Get Mystery Box with random crypto!

መንፈሳዊ ግጥሞች እና ወጎች

የቴሌግራም ቻናል አርማ melikt_weg_gitim — መንፈሳዊ ግጥሞች እና ወጎች
የቴሌግራም ቻናል አርማ melikt_weg_gitim — መንፈሳዊ ግጥሞች እና ወጎች
የሰርጥ አድራሻ: @melikt_weg_gitim
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.16K
የሰርጥ መግለጫ

✞ ይህ ቻናል መንፈሳዊ የሆኑ ግጥሞች ፣ ወጎች እንዲሁም መልዕክቶች የሚቀርቡበት ነው ✞
አስተያየት ካለ እንዲሁም ግጥም ወግ እንዲተላለፉ የምትፈልጓቸው መንፈሳዊ መልክቶች ለማድረስ https://t.me/ a3-5g5CslOkwNjBk ተጠቀሙ

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-07-22 06:53:22 #ምነው



በፈጣሪ አምሳል የተበጀን ገላ፣
ህይወቱ እንድታልፍ በቃታ በቢላ፣
ካሰቃዩት ዃላ፣
የመዳንን ምስጢር ፍቅርን ወዲያ ጥለው፣
ቤንዚን አርከፍክፈው በቁም ሳለ አቃጥለው፣
ሞቶ ያሸነፈን ያን መሲሕ ዘንግተው፣
የተሰጣቸውን ህያው ቃሉን ትተው፣
ግዳይ እንደጣሉ ደረት እየነፉ፣
ጎምለል ቀብረር ብለው በአደባባይ ሲያልፉ፣
ከትቢያ ተናንሶ የሰው ሰውነቱ፣
ሀገሬ ላይ ባየው ባ'ይኔ በብረቱ፣
የወገኔ ሲቃ ከአርያም ሲደርስ አድማስ ሲያስተጋባ፣
ወደ ውስጤ አልቅሶ ልቤም የደም ዕምባ፣
እንደዚህ የሚቀኝ መልስ ያጣ ጥያቄ ከነፍሴ ውስጥ ገባ።


እንዲህ ይላል ጥያቄው፣
መልሱን ምን አውቄው?


እስኪያስረሳን ድረስ የመቅደሱን እጣን፣
እውን ግን ሚያባላን ስልጣንነው ወይሰይጣን?

አትናቴዎስ ስሜ



@Melikt_weg_gitim
@Melikt_weg_gititm

#join and #share
687 views𝓜𝓮𝓷𝓽𝓮 ²⁵, 03:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 20:03:47 ሴት በወር አበባዋ ጊዜ መጸለይ ትችላለች
ግለ አውናን / ሴጋ /ማስተርቤሽን/ የፈጸመ ሰው ተክሊል ማግባት ይችላልን
በሱባኤ ወቅት ህልመ (ዝንየት) ቢመታን ምን እናደርጋለን በሕልመ
ሕልመ ሌሊት በራሱ ኃጢአት ነውን
ሕልመ ሌሊት በምን ይከሰታል
ሌሊት ከዝሙት አጋንንት እና ከዝንየት በተጨማሪ ሌሊት የሚፈትነን አጋንንት የትኛው ነው
የሕልመ ሌሊት መፍትሔ ምንድን ነው
ቁርባን ቆርበን ሕልመ ሌሊት እንዳይጸናወተን ምን ማድረግ አለብን

በእነዚህ ትምህርቶች ዙርያ እየተማማርን እንገኛለን እርሶም እውቀቱ እንዲኖርዎ ከፈለጉ ይህን መስፈንጠርያ ይንኩ


█▓▒░► 𝑶𝑷𝑬𝑵 ░ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ▒▓█
█▓▒░► 𝑶𝑷𝑬𝑵 ░ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ▒▓█
█▓▒░ ► 𝑶𝑷𝑬𝑵 ░ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ▒▓█
█▓▒░► 𝑶𝑷𝑬𝑵 ░ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ▒▓█

ይቱብ ቻናላችን ብሰብስክራይብ ሼር ያድርጉ

ምልዕተ ፀጋ ጥዕውም ዝማሬ






ለጥያቄዎመልስ አዲስ ስብከት




















ኦርቶዶክሳዊ ህይወት
የነፍሴ ጥያቄዎች
ማህተቤ ክብሬ ነው
ናታኒም ቲዩብ
𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 ‌‌
21 viewsማኔ ቴቄል ፋሪስ, 17:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 13:02:01 ሐምሌ 7

