዚአብሔር ነኝ ሲል እንመለከታለን። በቁ.1 ላይ ራሱ ተናጋሪ በእግዚአብሔር እንደተላከ ይናገራል። ነገር በዚህ በቁ.8 ላይ እርሱ ራሱ እግዚአብሔር መሆኑን ገልጿል። ይህ ማለት፥ ተናጋሪው ሰው ብቻ የሆነ አካል ወይንም ሌላ ፍጡር ሳይሆን፥ እግዚአብሔር ነው ማለት ነው። ይህ እውነት፥ ተናጋሪው መሲሁ ለመሆኑ ሌላ ማስረጃ ነው

ምክንያቱም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከእግዚአብሔር በአካል ተነጥሎ፥ እግዚአብሔር አስነስቶት፥ ነገር ግን "እግዚአብሔር" በመባል የተጠራው መሲሁ ነው። ስለዚህ በቁ.1 ላይ በእግዚአብሔር እንደተላከ ተናግሮ፥ በቁ.8 ላይ እግዚአብሔር ነኝ ያለው መሲሁ ነው ማለት ነው፦

(ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ 23)
----------
5፤ እነሆ፥ ለዳዊት ጻድቅ #ቍጥቋጥ #የማስነሣበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል #እግዚአብሔር፥ እርሱም እንደ ንጉሥ ይነግሣል፥ ይከናወንለታልም፥ በምድርም ፍርድንና ጽድቅን ያደርጋል።

6፤ በዘመኑም ይሁዳ ይድናል እስራኤልም ተዘልሎ ይቀመጣል፥ #የሚጠራበትም ስም። #እግዚአብሔር ጽድቃችን ተብሎ ነው።

በዚህ ክፍል ላይ እግዚአብሔር መሲሁን እንደሚያስነሳ ቃል ሲገባ እንመለከታለን። ለዳዊት ቁጥቋጦን እንደሚያስነሳ በቁ.5 ላይ ቃል ይገባል። የሚያስነሳው ቁጥቋጦ "ለዳዊት" የተባለበት ምክንያት፥ እግዚአብሔር ለዳዊት ከሆዱ ፍሬ በዙፋኑ ላይ ለዘላለም እንደሚያስቀምጥ ቃል ስለገባለት ነው (መዝ 132:11 መዝ 132:17 2 ሳሙ 7:12-16) ይህ መሲሃዊ ትንቢት ነው። እግዚአብሔር፥ የንጉሥ ዳዊት የስጋ ልጅ የሆነው መሲሁን በዙፋኑ ላይ ያስቀምጠዋል። ለዚህ ነው በኤር 23:5-6 ላይ "ለዳዊት" አስነሳለሁ ያለው።

ቀጥሎም በዚያው በቁ.5 ላይ የሚያስነሳውን ንጉሥ "ቁጥቋጦ" በማለት ይጠራዋል። በመላው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፥ ይህ የመሲሁ ስያሜ ነው። መሲሁ በብዙ ስሞች የተጠራ ሲሆን፥ ከነዚህ ስያሜዎች አንዱ "ቁጥቋጥ" ነው። (ኤር 33:15-16 ዘካ 3:8 ዘካ 6:12 ኢሳ 4:2) ስለዚህ በክፍሉ እየተነገረ ያለው ስለ መሲሁ ነው ማለት ነው። በተጨማሪም በዚያው በቁ.6 ላይ እንደ ንጉሥ እንደሚነግስ ተገልጿል። እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ደግሞ እንደ ንጉሥ የሚነግሰው መሲሁ ነው (ሆሴ 3:5 ዘካ 9:9-10 መዝ 45:1) ይህ ኤር 23:5-6 መሲሃዊ ትንቢት መሆኑን ያረጋግጣል።

➣ ነገር ግን ይህ እግዚአብሔር የሚያስነሳው መሲህ፥ በራሱ በእግዚአብሔር "እግዚአብሔር ጽድቃችን" ተብሎ ሲጠራ እንመለከታለን። ስለዚህ እግዚአብሔር የሚያስነሳው ይህ መሲህ፥ ፍጡር ሳይሆን እግዚአብሔር ነው ማለት ነው። በቀጥታ እግዚአብሔር ተብሎ ተጠርቷልና።

