Get Mystery Box with random crypto!

ሀበሻ 050

የቴሌግራም ቻናል አርማ joyyeg — ሀበሻ 050
የቴሌግራም ቻናል አርማ joyyeg — ሀበሻ 050
የሰርጥ አድራሻ: @joyyeg
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 544
የሰርጥ መግለጫ

ይ channel
ወቅታው መረጃ በፊጥነት እናደርሳለን
ቴክ
ፍቅር
ጥበብ
ግጥም
በሴፍው የምዳስስ ነው

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-21 22:10:08 ::::::::::::::መንታ መንገድ::::::::::::

ክፍል አስረሰአንድ /


አዲስ አበባ በመጣሁ በመጀመሪያዉ ቀን ተጣልቼ ጣቢያ መግባቴ ለራሴም ገረመኝ። ጣቢያ ዉስጥ ትንሽ እንደቆየሁ አባዬ ሲከንፍ ደረሰ። ለመርማሪዉ የተፈጠረዉን ነገር በሙሉ ሳስረዳዉ ወደ ልጁ እየዞረ "እኔ ብሆን አንገትህን ነበር የምቆርጥልህ!" አለዉ። ሳቄ መጣ። መርማሪዉ ወደ ክስ ሳይሄድ ነገሩን በእርቅ እና በምክር ለመፍታት ያሰበ ይመስላል። መርማሪዉ መርየምን ከዚህ በኋላ በተመሳሳይ ጉዳይ ቢያገኛት እንደማይለቃት አስፈራርቷት ሸኘን። ልጁን ትንሽ እጃቸዉን አፍታተዉበት የሚለቁት ይመስለኛል። ያዉ የኛ ሀገር ፖሊሶች አመል የታወቀ ነዉ። በስህተት መርማሪ ቢሮ የገባ ፖሊስ ሳይቀር ነዉ እንደ ቡናቁርስ አገላብጦህ የሚወጣዉ።
.
ቤት እንደገባን መርየም ቀና ብላ ልታየን አፈረች። ልቧ እንዳይሰበር ቀስ ብዬ ወደ መኝታ ክፍል ወስጄ ለረዥም ሰዓት መከርኳት። እሷም ይቅርታ ጠየቀችኝ። ለሻከረዉ ግንኙነታችን መሻሻል መልካም ዕድል የተፈጠረ መሰለኝ። ከችግር ጋር ምቾት አለ። ከሰዉ ጋር መደባደቤ ፣ እህቴ በባዳ ወንድ ስትነካ ማየቴ ቢያቆስለኝም በሱ ምክንያት ከእህቴ ጋር ያለኝ ቅርርብ መሻሻሉ አስደሰተኝ። ፈጣሪ መልካም ነገርን የትኛዉ ብልቃጥ ዉስጥ እንደሚያስቀምጥ አይታወቅም። ብዙ ጊዜ ደሞ ጣፋጭ ነገሮች በእሾህ የተከበቡ ናቸዉ። አባዬን እንዳይቆጣት እና ሁሉንም እኔ እንደማስተካክለዉ ነግሬ የመርየምን ጭንቀት አቀለልኩላት። ከእህት ጋር እንደወንድም መወያየት መቻልን የመሰለ ምን ደስታ አለ? ምንም!!
.
ከባህርዳር ከተመለስኩ ሁለት ሳምንት ሞላኝ። ራሄል ሳትደዉል አድራ አታዉቅም። የኔ ቀዉስ!
ከሀያት ጋር አንዴ በአካል ተገናኝተናል። ለቤተሰቦቿ ተናግራ ኺጥባዉን እንድንጀምረዉ ጠይቃኝ ነበር። እኔ ግን ትንሽ እንድናርፍ ስለጠየቅኳት አስቤበት ስዘጋጅ እንድነግራት ነግራኝ ተለያየን። ሰሞኑን ከአባቴ ጋር የስራ ቦታዉ ነዉ የምዉለዉ። የአባቴን ስራ ማስተዳደር እንድችል አባዬ እያለማመደኝ ነዉ።
የአባዬ ቢሮ ተቀምጬ ሀዩ ደወለች። አነሳሁትና "ወዬ ሀዩና!" አልኩ።
"ባክህ ደስ የማይል ዜና አለ!" አለችኝ ድምጿ ዉስጥ ድብርት አለ።
"ምነዉ ሀዩ ችግር አለ?" አልኩ ስለደበራት እየደበረኝ። ሀያት ስትስቅ ነዉ የምታምረዉ ፣ ፍልቅልቅ ስትል። በሳቋ ዉስጥ የሚንቆረቆር የሆነ ለየት ያለ ዜማ አለ። ስትስቅ ሌላዉንም እንዲስቅ የሚያስገድድ ልዩ ሀይል አላት።
"አኩዬ ብራዘር ካልዘየራችሁኝ ብሎ ቲኬት ልኳል። ክረምቱን ስዊዘርላንድ ላሳልፍ ነዉ።" አለችኝ። ድብርቷ በክረምት እንድናደርገዉ ያሰበችዉ መተጫጨት ስለከሸፈ መሆኑ ገባኝ። እኔ ግን ትንሽ እረፍት ተሰማኝ።
