Get Mystery Box with random crypto!

ማቲ ሸገር - Mati Sheger®

የቴሌግራም ቻናል አርማ matiosbirhanu — ማቲ ሸገር - Mati Sheger®
የቴሌግራም ቻናል አርማ matiosbirhanu — ማቲ ሸገር - Mati Sheger®
የሰርጥ አድራሻ: @matiosbirhanu
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.81K
የሰርጥ መግለጫ

ስለ ፍትህ ስለ እኩልነት እና ስለ ዲሞክራሲ

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-08-30 16:11:07 እናሸንፋለን!

ለማሸነፍ ግን:_

ዳር ላይ ያለች ትንሽ ከተማ ተያዘችም፣ ትልቅ ከተማ ተያዘም ክብራችን ተነክቷል። የቀበሌ፣ የወረዳ፣ የዞንና የክልል ከተማ ቢያዝ ከብዙ ፋይዳ አንፃር ሊታይ ይችላል። ክብር ግን የትኛም ላይ ተመሳሳይ ነው። ከራሱ ድንበር አንድ ኢንች ሲያልፍ ተወርረናል የሚል ስሜት መኖር አለበት። ትንሽ ከተማ ሲያዝ ምንም የማይመስለን፣ ትልቅ ሲያዝ እንቅልፍ የምናጣ መሆን የለብንም። ከሩቅ ያለቦታ ሲያዝ ግድ የለሽ ወደእኛ ሲቀርብ የምንሰጋ መሆን የለብንም።

ትህነግ የራሱን አልፎ ከመጣ ቆይቷል። አሁን የራሳችን ከተማ የምንቆጥርበት አካሄድ መቆም አለበት። ከወረረው እስካልወጣ ድረስ የትም ይሁን የት ህመሙ እኩል መሆን አለበት። የራሳችን ከተማ እየተወረረ ዛሬ ከዚህ ደርሷል፣ ነገ ከዚህ ይደርሳል እያልን መቁጠር ለውጥ አያመጣም። ከየትኛውም እንዲወጣ የሚያስችል ስራ መስራት አለብን።

የትም ደረሰ፣ የት እንደምናሸንፈው ደግሞ ጥርጥር የለውም። ባለፈው ገና ከራያ ጀምሮ ባለው ከህዝባችን ከፍተኛ ትግል ገጥሞታል። በየመንደሩ ሲያልፍ በጀግናው ህዝባችንና ሰራዊቱ በርካታ ኃይሉን እያጣ ነው ሸዋና ጎንደር ድረስ የደረሰው።

ሸዋ ደርሶ ተመትቶ ተመልሷል። ከደብረታቦር ቅርብ ርቀት ደርሶ ተመትቷል። ከደባርቅ ቅርብ ርቀት ደርሶ ተመትቷል። ተስፋ በቁረጡት ሳይሆን ተስፋ ባልቆረጡት ተሸንፏል። ወገናቸውን በጎነተሉት ሳይሆን በቻሉት ከወገናቸው ጋር በቆሙት አቅም ተመትቷል። ባቅማሙት ሳይሆን በቆረጡት ተመትቷል። ሰራዊቱ ሸሸ ብለው ባራገቡት ሳይሆን ያለበት ድረስ ሄደን እንገጥዋለን ባሉ ክንደ ብርቱዎች ተመትቷል። ከቻልን አሁን ባለበት አስቁመን ወደመጣበት ለመሸኘት መስራት ነው። ባይቻል ደግሞ የትም ይግባ የት መሸነፉ እንደማይቀር አምነን መስራት አለብን። ደብረብርሃን ይድረስ ጎንደር፣ ላሊበላ ይድረስ ደጀን እንደምናሸንፈው ሳንጠራጠር መስራት አለብን።

እነሱ ዋሻ ገብተው ወጥተዋል። መቀሌም ይሁን አዲግራት ሲያዝባቸው ሰራዊቱ ሸሸ ብለው ብዙ አጀንዳ አላደረጉትም። ሲይዙ እንጅ ሲያዝባቸው ከተማ አልቆጠሩም። ከማን ጋር እንደገጠምን ማወቅ አለብን። የራስን ከተማ መቁጠር መቆም አለበት።

