Get Mystery Box with random crypto!

ምጥን ቅመም (Mitin Kimem)

የቴሌግራም ቻናል አርማ mitinkimem — ምጥን ቅመም (Mitin Kimem)
የቴሌግራም ቻናል አርማ mitinkimem — ምጥን ቅመም (Mitin Kimem)
የሰርጥ አድራሻ: @mitinkimem
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 1.09K
የሰርጥ መግለጫ

እያሳሳቁ ቁም ነገር የሚያስጨብጡ ጽሁፎችን እናደርሶታለን።
https://t.me/joinchat/AAAAAEW4c6a4s66UQCzegg

Ratings & Reviews

5.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

3

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-03-04 12:52:38 አርምሞ

ግማሹን ዘመናቸውን ክፉም ሆነ ደግ ከአንደበታቸው ሳይሰማ፣ ስለደረሰባቸው መገፋትም ይሁን ስደት ማንንም ሳይወቅሱ እና ሳይከሱ፣ ዘመናቸውን በጽሙና፣ በጸሎት እና በአርምሞ (በዝምታ) ሆነው ነው የፈጸሙት።

በትምህርተ ክርስትና ዝምታ (አርምሞ) አንዱ የመንፈስ ልእልና (የቅድስና) መገለጫ ነው። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ጸጋ በቅዱስ መጽሐፍ ስማቸው ከሚጠቀሱ ቅዱሳን አንዷ በመሆን ትታወቃለች። ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ “ማርያም ግን ይህን ነገር ሁሉ በልብዋ እያሰበች ትጠብቀው ነበር።” ሲል ገልጦታል። (ሉቃስ 2፥19)

ጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ያለበደሉ በፍርድ አደባባይ ቆሞ በሚከሱት፣ በሚወቅሱት ፊት በዙሪያው የነበሩት ሁሉ እስኪደነቁ ድረስ ዝም ማለቱ ተጽፏል። "ሊቀካህናቱም እነዚህ ለሚመሰክሩብህ አንድ ስንኳ አትመልስምን? አለው። ኢየሱስ ግን ዝም አለ፦ (ማቴ 26፥63)

መናገር እየቻሉ፣ ለከሰሳ እና ለወቀሳ መልስ መስጠት እየቻሉ፣ ማስረጃ እና መረጃ አቅርቦ ማሳጣት እየቻሉ፣ ሌላው የተሰወረበትን ገላልጠው እያወቁ ... ሰምተው እንዳልሰሙ፣ አውቀውም እንዳላወቁ ሁሉን በሆድ ችለው ዝም ማለት እንደምን ይቻላል? እንዲህ ዓይነት ትህትና እንደምን ይደንቃል ! ምን ዓይነት ሀብተ መንፈስ ቅዱስ ነው?

ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬም "ናርምም እስመ ኢንክል ፈጽሞ ጥንቁቀ ነጊረ" (ይህንን ነገር ፈጽመን መናገር አይቻለንም እና ዝም እንበል) እንዳለው ዝም ከማለት በስተቀር ይህንን እንደምን ዘርዝሮ መጻፍ ይቻላል?

አባታችን በረከትዎ ትድረሰን!
https://t.me/Gamel_Tube
948 viewsYishak Kelemework, 09:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-04 09:13:23 #SafaricomEthiopia :ወድ ኢትዮጵያዊያን ቤተሰቦቻችን ድርጅታችን ሚያዚያ ሁለት በ+2517 የመለያኮድ የስልክ አገልግሎት የሚጀምር መሆኑን ማሳወቃችን ይታወቃል እንዲሁም መረጃዎችን ተደራሽ ለማድረግ እንዲረዱን የከፈትናቸው የማህበራዊ ሚዲያ ገፆቻችን ተከታይ በመሆን ና በማጋራት ተደራሽ ያደረጉ ብዙ ቤተሰቦቻችንን ሸልመናል። ለበለጠ መረጃ ቻናሉን ይቀላቀሉ። ወደ ቻናሉ ለመግባት
https://t.me/Safaricom_ethiopia_new_bot?start=r0162424483
871 viewsYishak Kelemework, 06:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-14 14:19:00 "ጋሜል ብሂል ግሩም እግዚአብሔር።"
"ጋሜል" ማለት "እግዚአብሔር ሊመረመር የማይቻል ግሩም ድንቅ ነው።" ማለት ነው።
መዝሙረ ዳዊት 118÷7