"ወይኔ ሀዩዬ ልትናፍቂን ነዋ!" አልኩ ክረምቱን ሙሉ እንደማናገኛት እያሰብኩ
"አዎ በአላህ አክረሜ! በጣም ነዉ የምትናፍቀኝ እሺ ሁቢ!" አለች ድምጿን ሳግ እያፈነዉ! ሁቢ ማለት በአረብኛ ዉዴ ማለት ነዉ። ሁሌም ሀዩ አማርኛዉን ከመጠቀም ይልቅ አረብኛዉን ትመርጣለች።
"ሀዩዬ ስታለቅሺ አያምርብሽም! አይዞን ሁለት ወር ቅርብ ናት። ደሞ በስልክ እንገናኛለን።"አልኩ ላፅናናት በማሰብ
"እሺ አኩዬ በስልክ ግን እንዳትጠፉብኝ። ለማንኛዉም ከነገ ወዲያ ነዉ የምበረዉ።" አለችኝ የመለየት ስጋት በወገረዉ ድምፅ። ስልኩን እንደዘጋሁት ሀዩን አሰብኳት። የሀይማኖት ዕዉቀቷ ገራሚ ነዉ። ሁሌም የምትለብሳቸዉ ሰፋፊ ዉብ ቀሚሶች ፣ ቀይነቷን የሚያንቦገቡጉት ሁሌም የምትለብሳቸዉ ጥቁር ሂጃቦች በሷዉ ተለብሰዉ በአይኔ ላይ ዉል አሉ። ሳቋ አይኔን ሞላዉ። ስነ ስርዓቷ ትዝ አለኝ። ስታኮርፍ ሳልኳት በጣም ደስ ትላለች። ቆይ ምንድነዉ?! ሳትሄድ ልትናፍቀኝ ነዉ እንዴ? "ሄይ አኩ ተረጋጋ" አልኩት ለራሴ።
.
የሀያት ስዊዘርላንድ መሄድ ትንሽ ዉጥረቴን አረገበልኝ። በርግጥ ናፍቆቷ ሊያሳብደኝ ምንም አልቀረዉም። በስልክ ባንገናኝ ኖሮ ምን እንደምሆን እኔንጃ! የሰዉን ልክ የምታዉቀዉ ከአጠገብህ ሲርቅ ነዉ። ሀጅራም ንፍቅ ብላኛለች። የኮምቦልቻዋ ጨዋ! ርጋታዋ በፍፁም ከአይኔ አይጠፋም። ከራሄል ጋር እሁድ እሁድ እንገናኛለን። ከራሄል ጋር ስገናኝ ልቤ ሀሴት ታደርጋለች። ከእሁድ ዉጪም ትርፍ ጊዜ ሲኖረኝ አገኛታለሁ። የጥበብ ጥማቴንም የሰዉ ረሀቤንም በአንዴ ስለምታስታግስልኝ ደስ ይለኛል። ከእሁድ ዉጪ ያለዉን ሌላዉን ቀን ከአባቴ ጋር በስራ ነዉ የማሳልፈዉ። ራሄል "እኔ አይንህን ካየሁ ይበቃኛል፤ እንዴት የኔ እንደማደርግህ እኔ አዉቃለሁ!" ትላለች ሁሌም ስንገናኝ።
.
ወራቱ እንደ አንድ ቀን እየተጠቀለሉ ክረምቱ ተጠናቆ አዲስ አመት ተበሰረ። "ሄይ አኩዬ የት ነህ?" አለችኝ ሀያት ደወለችና
"ስዊዘርላንድ ሱፐርማርኬቱ ጋር!" አልኩ እየሳቅኩ መቸስ ስዊዘርላንድ ሱፐር ማርኬት አይጠፋም በሚል ግምት
"አኩዬ አትቀልድ በአላህ ላገኝህ እፈልጋለሁ ናፍቀኸኛል።" አለችኝ እየተነጫነጨች
ስልኬን ከጆሮዬ ላይ አንስቼ ቁጥሩን አየሁት። የኢትዮጵያ ስልኳ ነዉ። የሆነ ደስታ ዉርር አደረገኝ።
"ሀዩዬ የፈለግሽበት ልምጣ በአላህ የት ነሽ?" አልኩ ድምጼ ዉስጥ ናፍቆት አለ።
"ቤት ነኝ። የት እንገናኝ?" አለች ሀዩ!
ከሰፈራችን አማካይ ላይ ያለ አንድ ካፌ ተቀጣጠርን። ሀዩዬ የኔ ቀዉስ ከሁለት ወራት ናፍቆት በኋላ ላገኛት ነዉ!
.
ሀዩ ለራሄልም ደዉላላት ስለነበር ሶስታችንም አብረን ተገናኝተን ደስ የሚል ጊዜ አሳለፍን። አብረን ሆነንም ሀጅራ ጋር ደዉለን አወራናት። ሀጁ ናፍቆታችን ሊያሳብዳት ደርሷል። ለነገሩ ከአስር ቀናት በኋላ ወደ ግቢ ተጠርተናል።
.
ወደ ግቢ ተመልሰን የአመቱ ትምህርት ተጀመረ። በነገራችን ላይ ዉጤትም ተቀብለናል። ሀያት የክፍላችን ሰቃይ ሆናለች። አራት ነጥብ ነዉ በሁለቱም ሴሚስተር ያስመዘገበችዉ። እኔና ራሄል ሶስት ነጥብ ዘጠኝ ፣ሀጁ ደግሞ ሶስት ነጥብ ስምንት አስመዝግበናል። የክፍሉ ትልቁ ዉጤት በአራታችን መያዙ በጣም አስደስቶኛል።