ቅድስት ሥላሴ በአብርሃም ቤት

ሐምሌ ሰባት በዚች ቀን ሥሉስ ቅዱስ በአብርሃም ቤት የተገለጠበት ነው፡፡ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በስም በአካል በግብር ሦስትነት በባሕርይ በሕልውናና በፈቃድ አንድነት የጸኑ ናቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ተገኙ፣ በዚህ ጊዜ ያልፋሉ አይባሉም መጀመሪያም መጨረሻም እነርሱ ናቸውና፡፡ ርሕሩሐን ናቸውና በእናት ሥርዓት ‹‹ቅድስት ሥላሴ›› እንላቸዋለን፡፡
የሚጠላቸው (የማያምንባቸውን) አይጠሉም፡፡ የሚወዳቸውን ግን እጽፍ ድርብ ይወዱታል፣ በቤቱም መጥተው ያድራሉ፡፡ ከፍጥረታት ወገን ከእመቤታችን ቀጥሎ የአብርሃምን ያህል በሥላሴ ዘንድ የተወደደ ፍጡር የለም፡፡ አባታችን ቅዱስ አብርሃም የደግነት ሁሉ አባት ነውና በኬብሮን በመምሬ ዛፍ ሥር ሥላሴን ተቀብሎ አስተናግዷል፡፡

አባታችን አብርሃም በ99 ዓመቱ እናታችን ሣራ በ89 ዓመቷ ሥላሴን በድንኳናቸው አስተናገዱ፡፡ አብርሃም እግራቸውን አጠበ፡፡ በጀርባውም አዘላቸው፡፡ ምሳቸውንም አቀረበላቸው፡፡ እነርሱም እንደሚበሉ ሆኑለት፡፡ በዚያው ዕለትም የይስሃቅን መወለድ አበሠሩት፡፡ አብርሃም ከደግነቱና እንግዳ ከመውደዱ የተነሣ በተመሳቀለ ጎዳና ላይ ድንኳን ሠርቶ የወጣ የመረደውን፣ የመጣ የሄደውን ሁሉ እየተቀበለ እግዚአብሔርን እያገለገለ የሚኖር ጻድቅ ነበር፡፡
ለዚህም ነው አብርሃም በወይራ ግራር (በመምሬ) ዛፍ ሥር ተቀምጦ ሳለ እግዚአብሔር አንድነቱን ሦስትነቱን የገለጠለት፡፡ ዘፍ 18፡1-25፣ ሮሜ 4፡-3፡፡ ቀትር ሰዓት ላይ በድንኳኑ ደጅ ተቀምጦ እንግዳ ሲጠብቅ እግዚአብሔር ታየው ተነጋገረው፡፡ አንገቱን ቀና አድርጎ ዐይኑን አራምዶ በተመለከተ ጊዜ እነሆ ሦስት ሰዎች ከበላዩ ባለ ተራራ ላይ ቆመው አያቸው፣ ወደ እርሱም ሲወርዱ አይቶ ፈጥኖ ሄዶ ከሰግደላቸው በኋላ ‹‹አቤቱ በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ እንደሆነ ባሪያህን አትለፈኝ ብዬ እለምናለሁ፤ ጥቂት ውኃ ይምጣላችሁ እግራችሁን ታጠቡ…›› እያለ በትሕትና በመጋበዝ ወደ ድንኳኑ አስገብቶ በሚገባ ጋበዛቸው፡፡ ‹‹በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ›› ብሎ አንድነታቸውን፣ ‹‹ጥቂት ውኃ ይምጣላችሁ እግራችሁን ታጠቡ›› ብሎ የሦስትነታቸውን ምስጢር ገልጾአል፡፡

ያች ሥላሴ የገባባት የአብርሃም ድንኳን የእመቤታችን ምሳሌ ናት፡፡ ሥላሴ ወደ አብርሃም ድንኳን እንደገቡ ሁሉ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያምም አብ ለአጽንዖ፣ መንፈስ ቅዱስ ለአንጽሖ፣ ወልድ በተለየ አካሉ ሥጋዋን ለመዋሐድ የማደራቸው ምሳሌ በመሆኑ አማናዊቷ የሥላሴ ማደሪያ የአብርሃም ድንኳን እመቤታችን ናት፡፡ ሉቃ 1፡35፡፡