"Gamel" means "God is wonderful beyond measure."
Psalm 118 ÷ 7

ኑ አብረን እንማማር። በአንድ ልብ መካሪ በአንድ ቃል ተናጋሪ ሆነን ቤተ ክርስቲያናችንን እንጠብቅ እናስጠብቅ።

ሼር በማድረግ ለወዳጅዎ ያጋሩ።

ጸልዩ በእንተ ሰላመ ቤተ ክርስቲያን አሐቲ ቅድስት ጉባዔ እንተ ሐዋርያት ርትዕት በኃበ እግዚአብሔር።

https://t.me/Gamel_Tube
https://t.me/Gamel_Tube
https://t.me/Gamel_Tube
1.6K viewsYishak Kelemework, 11:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-14 21:19:50 "መዳን በሌላ በማንም የለም"
✞Share ያድርጉና ለሌሎችም ያካፍሉ✞
"መዳን በሌላ በማንም የለም" የሚለውን የቅዱስ መፅሀፍን ቃል ለምንፍቅናና
ለጥርጥር ትምህርት በማዋል የእመቤታችንና የቅዱሳንን ማዳን በይፋና በስውር ለሚቃወሙ የተሀድሶ መናፍቃን የተሰጠች አጭር ምላሽ፡፡
እንዲህ በክፋትና በተንኮል አጥማጅና አሰናካይ ርኩሰታዊ ፈተና ሊጥለን ዛሬም
የሚታገለን አስቀድሞ በገነት ዛፎች መካከል በእባብ ገላ ተሰውሮ
ከአምላካችንና ከአባታችን የለየን ድያብሎስ ነው፡፡ እርሱን የምታገኙት በነዚህ በመናፍቃን ልቡና ተሰውሮ ነውና፡፡ ሰይጣን በተንኮሉ ሄዋንን እንዳሳታት በጣም የዋሃን የሆንነውን፡
መንፈሳዊ ጥበብንና መዳን የሚገኝበትን ትምህርት ከአባቶቻችን እግር ስር
ተቀምጠን ያልተማርነውን ብዙዎቻችንን እንዳያቆሽሸን ፡ እምነታችንንና ለክርስቶስ
ማደሪያ የሚሆን ልቡናችንን እንዳያረክስብን በብርቱ መጠንቀቅ ይገባል፡፡
እንግዲህ ወደ ባላጋራችን የማጥመጃ ሀሳብ እንመለስ ፡ ጠላት ወጥመድን
እንደሚያጠምድ ፡ ቢቻለው ብዙዎችን ለመያዝና ከህይወት ለመለየት እንቅልፍ
የሌለው መሆኑን ቅዱሳት መፃህፍት ያስረዳሉ፡፡ እኛ የምናምነውን መጠየቅ
ያለብን እኛው ነን፡፡ እራሳቸው ለራሳቸው ስለኛ እምነት ተናጋሪዎች ፡ ወሳኞች ፡
ተቺዎችና ነቃፊዎች ሆነው በሚነሳው ግርግር እንደለመዱት ነብሳትን ለመዝረፍ
የሚያደርጉት ክፋት ግን የበለጠ የሰይጣን አገልጋይ መሆናቸውን
ይገልጥባቸዋል፡፡

እስቲ ጥቂት ሰይጣን ከላይ ያነሳውን የተንኮል ሀሳብን የሚያሳፍር አጭር ምላሽ እንናገር፡፡ ለዚህ ርካሽ ሀሳብ መቼም ሊቃውንት መጠራት አለባቸው አንልም፡፡ እንደ አንድ ምዕመን ይህቺን እንበል፡፡ በቅድስት ቤተክርስቲያን አስተምህሮ መሰረት እግዚአብሔር በባህርይው አዳኝ ነው፡፡ በባህርይው አዳኝ ነው ስንል፦ ማዳንን ከማንም ያልተዋሰው ያልተቀበለው ፡ በራሱ ለራሱ ያለው ፡ ለወደደው ፡ ለፈቀደው በስጦታ የሚሰጠው ማለታችን ነው፡፡ ለእግዚአብሔር ማዳን ለኢየሱስ ክርስቶስ ማዳን ሌላ ምንጭ የለውም፡፡
ለማንም ማዳን ግን ምንጩ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ስለዚህም ኢየሱስ ክርስቶስ ያድናል ስንልና ቅዱሳን ያድናሉ ስንል ከዚህ ከአለት ከሚፀና እምነትን መሰረት አድርገን ነው፡፡