ይቀላቀሉን.............

@joyyeg
@joyyeg
36 viewsHabesha, 19:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 23:02:49 ::::::::::::መንታ መንገድ::::::::

ክፍል


እስሪታ ምርጥ ያለችዉ ካፌ ስንገባ እንደጠበቅኩት መርየም ከአንድ ጨበሬ ጋር ተቀምጣለች። ከእይታችን በማትርቅበት መልኩ ራቅ ብለን ተቀመጥን። ኢስራእ ዝም እንድትል ስለነገርኳት የማደርገዉን ዝም ብላ መከታተል ጀመረች። ፒዛ አዝዘን እየጠበቅን በአይኔ እነመርየምን እሰልላለሁ። መርየም ጀርባ ሰጥታን ነዉ የተቀመጠችዉ። ልጁ ወደኛ ዞሯል። የሆነ አመድ ነዉ የሚመስለዉ! እዉነት ለመናገር ከመርየም ጋር በፍፁም አይመጣጠንም። እሷ እኮ እዉቀት የላትም እንጂ በጣም ቆንጆ ናት። ሄጄ ልለያያቸዉ አሰብኩ ግን እኔ ራሱ ከሌላ ሰዉ እህቶች ከነራሄል ጋር እንዲህ እንደምሆን ሳስበዉ ሞራል አጣሁ። ግን መቼስ እንዲህ አንድ ለአንድ ካፌ ተገናኝተዉ ተራ ጓደኛ ናቸዉ ማለት ይከብዳል። ደሞ መርየም ተሽቀርቅራ ነዉ የወጣችዉ።
.
ፒዛዉ ቀርቦልን እየበላን እስሪን ላጎርሳት ቀና ስል ልጁ የመርየምን ጭን ሲደባብስ አየሁት። ይሄኔ ፊቷ ቲማቲም መስሏል። ንዴት ሙሉ ሰዉነቴን ተቆጣጠረኝ። እህቴን ፊቴ ላይ ሲያባልግ ብሽቅ አልኩኝ።
ወንድ ልጅ የአመራር መሰረት ነዉ። ሴት ልጅ በመሰረቱ ላይ የምትደላደል ግንባታ ናት። ያለ መሰረት እቆማለሁ ያለች ቀን ትፈርሳለች። መሰረቱም ስለ ግንባታዉ ምን አገባኝ ያለ ጊዜ ግርማዉን ያጣል። ወንድ ልጅ ስለ እህቱ እና ስለ ሚስቱ አይመለከተኝም ያለ ቀን የትዉልድ ስነ ምግባር ይዘቅጣል። ፈጣሪ ለወንድ ልጅ ጉልበትን እና የመሪነት ባህሪን በተፈጥሮ አላብሷል። ወንድ ሴቷ ፍላጎቷ ሚዛን የሳተ ጊዜ የምትፈልገዉን ሳይሆን የሚያስፈልጋትን አዉቅልሻለሁ ሊላት ይገባል። ስታፈነግጥ አልመለስ ካለች በአግባቡ ጉልበቱንም ሊጠቀም ያስፈልጋል። ይሄ የነፃነት ጥያቄ አይደለም። ይሄ ስርዓት ያለዉ ማህበረሰብ የማነፅ ጉዳይ ነዉ።
.
ልጁ ካፌ ዉስጥ እንዲህ ለማድረግ መድፈሩ አናደደኝ። ሲጀመር እህቴ ናት ጥፋተኛ የትም እንደ ሎሚ የምትታሽ! ሰፈሯ ዉስጥ ትንሽ አታፍርም? ወንጀል እኮ ይታፈራል።
አሁን የጥፋቱን ምንጭ ማሰብሳይሆን ክብርን ማትረፍ ይቀድማል።

