Get Mystery Box with random crypto!

መንፈሳዊ ግጥሞች እና ወጎች

የቴሌግራም ቻናል አርማ melikt_weg_gitim — መንፈሳዊ ግጥሞች እና ወጎች
የቴሌግራም ቻናል አርማ melikt_weg_gitim — መንፈሳዊ ግጥሞች እና ወጎች
የሰርጥ አድራሻ: @melikt_weg_gitim
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.16K
የሰርጥ መግለጫ

✞ ይህ ቻናል መንፈሳዊ የሆኑ ግጥሞች ፣ ወጎች እንዲሁም መልዕክቶች የሚቀርቡበት ነው ✞
አስተያየት ካለ እንዲሁም ግጥም ወግ እንዲተላለፉ የምትፈልጓቸው መንፈሳዊ መልክቶች ለማድረስ https://t.me/ a3-5g5CslOkwNjBk ተጠቀሙ

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-06-23 11:38:02 #ፍቅር

የማይሞተው ሊሞት ባልፈፀመው ነገር

ከወንበዴዎች ጎን ከችሎት ሲገተር

የደካሞች ሸክም በርሱ ላይ ተጭኖ

ሳይሰርቅ እንደ ሌባ ወንጀለኛ ሆኖ

የጠሉትን ቢወድ ሲፈርዱበት ቢምር

ትህትናን ቢሰብክ ምህረትን ቢያስተምር

እርሱ ዳኛ ሳለ ተዳኘ በምድር

በሽፍቶች ታጅቦ ተነዳ ወደ ሞት

ተሰዋ ለፍቅር ፍቅርን ፍቅር ይዞት



ሊዲያ ኑርልኝ


@Melikt_weg_gitim
@Melikt_weg_gititm

#join and #share
833 views𝓜𝓮𝓷𝓽𝓮 ²⁵, 08:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-21 12:30:24 #የልቤ_ማድጋ

ዘወትር ጠዋት ማታ
ስለፋ ስተጋ
እሞላለሁ ብዬ
የልቤን ማድጋ
ዛሬ በንስሃ
ሞላችልኝ ብዬ
በሀሴት ስቦርቅ
አይሎ ደስታዬ
ነገ ደግም ባዶ
ኦና ሆና ሳያት
ኀዘኔ በርትቶ
ስሞክር ልሞላት
ጠብም ላይልላት
ደግሞ እየሞላች
ዳግም ስትጎድል
ምሬቴ አይሎ
ደክሜ እንዳልዝል
ከዚያ ከምንጩ ዳር
አግኝቼ አምላኬን
ዳግም ላይጎድልብኝ
ሞልተህ ማድጋዬን
ለስምህ ልዘምር
ላብዛ ምስጋናዬን።

መሰረት አለሙ


@Melikt_weg_gitim
@Melikt_weg_gititm

#join and #share
781 views𝓜𝓮𝓷𝓽𝓮 ²⁵, 09:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 07:00:30 #የአፎምያ_አጽናኝ

ከቀደመው መንገድ ከላይ በተሰጠን
ዕድሳት በማያውቅ በማይሻርው ዘመን
በድንቅ ምስክሮች ብርሃን በሆኑን
እንድንጓዝ ሁሌም የአፎምያ አጽናኝ
ጠላት ቀስቱን ሰብቆ ሊያጠፋን ሲመጣ
እንደ ቋጥኝ ከቦን የዚህ አለም ጣጣ
በከንቱ ስንሮጥ ኋላ እንዳንቀጣ
አማልደን መላኩ የነፍሳችን ዕጣ
የሁሉንም ጸሎት ከአምላክ የምታደርስ
ፍቅር እና ርህራሄ በሰው የምታለብስ
ልክ እንደ ትላንቱ ዛሬም ፈጥነህ ድረስ
በአንደበትህ ፍሬ ውስጣችን ይታደስ
የዳንኤል አጽናኝ የአፎምያ ረዳት
በህይወት የቀየርክ የባህራንን ጽሕፈት
በለአምን የታደክ ከእርግማን መቅጸፍት
እኛንም ጠብቀን ከምናየው መአት
የምጽአት ዋዜማ ለመሆኑ ምስክር
በመጽሐፍ ያለው ቃሉ ሲተገበር
መተማመን ጠፍቶ ሲቀዘቅዝ ፍቅር
በወንጌሉ አንድምታ ልባችን ይታጠር
ይቅርታ ምህርቱ ይምጣልን የእግዚአብሔር
እረኛ እንደሌለው ሲጨነቅ ትውልዱ
ተመሳስሎ ቆሞ ሲያስት በመንገዱ
ግራ በመጋት ስንቶቹ ተጎዱ
በየዋህነታቸው አብረው ተሰደዱ
ዘንዶ አፉን ከፍቶ ነፍሳት እንዳይወጥ
የተዋህዶን መዝገብ እውነቱን ለመግለጥ
የቆመውን ሁሉ በአውደ ምህረቱ
ያበረታን አምላክ እሰከ ምጽአቱ።


እንኳን ለሊቀመላአኩ ለቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ የንግስ ክብር በዓል በሰላም አደርሳቹ አደረሰን የመላአኩ ረድኤት እና ምልጃው አይለየን አሜን!


@Melikt_weg_gitim
@Melikt_weg_gititm

#join and #share
744 views𝓜𝓮𝓷𝓽𝓮 ²⁵, 04:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 05:50:28 ​​​​ሰኔ 12 #የቅዱስ_ሚካኤል ዓመታዊ በዓል!