ይህ እግዚአብሔር አስነስቶት እንኳ፥ እግዚአብሔር ተብሎ የሚጠራው መሲሁ መሆኑን ያረጋግጣል። በኢሳይያስ 61 ላይ ያለው ተናጋሪም፥ በእግዚአብሔር የተላከ ቢሆንም እንኳ እግዚአብሔር መሆኑን ተናግሯል። ስለዚህ እርሱ በኤር 23:5-6 ላይ የተተነበየለት መሲህ መሆኑን ያረጋግጣል።

"በአምላካቸው #በእግዚአብሔር #አበረታቸዋለሁ፥ በስሙም ይመካሉ፥ ይላል እግዚአብሔር።"
(ትንቢተ ዘካርያስ 10:12)

በዚህም ክፍል ላይ እግዚአብሔር መሲሁን እግዚአብሔር በማለት ሲጠራው እንመለከታለን። የዘካርያስ 10 ጠቅላላ አውድ፥ በመጨረሻው ዘመን እንዴት የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔር ለአባቶቻቸው ሊሰጣቸው ወደማለላቸው ምድር እንደሚመለሱ የሚናገር ክፍል ነው። የእስራኤል ልጆች ወደ ምድራቸው በሚመለሱበት ሰአት፥ እግዚአብሔር በአምላካቸው በእግዚአብሔር እንደሚያበረታቸው በቁ.12 ላይ ይናገራል። እዚህ ጋር እግዚአብሔር "እግዚአብሔር" በማለት የጠራው መሲሁን ነው

ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስን ስናጠና፥ የእስራኤልን ሕዝብ ወደ ምድራቸው የሚመልሳቸው መሲሁ መሆኑን እንረዳለን። እንደ ቃሉ አስተምህሮ መሰረት፥ መሲሁ በሕያዋንና በሙታን ሊፈርድ ዳግም ወደ ምድር በሚመለስበት ሰአት በአራቱም የምድር ማዕዘናት ተበትነው የነበሩትን የእስራኤል ልጆች ወደ ገዛ ምድራቸው ይመልሳቸዋል (ኢሳ 11:12 ኤር 23:5-8 ሕዝ 34:13-24 ኤር 33:10-16 ሕዝ 37:21-25 ኤር 30:3-10) ይህ ትንቢት የሚፈጸመው በመሲሁ ዳግም ምጽአት ነው። ስለዚህ በዘካ 10:12 ላይ እግዚአብሔር "እግዚአብሔር" በማለት የጠራው መሲሁን ነው ማለት ነው። ይህ የሚሆነው በእርሱ አማካኝነት ነውና።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ "በ" መካከለኝነትን የሚያመለክት ነው። እግዚአብሔር በሆነ አካል አማካኝነት ስራውን ሲሰራ፥ "በ" እርሱ ሰራ ይባላል። ለምሳሌ፦ እግዚአብሔር በሙሴና በአሮን እጅ ሕዝቡን መርቷል (መዝ 77:20) "በ" ሙሴና "በ" አሮን ሊባል የቻለው፥ እግዚአብሔር እነርሱን ስለላካቸው ነው (ሚክ 6:4) ስለዚህ "በ" መካከለኝነትን ወይንም intermediary መሆንን ያሳያል።

በዘካ 10:12 ላይም "በ" እግዚአብሔር አበረታቸዋለሁ ያለው፥ እግዚአብሔር ሕዝቡን በመሲሁ በልጁ በክርስቶስ ኢየሱስ ስለሚያበረታቸው ነው። ይህ የሆነው ደግሞ መሲሁ በእግዚአብሔር የተላከ በመሆኑ ነው (ኢሳ 61:1) ስለዚህ በኢሳይያስ 61:8 ላይ እግዚአብሔር መሆኑን የተናገረው ተናጋሪ፥ በዘካ 10:12 ላይ እግዚአብሔር ተብሎ የተጠራው መሲሁ ነው ማለት ነው
559 views11:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-16 22:44:09 ዓሌይሂ ሰላም፦ ሌላኛው እስላማዊ ኩረጃ

ሙስሊሞች ስላለፉት ነቢያት ሲናገሩ "..ዓሌይሂ ሰላም" ይላሉ። "ዓሌይሂ ሰላም" ማለት "..በእርሱ ላይ ሰላም ይሁን" ማለት ነው። ይህን አባባል ላለፉት ነቢያት ሆነ ለመሐመድ የሚጠቀሙት ሲሆን፥ በሀዲሳትም ውስጥ በጣም ተደጋግሞ እንመለከተዋለን።

ነገር ግን ይህ አባባል ከአይሁዶች ታልሙድ የተኮረጀ መሆኑን ያውቁ ኖሯል?

