Get Mystery Box with random crypto!

በመጨረሻው ምዕራፍ ለቡድን ሁለት የሞጁላር ሰልጣኞች የመመዘኛ ፈተና ተሰጠ በገቢዎች ሚኒስቴር የም | M.O.R East Addis Ababa Branch

በመጨረሻው ምዕራፍ ለቡድን ሁለት የሞጁላር ሰልጣኞች የመመዘኛ ፈተና ተሰጠ

በገቢዎች ሚኒስቴር የምስራቅ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በመጨረሻው ምዕራፍ ለቡድን ሁለት የሞጁላር ሰልጣኞች ሰኔ 28 ቀን 2014 ዓ.ም የመመዘኛ ፈተና ሰጥቷል፡፡

የመመዘኛ ፈተና የወሰዱ ግብር ከፋዮች በ3 ምዕራፍ ተከፋፍሎ ሲሰጡ የነበሩ የታክስ ትምርቶችን በሚገባ ተከታትለው ያጠናቀቁ ሲሆኑ በምዕራፍ አንድ ከመቀጠር ሚገኝ ገቢ ግብር፣ የቤት ኪራይ እና የንግድ ስራ ገቢ ግብ እና ቅድመ ግብር በምዕራፍ ሁለት ተጨማሪ እሴት ታክስ፣ ተርን ኦቨር ታክሰ፣ኤክሳይ ታክስ፣ ቴምብር ቀረጥ እና ሱር ታክስ እንዲሁም በምራፍ ሦስት የታክስ ከፋይ ምዝገባ፣ ስረዛ እና ክሊራንስ አሠጣጥ፣ ደረሰኝ እና ሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ አጠቃቀም፣ የታክስ ማስታወቅና ቅጻ ቅጾች፣ የታክስ ስሌት፣ሌሎች ክፍያዎችን ስለ ማስከፈል እና ተመላሽ አሰራር ፣የታክስ አስተዳደር እና የወንጀል ቅጣት እና ተያያዥ ጉዳዮችን የሚሉ ርዕሰ ጉዳዮችን 90 Credit Hours በሚሸፍን ጊዜ መሰልጠን ችለዋል፡፡

የገቢዎች ሚኒስቴር በ2014 ዓ.ም ከሁሉም ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ተከታታይ የሞጁላር ስልጠና የወሰዱ ግብር ከፋዮችን ለማስመረቅ የተለያዩ ቅድመ ሁኔታዎችን እየከወነ ሲሆን ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ከ200 በላይ የሚሆኑ ሰልጣኝ ግብር ከፋዮችን የሚያስመርቅ ይሆናል፡፡