ባለፈውም ዘንድሮም መወረር አልነበረብንም። ግን ሆኗል። በሆነ ጉዳይ ጉንጭ ማልፋት የለብንም። ባለፈው እንዳደረገው ዘንድሮም ከራያ ጀምሮ ሕዝባችን የቻለውን እያደረገ ነው። ትልቅ መስዋዕትነት እየከፈለ ነው። ወደፊት ሲያልፍ አጨብጭቦ አያሳልፈው፣ ባገኘው አጋጣሚ እየገጠመው ኃይሉን እያጣ ነው የሚያልፈው። የትም ይድረስ የት ተመትቶ ይመለሳል።

ባለፈውም ብለናል። ሆኗልም። እንዳትጠራጠሩ እናሸንፋለን!

የቴሌግራም ቻናል:- T.me/matiosbirhanu
564 viewsMati Sheger, edited  13:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 16:08:38
የቀድሞው የወልድያ ከንቲባ አቶ ሙሃመድ ያሲን ከባህርዳር ተነስተው አለሁ ለወገኔ ብለው ወልድያ ከትመዋል

ህዝቡንም በማረጋጋት እና ለሰራዊቱ ለልዩ ሃይሉ እና ለፋኖው ድጋፍ እያስተባበሩ ይገኛሉ።

ኢትዮጵያዊነት ሲሞቅም ሲበርድም አይለወጥም አይወርድም

የቴሌግራም ቻናል:- T.me/matiosbirhanu
541 viewsMati Sheger, 13:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 14:58:14
553 viewsMati Sheger, 11:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 22:43:44 ቆቦ ስልክ ይሰራል
"ገብተው የተደበቀ መከላከያ ወይም ሌላ ሀይል ካል ያያሉ እዛው የቀረን ሰውም ፋኖ ነህ ምንድን ነህ ብለው ያጣራሉ !! እስካሁን ሌላ ምንም አላረጉም። እሚዘርፉት ከባባድ የሆኑ የመንግስት ንብረት ነው" ከቆቦ ነዋሪ በስልክ ያገኘሁት መረጃ ነው።(አዩ)

የቴሌግራም ቻናል:- T.me/matiosbirhanu
333 viewsMati Sheger, edited  19:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 22:35:28
የምድር ድሮኖች አፋሮች ከያለበት ቤቱ ድረስ የመጣውን ወራሪ ለመመከት ወደ ግምባር እየተመመ ነው...

በመቀጠል የማሳስበው ...ውሸት ሃራም ነው..!!
በየትኛውም አይነት መንገድ ውሸት የሰው ልጅ ክብርን ዝቅ የሚያደርግ ምንም ጥቅም የሌለው ነገር ነው ከጁንታው ውጭ ላለ ሰው። እኔም ለመወሸት የሚያስገድደኝ ምንም ነገር የለም በተቻለኝ መጠን ለሚያከብሩኝ ለማከብራቸው ለተከታዮቼ እውነተኛ መረጃ ለማቅረብ እሞክራለሁ ኢንሻአላህ ። ግን የኢትዮጵያና የመከላከያ ሰራዊት ስም ሲጠራ አይኑ ደም ስለሚለብሰው ባንዳ ስድብ ጆሮ አልሰጥም።

ተወደደም ተጠላም ኢትዮጵያ ታሸንፋለች

የቴሌግራም ቻናል:- T.me/matiosbirhanu
324 viewsMati Sheger, 19:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 22:23:32
«...ይህ ጦርነት እንዲቆም እማጸናለሁ! »