እግዚአብሔርም አብርሃምን የዛሬ ዓመት ልጅ እንደሚወልድ ነግሮት በዓመቱ ይስሐቅን ወልዷል፡፡ ሁለቱ ሰዎች ከአብርሃም ድንኳን ወጥተው ወደ ሰዶም ወደ ገሞራ ሄዱ፣ አብርሃምም ይሸኛቸው ዘንድ አብሯቸው ሄደ፡፡ የሄዱትም ሁለቱ ሰዎች አብና መንፈስ ቅዱስ ናቸው፡፡ ነገር ግን አንዱ ወልድ በአብርሃም ቤት ቀርቷል ይኸውም ከቤተ አብርሃም ሰው እንደሚሆን ለማጠየቅ ነው፡፡ አብርሃምም ተመልሶ በእግዚአብሔር ፊት ቆመ፡፡ እግዚአብሔርም የሚሠራውን ሁሉ ከአብርሃም አይሠውርም ነበርና የሰዶምን የገሞራን ጥፋት ነገረው፡፡ አብርሃምም ይቅር እንዲላቸው አብዝቶ ለመነላቸው፡፡ ሥሉስ ቅዱስን የአብርሃሙ ሥላሴን በምግባር በሃይማኖት ሆነን እናገለግል ዘንድ የቅዱሳኑ ጸሎት ይርዳን!

➥የእኛንም ጓዳ ጎድጓዳ አጋዕዝት ዓለም ቅድስት ሥላሴ በምህረቱ የጎብኝልን አሜን
204 views𝓜𝓮𝓷𝓽𝓮 ²⁵, 10:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 05:23:34
ልቡናውን ሰብስቦ መጸለይ አልችል ያለው ሰው አንድ ታላቅ አባትን እንዲህ ሲል ጠየቃቸው ፦ "አባቴ! የጸሎት መጽሐፍ ይዤ ሳነብ ልቡናዬ አይሰበሰብልኝም፡፡ አፌ ቢያነብም ልቡናዬ አይተረጕምም፡፡ እርስዎ እንደነገሩኝ ደግሞ ቅዱሳን በፍጹም አሳባቸው እያሰቡና እያራቀቁ እንባንና ጸጸትን እየጨመሩ የደረሱትን እኛ በልባችን ሌላ እያሰብን በአፋችን ብቻ እንደነርሱ ብንናገር እንደ ገደል እንደ ዋሻ ሆነን በእግዚአብሔር እንደመቀለድ ነው፡፡ ጸሎትም አይሆንልንም፡፡ እንግዲህ ያፍ ጸሎቴ ቅድመ እግዚአብሔር የማይደርስ ከሆነ ጸሎቴን ብተወው ይሻላል ወይስ ባልተወው ይሻላል ? "

እርሳቸውም እንዲህ ሲሉ መለሱለት፦ "ዕውር ሰው በዘንጉ ምድር እየመታ ሲሄድ ከመንገድ ላይ ያለ እባብ ለጊዜው ድምጹን ሰምቶ ይመታኛል ብሎ እንደሚሸሽለት ሁሉ አንተም አስተውለህ ባትጸልይም ባፍህ ውስጥ የቃለ እግዚአብሔርን መንኳኳት እየሰሙ አጋንንት መሸሻቸው አይቀርምና ምንም ቅድመ እግዚአብሔር ባይደርስም ጸሎትህን አትተው፡፡ አጋንንትን ማባረርም ጥቅም ነውና፡፡ ብዙ ከምትጸልየውም አንዳንድ ጊዜ ልብህ የሚወድቅባት ቃል ተጠራቅማ ወደ እግዚአብሔር ትደርሰልሃለች ምንም ዝርወ ልብ ብትሆንም አፍህም ፍጥረቱ ነውና አንተው በዳይ አንተው አኵራፊ እንዳትሆን ባፍህም ብቻ ቢሆን መነጋገሩን አትተወው፡፡"
279 views𝓜𝓮𝓷𝓽𝓮 ²⁵, 02:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 23:39:31 ሴት በወር አበባዋ ጊዜ መጸለይ ትችላለች
ግለ አውናን / ሴጋ /ማስተርቤሽን/ የፈጸመ ሰው ተክሊል ማግባት ይችላልን
በሱባኤ ወቅት ህልመ (ዝንየት) ቢመታን ምን እናደርጋለን በሕልመ
ሕልመ ሌሊት በራሱ ኃጢአት ነውን
ሕልመ ሌሊት በምን ይከሰታል
ሌሊት ከዝሙት አጋንንት እና ከዝንየት በተጨማሪ ሌሊት የሚፈትነን አጋንንት የትኛው ነው
የሕልመ ሌሊት መፍትሔ ምንድን ነው
ቁርባን ቆርበን ሕልመ ሌሊት እንዳይጸናወተን ምን ማድረግ አለብን