እንኳን ለመልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ለእናታችን ቅድስት አፎሚያ አመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ። ሰኔ 12 ቅዱስ ሚካኤል እናታችን ቅድስት አፎሚያን ከጠላት ዲያብሎስ እጅ ያዳነበት ፣ እናታችን ቅድስት አፎሚያ እረፍቷ ነው ።እግዚአብሔር ከቅዱሱ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ፣ ከእናታችን ቅድስት አፎሚያ በረከት ተካፋይ ያድርገን

በወርኃ ሠኔ መታሰቢያ ከሚደረግላቸው ቅዱሳን መካከል እግዚአብሔርን የሚፈራ የአስተራኒቆስ ሚስት የሆነች የቅድስት አፎምያን ታሪክ በአጭሩ እንዳስሳለን

ቅድስት አፎምያ በትዳር በነበረችባቸው ዘመናት እግዚአብሔርን ከሚወድ ባለቤቷ ጋር እግዚአብሔርን ስታገለግለው የኖረች ሴት ነበረች፡፡ በየወሩ በ29 ቀን የጌታችንን የልደቱን፣ ወር በገባ በ21 የእመቤታችንንና ወር በገባ በ12 የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ እያደረጉ ነዳያንን ይጎበኙ እንደነበር ታሪካቸው ይነግረናል

ባለቤቷ አስተራኒቆስ ከዚህ ዓለም የሚያርፍበት ጊዜ እንደደረሰ ባወቀ ጊዜ ይሰጡት የነበረውን ምጽዋት እና የሦስቱን በዓላት መታሰቢያ ማድረግ እንዳታስታጉል ከአደራ ጋር አዘዛት፡፡ እሷም የመልአኩን የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል ያሥልላት ዘንድ ባለቤቷን ጠይቃ አሠርቶ ሰጣት፡፡ በከበረ ቦታም አኖረችው

ባሏ ካረፈ በኋላ ያዘዛትን መንፈሳዊ ሥራ ከወትሮው አስበልጣ መሥራት ቀጠለች፡፡ የሰው ልጆች ጠላት የሆነው ሰይጣንም በመልካም አገልግሎት ስትበረታ ባያት ጊዜ ዝም ብሎ ሊተዋት አልወደደም፡፡ በመጀመሪያ ባል ሳታገባ ማገልገሏን ትታ፣ ሌላ ባል አግብታ፣ ልጅ ወልዳ እንድትኖር በብዙ ማባበል ጠየቃት፡፡ ባሏ መንግሥተ ሰማያትን ስለወረሰ ምንም ምጽዋት እንደማይሻ አስመስሎ ነገራት

ቅድስት አፎምያ ግን ዳግመኛ ትዳር ላለመመሥረት ቃል ኪዳን እንደገባች ርግብንና ዖፈ መንጢጥን አብነት አድርጋ፤ እነሱ እንኳ በሕይወት ዘመናቸው ከአንድ ባል ውጪ ሌላ ባል እንደማያውቁ በመጥቀስ አሳቡን እንደማትቀበለው ገለጸችለት፡፡ ሰይጣንም አስመሳይ መሆኑ አላዋጣ ሲለው ማንነቱን ቀይሮ ሊያንቃት ቢሞክር የእግዚአብሔርንና የቅዱስ ሚካኤልን ስም ጠርታ አባረረችው፡፡ እሱም ተመልሶ መጥቶ እንደሚያጠፋት ዝቶባት እንደአቧራ በኖ፤ እንደ ጢስም ተኖ ጠፋ

በሠኔ ፲፪ ቀን የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ እያዘጋጀች ሳለች ሰይጣን ብርሃናዊ መልአክ መስሎ መጣ፡፡ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል እንደሆነ ገልጾ የመጀመሪያውን የመሰለ ከንቱ ምክሩን አሰማምሮ አቀረበላት፡፡ አሳቡንም የእግዚአብሔር ፈቃድና አሳብ እንደሆነ አድርጎ ለማሳመን ሞከረ፡፡ ሰይጣን አስቀድሞ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በገዳመ ቆሮንቶስ መጻሕፍትን እየጠቀሰ እንደተፈታተነው ሁሉ ቅድስት አፎምያንም ለማሳመንም አብርሃምን፣ ይስሐቅን፣ ያዕቆብን፣ ዳዊትን የመሳሰሉ ደጋግ አባቶችን ታሪክ እየጠቀሰ ወደ ትዳር እንድትገባ ደጋግሞ ወተወታት

ቅድስት አፎምያም በእግዚአብሔር ኃይል ጸንታ በቅዱስ ሚካኤልም ተራዳኢነት ታምና “የእግዚአብሔር መልአክ ከሆንክ መንፈሳዊ ማረጋገጫህ የሆነው የመስቀል ምልክት የታለ?” በማለት በምድራዊ ንጉሥና በጭፍራው መካከል የሚኖርን የጋራ መግባቢያ መንገድ ዋቢ አድርጋ ጠየቀችው

ለጊዜው “በኛ በመላእክት ዘንድ እንዲህ አይደለም” ብሎ ሊሸነግላትና አቋሟን ሊያስቀይራት ሞከረ፡፡ ከቤቷ ያለ የቅዱስ ሚካኤል ሥዕል ላይ ያለውን ምልክት አብራርታ የእሱ ግን ከዛ ጋር አንድነት እንደሌለው አረጋገጠችበት፡፡ ከቤቷ ላለው ለቅዱስ ሚካኤል ሥዕል እጅ እንዲነሣ ጠየቀችው፡፡ በዚህ ጊዜ መልኩ ወደ ትክክለኛ ማንነቱ ተለወጠና ጨለማ ለብሶ እየዛተ አነቃት፡፡ ቅድስት አፎምያም የከበረ መልአክ ቅዱስ ሚካኤልን “ድረስልኝ” እያለች በጠራችው ጊዜ መልአኩም ፈጥኖ በመድረስ ከሰይጣን እጅ አዳናት

የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም ለሰይጣኑ ተገቢውን ቅጣት ሰጥቶ ቅድስት አፎምያን ባረካት፡፡ የዕረፍት ቀኗ በዚህ ቀን መሆኑን ነግሮ ቤቷን እንድታዘጋጅ አዘዛት፡፡ የበዓሉን ዝግጅት አከናውና ሥጋ ወደሙን ተቀብላ ኤጲስ ቆጶሱንና ካህናቱን እንደየመዓርጋቸው ጠርታ በቤቷ አክብራ ተቀበለቻቸው፡፡ ለነዳያንና ለጾም አዳሪዎች በኤጲስ ቆጶሱና በካህናቱ እጅ ገንዘቧን መጽውታ መንገዷን አሳመረች፡፡ ስለ ኃጢአቷ እንዲጸልዩላት ተማፅና በፊታቸው ተንበርክካ ጸለየች፡፡ ባሏ ያሠራላትን የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል አቅፋ ስማ ከተማጸነች በኋላ ሠኔ ፲፪ ቀን በሰላም ዐረፈች

ይህች የታመነች ቅድስት አፎምያ በሰላም እስክታርፍ ጊዜ ድረስ የተጓዘችበትን መንፈሳዊ ጎዳና አስተውለን ይሆን? አስቀድማ ከባሏ ጋር አንድ ሆና በታማኝነት ፈጣሪዋን አገለገለችው፡፡ በኋላም የባሏን ኑዛዜ አክብራ ምንም እንኳን ኃጢአት ባይሆንባትም በሁለተኛ ትዳር ራስዋን ማጠላለፍ አልፈለገችም፡፡ በጎ ሥራ አብልጣ በመሥራት እግዚአብሔርን ደስ ለማሰኘት ተፋጠነች እንጂ

ሰይጣን ልጅ አለመውለዷን ተጠቅሞ ያቀረበላትን የጋብቻ ጥያቄ ውድቅ በማድረግ “መንፈስን ሁሉ አትመኑ፤ መናፍስት ከእግዚአብሔር እንደሆኑ መርምሩ” ተብሎ በቅዱሳት መጻሕፍት የታዘዘውን መመሪያ ተጠቅማ ሰይጣንን በተወክሎ እግዚአብሔር ተቃውማ አሸነፈችው፡፡ የቅዱስ ሚካኤልን ርዳታ ያገኘችውና በሰላም ዐርፋ ወዳገለገለችው እግዚአብሔር በክብር የሔደችው በጽናት ተጋድላ ነው

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፤ እኛንም በጸሎቷ ይማረን፤ የቅዱስ ሚካኤል የረድኤቱ ኃይል ሁላችንንም ይጠብቀን፣ ለዘለዓለሙ አሜን
565 views𝓜𝓮𝓷𝓽𝓮 ²⁵, 02:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 21:44:41 እንኳን ለሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ


 ድርሳነ ሚካኤል ዘወርሃ ሰኔ
በእስክንድርያ ሃገር እግዚአብሔርን የሚፈራ አንድ ሰው ነበር በየወሩም የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ ያደርግ ነበር ጎረቤቱም አንድ ክፉ ባለጠጋ ነበር ይህ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ በሚያደርግበት ጊዜ ያ ባለጠጋ ግን በሰውየው ላይ ይዝትበት ነበር
ይህ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰውም እንደሚሞት ባወቀ ጊዜ ለባለቤቱ የመልአኩ የቅዱስ ሚካኤልን ዝክር እንዳታቋርጥ ነገራት በተለይም በህዳር 12 እና በሰኔ 12 በልዩ ዝግጅት የቅዱስ ሚካኤልን በዓል እንድታደርግ አዘዛት
ከዚህ በኋል ያ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው አረፈ እርሱ ባረፈበት ወራት ባለቤቱ ፀንሳ ነበር የመውለጃዋ ቀን ደርሶ በምጥ ተያዘች መከራውም እጅግ ፀናባት ወደ ቅዱስ ሚካኤል አሰምታ ጮኸች ይህንንም እንደተናገረች ያለችበት ቤት በብርሃን ተሞ ላ ከጭንቋ ድና መልኩ ያማረ ወንድ ልጅንም ወለደች የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ሚካኤልም ከሰማይ ወረደ የወለደችውንም ህፃን ባረከው እናቱንም እንዲህ አላት ይህ ብላቴና ምህረት ከሌለው የጎረቤትሽን የዚህንባለፀጋ ገንዘብ ሃብቱን ንብረቱን ሁሉ ይወርሳል ብሏል እግዚአብሔር አላት ታዲያ ይህ ሁሉ ሲሆን ያ ባለፀጋ በሴቲቱ ቤት መስኮት በኩል ሆኖ ይመለከት ነበርና ይህን ሲሰማ ተቆጣ ብላቴናውንም ለመግደል ምክንያትን ይፈልግ ጀመር ከእለታት አንድ ቀንም እድሜው 10 ዓመት ሲሆን የእናቱ ገንዘብ አለቀ ያም ባለጸጋ የሴቲቱን ችግር አይቶ ልጅሽን እንዳሳድገው ስጪኝ እኔ አበላዋለሁ እኔ አለብሰዋለሁ ላንቺም 20 ወቄት ወርቅ እሰጥሻለሁ አላት ያችም ሴት ከባለጸጋው ይህንን ስትሰማ ተቸግራ ስለነበር ደስ አላት ባለጸጋውም 20 ወቄት ወርቅ ሰጣት እርሷም ልጅዋን ሰጠችው ከዚህ በኋላ ብላቴናውን እንዴት መግደል እንዳለበት ያሴር ጀመር በብላቴናው ቁመት ልክ ሳጥን አሰርቶ ብላቴናውን ከሳጥን ከቶ ቆልፎ ከባህር ውስጥ ወረወረው ያ ሳጥን ግን በእግዚአብሔር ፈቃድ ወደ አንድ የባህር ወደብ ደረሰ አንድ ሰውም በጎቹን አሰማርቶ እየጠበቀ ሳለ ከባህሩ አጠገብ አንድ ሳጥን ከባህሩ ላይ ተንሳፎ አየ ሳጥኑንም ከባህሩ ካአወጣው በኋላ እንዴት እንደሚከፍተው ያስብ ያሰላስል ጀመር
ሳጥኑንም ወደ ቤቱ ይሆት ሔደ በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር ይህንን ሰው ዳግመኛ ወደ ባህር እንዲሄድ አዘዘው ፈጥኖም ወደ ባህር ሔደ በዚያም አንድ አሣ አጥማጅ አገኘ ይህም ሰው ለአሣ አጥማጁ መረቡን ስለእርሱ እንዲጥለው አዘዘው አጥማጁም እንዳዘዘው አደረገ ትልቅም አሣ ያዘ ለአሣ አጥማጁም ዋጋውን ሰጥቶ ወደ ቤቱ ይዞት ተመለሰ አሣውንም ለማዘጋጀት ፈልጎ ሲቀደው የሳጥኑን መክፈቻ አገኘ የእግዚአብሔ ር ስራው ድንቅ ነውና ሳጥኑን ለመክ ፈት ሲሞክር ፈጥኖ ተከፈተ በሣጥኑ ውስጥም ያ ክፉ ባለጸጋ የጥለው ብላቴና አገኘ የበግ ጠባቂው ፈጽሞ ተደነቀ ልጅም ስላልነበረው እጅግ በጣም ተደሰተ ብላቴናውንም ከባህር ስላገኘው ባህራን አለው በግ ጠባቂውም ልክ እንደ ልጁ አድርጎ አሳደገው ተንከባከበው
ከብዙ ጌዜ ቆይታ በኋላ ያ ጨካኝ ባለጸጋ ለንግድ ወደ ሩቅ ሃገር ለመሔድ መንገድ ጀመረ ከአንድ የባህር ወደብ ሲደርስ ፀሐይ ጠለቀችበት በባህሩም አጠገብ ባህራንን ያገነውን የበጎች ጠባቂ አገኘው ወደ እርሱም ተጠግቶ ማደሪያ ካለው እንዲያሳድረው ለመነው የበግ ጠባቂውም እንግዳውን በክብር ወስዶ አሳደረው በቤቱም ሳሉ በግ ጠባቂው ባህራን ባህራን ብሎ ሲጣራ ያ ባለጸጋ ሰማና ልጅህ ነው? ሲል ጠየቀው በግ ጠባቂውም አዎን ልጄ ነው ህፃን ሳለ ከባህር ስላገኘሁት ስሙን ባህራን አልኩት አለው
ባለጸጋውም ወደባህር የጣለው ህጻን መሆኑን አውቆ በልቡ እጅግ ተበሳጨ ዳግመኛም ብላቴናውን እንዴት መግደል እንዳለበት ያሴር ጀመር ለበግ ጠባቂውም ይህንን ብላቴና ወደቤቴ ልላከው የረሳሁት እቃ ስላለ ያምጣልኝ ለአንተ 20 ወቄት ወርቅ እሰጥሃለሁ አለው የበግ ጠባቂውም ስለሚሰጠው ወርቅ ተደስቶ ባህራንን ጠርቶ ይህ የከበረ ሰው ወደቤቱ ሊልክህ ነውና ተላከው አለው
ባህራንም ትዕዛዙን በእሺታ ተቀብሎ ባለጸጋው የሰጠውን ደብዳቤ ይዞ መንገድ ጀመረ ባለጸጋው የፃፈውም ደብዳቤ እንዲህ ይል ነበር ይህ ደብዳቤ በተነበበ ጊዜ ያመጣት ስሙ ባህራን የተባለውን ሰው ገድለህ ከጉድጓድ ጣለው ይህንንም ነገር ማንም እንዳያውቅ ብሎ ወደ ሱሙ ላከ በደብዳቤውም መጨረሻ በመካከላቸው ያለውን ምልክት ፃፈበት ባህራንም የሞቱን ደብዳቤ በእጁ ጨብጦ ወደተላከበት ሃገር ሄደ
በመንገድም ሳለ ቅዱስ ሚካኤል የንጉሱን መልዕክተኛ መስሎ በነጭ ፈረስ ላይ ተቀምጦ ወደ ባህራን መጣ እንዴት አደርክ? ወዴት ትሄዳለህ? ምንስ ይዘሃል? አለው ባህራንም አንድ ባለጠጋ ወደቤቱ ልኮኛል የመልዕክትም ደብዳቤ ይዣለሁ አለው ቅዱስ ሚካኤልም ደብዳቤውን አሳየኝ አለው ባህራንም ያቅዱስ ሚካኤልን ግርማውን ፈርቶ በእጁ ያለውን ደብዳቤ አሳየው ቅዱስ ሚካኤል እፍ ሲልበት ያባለፀጋው ደብዳቤ ተቀየረ እንዲም ሆነ እኔ ባለጸጋው እገሌ ነኝ ይህን ደብዳቤ የያዘው ሰው ወደ እናንተ ልኬዋለሁ እገሊት የምትባል ልጄን ዳሩት ገንዘቤን ሁሉ ሰጥቼዋለሁ በቤቴ የወደደውን ያድርግ እኔ በንግድ እቆ ያለሁና አትጠብቁኝ በእኔና በእናንተ መካከል ይህ ምልክት ነው የሚል ነበር
ከዚህ በኋላ ቅዱስ ሚካኤል ባህራንን ወደ ባለጸጋው ቤት ሂድ እኔ መንገድ እንዳገኘሁህ አትናገር ይህንንም ደብዳቤ ለታዘዝከው ስጥ አለና ከፊቱ ተሰወረ ባህራንም ወደተላከው ሹም ሄደ ደብዳቤውንም ሰጠው ሹሙም ደብዳቤውን ካነበበ በኋላ በንጉሱና በእርሱ መካከል ያለውን ምልክት አየ።ከዚህ በኋል ለባህራን ሰርግ ታላቅ ዝግጅት ተደረገ ከባለጸጋውልጅ ጋር በእግዚአብሔር ቤት በሥርዓተ ተክሊል አጋቡት የሰርጉንም ደስታ ምክንያት በማድረግ 40 ቀን ተቀመጡ ሰርጉም ካለፈ በኋላ ያ ባለጸጋ ወደቤቱ ተመለሰ በመንደሩም የደስታ ድምጽ ሰምቶ ምንድነው የምሰማው ብሎ ጠየቀ ሰዎችም ባህራን በሚል ልጅ ደብዳቤህ ስለደረሰን ልጅህን እንዲያገባ ሃብትህን ንብረትህን እንዲወርስ ስላዘዝከን ትዕዛዝህ ሁሉ ተፈጽሟል እንሆ ደስታ ስናደርግ 40 ቀን አለፈ አሉት
በዚህን ጊዜ ያ ክፉ ባለጸጋ በታላቅ ቃል ጮኸ ከመሬት ላይ ወድቆ ሞተ

የሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ተራዳይነት አይለየን

< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >

    
584 views𝓜𝓮𝓷𝓽𝓮 ²⁵, 18:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-16 06:44:26 እኔስ እሱን ለማለት የቱ አቅም ኖሮኝ
ከውልደት እስከ ሞት ይኸው አለ አብሮኝ
አባትነትን በ'ራሱ እናትነትን በ'ናቱ
አ'ርጎ አሳይቶኛል በ'ሷ ወላዲቱ
የጌቶች ጌታ ነው የአምላኮች አምላክ
ሁሉ የሱ ሆኖ ነው እኔ እሱን 'ማመልክ
ምስጢሬን ነግሬው ይደብቅልኛል
ኃጥያቴን አይቶ ይቅርም ይለኛል
አልወድህም ብዬው እሱ ይወደኛል
እራሱን ሰውቶ እኔን አኑሮኛል
ስጨነቅ ተንፍሼ 'ምገላገልበት
ስደሰት ፈንድቄ ተመስገን 'ምልለት
ከላይ የተሰጠኝ አለኝ ክቡር አባት
የፍቅርን ጥግ በ'ሱ አያለሁ
ከሱ ውጪ እኔ ምንም ነኝ ብያለሁ
የጌታዬ ፍቅር ከማንም በላይ ነው
በሱ ተፈጥሬ በሱ እኖራለው
'ምለው የለኝም ተመስገን ብቻ ነው!!!

ሀዊ አስመራ


@Melikt_weg_gitim
@Melikt_weg_gititm

#join and #share
605 views𝓜𝓮𝓷𝓽𝓮 ²⁵, 03:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-14 06:07:11 እስካሁን ዘጠና ዘጠኝ ሰዎች ገድያለሁ አንተ መቶኛው ትሆናለህ!

አንድ ካህን በሞቃታማ ዕለት ብቻቸውን ጭር ባለ ጎዳና ላይ ሲሔዱ አንድ መሣሪያ ያነገተ የሚያስፈራ ሰው ድንገት ከዛፎች መሃል ዘልሎ ወጣና ከፊታቸው ቆመ።

ቄሱ ላይ አፍጥጦ "እስካሁን ዘጠና ዘጠኝ ሰዎች ገድያለሁ አንተ መቶኛው ትሆናለህ!" አላቸው።

ካህኑም መልሰው "ለመሞት ዝግጁ ነኝ ፣ ነገር ግን በጣም ስለጠማኝ ትንሽ ውኃ ሥጠኝና ትገድለኛለህ" አሉት። ነፍሰ ገዳዩ ለአፍታ ግራ ከተጋባ በኋላ በቄሱ ላይ መሣሪያውን እንደደገነ በዛፎቹ መካከል ካለው ምሽጉ ውስጥ በኩባያ ውኃ አምጥቶ እንዲጠጡ ሠጣቸው።

ካህኑ ውኃውን እየጠጡ እያለ ግን ሽፍታው ድንገት በልብ ድካም ሕይወቱ አለፈች።

የዚህን ሰው ነፍስ ወደ ገነት ለመውሰድ መላእክት በመጡ ጊዜ አጋንንት ነፍሱ የእኛ ፈንታ ናት ብለው ተከራከሯቸው። "ይህ ሰው ዘጠና ዘጠኝ ሰዎችን የገደለ ሲሆን እጅግ ብዙ ትንንሽ ኃጢአቶችንም ፈጽሟል። ነፍሱ የሚገባው ለእኛ ነው" አሉ።

መላእክቱ ግን እንዲህ ብለው ለአጋንንቱ መለሱላቸው "ያደረገው እንዳለ ሆኖ ይህ ሰው ከሠራቸው ኃጢአቶች የበለጠ የሚመዝኑ በክርስቶስ ወንጌል የታዘዙ ሁለት ታላላቅ ተግባራትን ፈጽሟል። የመጀመሪያው ዘጠና ዘጠኝ ሰው እንደገደለ ለካህን መናዘዙ ሲሆን ሁለተኛው ለተጠማ ውኃ ማጠጣቱ ነው!" አሏቸው።

የትኛውንም ያህል ቢደጋገም እንኳን ከእግዚአብሔር ምሕረት ሊበልጥ የሚችል ኃጢአት የለም!

