2022-12-18 15:19:36
" ምባፔ ስለ እግር ኳስ በቂ እወቀት የለውም "
የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ግብ ጠባቂ ኤሚሊያኖ ማርቲኔዝ የፈረንሳዩን አጥቂ ኪሊያን ምባፔ " በቂ የእግር ኳስ እውቀት የለውም " ሲል ትችቱን አሰምቷል።
ኪሊያን ምባፔ ከወራቶች በፊት " የደቡብ አሜሪካ እግር ኳስ እንደ አውሮፓ አይደለም ፣ አርጀንቲና እና ብራዚል በዓለም ዋንጫው የማሸነፍ እድላቸው አነስተኛ ነው " ማለቱ ማርቲኔዝን አስቆጥቷል።
ኤምሊያኖ ማርቲኔዝ በጉዳዩ ላይ ከጋዜጠኞች ጥያቄው ሲነሳለት " ስለ እግር ኳስ በበቂ ሁኔታ እውቀቱ የለውም ፣ በደቡብ አሜሪካ አንዴም ቢሆን ተጫውቶ አያውቅም።
ይህ ልምድ ሳይኖርህ ማውራቱ ተገቢ አይደለም ፣ እኛ እውቅናን ያገኘን ትልቅ ብሔራዊ ቡድን ነን " በማለት ኤሚሊያኖ ማርቲኔዝ ተናግሯል።
911 viewsIts me, 12:19