በእነዚህ ትምህርቶች ዙርያ እየተማማርን እንገኛለን እርሶም እውቀቱ እንዲኖርዎ ከፈለጉ ይህን መስፈንጠርያ ይንኩ


█▓▒░► 𝑶𝑷𝑬𝑵 ░ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ▒▓█
█▓▒░► 𝑶𝑷𝑬𝑵 ░ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ▒▓█
█▓▒░ ► 𝑶𝑷𝑬𝑵 ░ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ▒▓█
█▓▒░► 𝑶𝑷𝑬𝑵 ░ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ▒▓█

ይቱብ ቻናላችን ብሰብስክራይብ ሼር ያድርጉ

ምልዕተ ፀጋ ጥዕውም ዝማሬ






ለጥያቄዎመልስ አዲስ ስብከት




















ኦርቶዶክሳዊ ህይወት
የነፍሴ ጥያቄዎች
ማህተቤ ክብሬ ነው
ናታኒም ቲዩብ
𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 ‌‌
252 viewsማኔ ቴቄል ፋሪስ, 20:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 20:04:32 ሴት በወር አበባዋ ጊዜ መጸለይ ትችላለች
ግለ አውናን / ሴጋ /ማስተርቤሽን/ የፈጸመ ሰው ተክሊል ማግባት ይችላልን
በሱባኤ ወቅት ህልመ (ዝንየት) ቢመታን ምን እናደርጋለን በሕልመ
ሕልመ ሌሊት በራሱ ኃጢአት ነውን
ሕልመ ሌሊት በምን ይከሰታል
ሌሊት ከዝሙት አጋንንት እና ከዝንየት በተጨማሪ ሌሊት የሚፈትነን አጋንንት የትኛው ነው
የሕልመ ሌሊት መፍትሔ ምንድን ነው
ቁርባን ቆርበን ሕልመ ሌሊት እንዳይጸናወተን ምን ማድረግ አለብን

በእነዚህ ትምህርቶች ዙርያ እየተማማርን እንገኛለን እርሶም እውቀቱ እንዲኖርዎ ከፈለጉ ይህን መስፈንጠርያ ይንኩ


█▓▒░► 𝑶𝑷𝑬𝑵 ░ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ▒▓█
█▓▒░► 𝑶𝑷𝑬𝑵 ░ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ▒▓█
█▓▒░ ► 𝑶𝑷𝑬𝑵 ░ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ▒▓█
█▓▒░► 𝑶𝑷𝑬𝑵 ░ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ▒▓█

ይቱብ ቻናላችን ብሰብስክራይብ ሼር ያድርጉ

ምልዕተ ፀጋ ጥዕውም ዝማሬ






ለጥያቄዎመልስ አዲስ ስብከት




















ኦርቶዶክሳዊ ህይወት
የነፍሴ ጥያቄዎች
ማህተቤ ክብሬ ነው
ናታኒም ቲዩብ
𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 ‌‌
258 viewsማኔ ቴቄል ፋሪስ, 17:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 06:33:07 #አንቺ_ትኖሪያለሽ

የኑፋቄ ትምህርት እንክርዳድ ቢዘራ
ያሸነፈ መስሎት አሕዛብ ቢያቅራራ
ወጀብ ቢወጅብም ቢነሳ ዐውሎ ነፋስ
ውቅያኖስ ቢያናውጽ ዛፍን ቢገረስስ
ንውጽውጽታ በዝቶ ቢሰማ ነጐድጓድ
ሜዳው ቢጥለቀለቅ ተራራውም ቢናድ
እልፍ ቢኮበልል ጥርጥሩ በዝቶ
ሚሊዮኑ ቢክድ መከራውን ፈርቶ
ወይም ሌላው ማስተዋል ቢያቅተው አዕምሮውን አጥቶ ብኩርናውን ንቆ ለምሥር ወጥ ጓጉቶ
ሊሸጥሽ ቢስማማ ሊኖር ሆዱን ሞልቶ።
የጥፋት ደመና ከሰማይ ቢያንዣብብ
ዝናቡ ቢዘንብ ወጀቡ ቢወጅብ
ምንም ቢመስላቸው የምትሰጥሚ በቅርብ
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አማናዊት መርከብ።
የእነ ጴጥሮስ እምነት ኰኵሐ ሃይማኖት
የቀጠቀጠባት የአርዮስን ክህደት
የተቀደሰችው የአትናቴዎስ እምነት
በፍጹም አትፈርስም ከቶም አትሞከር
የገፋሽ ሊወድቅ የቀሰጠሽ ሊያፍር
አፍራሽሽ ሊፈርስ ቀባሪሽ ሊቀበር
ቃል እንደገባልሽ አምላክሽ እግዚአብሔር
ትናንትን እንዳለፍሽ በወጀብ መካከል ክር
ላያቃጥል እሳት ሲንቀለቀል
ጸጥ እረጭ ሊል እሱ ሲቀሰቀስ ማዕበል
ቢነሳ ዐውሎ ነፋስ ቢነፍስ
በከሀዲ ክፋት ቢፈርስ መቅደስሽ
እሱ እንደፈረሰ አንቺ ግን እንዳለሽ
የዛሬው እንክርዳድ ወደ እሳት ተጥሎ
የዘመኑ ዑደት ሒደቱን ቀጥሎ
ጌታ እስከሚመጣ እስከ ምጽአት ድረስ
ስሙን እየቀደስሽ ክብሩን እያወረስሽ
አጥፊሽ እየጠፋ አንቺ ትኖሪያለሽ።