"...ከእናንተ የምመኘውን ልንገራችሁ። ሀገራችን ከዚህ የደረሰችው ብዙ ኢትዮጵያውያን፣ኢትዮጵያዊያት ሕይወታቸውን ጭምር ሰጥተው፣መስዋእት አድርገው ነው። አንድነቷ ተከብሮ፣በነጻነቷ ደምቃ ለአፍሪካውያን የኩራት፣የክብር ተምሳሌት ሆና አገራችን የቆየችው በዚህ መንገድ ነው። አልተማሩም ያልናቸው ወገኖቻችን በዚህ መልኩ ያቆዩዋትን ሀገራችንን ተማርን ያሉ ሰዎች በየቀኑ የመለያየት ፈጠራ፣የማፍረስ ፈጠራ እየፈጠሩ ወገንን ከወገን ሲለያዩ የተገነባውን ሲያፈርሱ እየተመለከታችሁ፤ እየተመለከትን ነው። ስለዚህ እናንተ የጥፋት ተቃራኒውን የሆነውን ልማትን እንድታለሙ፣ ራሳችሁን እረድታችሁ ሀገራችሁን እንድትረዱ ይልቁንም አንድ የሆነችው ሀገራችሁ፤ አንድ የሆነ ህዝባችሁ በአንድነቱ እንዲቀጥል፣ ደካሞች ያፈረሷትን ሀገራችሁን እናንተ እንድትገነቡ ልታስቡ፣ በዚህ ልክ 'ምን ላድርግ? ምን ልስራ?' ብላችሁ ፈጠራ ልትፈጥሩ ይገባል ብዬ እጠብቃለሁ።"
"...ይሄ ጦርነት እንዲቆም እማጸናለሁ። ለማንም ሲበጅ አላየሁም። በዚያ ክፉ ሰዓት በጦርነቱ መካከል ነበርኩኝ። ከግራ ቀኝ ሲያተርፍ ማንንም አልተመለከትኩም። ሲከስር ሲያጣ ነውና። አሁን ደግሞ ይህ በመሆኑ በእውነት ልንቆጭ ይገባል። ክፉ አስበው ክፉ ለሚሰሩ ሰዎች አምላካችን እግዚአብሔር ልብ ይስጣቸው እላለሁ። አምላካችን እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ህዝቦችዋን ይጠብቅልን። አሜን።"
ነሐሴ 21 ቀን 2014 ዓ.ም

(ብፁዕ አቡነ ኤርሚያስ የተበረከተላቸውን የክብር ዶክትሬት ዲግሪ መነሻ አድርገው ለባህር ዳር ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ካስተላለፉት መልእክት)

የቴሌግራም ቻናል:- T.me/matiosbirhanu
344 viewsMati Sheger, 19:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 22:18:03
ከአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የተሰጠ መግለጫ

የቴሌግራም ቻናል:- T.me/matiosbirhanu
302 viewsMati Sheger, edited  19:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 22:14:56 ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የተሰጠ መግለጫ

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ካለፉት አራት ዓመታት ጀምሮ የክልሉን ሕዝብ በኢትዮጵያ ኅብረ ብሔራዊ አንድነት ሥር ተጠቃሚ የሚሆንበትን ወሳኝ ተግባራት አከናውኗል።  ይህን ሁኔታ የተረዳው አሸባሪው የሕወሐት ቡድን  የአማራ ሕዝብና መንግሥት የራሱን የመልማት ዐቅም ተጠቅሞ የራሱን ዕድገት የሚያረጋግጥበትን ዕድል ለማጨናገፍ ከመነሻው ዓላማ ይዞ እንደሚንቀሳቀስ ይታወቃል።

በቀጥተኛ እና በተዘዋዋሪ መንገድ በመላ ኢትዮጵያ በሚገኘው የአማራ ሕዝብን  ላይ የተጠኑ፤ ተከታታይነት ያላቸው፣ አሰቃቂ ዘር ተኮር ጥቃቶችን፤ ግድያዎችን፤ ዝርፊያና መፈናቀል እንዲደርስበት በማድረግ አማራን ማኅበራዊ ዕረፍት የመንሣት ስልትን ሲከተል ከርሟል፡፡