አንድ ወጠጤ በጋብቻ ያልሰጠኸዉን እህትህን ሲያባልግ እያየህ ስለ ምክንያታዊነት አታስብም። እጄ ላይ የያዝኩትን ቢላ እና ሹካ ጠረጴዛዉ ላይ ወርዉሬ ወደነመርየም ጠረጴዛ ተንደረደርኩ። ኢስራዕ ልጣላ መሆኑ ገብቷት "አኩሻ በአላህ ተረጋጋ!" እያለች ከኋላዬ ተከተለችኝ።
ልጁ ወደሱ እየተንደረደርኩ መሆኑን ሲያይ እጁን ከጭኗ ላይ አነሳ።
በቦክስ ልጁን ከነወንበሩ መሬት ላይ ዘረርኩት። መርየም ደንግጣ ከመቀመጫዋ ተነሳች። ልጁን አስተናጋጆች እስኪገላግሉት ድረስ በቦክስ ነረትኩት። መርየም ቆማ ታለቅሳለች። ልጁ ነስር በነስር ሆነ። አስተናጋጆቹ ፖሊስ ጠርተዉ አስረከቡን። ፖሊሶቹ እጃቸዉን እያፍታቱብን ሰፈራችን ወደሚገኘዉ ጣቢያ ይዘዉን ሄዱ። ሁለታችንንም መምታታቸዉ ገርሞኛል። ተበዳይ ይመታል እንዴ? ኧረ በዳዩንም የመምታት ስልጣን የላቸዉም።
ኢስራዕ አባዬ ጋር ደወለች። መርየምም አብራን ወደጣቢያ መጥታለች። ልጁ ጀንተል ብሎ ሲያሻሽ እንዳልነበረ ጣቢያ ስንደርስ እናቱ እንደተገደለችበት h'tsan menefarek jemere ::

ይቀጥላል.................

@joyyeg
@joyyeg
87 viewsHabesha, 20:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 17:47:12
"ብቸኝነት በተሰማህ ሰዓት አንድ ነገር አስተውል። አላህ ሁሉንም ሰው ከአጠገብህ አርቆ ለአንተ እና ለሱ ጊዜ መስጠቱ ነውና ሰዓት ለዱዓ ተጠቀምበት።"
@joyyeg
100 viewsyuyo, 14:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-19 10:59:31 ጥያቀ
1 አንድ ህፃን ምን ሀይል ግዜ ነው የእናቱን ጡት ምጠባው?
መልስ በዝ መስመር @tibebzjo
134 viewsyuyo, 07:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-19 10:57:23 ይህን ያውቃሉ
በአሜርካ ውስጥ ብቻ ሶስት ሚሊዮን ሰዎች በየቀኑ የስነ ልቦና ባለሙያዎችን ያማክራሉ።
@joyyeg
132 viewsyuyo, 07:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 21:09:00 ሰይጣን ተስፋ ሊያስቆርጥህ
የኋላህን ሊያስታውስህ ሲሞክር
አንተም የወደፊት እጣ ፈንታውን
አስታውሰው
@joyyeg
@joyyeg
162 viewsHabesha, 18:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 21:01:30 :::::::::::መንታ መንገድ::::::::::::::