✞ወስብሐት ለእግዚአብሔር✞
✞ወለወላዲቱ ድንግል✞
✞ወለመስቀሉ ክቡር✞
✞አሜን✞


@Melikt_weg_gitim
@Melikt_weg_gititm

#join and #share
320 views𝓜𝓮𝓷𝓽𝓮 ²⁵, edited  03:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 08:35:58 #እንኳን_ደስ_አላችሁ


እውቀት እና ጥበብ ለማወቅ ሽታቹ
በእየድሜያቹ ልክ እጅጉን ለፍታቹ
ፈተና ፕሮፖዛል ፖሮጀክት አሳይመንት
ሪፖርትና ሪሰርች ስትሰሩ በትጋት
በቀራቹ ጊዜም ሳትሰላቹ ምንም
በስግደት በፀሎት ሱባኤና ፆም
ዘውትር የጠናቹ ወደ ፈጣሪያቹ
በአገልግሎት ጭምር እጅግ የተጋቹ
የድካማቹን ፍሬ አምላክ ቆጥሯልና
እንኳን ደስ አላቹ አልኩኝ እንደገና።


ከቃልኪዳን ተፈራ


@Melikt_weg_gitim
@Melikt_weg_gititm

#join and #share
604 views𝓜𝓮𝓷𝓽𝓮 ²⁵, 05:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 07:24:13 #የማርያም_ነን


ጥቂት አናልምም
መንገድ አንጀምርም
እኛ ያለማርያም
ሀቅ ህይወት የለንም
ክርስትና ማለት ተዋህዶ ሰምሮ
የአምላክ ሰው መሆን የህይወት ጅማሮ
አንቺ ማለት ለኛ
የሰላም ማህደር የፍቅር ማሰሮ
የነብሳችን እረፍት ከጥንትም ጀምሮ።

ማርያማዊት አማኑኤል


@Melikt_weg_gitim
@Melikt_weg_gititm

#join and #share
688 views𝓜𝓮𝓷𝓽𝓮 ²⁵, edited  04:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 06:30:27 እንዳይፈረድብህ በባልንጀራህ ላይ አትፍረድ

በአንድ ወቅት በግብጽ ገዳማት አንድ ወጣኒ መነኩሴ “ጥፋት አጠፋ፣ ሥርዓተ ገዳም አፋለሰ” ተብሎ መናንያኑ ጉዳዩን እንዲያዩና እንዲወስኑበት ከየበአታቸው ተጠሩ፡፡ ከተጠሩት መነኮሳት መካከል አንዱ ጥቁሩ ኢትዮጵያዊው ሙሴ ጸሊም ነበር፡፡ እርሱም ሁሉም ከተሰበሰቡ በኋላ ዘግይቶ በተቀደደ አቁማዳ አሸዋ በጀርባው አዝሎ አሸዋውን ከኋላው እያፈሰሰ መጥቶ በመሃላቸው ተገኘ፡፡

የተሰበሰቡት መነኮሳትም አባ ሙሴን ይህን ስለምን አደረግከው ብለው በጠየቁት ጊዜ በሀዘን ተውጦ “በጀርባዬ የማላያቸውን ስፍር ቁጥር የሌላቸው ኃጢአቶቼን ተሸክሜ ሳለሁ በወንድሜ ለመፍረድ መጥቻለሁ” አላቸው፡፡ መነኮሳቱም እጅግ ተጸጸቱ፡፡ ጉባኤውም ፍርዱን ትቶ ተበተነ፡፡

“እንዳይፈረድብህ በባልንጀራህ አትፍረድ” የሚለውን የወንጌል ቃልም በተግባር አስተማራቸው፡፡ልብን በሚነካ በዚህ በጎ ትምህርቱም መነኮሳቱን ከመፍረድ ሃጢአት ታደጋቸው፡፡
622 views𝓜𝓮𝓷𝓽𝓮 ²⁵, 03:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