አዎ፥ ይህ ታዋቂ የሙስሊሞች አባባል ከአይሁዳውያን ታልሙድ የተኮረጀ ነው። አይሁዳውያን በታልሙዳቸው ስለ ቀደሙት ነቢያት ሲናገሩ፥ "..አላቫ ሻሎም" ወይንም "ሰላም በእርሱ ላይ ይሁን" ይላሉ። ዓሌይሂ ሰላም የዚህ አባባል አረብኛ ግልባጭ ነው። መሐመድ፥ አይሁዶች ስለ ቀደሙት ነቢያት ሲናገሩ የሚጠቀሙትን አባባል ሰምቶ፥ ወደ እስልምና ያካተተው ኩረጃ ነው። ማስረጃው እነሆ፦

"..with ten tests Abraham, our father, was tested - and he withstood them all; in order to show how great his love was, #peace_be_upon_him" (Pirkei Avot 5:3)

[ http://sefaria.org/Pirkei_Avot.5.3?ven=Open_Mishnah&lang=bi&with=all&lang2=en ]

"..Rabbi Elazar of Modi'in says: One who profanes the Kodeshim (sacred material); one who desecrates the holidays; one who whitens (embarrasses) the face of another in public; one who nullifies the covenant of Abraham our father, #peace_be_upon_him; one who reveals meanings in the Torah that run contrary to the law" (Pirkei Avot 3:11)

[ www.sefaria.org/Pirkei_Avot.3.11?ven=Sefaria_Community_Translation&lang=bi&with=all&lang2=en ]

"..the son of Rabbi Yose HaGelili, they said, "From where do we know that the essence of prayer is a commandment? From here - 'You shall fear the Lord, your God, and you shall serve Him' (Deuteronomy 6:13)." And they said, "Serve Him through His Torah; serve Him in His Temple." This means, direct yourself towards it, to pray towards there, as Solomon, #peace_be_upon_him, explained." (sefer hamizvot, positive commandments 5:1)

[ https://www.sefaria.org/Sefer_HaMitzvot%2C_Positive_Commandments.5.1?ven=Sefaria_Edition_2021,_Translated_by_Rabbi_Francis_Nataf.&with=all&lang=bi ]

"..On the fifth of Shevat the elders who were in the days of Joshua died. On the twenty-third of it all of Israel gathered against the tribe of Benjamin on account of the concubine in Gibeah. On the seventh of Adar Moses, our Teacher, may #peace_be_upon_him, died. On the ninth of it Beit Hillel and Beit Shammai divided." (Shulchan Arukh, Orach Chayim 580:2)

[ https://www.sefaria.org/Shulchan_Arukh%2C_Orach_Chayim.580.2?ven=Sefaria_Community_Translation&with=all&lang=bi ]

"..since he is not the cause of his evil, but rather the sin is the cause; like David, #peace_be_upon_him, stated (II Samuel 16:11), "leave him to curse, since the Lord told him so" - he made the matter depend upon his own sin, and not upon Shimei ben Gera." (Sefer HaChinuk 241:2)

[ https://www.sefaria.org/Sefer_HaChinukh.241.2?ven=Sefer_HaChinukh,_translated_by_R._Francis_Nataf,_Sefaria_2018&with=all&lang=bi ]

"..This too is a bad trait. And King Solomon, #peace_be_upon_him, said (Proverbs 22:28), “But one who really heard will speak forever.” Its explanation is that a man who puts into his heart to listen and audit to the essence of the words that they speak into his ears - in order that he can tell them correctly to others, and not have a treacherous tongue in his mouth - “will speak forever." (Shaarei Teshuvah 3:181)

[ https://www.sefaria.org/Shaarei_Teshuvah.3.181?ven=Sefaria_2020_Edition,_Translated_by_R._Francis_Nataf&with=all&lang=bi ]

"..And it is like Jeremiah, #peace_be_upon_him, stated (Jeremiah 18:23), "let them be made to stumble before You; act against them in Your hour of wrath!" - even in the time that they do charity, make them stumble that they should give it in the incorrect place." (Rabbeinu Yonah on Pirkei Avot 1:2:5)