ክፍል ኝ

ፀሀፊ fuad seid

ጁምዓ(አርብ) ጠዋት ሀጅራ ተሰናብታን ወደ ኮምቦልቻ ሄደች። እኔ ሀያት እና ራሄል አራት ሰዓት ላይ ባጃጅ ተኮናትረን ወደ ኤርፖርት ሄድን። ወደ አዲስ አበባ አምስት ሰዓት ላይ ልንበር ትኬት ቆርጠናል። በርግጥ ባለፈዉ ሴሚስተር በሰላም ባስ ነበር የሄድነዉ። መንገዱ ረዥም ስለሆነ እየተጫወትን ቆንጆ ጊዜ አሳልፈናል። ባሁኑ ግን ራሄል የአባይ በረሀ መንገድ ሙቀቱም የመንገዱም አስፈሪነት ስለከበዳት በአዉሮፕላን እንሂድ ስላለች ለሷዉ ብለን ነዉ በአዉሮፕላን ለመሄድ የወሰንነዉ።
.
እኔ ከነሀያት እና ራሄል ተነጥዬ ወደዛ ጭቅጭቅ ወደማያባራበት ቤት ልመለስ መሆኑን ሳስበዉ ሸከከኝ። እዛ ቤት ዉስጥ ከአባቴ በስተቀር ማንም ጉዳዬ አይደለም። እናቴ ደዉላ ዛሬ እንደምመጣ ስነግራት በጣም ነበር ደስ ያላት! ስመለስ መርዝ ምላሷ ዕረፍት ይሰጠኝ ይመስል።
ሀያት አዉሮፕላን ዉስጥ እንደገባን "የቁርጡ ቀን ደረሰልህ!" አለችኝ ወደኔ እየዞረች። ሀያት ከፊት ለፊቴ ነበር የተቀመጠችዉ። እኔና ሪቾ ደሞ አንድ ላይ!
"በየቀኑ ላንገናኝ መሆኑን ሳስበዉ ይቀፈኛል።" አለች ራሄል የሀያትን ንግግር እንዲሁ ተረድታዉ። ሀያት ግን ለኔ የመተጫጨቱ ጊዜ ደረሰ ለማለት ነበር እንደዛ ያለችዉ። አይኖቿ ዉስጥ ትርጉም ነበር።
"አዎ ሪቾ አሁን ከናንተ ጋር መብላት ለምጄ ቤት እንዴት እንደሚበላልኝ እኔንጃ" አልኩ ያሳለፍናቸዉ ጊዜዎች ዉል እያሉብኝ።
"እኔ ራሱ!" አለች ሀያት በረዥሙ እየተነፈሰች።
"አቦ ሀጅራም አለች ኮምቦልቻ ያለችዉ ክረምቱን ሙሉ የማታገኘን እኛ እኮ ሸገር ነን ፈታ በሉ!" አለች ሪቾ ራሷ በጀመረችዉ ጨዋታ ስንተክዝ ደብሯት።
ጓደኝነት ግን ከየትኛዉም ግንኙነት የላቀ አስደሳች ግንኙነት ነዉ። ባላሰበከዉ ሰዓት ወደ ህይወትህ የሚመጡ ሰዎች የህይወትህን አዳፋ ሁሉ አጥርተዉ የማይረሳ ትዝታ ያትሙብሀል። ግን ችግሩ ጓደኝነቱ በተቃራኒ ፆታ መካከል ሲሆን ወደ ፆታዊ ፍቅር የመቀየር እድሉ ከፍተኛ መሆኑ ነዉ። ይኸዉ የኔ ጉዶች ሀጅራ ብቻ ናት እኮ አፈቀርኩህ ያላለችዉ።
.
አዲስ አበባ ደርሰን ከቦሌ አየርመንገድ ስንወጣ ሀዩ እናቷ እና ታናሽ እህቷ መኪናቸዉን ተደግፈዉ ቆመዉ ሲጠብቋት አየቻቸዉ። የሀያት ታናሽ እህት መግፊራ ትባላለች። ስገምት 18 ዓመት ይሆናታል። ልክ እንደ ሀዩ ቀሽት ናት። ሀያት ፈገግ አለችና ሻንጣዋን ጥላ እየሮጠች ሄዳ መግፊራ ላይ ተጠመጠመች። ከዚያም እናቷ እያገላበጡ ሳሟት። ሀያት እና እህቷ በጣም ይዋደዳሉ። ባህርዳር ሆነን ራሱ በየቀኑ ለረዥም ሰዓት ነበር በስልክ የሚያወሩት። ሲያስቀኑ! አሉ እንጂ የእኔ እህቶች መልክ ብቻ የወንድም ፍቅር የማያዉቁ ደነዞች!