ይህንን አባቶቻችን በምሳሌ ሲያስረዱ እሳት በባህሪው ያቃጥላል እሳት የሚያቃጥለው ማቃጠልን ከሌላ ነገር ወስዶ አይደለም፡፡ መቼም
የማያቃጥል እሳት የለም፡፡ እሳት ከሆነ እርሱ ያቃጥላል፡፡ ማቃጠል የግል ገንዘቡ ነው በራሱ ያቃጥላልና፡፡ ብረትና እንጨት ደግሞ በተፈጥሮ አያቃጥሉም፡፡ ነገር ግን እንዲያቃጥሉ ማድረግ ይቻላል፡፡ እንዴት? ብረቱን ወስደን : እንጨቱን ወስደን ከእሳት ውስጥ ብንጨምረው ፍም ሆኖ ይግልና ከዛ ያቃጥላል፡፡ መቼም እሳት ውስጥ ገብቶ የማያቃጥል ብረትም ሆነ እንጨት አለ የሚል እምነት ያለው ሰው አለ የሚል እምነት የለኝም፡፡ እሳት ውስጥ
ገብቶ ብረቱ ወይም እንጨቱ ካላቃጠለ አለማቃጠሉ ችግሩ የብረቱ ወይም
የእንጨቱ ችግር አይደለም፡፡ እሳቱ ራሱ አያቃጥልም ማለት ነው፡፡ አሁን
ከመናፍቃን በቀር ስለምን እያወራን እንዳለ ሁሉም የክርስቶስ ቤተሰብ ይረዳል የሚል እምነት አለኝ፡፡ የድንግል ልጅ ወልድ ዋህድ ክርስቶስ በባህሪው አዳኝ ነው፡፡ ቅዱሳን ደግሞ ወዷቸው ፡ መርጧቸው ፡ ለይቷቸው ፡ ሾሟቸው በፀጋ ያድናሉ፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር አንድነቱ የተጠበቀ የእግዚአብሔር ቅዱስ ፡ ፃድቅና ሰማዕት የማያድንበት ምንም ምክንያት የለም፡፡ ካላዳነ ግን አለማዳኑ የፃድቁ ወይም የቅዱሱ ሰው ሳይሆን እግዚአብሔር ራሱ ማዳን ትቷል ማለት ነው፡፡ ወይም ያ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር አንድነትና ህብረት የለውም ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ቅዱሳን ፃድቃን ሰማዕታ ሁሉ ያድናሉ፡፡ ይሁዳ ግን አያድንም፡፡ ሐዋርያ ነበር ከግንዱ ከክርስቶስ ተቆርጦ ወደቀ፡፡ ሰይጣንም አያድንም ለራሱም አይድንም፡፡ መልአክ ነበር ከምንጩ ከክርስቶስ ተቆርጦ ወደቀ፡፡ ነገር ግን አለምን የካዱ ፡ የአለምን ነገር ስለ ክርስቶስ የሰቀሉ ፡ በተጋድሎ የፅድቅ ፍሬን ያፈሩ ቅዱሳን ፡ ፃድቃን ፡ ሰማዕታት ግን ያድናሉ፡፡ መፅሀፍ ቅዱስ ይናገር ካልን ደግሞ በድን የሆነ የፊደል ችርቻሮን ከሚነግዱትና ቅዱሱን ቃል በከንቱ ተሸክመውት ከሚዞሩ መናፍቃን በቀር ሁሉም ክርስቲያን እንደሚያስተውለው በሐዋርያት ገድል ላይ ተመስርቶ የተፃፈው የሐዋርያት ሥራ እንደሚያስተምረን በቅዱሳን እጅ ድንቅ
ተዓምር እንደሚደረግ እናስተውላለን፡፡ አባታችን ቅዱስ ጴጥሮስ በጥላው ሙት
እንዳስነሳ ፡ ለምፅ እንዳነፃ ፡ ድውይ እንደፈወሰ ፡ ሽባ እንደተረተረ ፡ አጋንንትን
እንዳሳደደ ፡ አባታችን ቅዱስ ጳውሎስም በጥላው ብዙዎችን እንደፈወሰ
ተመዝግቧል።
/ሐዋ 5፥15, ሐዋ 19፥11/
የአባቶቻችን ቅድስናና ስልጣን ከነሱ
አልፎ ለልብሳቸው ዘርፍና ለጥላቸው ፡ ለረገጡት አፈር ሁሉ መትረፉን ቅዱስ
መፅሀፍ ያስተምረናል፡፡ እኛም የክርስቶስ ልጆች የድንግል ማርያም ወዳጆች
በእውነት እናምናለን፡፡ ብዙ ድንቅ ነገርም ተደርጎልናል፡፡ በመጨረሻው ቀንም
የክርስቶስ ቅዱሳንን የሚያሳድዱና በቅዱሳን ደም በሰከሩ በመናፍቃን ላይ ቃሉ ይፈርዳል፡፡ በንስሀ እስካልተመለሱ፡፡