ቅዱስ ኒኮላይ ቬሊሚሮቪች (St. Nicholai Velimirovich)
ምንጭ: Anicent Christian Wisdom

ትርጉም: ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
798 views𝓜𝓮𝓷𝓽𝓮 ²⁵, 03:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-11 07:12:18 በዓለ ጰራቅሊጦስ

‹‹ወላጆች እንደሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም›› /ዮሐ. 14፥18/
ጰራቅሊጦስ፡- ቃሉ ግሪክ ነው፡፡ ጰራቅሊጦስ ማለት መጽንኢ በእምነት የሚያጸና፣ መንጽሒ ከኃጢአት የሚያነጻ፣ ናዛዚ ያዘኑትን የሚያረጋጋ፣ መስተፍስሒ፣ የተጨነቁትን የሚያስደስት፣ ከሣቲ ምስጢርን የሚገልጽ ማለት ነው፡፡ 
ጰራቅሊጦስ፡- መንፈስ ቅዱስ ነው፡፡ የጰራቅሊጦስ በዓል ታሪክ እንደሚከተለው ተገልጿል፡፡ 
ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዓለም የሚሠራውን ሥራ ከጨረሰ በኋላ ቅዱሳን ሐዋርያትን ወደ አባቴ እሄዳለሁ (አርጋለሁ) ሲላቸው ደነገጡ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስም መደንገጣቸውን አይቶ ‹‹ኢይደንግድክሙ ልብክሙ እመኑ በእግዚአብሔር ወእመኑ ብየ እስመ ውስተ ቤተ አቡየ ብዙኅ ማኅደር ወምዕራፍ ቦቱ›› (ልባችሁ አይደንግጥባችሁ በእግዚአብሔር እመኑ በእኔም እመኑ በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ ማለት ባባቴ ቤት በመንግሥተ ሰማያት ብዙ ማዕርገ ሀብታት አለ) /ዮሐ. 14፥1)
እንዲሁም /በዚሁ በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 14፥18/ ላይ እንደተጻፈው ‹‹ኢየጎድገክሙ ዕጓለ ማውታ ትኩኑ›› (ወላጆች እንደሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም) ሲል መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱሳን ሐዋርያትን አጽናንቷቸዋል፡፡ 
/በሉቃስ ወንጌል 24 ቁጥር 49/ ላይ እንደተጻፈው የሰላም አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ ሊያርግ ሲል ቅዱሳን ሐዋርያትን ‹‹አንትሙሰ ንበሩ ሀገረ ኢየሩሳሌም እስከ ትለብሱ ኃይለ እምአርያም›› (እናንተ ግን ከላይ ኃይልን እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ተቀመጡ) አላቸውና ዐረገ፡፡ እነርሱም ይህን አምላካዊ ቃል መሠረት በማድረግ በኢየሩሳሌም በጽርሐ ጽዮን በማርቆስ እናት በማርያም ቤት ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው ተሰብስበው ሳሉ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአረገ በአሥረኛው ቀን በተነሣ በሃምሳኛው ቀን የጰራቅሊጦስ እለት ጧት በሦስት ሰዓት ለቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ በእሳት አምሳል ወረደላቸው ከዚህ በኋላ ፍርሃት ከውስጣቸው ወጣ መንፈሳዊ ድፍረት አገኙ፡፡ አንድ የዕብራይስጥ ቋንቋ ብቻ ነበር የሚያውቁት ሰባ አንድ ዓይነት ቋንቋ (የአገሩ ሁሉ ቋንቋ) ተገለጸላቸው፡፡ ከእነርሱ ጋር በሰባ ሁለት ዓይነት ቋንቋ ተናገሩ፡፡ የአገሩ ሁሉ ቋንቋ የተገለጸላቸውም ሁሉንም በአገሩ ቋንቋ እንዲያስተምሩ ነው፡፡ ከተለያየ ክፍለ ዓለም የመጡ ነበሩ፡፡ እነዚህ የገሊላ ሰዎች አይደሉምን? እንዴት የእኛን አገር ቋንቋ ሊናገሩ ቻሉ? በማለት ተገረሙና አመንትተው እርስ በርሳቸው እንጃ ይህ ምን ይሆን? አሉ፡፡ ሌሎች ግን ጉሽ የወይን ጠጅ ጠጥተው ሰክረው ነው አሉ  ነገር ግን 
ቅዱስ ጴጥሮስ ከአሥራ አንዱ ጋር ቆመ ድምፁንም ከፍ አድርጎ እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፡- የይሁዳ ሰዎች በኢየሩሳሌምም የምትኖሩ ሁላችሁ፡- ይህ በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን ቃሎቼንም አድምጡ፡፡ ለእናንተ እንደመሰላችሁ እነዚህ የሰከሩ አይደሉም ከቀኑ ገና ሦስተኛ ሰዓት ነውና ነገር ግን ይህ በነቢዩ ኢዩኤል የተነገረው ይፈጸም ዘንድ ነው፡- ይህም ‹‹እግዚአብሔር ይላል በኋለኛይቱ ቀን እንዲህ ይሆናል ሥጋ በለበሰ ሁሉ ላይ ከመንፈሴ አፈሳለሁ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁም ትንቢት ይናገራሉ ጎበዞቻችሁም ራእይ ያያሉ ሽማግሌዎቻችሁም ሕልም ያልማሉ ደግሞም በዚያች ወራት በወንዶችና በሴቶች አገልጋዮች