እኔና ሪቾ የራሳችንን እና የሀዩን ሻንጣ እየገፋን የነሀዩ መኪና ጋር ደረስን።
ሀያት እናቷን እና እህቷን አስተዋወቀችን! በስም እንኳ በደንብ ያዉቁናል።
"አክረም እሱ ነዉ" አለች ሀያት ወደ እኔ እየጠቆመች።
"ዋዉ መግፊራ እባላለሁ" አለች እህቷ ፍጥን ብላ። ሀያት ያን ተፍለቅላቂ ሳቋን ለቀቀችዉ። የእህቷ አባባል በጣም ያስቅ ነበር። ሀዩ እንዳፈቀረችኝ ለእህቷ ነግራት እንደነበር ከመግፊራ አኳኋን ተረዳሁ።
"ሴት አይጨብጥም ያልሽኝ እሱን ነዉ? ማሻ አላህ ልጅ እንዲህ ሲያድብ ደስ ይላል!!" አሉ የሀያት እናት።
ሀዩ ጠቅሳኝ ወደ መኪናዉ ገባች። መኪናዉን አስነስተዉ ሲሄዱ መግፊራ እጇን የስንብት አዉለበለበችልን።
.
ቤት እንደገባሁ እህቶቼ መጥተዉ ተጠመጠሙብኝ። ምን ያስመስላሉ?! ከናፈቅኳቸዉ አይደዉሉልኝም ነበር?! እዚ ከአስሩ ጎረምሳ ጋር ከሚጀናጀኑ! ብሽቆች!
እናቴ "አክረሜ የኔ አንበሳ! ለምን የምትደርስበትን ሰዓት አልነገርከንም? በመኪና አመጣህ አልነበረም በኮንትራት ከምትመጣ?!" አለች ሱፍራ እያነጠፈች። ሱፍራ ምግብ ሲቀርብ ምንጣፍ ላይ እንዳይንጠባጠብ ለመከላከል የሚነጠፍ ላስቲክ ነዉ።
ፈገግ ብዬ ዝም አልኩኝ ምንም ማዉራት አልፈለግኩም። ከሁለቱ እህቶቼ ትንሿ ትንሽ ትሻላለች 16 ዓመቷ ነዉ። ኢስራዕ ትባላለች። ትልቋ ደሞ 18 ዓመቷን ልትይዝ ምንም አልቀራትም። መርየም ትባላለች። እማዬ ምግብ አቅርባልኝ ስትወጣ ኢስራዕን ጠራኋት። ልክ አጠገቤ እንደተቀመጠች "ኢስሩ አክስቴ አዚዛ እና ሰሚራ እዚህ መምጣት ያቆሙት ለምንድነዉ?" አልኳት።
ድምጿን ዝቅ አድርጋ "ሁለቴ የመጡ ቀን ማማ ባዶ ቤት ትታቸዉ ወጣች። ከዛ በኋላ መጥተዉ አያዉቁም።" አለችኝ።
ሰዉ እንዴት እድሜዉ ሲጨምር አስተሳሰቡ አብሮ አያድግም? ለሰዉ እኮ እድሜ ራሱ ትምህርት አለዉ። እናቴ ከምወዳቸዉ አክስቶቼ ጋር እንደቆራረጠችን ሳስብ ተናደድኩ። እናቴ መልከኛ ናት ግን ፀባይ አላደላትም። እኔም ቤት ስለማላዘወትርና ሀይማኖታዊ ቡድኖች እንዲሁም የኪነ ጥበብ ማህበሮች ዉስጥ በመሳተፍ ራሴን ስለማጨናንቅ እንጂ የእናቴን ፀባይ እወርስ ነበር።
በመሀል መርየም "በቃ አክረሜ መዉጣቴ ነዉ!" ብላኝ ወጣች። አለባበሷ ይሰቀጥጣል። ቀሚሱ የመቀመጫዋን እንቅስቃሴ በደንብ ነዉ የሚያሳየዉ። ገና ከመምጣቴ መጨቃጨቅ ስላልፈለግኩ ዝም አልኳት። እንዲህ ተኳኩላ የት ልትሄድ እንደምትችል አይጠፋኝም። ጓደኞቼ እኮ ሴቶች ናቸዉ።
.
ትንሽ እንደቆየሁ ኢስራዕን "እስሪ እስኪ ነይ ምርጥ ካፌ ዉሰጂኝ ፒዛ ልጋብዝሽ!" አልኳት ኢስራዕ ፒዛ ነፍሷ ነዉ። እኔ የሰፈራችን ካፌዎች ጠፍተዉኝ ሳይሆን በኢስራዕ እይታ ምርጥ የሚባለዉን ካፌ ለማወቅ ነዉ። በርግጠኝነት ደሞ መርየምን እዛ አገኛታለሁ።