አባቶቻችን ቅዱሳን በብርሃን ከተማ
ከክርስቶስ ጋር ለመኖር ከሄዱ በኃላም የረገጡት አፈር ፡ የፀለዩበት በዓታቸው ፡
የሰገዱበት ስፍራ ፡ ያረፋበት መቃብራቸው እኛ የሥላሴ ልጆችን ያድናል፡፡ ለኛ የተደረገልንን ትተነው የሉተር ልጆች በከንቱ ተሸክመውት ከሚሄዱት በአዳራሽም ሽለላና ቀረርቶ ከሚያሰሙበት ከመፅሃፍ ቅዱስ ከመፅሃፈ ነገስት ላይ አባታችን
ኤልሳ ከተቀበረበት መቃብር አፈር ላይ የወደቀ አንድ የሞተ ሰው አፈፍ ብሎ
መነሳቱን እንዲያነቡት እንጋብዛቸዋለን።
/2ነገ 13፥31/፡፡
ለማስተዋልና ለማመን የሚያስችላቸውን የእምነት ብኩርናን በምስር ወጥ አስወስደው ዛሬ የቀደመች
እምነታቸውን ለመሳደብ ፡ ለመራገም ፡ በእርሷ ላይ ለመሳለቅ ተፈረደባቸው
እንጂ፡፡ እግዚአብሔር ይምራቸው ዘንድ ቤተ ክርስቲያናችን ሁሌ ወደ
እግዚአብሔር ትማልዳለች፡፡ ሌላም ካሻቸው ፀበል እንደሚያድን ሶርያዊው
ንዕማን በፍርድ ቀን ይመሰክራል፡፡ መስቀሉ እንደሚያድንና የእሳት ባህርን
እንደሚያሻግር ፡ አጋንንትንም ከጥልቁ እንደሚያወርድ ቅዱሳኑ ሁሉ በአለም ላይ
ይመሰክሩበታል፡፡
ታዲያ አብረውት ለሶስት አመት ከሶስት ወር የተመላለሱት ቅዱሳን ሃዋርያት
ጥላቸውና የልብሳቸው ዘርፍ ካዳነ በማህፀኗ ያደረባት ፡ ከስጋዋ ስጋን ከነብሷ ነብስን የነሳባት ፡ በክንዶቿ እቅፍ ያረፈባት ፡ ጡቶቿን ጠብቶ ያደገባት ፡ በጀርባዋ ታዝሎ በበረሃ የተሰደደባት ፡ እናቱ ፡ እናቱ ፡ እናቱ ድንግል ማርያምማ እንደምን ከመከራ ስጋ ከመከራ ነብስ አታድን??!! ከእግዚአብሔር ከተሰጡት ፀጋዎች ከእመቤታችን የሚጎድልባት የትኛው ነው፡፡ የራማው ልዑል ቅዱስ ገብርኤል ይመስክራ ፡ ሀሰት በአንደበቱ ያልተገኘበት በእግዚአብሔር ፊት የሚቆመው መልአኩ ገብርኤል ይመስክራ። ይቀጥላል።
1.6K viewsYishak Kelemework, 18:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-02 09:52:14 ተወዳጆች ሆይ! አንድ እንግዳ ወደ ቤታችን ሲመጣ ቤታችንን እንደምን እንደምናሰናዳው ሁላችንም እናውቀዋለን፡፡ ሁላችንም እንግዳችንን ደስ የሚያሰኘው ነገር ለማድረግ የምንቻኰል አይደለንምን? ለእንግዳችን የሆነ ነገር ባናደርግለት፥ እንግዳችን በመምጣቱ ደስ ተሰኝተን እርሱን ደስ የሚያሰኝ ነገር ባናደርግለት፥ ግን ደግሞ በመምጣቱ ደስ እንደተሰኘን ብንነግረው እንግዳችን በፍጹም አያምነንም፡፡ በእንግዳችን መምጣት ደስ እንደተሰኘን ከቃላት ባለፈ በገቢር መግለጥ አለብንና፡፡ እንኪያስ የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሕይወታችን ከመጣ ደስ መሰኘታችንን በገቢር ልንገልጽ ያስፈልጋል፡፡ እንግዳችን ክርስቶስን የሚያስቈጣ ነገር ልንፈጽም አይገባንም፡፡