[ https://www.sefaria.org/Rabbeinu_Yonah_on_Pirkei_Avot.1.2.5?ven=Sefaria_Community_Translation&with=all&lang=bi ]

ይህ አባባል የአይሁዶች ለመሆኑ ከዚህም በላይ ማስረጃ ማቅረብ እንችላለን። የቀደሙትን ነቢያት ስም አንስቶ "..ሰላም በእርሱ ላይ ይሁን" ማለት ታልሙዳዊ ምንጭ ያለው አባባል ነው። መሐመድ ግን ከእነርሱ በመስማት የእስልምና አንዱ አካል አደረገው።

ኮራጆቹ አይሁዳውያኑ ናቸው ማለት አይቻልም። ምክንያቱም አይሁዶቹም ታልሙዳቸውም መሐመድ ከመወለዱ ከምዕተ አመታት በፊት ነበሩ። ስለዚህ የኩረጃ ጉዳይ ቢነሳ፥ ኮራጁ ማን እንደሆነ አያጠራጥርም። አባባሉን፥ በዙሪያው ከነበሩት አይሁዳውያን ሰምቶ መቅዳቱ ግልፅ ነው። ይህ አሁንም፥ እስልምና ከብዙ ምንጮች ተኮርጆ የተውጣጣ የውሸት ሃይማኖት መሆኑን ያሳያል። መሐመድም በዙሪያው ያሉትን ነገሮች ቀድቶ እንደ አዲስ መገለጥ ያቀረበ ሰው እንጂ እውነተኛ ነብይ እንዳልነበር በይበልጥ ያረጋግጣል።
306 views19:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-12 16:51:36 በዚሁ ሥፍራም እግዚአብሔር በነቢዩ ኤርምያስ አማካኝነት፥ መሲሁ አለምን ሁሉ ሊገዛ ተመልሶ ሲመጣ የሚሆነውን ነገር ሲናገር እንመለከታለን። ለአባቶቻቸው ወደ ሰጣቸው ምድር እንደሚመልሳቸው ይናገራል። ይህ ማለት፥ ከተበተኑበት አገራት በሙሉ ወደ ምድራቸው እንደሚመለሱ ያሳያል።

በዚያም ዘመን፥ ሌሎች አሕዛብ እንደማይገዟቸውና ለአምላካቸው ለእግዚአብሔር ለሚያስነሳላቸው ለንጉሳቸው ለዳዊት (መሲሁ) ይገዛሉ። ከላይ እንደተነጋገርነው፥ መሲሁ በመጽሐፍ ቅዱስ ከተጠራባቸው ስሞች መካከል አንዱ ዳዊት ነው። በዚያ ዘመን ሌሎች አሕዛብ አይገዟቸውም ማለት ደግመው ወደ ምርኮ አይሄዱም ማለት ነው። ደግመው ከምድራቸው አይፈልሱም ማለት ነው። እግዚአብሔር ለአባቶቻቸው በማለላቸው ምድር ለአምላካቸው ለእግዚአብሔርና ለልጁ ለመሲሁ ለኢየሱስ ክርስቶስ ይገዛሉ ማለት ነው።

ይህ በሚገባ መሲሁ ሊገዛ ሲመለስ፥ እስራኤል በምርኮ ከተበተኑባቸው ስፍራዎች በሙሉ እንደሚመለሱ ያረጋግጣል። ለዚያም ነው በቁ.9 ለእግዚአብሔርና ለመሲሁ እንደሚገዙ ከተናገረ በኋላ፥ በቁ.10 ላይ "ባሪያዬ ያዕቆብ አንተን ከሩቅ፥ ዘርህንም ከምርኮ አገር አድናለሁ" የሚለው። መሲሁ በሚነግስት ዘመን፥ እስራኤል ከምርኮ አገር በእግዚአብሔር ይድናሉ። ከምርኮ አገር ወደ ሀገራቸው ይመለሳሉ። ይህ መሲሁ፥ ሊነግስ ተመልሶ በሚመጣበት ጊዜ የአይሁድ ሕዝብ በሙሉ እግዚአብሔር ወደ ማለለት ምድር እንደሚመለስ ያረጋግጣል። ከምርኮ የሚድኑበት ዘመን ለእርሱና ለአባቱ የሚገዙበት ዘመን ነውና