ይቀጥላል..............

ይቀላቀሉን
@joyyeg
@joyyeg
151 viewsHabesha, 18:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-17 21:36:37 :::::::::::መንታ መንገድ: :::::::::::::

ክፍል ስምንት/ ት

ፀሀፊ fuad seid

ትወደኛለህ አለችኝ ሰዉነቷን ወደኔ ሙሉ ለሙሉ እያዞረች!
እዉነት ለመናገር ራሄል በጣም ደስ ትለኛለች። እብድነቷ ፣ አነጋገሯ ፣ በዛ ላይ ደግሞ ግጥም ትፅፋለች።
ግን ደግሞ በዚህ በኩል ሀያት የሌላ ስሆን ከምታይ ሞቷን ትመርጣለች። ራሄል የሀያት ስሆን ካየች ደግሞ ጓደኝነታችን ሊበጠበጥ ነዉ።እኔ በመሀል እንደ ድፎ ዳቦ ልለበለብ ነዉ። ራሄል ልትስመኝ ከንፈሯን ወደ ከንፈሬ አስጠጋች ፣ነዘረኝ። አቀረቀርኩ። ብስማት አልጠላም ፣ ግን የሀይማኖቴ "ያላገባሀትን ሴት አትንካ" የሚል ክልከላ አለ።
"ገባኝ! እንደዚህ አይነት ነገር ዉስጥ ከጋብቻ በፊት መግባት አትፈልግም።" አለችና ፊቷን ከኔ እየመለሰች "ግን አንተን የኔ ከማድረግ ሀይማኖትም ይሁን ምንም አያግደኝም!" አለች። ዉስጧ ላይ እልህ አለ። እልኋ ዉስጥ ፍቅር አለ። ሁሉ ነገሯ ዉስጥ ደሞ ዉበት አለ። ወደድኳት እንዴ? አላዉቅም።
.
ሀያት እና ሀጅራ የሰዉነገርን ጎብኝተዉ ተመለሱ።
"ደብሬ መጥተዋል አቅርቢልን" አለች ራሄል ምንም ያልተፈጠረ ለማስመሰል እየሞከረች። ደብሬ ስምንት ትናንሽ አሳዎችን በሳህን በሳህን ሁለት ሁለት አድርጋ ከዳቦ ጋር አቀረበችልን። አሳዎቹ እንደቀረቡ ሀዩ አንዱን የኔን አሳ አንስታ እሾሁን ታወጣልኝ ጀመረች። ራሄል ተከትላት የሌላኛዉን አሳዬን እሾህ ማዉጣት ጀመረች። ሀጅራ እያየ