እንግዳ ሲመጣ ቆሻሻ ልብስ አይለበስም፡፡ እንግዳ ሲመጣ የሚያስጸይፍ ነገር አይነገርም፡፡ ክርስቶስ በሕይወታችን ውስጥ እንዲኖር ስንፈልግም ቆሻሻ ልብሳችንን (ማንነታችንን) አውልቀን ልንጥል ያስፈልጋል፤ አስጸያፊ ነገራችንን ልንተው ያስፈልጋል፡፡ እንግዳ ሲመጣ ቤት ያፈራው ሁሉ ይቀርብለታል፡፡ ክርስቶስ ወደ ቤታችን ሲመጣም የሚበላ ነገር ልናቀርብለት ይገባል፡፡ ለመሆኑ የክርስቶስ መብል ምንድነው? ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን ጥያቄ ሲመልስልን እንዲህ ብሏል፡- “የእኔስ መብል የላከኝን ፈቃድ አደርግ ዘንድ ሥራውንም እፈጽም ዘንድ ነው” ዮሐ.፬፡፴፬፡፡

እንኪያስ ክርስቶስ የራበው ይኸው ነውና እንመግበው፤ ኢየሱስ የጠማው ይኸው ነውና እናጠጣው፡፡ እርሱም ይቀበለናል፡፡ አንዲት ኩባያ ቀዝቃዛ ውኃ ብንሰጠው እንኳ ይቀበለናል፡፡ ስለብዛቱ ሳይሆን ስለፍቅሩ ብሎ ይቀበለናል፡፡ እኛን ስለመውደዱ ይቀበለናል፡፡ የምንወደው ሰው የሰጠነውን የሚቀበለን ስለ መጠኑ አይደለም፤ ስጦታው የወዳጅ ስለሆነበት እንጂ፡፡ ሰው ወዳጁ ጌታም ሁለት ሳንቲም ብንሰጥ እንኳ ብዙ እንደሰጠን አድርጐ ይቀበለናል፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስጦታችንን የሚቀበለው ድሃ ስለሆነ አይደለም፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የድሃውም የባለጸጋውም ስጦታ እኩል የሚቀበለው ስለ ልቡናችን ኀልዮት እንጂ ስለ ስጦታው ትልቅነት ወይም ዋጋ አይደለም፡፡ ስለዚህ ክርስቶስን እንደምንወደው ለመግለጽ የግድ ብዙ ወይም በውድ ዋጋ የተገዛን ስጦታ መስጠት አያስፈልገንም፡፡ ስጦታችን እርሱ ወደ እኛ ስለመጣ ደስ የመሰኘታችን መግለጫ ነውና ስለ ስጦታችን መጠን ልንመለከት አይገባም፡፡



"ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ"
2.3K viewsYishak Kelemework, 06:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-19 11:50:09 መሰላሉን ተከትሎ ወደታች መውረድ ክልክል ነው።
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
ትሰሙኛላችሁ? ተዉ ወደታች አትውረዱ!
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
ሃሎ...? ተው አትሂዱ ብያለሁ
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
ቁም! ከዚህ በታች መውረድ አይቻልም!
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
እሺ ምን ይደረጋል እንግዲህ ጨክናቹ መውረድ ከፈለጋቹ ውረዱ። እኔ ግን የለሁበትም።
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
እምቢ አላችሁ አይደል? ዝም ብላችሁ እየወረዳችሁ ነው ታውቋችኋል ግን?
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
ከዚህ በኋላ ሁለተኛ አልናገርህም።
ምን አገባኝ?
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
ተው ግን የመጨረሻ ልለምናችሁ አትውረዱ ለእናንተ ጥሩ አይደለም።
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
ኧረ እባካችሁ ስሙኝ?
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
መስሚያ የላችሁም እንዴ? ተዉ ይቅርባችሁ።
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
እሺ ይህ የመጨረሻ ነው። ተዉ አትውረዱ!
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
የምሬን ነው ኧረ በቃችሁ አትውረዱ!!
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
አሁንም እየወረዳችሁ ነው?
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
የመጨረሻ እድል ልስጣችሁ መውረድ አቁሙ!!!
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
╬═╬
በቃ ጨክናቹ መጣቹ??? ትዕዛዝ አለማክበር ከባድ ነው።
ለማንኛውም ከመጣችሁ አይቀር በባዶ እንዳትመለሱ ያክል.......
መልካም የደብረ ታቦር (ቡሄ) በዓል ይሁንላችሁ።
1.5K viewsYishak Kelemework, 08:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-06 05:29:16 ወድደውታል?
1.3K viewsChannel Like Bot, 02:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-06 05:29:13 ✞✞ ፆመ ፍልሰታ✞✞☞
☞ እባካችሁ አንብቡና በጣም ለምትወዱት ሰው ሼር አድርጉት

(ጾመ ፍልሰታ) የፍልሰታ ፆም(ጾመ ማርያም) ሞት በጥር በነሀሴ መቃብር።

የፍልሰታ ፆም ከነሐሴ 1 እስከ 15 ነው።

በቤተ ክርስቲያናችን እደሚገለፀው "እመቤታችን ያረፈችው ጥር 21ቀን ነው።

ሐዋርያት በድኗን ሊቀብሯት ወደ ጌተሰማኒ ይዘዋት ሲሄዱ አይሁድ አይተዋቸው በተኗቸው፤ በዚህ ጊዜ መላእክት የእመቤታችንን አስክሬን ወስደው በገነት አኑረውታል።
ከ8ወር በኋላ በነሐሴ ሐዋርያት አስክሬኗን እንደገና ከጌታ ተቀብለው በፀሎትና በምህላ ቀብረዋታል። በዚህ የቀብር ሥነ-ስርዓት ላይ ከ12 ሐዋርያት አንዱ ቶማስ አልነበረም።

ቅዱስ ቶማስ ከሀገረ ስብከቱ በደመና ተጭኖ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመጣ ያገኛታል፤ በዚህ ጊዜ ትንሳኤዋን ሌሎች ሐዋርያቶች አይተው ለእሱ የቀረበት መስሎት ተናዶ በፊት የልጅሽን ትንሳኤ ሳላይ ቀረው አሁን ደግሞ የአንቺን ትንሳኤ ሳላይ ቀርቼ ነበር ብሎ ከደመና ሊወረወር ቃጣው በዚህ ጊዜ
እመቤታችን ቶማስን አፅናንታ ከእሱ በቀር ሌላ ትንሰኤዋን እንዳላየ ነገረችው።