ስለዚህ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ መሰረት፥ በዳግም ምጽአቱ የእስራኤልን ሕዝብ ወደ ምድራቸው የሚመልሳቸው መሲሁ ነው። ይህ ከመሲሁ ተልዕኮዎች አንዱ ነው። በኢሳይያስ 61:4 ላይ የምንመለከተው ይህንኑ ነው። ተናጋሪው በሚገዛበት ሰአት የፈራረሱት ከተሞች ተመልሰው ይሰራሉ። ምክንያቱም እስራኤል ወደ ምድራቸው ይመለሳሉና። ይህ በእርግጥም የኢሳያስ 61 ተናጋሪ መሲሁ መሆኑን ያረጋግጣል

ይቀጥላል
286 viewsedited  13:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-12 16:51:36 በዚያም ሰአት በላያቸው አንድ እረኛን እንደሚያቆም ቃል ይገባል። ያም እረኛ ባሪያው ዳዊት ነው። በዚህ ስፍራ "ዳዊት" ተብሎ የተጠራው መሲሁ ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ መሲሁ ብዙ ስሞች አሉት። ከነዚህ ስሞች መካከል አንዱ ዳዊት ነው። እግዚአብሔር ለዳዊት ከሆዱ ፍሬ በዙፋኑ ላይ እንደሚያስቀምጥ ቃል ስለገባለት (2 ሳሙ 712) ከእርሱ የዘር ሀረግ የሚወለደው ክርስቶስ "ዳዊት" ተብሎ ተጠርቷል። (ሆሴ 3:4 ኢሳ 55:3-5) መሲሁ ተመልሶ በመጣ ጊዜ ለእስራኤል ሕዝብ እረኛ ይሆናል። በመካከላቸው ይነግሳል እረኛቸውም ይሆናል

ይህ እንደሚያረጋግጠው፥ መሲሁ ተመልሶ በመጣ ጊዜ ከሚሆኑት ነገሮች አንዱ የተበተኑት እስራኤላውያን ወደ ምድራቸው መመለስ ነው። መሲሁ እንደ እረኛ በሚነሳላቸው ሰአት እግዚአብሔር በመሲሁ አማካኝነት ወደ ምድራቸው ይመልሳቸዋል። ለዚያም ነው በክፍሉ እግዚአብሔር እንደ በጎች እረኛ እንደተመሰለው ሁሉ መሲሁም እረኛ ተብሎ የተጠራው። ልክ እንደ አባቱ ሕዘቡን ወደ ምድራቸው ይመልሳቸዋልና

"10፤ እግዚአብሔር እንዲ ይላል። እናንተ። ያለ ሰውና ያለ እንስሳ ያለች ባድማ ናት በምትሉአት በዚህች ስፍራ፥ የሚቀመጥባቸው በሌላ፥ ያለ ሰውና ያለ እንስሳ ባድማ በሆኑ #በይሁዳ #ከተሞችና #በኢየሩሳሌም #አደባባይ፥ 11፤ የሐሤት ድምፅና የደስታ ድምፅ፥ የወንድ ሙሽራ ድምፅና የሴት ሙሽራ ድምፅ። እግዚአብሔር ቸር ነውና፥ ምሕረቱም ለዘላለም ነውና የሠራዊትን ጌታ እግዚአብሔርን አመስግኑ የሚሉ ድምፅ፥ ወደ እግዚአብሔርም ቤት የምስጋናን መሥዋዕት የሚያመጡት ድምፅ እንደ ገና ይሰማል። #የምድርን #ምርኮ #ቀድሞ እንደ #ነበረ #አድርጌ #እመልሳለሁና፥ ይላል እግዚአብሔር። 12፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ባድማ ሆኖ፥ ያለ ሰውና ያለ እንስሳ ባለው በዚህ ስፍራ በከተሞችም ሁሉ መንጎቻቸውን የሚያሳርፉት #የእረኞች #መኖሪያ #ይሆናል። 13፤ በደጋው ላይ ባሉ ከተሞች በቈላውም ባሉ ከተሞች በደቡብም ባሉ ከተሞች፥ በብንያምም አገር በኢየሩሳሌምም ዙሪያ ባሉ ስፍራዎች፥ በይሁዳም ከተሞች መንጎቹ በተቈጣጣሪው #እጅ እንደ #ገና #ያልፋሉ፥ ይላል እግዚአብሔር። 14፤ እነሆ፥ ስለ እስራኤል ቤትና ስለ ይሁዳ ቤት የተናገርሁትን #መልካም #ቃል የምፈጽምበት #ዘመን #ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር። 15፤ #በዚያም_ዘመን በዚያም ጊዜ ለዳዊት #የጽድቅን #ቍጥቋጥ #አበቅልለታለሁ፤ እርሱም ፍርድንና ጽድቅን በምድር ያደርጋል። 16፤ በዚያም ዘመን ይሁዳ ይድናል ኢየሩሳሌምም ተዘልላ ትቀመጣለች፤ የምትጠራበትም ስም። #እግዚአብሔር #ጽድቃችን ተብሎ ነው።
(ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ 33:10-16)

