Get Mystery Box with random crypto!

እምነ ጽዮን መንፈሳዊ ማህበር

የቴሌግራም ቻናል አርማ mahibere_tsion21 — እምነ ጽዮን መንፈሳዊ ማህበር
የቴሌግራም ቻናል አርማ mahibere_tsion21 — እምነ ጽዮን መንፈሳዊ ማህበር
የሰርጥ አድራሻ: @mahibere_tsion21
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 206
የሰርጥ መግለጫ

የመዝሙር ግጥምና ዜማ
ገድለ ቅዱሳን ይገኝበታል፡፡

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-05 18:39:57
ወንድሞቼ! ከእናንተ መካከል አንድ ዐይነ ሥውር ሰው ወደ ጉድጓድ ገብቶ ሊወድቅ ሲል እጁን ዘርግቶ የማይደግፈው ማን ነው ? ታዲያ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በልቡናቸው ታውረው ወደ ሲዖል ጉድጓድ ለዘላለም ሲወድቁ እንድምን እጃችን የበለጠ አይዘረጋም ? ወገኖቼ! በነፍስም በሥጋም የታመመ ሰው ስታዩ " የእኔ ሥራ አይደለም፣ የቀሳውስቱና የመነኮሳት ሥራ እንጂ። " አትበሉ። አንድ ትልቅ በወርቅ የተሞላ ሳጥን ወድቆ ብታዩ " ይህ እኔን አይመለከተኝም ሌሎች መጥተው ያንሡት እንጂ " ትላላችሁን ? ግራ ቀኛችሁን አይታችሁ በፍጥነት የምታነሱት አይደለምን ? ይህ ወደ ዘላለም ጉድጓድ እየወደቀ ያለው ወንድማችሁም ከዚያ ወርቅ በላይ ውድ የእግዚአብሔር ሀብት ነውና አንሡት እንጂ የበለጠ እንዲወድቅ አትደግፉት።

ሰማዕትነት አያምልጣችሁ
ተርጓሚ ገብረእግዚአብሔር ኪደ
26 viewsBereket Kebede, 15:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 16:14:42 +++ ‹‹ይህም ያልፋል›› +++

+++ አንድ ንጉሥ አማካሪዎቹን ሰበሰበና እንዲህ ሲል አዘዛቸው፡፡ ‹‹ስከብርም ሆነ ስዋረድ፣ ሳገኝም ሆነ ሳጣ፣ የሁሉም የበላይ ስሆንም ሆነ የበታች፣ እጅግ ስደሰትም ሆነ ስከፋ፣ ድል ሳደርግም ሆነ ድል ስሆን፣ ዝናዬ ሲናኝም ሆነ ሲከስም፣ ያንን ነገር በሰላምና በጥበብ እንዳልፈው የሚያደርግ አንድ ዐረፍተ ነገር ስጡኝ፡፡ ላስታውሰው የምችል፣ መንገዱንም የሚመራኝ፣ ከልክ አልፌ እንዳልሄድ፣ ከልክ ወርጄም እንዳልወድቅ፣ የሚያደርግ አንድ ዐረፍተ ነገር አምጡልኝ፡፡ የተወሳሰብ ፍልስፍና አልፈልግም፣ ቀላልና ግልጽ የሆነውን እሻለሁ፡፡ ይህንን ሳትይዙ እንዳትመለሱ››
አማካሪዎቹ ከቤተ መንግሥቱ ወጥተው ለአራት ወራት ያህል መከሩ፡፡ አነሡ ጣሉ፤ በመጨረሻም የደረሱበትን ሐሳብ በብራና ጽፈው ወደ ንጉሡ ዘንድ መጡ፡፡ የተጠቀለለውንም ብራና ሰጡት፡፡