ቶማስም ሐዋርያት ወዳሉበት ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ እመቤታችንን ቀበርናት ብለው ነገሩት እሱም አውቆ ምስጥሩን ደብቆ አይደረግም ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር? አላቸው። ለማሳየትም መቃብር ሲከፍቱ አጧት በዚህ ጊዜ "አታምኑኝም ብዬ ነው እንጂ እመቤታችን ተነስታ አርጋለች።'' ብሎ ሁኔታውን ተረከላቸው ለምስክርም ይሆናል ብሎ የሰጠችውን ሰበኗን (መቀነቷን) አሳያቸው። ሰበኗንም ለበረከት ቆራርጠው ተከፋፍለው ወደ ሀገረ ስብከት ተበታተኑ። በዓመቱም ትንሳኤሽን ቶማስ አይቶ እንዴት እኛ ይቀርብናል? ብለው ከነሐሴ 1 ጀምሮ ሱባኤ ገቡ በነሐሴ14 ቀንም ጌታችን ትኩስ በድን አድርጕ አምጥቶ ሰጣቸው። ከቀበሯትም በኋላ በነሐሴ16 ተነስታለች። በዚህ ቀን ጌታ ቀድሶ እመቤታችንም በልጇ እጅ ቆርባለች። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ የሐዋርያት ቤተክርስቲያን የእመቤታችንን በረከት ለማግኘት ይህችን ጊዜ ትፆማለች።
የእመቤታችን በረከቷ አማላጅነቷ ከሁላችንም ጋር ይሁን እናትነቷ ይብዛብን አሜን አሜን አሜን መልካም የፍልሰታ ፆም ይሁንልን ሀገራችንን ሰላም ታድርግልን አሜን ።

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
<< ወለወላዲተ ድንግል >>
<< ወለመስቀሉ ክቡር >>
@Mitinkimem
@Mitinkimem
@Mitinkimem
2.0K viewsYishak Kelemework, 02:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-04-26 19:27:20 የስልጤ ሰፈሩ #ሥላሴ ባለፈው በአህዛብ የድንጋይ ድብደባ የደረሰበት በሀራጅ ሊሸጥ ነው፡፡
መጀመሪያ ቦታው ሲመሰረት በአካባቢው ምንም አይነት ቤተክርስቲያን ስለሌለ የምእመናኑ ጥያቄ ስለነበር ነበር፡፡ እናም መስራች ኮሚቴው በአካባቢው ለቤተክርስቲያን የሚሆን ቦታ ይኖር ይሆን ብሎ ፍለጋ ጀመረ ምንም አይነት ምቹ ቦታ ግን ሊገኝ አልቻለም አማራጭ ሲጠፍ በአካባቢው በቆሻሻ መጣያነት የሚያገለግል ወንዝ ብዙ ሰዎች እየተዘረፉና እየተደፈሩ የወንበዴ ሰርቆ መደበቂያ ጎድጓዳ ቦታ ነበር፡፡ ለምን ቆሻሻውን አጽድተን ገደላማውን መሬት በሙሉም ባይሆን በጥቂቱ ደልድለን ቤተክርስቲያኑን እዚህ ቦታ ላይ አናሳርፈውም የሚል ሀሳብ መጣ ፡፡ መስራች ኮሚቴውም የተሻለ ቦታ እንደማይገኝ ስለተረዳ ባንድ ድምጽ አጽድቆ ወደ ስራ ገባ ፡፡ መንግስትም ቦታውን አጽድተን ወንጀል ከመስሪያ ቤተክርስቲያን እናድርገው ቦታውን ሲሉ ጠየቁት ፡፡ በየመስርያ ቤቱም በመዞር ህጋዊ ለመሆን የሚያስፈልገውን እርምጃ እየሄዱ ሳለ ለመጨረስ ጥቂት መንገዶች ሲቀራቸው ካህናቱ ታቦቱን አስባርከው ይዘው መጡ፡፡ አማራጭ ስላልነበረ ከወንዙ በቅርበት ባዶ ቦታው ጋር ወዳለው ክርስቲያን አመሩ ሐጥቂጥ ጊዜ ግማሽ ይዞታህን ልቀቅ ካጠገብህ ያለው ሜዳ ሲያልቅ ታቦቱ በሚሰራለት መቃኞ ያርፋል እስከዚያው አንተ ጋር ይረፍ ብለው ግማሹን ይዞታውን ለታቦቱ ከፍሎ እንዲሰጥ ተደረገ

በዚያችው 100 ካሬ ላይ ታቦቱ ገባ ማእጠንቱ ተጀመረ ኪዳኑም ቀጠለ..... ይህ ነገር ያልተመቻቸው የአካባቢው አክራሪ ሙስሊሞች ከቤተክርስቲያኑ ጀርባ ቤት በመከራየት ትላልቅ ስፒከር ሰቅለው መስኪድ አደረጉት ከዚያም ያ ለቤተክርስቲያን ሊሆን የታሰበውን ቦታ ለኛም ይገባናል ማለት ጀመሩ