በዚህም ሥፍራ ነቢዩ ኤርምያስ መሲሁ ተመልሶ ሲመጣ የሚሆነውን ነገር ሲተነብይ እንመለከታለን። በምርኮና በመበታተናቸው ምክንያት ባድማ የሆኑት የይሁዳ ከተሞችና የኢየሩሳሌም አደባባዮች ሰዎች እንደሚሞሉ ይናገራል። ለዚያም ነው በቁ.11 "የምድርን ምርኮ እንደ ቀድሞ አድርጌ እመልሳለሁ" የሚለው። ቀጥሎም ባድማ የነበሩት ከተሞች የእረኞች መኖሪያ እንደሚሆኑ፥ ሕዝቡም በተቆጣጣሪው እጅ እንደሚያልፉ ይናገራል። ቀጥሎም በቁ.14 ለእስራኤል ቤትና ለይሁዳ ቤት የተናገረው መልካም ቃል የሚፈጸምበት ዘመን ይመጣል ይላል። ይህ ማለት በተደጋጋሚ ስለ መሲሁ የገባላቸው ቃል ይፈጸማል ማለት ነው። መሲሁ ተመልሶ ሲመጣ ይሆናል አላቸው  ነገሮች በሙሉ የሚሆኑበት ዘመን ነው ማለት ነው።

ከዚያም በቀ.15 "በዚያም ዘመን በዚያም ጊዜ ለዳዊት የጽድቅን ቁጥቋጦ አበቅልለታለሁ" ይላል። ይህ ማለት እስራኤል ወደ ምድሩ በተመለሰ ጊዜ ይህ የጽድቅ ቁጥቋጦ ይበቅላል ማለት ነው። በዚህ ሥፍራ "ቁጥቋጦ" ተብሎ የተጠራው መሲሁ ነው። መሲሁ በመጽሐፍ ቅዱስ ከተጠራባቸው ስሞች መካከል አንዱ ቁጥቋጦ ነው። (ዘካ 3:8 ኢሳ 11:1 ኢሳ 4:2 ኢሳ 11:10) ያ ቁጥቋጦ (መሲሁ) በዚያ ዘመን ፍርድንና ጽድቅን በምድር ላይ ያደርጋል።

ይህ ማለት እስራኤል ወደ ምድሩ የሚመለስበትና የሚድንበት ዘመን መሲሁ ፍርድንና ጽድቅን በምድር ላይ በሚያደርግበት ዘመን ነው ማለት ነው። መሲሁ ሊነግስና ሊፈርድ ተመልሶ በሚመጣበት ሰአት እስራኤል ዳግም በምድሩ መኖር ይጀምራል። እግዚአብሔርም የገባላቸው ቃል ኪዳን ይፈጸምላቸዋል። ይህ በማያሻማ ሁኔታ እንደሚያረጋግጠው መሲሁ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ተመልሶ በሚመጣበት ሰአት እስራኤል ከተበታተኑበት ምድር በሙሉ ይሰባሰባሉ