+++ ንጉሡም ገለጠና አነበበው፡፡ እንዲህ ይል ነበር ‹‹ይህም ያልፋል››፡፡ ለምን? አላቸው ንጉሡ፡፡ በየትኛውም የሥልጣንና የሀብት ከፍታ ላይ ብትሆን፣ በየትኛውም የዝናና የክብር ሠገነት ላይ ብትደላደል፣ ‹ይህም ያልፋል› ብለህ ካሰብክ ግፍ አትሠራም፣ ፍትሕ አታዛባም፣ ድኻ አትበድልም፣ ከልክህም አታልፍም፡፡ ራስህን ዘላለማዊ አድርገህ ካሰብክ፣ ጊዜ የማይቀየር ዓለምም የማትዞር ከመሰለህ ግን ራስህን ለማስተካከል እንኳን ጊዜ ሳታገኝ ነገሮች ይቀየሩና በሠራኸው ወኅኒ ትወረወራለህ፣ ባወጣኸው ሕግ ትቀጣለህ፣ በቆረጥከው ዱላ ትመታለህ፣ ባሳደግከው ውሻ ትነከሳለህ፡፡ ስለዚህ አሁን የተቀመጥክበትን ዙፋን፣ የምታንቀጠቅጥበትንም ሥልጣን፣ ‹ይህም እንኳን ያልፋል› ብለህ አስበው፡፡

+++ ተቀናቃኞችህን ድል እንዳደረግክ፣ አገሩን ጠቅልለህ እንደያዝክ፣ ሁሉ በእጅህ ሁሉ በደጅህ እንደሆነ፣ በለስ እንደቀናህ፣ አንደኛ እንደወጣህ፣ እንደ ተጨበጨበልህ ፣ እንደታፈርክና እንደተከበርክ፣ አትቀርም፡፡ ይህም በጊዜው ያልፋል፡፡ እነዚህ ዛሬ በዙሪያህ ሆነው የሚያፍሱልህ የሚያጎነብሱልህ፣ ሳታስነጥስ ይማርህ፣ ሳትወድቅ እኔን የሚሉህ፤ ሳይበርድህ ካልደረብንልህ ሳታዝን ካላለቀስንልህ የሚሉህ፤ ሳትጠራቸው አቤት፣ ሳትልካቸው ወዴት የሚሉህ፣ ይኼ ሁሉ ሲያልፍ ያልፋሉ፡፡

+++ ካንተም በፊት ሌሎች ነበሩ፣ ካንተም በኋላ ሌሎች ይመጣሉ፡፡ ከፊትህ ሌላ ባይኖር ኖሮ ከኋላህ ሌላ ባልመጣም ነበር፡፡ በጊዜ ውስጥ ትናንት ዛሬና ነገ አሉ፡፡ ዛሬ ትናንት፣ ነገ ዛሬ እየሆኑ ያልፋሉ፡፡ አንተ ሌሎችን እንደተካህ ሁሉ የሚተካህም የግድ ይመጣል፡፡ አንተ ሌሎችን እንደረታህ ሁሉ የሚረታህም ነገ ይመጣል፡፡ አንተ ሌሎችን እንዳሠርክ ሁሉ የሚያሥርህም ነገ ይመጣል፡፡ አንተ እንደቀበርክ ሁሉ ቀባሪህም ነገ ይመጣል፡፡ እስኪ ለቀስተኞችን እይ፤ የዛሬ ቀባሪ ሁሉ ነገ በተራው ተቀባሪ ነው፡፡ ማንም ራሱን የሚቀብር የለም፡፡ ሌላውን እንደቀበረ ሁሉ እርሱን ሌላ ይቀብረዋል እንጂ፡፡ ‹ይህም ሁሉ ያልፋል› ብለህ ካሰብክ ሁሉን በልኩ፣ ሁሉን በደንቡ ታደርገዋለህ፡፡