ላይ ከመንፈሴ አፈሳለሁ ትንቢትም ይናገራሉ፡፡ ድንቆችንም በላይ በሰማይ ምልክቶችንም በታች በምድር ደምም፣ እሳትም የጢስ ጭጋግም ይሆናል የታወቀችዋም ታላቅዋ የእግዚአብሔር ቀን ሳትመጣ ፀሐይ ወደ ጨለማ ጨረቃም ወደ ደም ይለወጣል የእግዚአብሔርን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል›› /ኢዩ. 2፥28-32/ ይህን መሠረት በማድረግ ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ ልብን የሚነካ ትምህርት ሰጠ፡፡ ሕዝቡም ቅዱስ ጴጥሮስ በሰጠው ትምህርት ልባቸው ተነካ ቅዱስ ጴጥሮስንና ሌሎቹንም ሐዋርያት ወንድሞች ሆይ ምን እናድርግ? አሉአቸው፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስም ንስሐ ግቡ ኃጢአታችሁም ይሠረይ ዘንድ ተጠመቁ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ፡፡ የተስፋው ቃል ለእናንተና ለልጆቻችሁ አምላካችንም ወደ እርሱ ለሚጠራቸው በሩቅ ላሉ ሁሉ ነው 
ስለዚህ ራሳችሁን ከዚህ ክፉ ዓለም አድኑ ብሎ መከራቸው፡፡ በዚህ ቀን ሦስት ሺህ ሰዎች አምነው ተጠመቁ፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ተቀብለው የሞቱና የትንሣኤው ምስክሮች ሆኑ፡፡ የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ በነሱ ላይ ሲያድር ለቤተክርስቲያን ጉዞ አዲስ ምዕራፍ ተከፈተ፡፡ ይህ የጰራቅሊጦስ በዓል በግሪኮች ቋንቋ ጰንጠቆስጤ ይባላል፡፡ ጰንጠቆስጤ ማለት ሃምሳኛ ማለት ነው፡፡ ጌታችን ከተነሣ በኋላ ሃምሳኛው ቀን ነው፡፡ ይህም ዕለት በዓለ ሃምሳ፣ በዓለ ጰራቅሊጦስ ነው፡፡ 
እንዲሁም ታላቁ ሊቅ ቅ/ዮሐንስ አፈወርቅ ይህን በዓል በሚገባ አነጋገር ‹‹የቤተክርስቲያን የልደት ቀን›› ብሎታል፡፡ ይህ በዓል በብሉይ ኪዳን የእሸት በዓል (በዓለ ሰዊት) ይባላል፡፡ እስራኤል የነጻነት በዓላቸውን ከሚያከብሩበት ከበዓለ ፋሲካ ጀምረው ሃምሳውን ቀን በዓል አድርገው ይሰነብታሉ፡፡ በሃምሳኛው ቀን በዓለ 
ሰዊትን (የእሸት በዓላቸውን) ያከብራሉ፡፡ በሀገራቸው ከመጋቢት እስከ ግንቦት ያለው ወቅት በሀገራችን ከመስከረም እስከ ኅዳር እንዳለው የእሸት ወራት (የጸደይ ወራት) ነውና የእሸት በዓላቸውን የሚያከብሩት በኦሪት ዘሌዋውያን /ምዕራፍ 23፥10-17/ በታዘዘው መሠረት ማንኛውም እሥራኤላዊ ገበሬ ከዘራው ሁሉ በያይነቱ እሸቱን ቆርጦ ተሸክሞ ወደ ምኩራቡ ይመጣል፡፡ በቤተ መቅደስ 
የሚያገለግለው ካህን ተቀብሎ ባርኮ ጸልዮ የሚጠበሰው እየተጠበሰ የሚታሸው እየታሸ በማኅበር አንድነት ይበላል፡፡ ይህም ‹‹ቀዳምያት›› ይባላል፡፡ የመጀመሪያው ማለት ነው፡፡ ከማንኛውም በረከት የመጀመሪያው እግዚአብሔር ፊት መቅረብ፣ ለእግዚአብሔር መሰጠት እንዳለበት ታዟልና፡፡ 
በዚህ መሠረት ከበዓለ ጰራቅሊጦስ የምንማረው፡-ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱሳን ሐዋርያትን ‹‹እናንተ ግን ከላይ ኃይልን እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ተቀመጡ›› ባላቸው መሠረት በኢየሩሳሌም ተቀምጠው ተስፋውን ሲጠባበቁ መንፈስ ቅዱስ ወርዶላቸዋል፡፡ ዛሬ መንፈስ ቅዱስ የሚወርድባት ኢየሩሳሌም ቤተክርስቲያን ናት ‹‹ ሚ መጠን ግርምት ዛቲ ዕለት ወዕፅብት ዛቲ ሰዓት እንተ ባቲ ይወርድ መንፈስ ቅዱስ እመልዕልተ ሰማያት››     (ይህች ቀን ም ያህል የምታስፈራ ናት? ይህች ሰዓት ምን  ያህል የምታስጨንቅ ናት? መንፈስ ቅዱስ ከሰማየ ሰማያት የሚወርድባት) /ሥርዓተ ቅዳሴ/ ለቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ እንደ ወረደላቸው ለእኛም እንዲወርድልን ሁልጊዜ ቤተ ክርስቲያን መሄድ ይገባል፡፡ ከቤተክርስቲያን ተለይቶ ጽድቅ የለም
ቤተ ክርስቲያን፡- የመንግሥተ ሰማያት በር ናት ‹‹ዛቲ ይእቲ ኆኅታ ለሰማይ›› (ይህች የሰማይ ደጅ ናት) /ዘፍ 28፥17/
በዚህ መሠረት ለእኛም በ40 ቀንና በሰማንያ ቀን የተሰጠን ጸጋ መንፈስ ቅዱስ እንዳይለየን ሕጉን ትእዛዙን መጠበቅና ጧት ማታ ወደ ቤተ ክርስቲያን መገስገስ ይገባል፡፡ 
ለዚህም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እንዲሁም ቅዱሳን በአማላጅነታቸው ይርዱን፡፡ 
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፡፡
1.0K views𝓜𝓮𝓷𝓽𝓮 ²⁵, 04:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 07:28:03 " ሰይጣነ ጽርፈት "