በዚህ የጥፋትና የእልቂት ድርጊቶቹ ያልተገታው ሽብርተኛው የሕወሐት ቡድን የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት አደጋ ላይ የሚጥል ክህደት ፈጽሟል። በዚህም  በሀገር መከላከያ ሠራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ ወታደራዊ ጥቃት  አድርሷል። ከዚህም አልፎ  በመልከአ ምድራዊ አቀማመጡም ሆነ በባህላዊና ሃይማኖታዊ መስተጋብሮች የሺ ዓመታት የአብሮነት ታሪክ ባለው የአማራ ክልል ሕዝብ ላይ ወረራ በመፈጸም ከፍተኛ ሰብአዊ ጉዳቶችን አድርሷል። ከ288 ቢልዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው መሠረተ ልማቶችና ተቋማትንም አውድሟል፡፡

የክልሉ መንግሥት በአማራ ሕዝብ ላይ የህልውና አደጋ ጋርጠውበት የነበሩትን  እነዚህን ሁሉ ግፎች ለመከላከል ጥረት ከማድረግ በዘለለ ወደለየለት መጠፋፋት እንዳይገባ ከፍተኛ ጥንቃቄ በማድረግ የተፈጠሩት ግጭቶች ሁሉ በሰላማዊ መንገድ የሚፈቱበትን አማራጮች በማስቀደም ከሁሉም በፊት፤ከምንም በላይ ለሰላም ቅድሚያ ሰጥቶ ቆይቷል፡፡

ይሁን እንጂ ሽብርተኛው የሕወሐት ቡድን ለሰላም የተከፈተውን በር የጥፋት መናፍስቶቹ ማሹለኪያ በማድረግ በሚፈጽማቸው የጦርነት ትንኮሳዎችና ወረራዎች ስላለፈው የጋራ ታሪካችን እና ስለ መጪው  አንድነት፤ዕድገትና ተስፋችን ስንል ቅድሚያ የሰጠነውን የሰላም ዕድል በተደጋጋሚ አምክኗል፡፡

ዛሬም ቢሆን ለትግራይ ክልል አዋሳኝ በሆኑ የክልላችን አካባቢዎች ላይ ለአራተኛ ጊዜ ወረራ በመፈጸም ከወራት በፊት በክልላችን ሕዝብ ላይ የፈጸመውን ሁለንተናዊ ጥቃት ለመድገም እየተክለፈለፈ ይገኛል፡፡

ይህ ጦር ናፋቂ የሽብር ቡድን በንጹሐን ዜጎች፤በሃይማኖታዊ እና ዓለም አቀፋዊ የሰብአዊ ድጋፍ ሰጪ ተቋማት ላይ የፈጸማቸው ጥቃቶች የቡድኑን እውነተኛ ማንነት አጋልጠውታል። በመሆኑ መላው ሰላም ፈላጊ የሰው ዘር እና ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ የሽብር ቡድኑን ሊያወግዝ እና  ለፈጸመው ወንጀል ተጠያቂነት ሊያደርጉት ይገባል፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሁሉንም ዓይነት ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ ብቻ እንዲፈቱ የሰነቀው ልባዊ መሻት ጽኑ ነው። ነገር ግን በአሸባሪው የሕወሐት ቡድን እምቢተኝነት ምክንያት የሰላም አማራጮች የተዘጉ በመሆናቸው  የክልሉ መንግሥት የሕዝቡን ደኅንነት የማስጠበቅ መንግሥታዊ ግዴታውን እንዲወጣ አስገድዶታል።  ስለዚህም  በአሸባሪው የሕወሐት ቡድን የተቃጣበትን ወረራ ለመቀልበስ የሚያስችል አስፈላጊና ተመጣጣኝ ዝግጅት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
በመሆኑም መላው የአማራ ሕዝብ የክልሉ መንግሥት የሚያቀርበውን ጥሪ በንቃት እንዲጠብቅና ተገቢውን ሁሉ ዝግጅት እንዲያደርግ  የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ከወዲሁ ያሳስባል፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት


የቴሌግራም ቻናል :- T.me/matiosbirhanu
300 viewsMati Sheger, edited  19:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 21:59:29
ወሳኝ መረጃ

የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ሳዋ በልዩ ሁኔታ የሰለጠኑ በርካታ ቁጥር ያላቸው ወታደሮችና ልዩ ኮማንዶዎችን ዘመናዊ መሳሪያ በማስታጠቅ በዛላምበሳና አካባቢው ላይ ከመካናይዝድ ጦራቸው ጎን ተሰልፎ በተጠንቀቅ እንዲቆም አዘዙ፡፡

የቴሌግራም ቻናል:- T.me/matiosbirhanu
315 viewsMati Sheger, 18:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 21:51:06
ወቅቱን የዋጀ መልዕክት ነው
ፋኖ ማለት ለሕዝብ የቆመ እስከሆነ ድረስ በጎጃም፣ በሸዋና በጎንደር የምትኖሩ ፋኖዎች ተነጋግራችሁ ወደ አስቸኳይ መፍትሔ መግባት ይኖርባችኋል። የምሥራቅ ዐማራ ፋኖ የሚችሉትን እያደረጉ ናቸው። ለወንድሞቻችን የምንደርስበት ጊዜው አሁን ነው።
በዚህ ጊዜ ለዚህ መከረኛ ህዝብ ልትደርሱት ይገባል፤ ፊት እየመራችሁ ወጣቱን ከኋላ እያስከተላችሁ ይህን ወራሪ ልንመክተው ይገባል። ይህን የምታደርጉት ለማንም አይደለም አምጦ ለወለዳችሁ ህዝብ ስትሉ ነው። አውቃለሁ በዚህ ሥርዓት ታስራችኋል፣ ተሳዳችኋል፣ ያላስማችሁ ስም ተሰጥቷል፣ ይህ ሁሉ ግፍ የደረሰባችሁ ለዐማራ ህዝብ ስትሉ በመሆኑ ልትኩሩ ይገባል እንጂ "ብልፅግና በደል አድርሶብናልና አንዋጋም" ብላችሁ ህዝባችሁ ለዳግም ባርነትና ስደት ሲዳረግ በዝምታ ማዬት የለባችሁም።
እያያችሁ፥ እየሰማችሁ ነው እንቆምለታለን፣ እንሞትለታለን የምትሉት ህዝብ ዳግም በህወሓት ቅኝ ግዛት ሥር እየወደቀ ይገኛል። ይህን ጆሮ ጭው የሚያደርግ ዜና ሰምታችሁ ያስችላችኋል ብዬም አላስብም። ህዝባችሁ በማንም ወራሪ ሲዋረድ፣ ሲታረድ፣ ሲፈናቀልና ሲደፈር "ቆሜ አላይም አሻፈረኝ" ብላችሁ ተነሱ። በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ አገዛዝ ያልተከፋ አልነበረም፥ በጣሊያን ወረራ ጊዜ ግን "የተቀያየምነው ከሥርዓቱ እንጂ ከህዝቡ ጋር አይደለም" በማለት 'ኧረ ጥራኝ ጫካው' እያሉ አርበኝነትን፤ ፋኖነትን በይፋ ጀምረው ህዝባቸውን ነፃ አውጥተውታል።
እናተም የአባቶቻችሁን ገድል ድገሙት።እለምናችኋለሁ ፊት ሁናችሁ ምሩን እኛ እንከተላችኋለን። የሚያስፈልገውን ሎጂስቲክ እናቀርባለን። ዛሬ ቆቦ፣ ነገ ወልድያ፣ ከዛ ሐይቅና ደሴ ተያዙ የሚል ዜና መስማት የሞት ሞት ነው። እንደ ህዝብ መጥተዋል እንደህዝብ መመከት ነው።
ፋኖ ምሬ ወዳጆ

የቴሌግራም ቻናል:- T.me/matiosbirhanu
323 viewsMati Sheger, edited  18:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