ይህ አካሄድ ምእመናኑን እጅግ አሳዘነ ወደሚመለከተው አካል ብዙ አቤቱታዎች ቀረቡ ምንም መልስ የለም!! እንደውም አልፎ አልፎ በሚፈጠሩት በሁለቱ ቤተ እምነት አማኞችን ጸብ ምክንያት በማድረግ ቦታው ለማንም አይሆንም በማለት መንግስት ሙሉ በሙሉ እስከ ወንዙ ድረስ ታጥሮ እንዲቀመጥ አድርጎታል በኀላም የደሃ ደሃ ቤት መስሪያ ኘሮጀክት በሚል ሰበብ ቦታውን አሳልፎ ሰጥቶታል ፡፡ የካራ መስቀለ ሰላም ቅድስት ሥላሴ ግን በዚያች 100 ካሬ ቦታ ለ3 አመታት እንዲቀመጥ ተደረገ !!! እሱም ይሁን እግዚአብሔር ቀን አለው ቀን ይወጣለታል ብለን ቁጭ እንዳልን ሌላ ዱብዳ መጥቶብናል ፡፡ ደብሩ ያረፈበት ቦታ ባለቤት ነጋዴ ስለነበር ቦታውን መያዝ አድርጎ ከባንክ ብር ተበድሮበታል

ሆኖም ብዙ የመክፈል ሙከራ ቢያደርግም ሊሳካለት ስላልቻለ ደብሩ ላይ ሀራጅ ሊወጣ ግድ ሆኖ ነበር ግን የደብሩ አስተዳደር እና ሰበካ ጉባኤ ባደረገው ሰፈር ለሰፈር የድረሱልኝ ጥሪ 465,000 ብር በብድርና በስጦታ መልክ ሊያገኝ ችሏል!!! በዚህም ምክንያት ሀራጁ ተሰርዞ ለእፎይታ የምትሆን ትንሽ ጊዜም አግኝተን ነበር በአሁኑ ሰዓት ግን ባንኩ ከዚህ በኀላ በምንም አይነት መልኩ እዳው ካልተዘጋ ማለትም 772650.23 ብር ካልተከፈለ ሀራጁን እንደማያስቆም ነግሮን ጨረታውን በድጋሚ አውጥቶታል፡፡ የአካባቢው አክራሪ ሙስሊሞች ብር አዘጋጅተው ቦታውን ለመግዛት እንደወሰኑም መረጃው ደርሶናል ቀጣዩ ምን እንደሚሆን ማሰብ በጣም ይከብዳል ስጋ ወደሙ የተፈተተበት የአምላክ ደም የነጠበበት ቅዱስ ቦታ እንደ አግያ ሶፍያ መስኪድ ሊያደርጉት ዝግጅታቸውን የጨረሱ ይመስላል ለማንኛውም ሰበካ ጉባኤውና ልማት ኮሚቴው እንቅልፍ ካጣ ቆይቷል በዚህም ያቅሙን ሁሉ እየሞከረ ይገኛል በከተማዋ ያሉ አቅም ያላቸው የቤተክርስቲያን ልጆች ጋር በመዞር ወደ 260,000 አካባቢበ ሁለት ቀን ለመሰብሰብ ተችሏል ቀጣዩ ቀሪ ብር አሳሳቢ ነው እንግዲህ ሁሉም ካለፈ በኀላ ከሚፀፀት ከወዲሁ ያቅሙን ያደርግ ዘንድ አደራችንን እናስተላ
ልፋለን የካራ መስቀለ ሰላምየልማት ኮሚቴ አካውንት 1000387442344
2.5K viewsYishak Kelemework, 16:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-12-06 12:39:57 የካራ ቆሬ ረቢ ደብረ ጎልጎታ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን አካባቢ ምዕመናን መነጋገሪያ። በቀን ውስጥ በጣም ትንሽ በማንበብ የማንበብ ልምዳችንን እናዳብር። እግዚአብሔር የሐሉ ምስለ ኩልነ። እግዚአብሔር ከሁላችንም ጋር ይሁን።

@REBI_MEDHANIEALEM
@REBI_MEDHANIEALEM
@REBI_MEDHANIEALEM
2.9K viewsYishak Kelemework, 09:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