"ኧረመስተንግዶ አበዛችሁበት ይብላበት እንጂ!" አለች ሀጅራ አሁንም እየሳቀች።
.
በልተን እንደጨረስን የገብሬ ጀልባ ላይ ወጥተን ሀይቁ ላይ መንሳፈፍ ጀመርን። "ይኸዉ አባይ ጣናን ሲጋልበዉ!" አለ ገብሬ ጣናን ንጣፍ አድርጎ ከላይ የሚሄደዉን የአባይን ዉሀ እየጠቆመን።
ተፈጥሮ ይገርማል ፣ አባይ በጣና ላይ ምንም ከጣና ጋር ሳይቀላቀል ያልፋል።
በነገራችን ላይ ዛሬ ጣና ላይ መንሸራሸሩን ያቀድነዉ በዋነኛነት ከሀጅራ ጋር ስንብት እንዲሆነን በማሰብ ነዉ። እሷ የኮምቦልቻ ልጅ ስለሆነች ክረምቱን አናገኛትም። እኛ እንኳን የሸገር ልጆች ስለሆንን ከፈለግን እዛዉ መገናኘት እንችላለን።
"አኩ ጉማሬ! ጉማሬ! አለች ሀያት ከጀልባችን አቅራቢያ የሚዋኘዉን ዳለቻ ፍጥረት እያሳየችኝ። ራሄል የጀልባዉ ወንበር ላይ በጉልበቷ ተንበርክካ ከሀይቁ ዉሀ በእጇ እየዘገነች ትረጨን ጀመር። ሁላችንም የጣናን ዉሀ ተረጫጨነዉ። ራሄል ገብሬን ሳይቀር አበሰበሰችዉ። ጣና ላይ እስኪሰለቸን ከተሽከረከርን በኋላ "በሉ ወደ ደሴቷ እንመለስ ይመሽብናል።" አለ ገብሬ ጀልባዋን እያዞረ። ስንመለስ ሰዓቱ ለአስራ ሁለት ስለተጠጋ ንፋሱ ዉሀዉን ያንቀሳቅሰዉ ነበር። አንዴ በናጠን ቁጥር እነሀዩ ሲጮሁ እርስ በእርስ ሲያያዙ እኔና ገብሬ እንስቃለን።
.
ከጀልባዉ እንደወረድን ገብሬን ሞቅ ባለ ክፍያ አስደሰትነዉ። የሚሰራ ሰዉ ገንዘብ ሲያገኝ ደስ ይላል።ለአጭበርባሪ ለማኝ ገንዘብ ከመስጠት ለገብሬ አይነቱ እጥፍ መክፈል እርካታ ይሰጣል። ስንቱን ቀዳዳ እንደሚሸፍንበት ገብሬ ነዉ የሚያዉቀዉ።
.
ማታ ግቢ በር ጋር እራት እየበላን ቀጣዩን ቀን የምናስፈርማቸዉን ነገሮች ጨራርሰን ጁምዓ(አርብ) ወደየቤታችን ለመሄድ ወሰንን።ቆይ አሁን እንዴት ነዉ ከሀያት እና ከራሄል ጋር ወደ ሸገር የምመለሰዉ? ሀያት ገና የሄድን ቀን ኺጥባ(ለጋብቻ በተጫጩ ጥንዶች መካከል የሚካሄድ ዉይይት) ካልጀመርን ማለቷ አይቀርም።
ቆይ ራሄልስ ምን አስባ ነዉ እንደዛ በርግጠኝነት የራሷ እንደምታደርገኝ የዛተችዉ? እናያለና!

ይቀጥላል........

ይቀላቀሉን

@joyyeg
148 viewsHabesha, 18:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 22:58:46 እንኳን ደስ አለን

ለተሰንበት ግደይ የ18ኛዉ የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮን የሴቶች የ10,000ሜ አሸናፊ ሆናለች
@joyyeg
@joyyeg
136 viewsHabesha, 19:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 22:47:21 በ 18ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በአሁኑ ሰአት የ10,000 ሜትር የሴቶች የፍፃሜ ውድድር እየተከናወነ ይገኛል! በዚህም ለተሰንበት ግደይ ፣ እጅጋየሁ ታየ እና ቦሰና ሙላት ሀገራችንን ወክለው እየሮጡ ይገኛሉ።

መልካም እድል ለእምዬ ኢትዮጵያ!
@joyyeg
@joyyeg
133 viewsHabesha, 19:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