. 'ሰይጣነ ጽርፈት' ማለት ስድብን የሚያናግር ሰይጣን ማለት ነው፤

. ይኽ ሰይጣን ዋናው ሥራው፣
ሰው ሰውን እንዲሰድብ እና እንዲያዋርድ፣

ከዚያም ሲያልፍ በእግዚአብሔር እና በቅዱሳኑ ላይ የስድብን ቃል እንዲናገር ማድረግ ነው።

. በመጀመሪያ በቀልድ መልክ የተለያየ ስድብን እንድንሰዳደብ በማድርግ ያለማምደናል፤

. ብዙዎቻችን ጨዋታን፣
የመቀራረብ ምልክት ወይም
የፍቅር መግለጫ አድርገን ስለምናስብ፣ ኀጢአት አድርገን አንወስደውም።

. ከዚያም ጊዜያዊ ቊጣን ምክንያት በማድረግ ይኽንኑ የስድብ ኀጢአት፣ የቅርብ በምንላቸው ሰዎች ላይ እንድንናገር በማድረግ፣ አንድ ደረጃ ከፍ ያደርገዋል።

. ብዙዎቻችን በዚኽ ጊዜ ጭምር ንስሓ መግባት እንዳለብን አናስብም።

. ከዚያ ከፍ ሲል ኹለን ማዋረድ እና መሳደብ እንለማመዳለን፤

. ለእግዚአብሔር ክብር የሚሰጡትን ደግሞ፣ ጸሎት ሲጸልዩ፣ ቅዱሳት መጻሕፍትን ሲያነቡ፣ ለቅዳሴ ሲቆሙ፣ በቅዱሳት ሥዕላት ፊት ሲቆሙ፣ ... በኅሊናቸው የስድብን ነገር እያመጣ ያስደነግጣቸዋል፤ ያሰጨንቃቸዋል።

. ይኽ ኹሉ የሚያደረግ የጸሪፍ ሰይጣን ነው።

የጽርፈት/የስድብ/ሰይጣን እንዲጠጋ ምክንያት የሚኾኑ፦
ትዕቢት፣ ቁጣ፣ ንቀት፣ ፌዘኝነት፣ መማረር፣ ምስጋና ቢስ መኾን፣ በሌሎች ላይ መፍረድ፣ ለእግዚአብሔር እና ለቅዱሳኑ ክብር ከማይሰጡ ሰዎች ጋር ጓደኝነት እና ጽሑፎቻቸውን ማንበብ፣ ... ወ.ዘ.ተ.፤

መፍትሔ፦
የቀደመ ስህተት ካለ መርምሮ ንስሓ በመግባት፣
ውሏችን እና ጓደኝነታችንን መመርመር፣ የምናነባቸውን እና የምናያቸውን ነገር መምረጥ፣
ራስን መግዛት፣
አመስጋኝ መኾን፣
ምክረ አበውን በመቀበል የተለየ ጾም እና
ጸሎት መያዝ፣ ...
የመሳሰሉት ይገኙበታል።

[ "ራእየ ኒፎን" ትርጒም በቀሲስ ታምራት ውቤ፤ ፳፻፲፫ ዓ.ም.፤ ገጽ ፴/30፤ ]
642 views𝓜𝓮𝓷𝓽𝓮 ²⁵, 04:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-07 06:21:52 +++ "እግዚአብሔርን አልፎ ወደ እግዚአብሔር ጉዞ" +++

ጌታችን ስለ በጎ ባልንጀራ ተጠይቆ ለዚያ መልስ እንዲሆን በሰጠው ምሳሌ ላይ ያሉት ሁለቱ ሰዎች (ካህኑና ሌዋዊው) ያስገርማሉ። እነዚህ ሰዎች በመቅደሱ የሚያገለግሉ ሲሆኑ ቆስሎ የወደቀውን ታማሚ ያዩት ካህኑ የመቅደስ አገልግሎቱን ፈጽሞ ወደ ኢያሪኮ ሲወርድ ሌዋዊው ደግሞ ገና ለአገልግሎት ወደ ቤተመቅደስ ሲሄድ ሳይሆን አይቀርም።(ሉቃ 10፥30-35) ከቤተ መቅደስ የወጣውም ወደ ቤተ መቅደስ የሚሄደውም ያን በሽተኛ አይቶ ገለል ብሎት አለፈ።

ለምን? ከመቅደስ የወጣው ለእግዚአብሔር የሚገባውን አገልግሎት ጨርሻለሁ ብሎ ስላሰበ፣ ወደ መቅደስ የሚሄደው ደግሞ የወደቀውን ሲረዳ የምስጋና ሰዓቱ እንዳይታጎልበት ሰግቶ እንደ ሆነስ? ማን ያውቃል?!

ብቻ "ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁ ለእኔ አደረጋችሁ" በማለት የተናገረውንና ከታማሚው ጋር ያለውን እግዚአብሔር መንገድ ላይ ጥለው እግዚአብሔርን ለማመስገን ወደ ቤተ መቅደስ ሄዱ።

እግዚአብሔርን አልፎ ወደ እግዚአብሔር መሄድ የሚሉት ፈሊጥ ምን ዓይነት ይሆን?

ወደ ቤተ መቅደስ ስንሄድ ወይም ከቤተ መቅደስ ስንመለስ ስንት ጊዜ እግዚአብሔርን ገለል ብለን አልፈነው ሄድን?

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
654 views𝓜𝓮𝓷𝓽𝓮 ²⁵, 03:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