"21፤ አንተም እንዲህ ትላቸዋለህ። ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። እነሆ፥ #የእስራኤልን #ልጆች ከሄዱባቸው #ከአሕዛብ መካከል #እወስዳለሁ #ከስፍራም ሁሉ #እሰበስባቸዋለሁ ወደ ገዛ #ምድራቸውም #አመጣቸዋለሁ፤ 22፤ በምድርም ላይ #በእስራኤል #ተራሮች ላይ አንድ ሕዝብ አደርጋቸዋለሁ፥ አንድ ንጉሥም በሁላቸው ላይ ይነግሣል፤ ከዚያ ወዲያ ሁለት ሕዝብ አይሆኑም፥ ከዚያ ወዲያም ሁለት መንግሥቶች ሆነው አይለዩም። 23፤ ከዚያ ወዲያም በጣዖቶቻቸውና በርኵሰታቸው በመተላለፋቸውም ሁሉ አይረክሱም፥ ኃጢአትም ከሠሩባት ዓመፅ ሁሉ አድናቸዋለሁ አነጻቸውማለሁ፤ ሕዝብም ይሆኑኛል እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ። 24፤ ባሪያዬም ዳዊት #ንጉሥ ይሆናቸዋል፤ ለሁሉም አንድ እረኛ ይሆንላቸዋል፤ በፍርዴም ይሄዳሉ ትእዛዜንም ይጠብቃሉ ያደርጓትማል። 25፤ አባቶቻችሁም #በኖሩበት ለባሪያዬ ለያዕቆብ #በሰጠኋት #ምድር #ይኖራሉ፤ እነርሱና ልጆቻቸው የልጅ ልጆቻቸውም ለዘላለም ይኖሩባታል፤ ባሪያዬም ዳዊት ለዘላለም አለቃ ይሆናቸዋል።"
(ትንቢተ ሕዝቅኤል ምዕራፍ 37:21-25)

በዚሁ ሥፍራም፥ እግዚአብሔር መሲሁ በሚነግስበት ዘመን የሚሆነውን ነገር ሲናገር እንመለከታለን። መሲሁ በዳዊት ዙፋን ላይ ሊቀመጥ፥ ተመልሶ በመጣ ጊዜ እግዚአብሔር የእስራኤልን ሕዝብ ከሄዱበት ከአሕዛብ መካከል እንደሚወስዳቸው፥ ከስፍራም ሁሉ እንደሚሰበስባቸው፥ ወደ ገዛ ምድራቸውም እንደሚመልሳቸው ቃል ይገባል። በምድርም በእስራኤል ተራሮች ላይ አንድ ሕዝብ ያደርጋቸዋል።

በዚያም ጊዜ አንድ ንጉሥ በሁላቸው እንደሚነግሥና (ቁ.22) ያም ንጉም ባሪያው ዳዊት (መሲሁ) እንደሆነ (ቁ.24) ይናገራል። ይህ መሲሁ ኢየሱስ በዳዊት ዙፋን ላይ ሊቀመጥ ተመልሶ በሚመጣ ጊዜ አንድ ንጉሥና አንድ እረኛ እንደሚሆንላቸውና እነርሱም ከተበተኑበት የአሕዛብ ምድሮች እንደሚመለሱ ያረጋግጣል። ለዚያም ነው ቀጥሎ፥ አባቶቻችሁ በኖሩበት ለባሪያዬ ለያዕቆብ በሰጠሁት ምድር ይኖሩበታል የሚለው። መሲሁ በዳዊት ዙፋን ላይ ተቀምጦ ሊገዛ በሚመጣበት ሰአት የእስራኤል ሕዝብ ከተበተነበት የአሕዛብ አገሮች በሙሉ ተሰብስቦ አባቶቹ በኖሩባት ምድር መኖር ስለሚጀምር ነው።

"3፤ እነሆ፥ የሕዝቤን የእስራኤልንና የይሁዳን ምርኮ #የምመልስባት ዘመን #ይመጣልና፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ለአባቶቻቸውም ወደ #ሰጠኋት #ምድር #እመልሳቸዋለሁ፥ እነርሱም ይገዙአታል። 8፤ #በዚያ #ቀን #እንዲህ #ይሆናል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ ቀንበርን ከአንገትህ እሰብራለሁ፥ እስራትህንም እበጥሳለሁ፥ ከእንግዲህ ወዲህም #ለሌላ #አትገዛም፤ 9፤ ለአምላካቸው ለእግዚአብሔርም #ለማስነሣላቸው #ለንጉሣቸው #ለዳዊትም #ይገዛሉ እንጂ ሌሎች አሕዛብ እንደ ገና አይገዙአቸውም። 10፤ እነሆ፥ #አንተን #ከሩቅ #ዘርህንም #ከምርኮ አገር #አድናለሁና ባሪያዬ #ያዕቆብ ሆይ፥ አትፍራ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ አንተም እስራኤል ሆይ፥ አትደንግጥ፤ ያዕቆብም ይመለሳል ያርፍማል ተዘልሎም ይቀመጣል፤ ማንም አያስፈራውም።"
(ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ 30:3-10)
197 viewsedited  13:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