+++ የሌሎችን ታሪክ አጥፍተህ፣ የሌሎችን ሐውልት ሰብረህ፣ የሌሎችን ዋጋ አርክሰህ፣ የሌሎችን ስም ገድለህ መኖር ትችላለህ፤ ዐቅሙና ሥልጣኑ እስካለህ ድረስ፡፡ ነገር ግን ይህም ያልፋል፡፡ ያንተንም ታሪክ የሚያጠፋ፣ ያንተንም ሐውልት የሚሰብር፣ ያንተንም ስም የሚያጎድፍ፣ ያንተንም ዋጋ የሚያረክስ በተራው ይመጣል፡፡ የሚተካህን የምትፈጥረው ዛሬ በምታደርገው ተግባር ነው፡፡ ክፉ ከሆንክ ክፉ ይተካሃል፣ ርቱዕ ከሆንክ ርቱዕ ይተካሃል፡፡
+++ ይኼ ሁሉ ዓለም አልፎ ብትወድቅ፣ ብትሰበር፣ ብትታሠር፣ ብትረሳ፣ ብትሰደድ፣ ብታጣ፣ ብትነጣ፣ ከላይ ወደታች እንዳየኸው ሁሉ ከታች ወደ ላይ የምታይበት ዘመን ቢመጣ፣ ያሰብከው ቀርቶ ያላሰብከው ቢሆን፣ ‹ይህም ያልፋል› ብለህ አስብ፡፡ ‹ይህም ያልፋል› ብለህ ካሰብክ ተሥፋ አትቆርጥም፣ ነፍስህ ሳትወጣ አትሞትም፣ ራስህን ለብስጭትና ንዴት፣ ለቁጣና ትካዜ አሳልፈህ አትሰጥም። የሥልጣን ጫፉ መውረድ እንደሆነው ሁሉ የውርደት ጫፉ ሥልጣን ነው፡፡ የብርሃን ጫፉ ጨለማ፣ የጨለማም ድንበሩ ብርሃን ነው፡፡ የበሽታ ጫፉ ጤና፣ የጤናም ጫፍ በሽታ ነው፡፡ ዓለም ቋሚ አይደለችም፡፡ ጊዜ ወደ ፊት ብቻ ነው የሚሄደው፡፡

+++ እሥር ቤቱ ሲተከል የነበሩት አሁን የሉም፤ ስለዚህም አንተም እዚያ እሥር ቤት አትኖርም፡፡ ችግር ሲጀመር የነበሩት አሁን የሉም፤ አንተም ችግር ውስጥ የግድ አትሰምጥም፡፡ እንደሚያልፍ ካመንክ፡ ለማሳለፍ ትጥራለህ፡ እንደሚያልፍ ካላመንክ ግን ያለህበትን ትቀበለዋለህ፡፡...ይህም ያልፋል...!!!

ሀቁ ይህ ነው አንተምጋ ያለው ያልፋል።

❖ ወስብሐት ለእግዚአብሔር
❖ ወለወላዲቱ ድንግል
❖ ወለመስቀሉ ክቡር ይቆየን።
አሜን
እምነ ጽዮን መንፈሳዊ ማሕበር
151 viewsBereket Kebede, 13:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-14 11:51:10 "እንዲ እናምናለን አንታመናለን አብ ወልድ መንፋስ ቅዱስ አንድ እግዚአብሔር ብለን"
# እንኳን ለወርሐዊው የአብርሀሙ ሥላሴ በዓል እንዲሁም ለሌሎች ቅዱሳን መታሰቢያ በዓል በሰላም በጤና አደረሳችሁ፤ አደረሰን።
የአብርሐምን ቤት የባረኩ አጋዕይስተ አለም ሥላሴ እኛንም በህይወታችን፣ በኑሮአችን በአገልግሎታችን፣በትዳርአችን በትምህርታችን፣ በሥራችን ይባርኩን ።
ሥሉስ ቅዱስ ለምታምን ሁሉ እምነትን በረከትን ሀገራችን ኢትዮጽያን ሰላም ያድርጉልን አሜን ::
መልካም እለተ ይሁንልን
◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈◈
< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >
እምነ ጽዮን መንፈሳዊ ማህበር
49 viewsBereket Kebede, 08:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-24 10:04:16
መልካም የትንሣኤ በዓል
100 viewsBereket Kebede, 07:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-24 10:01:25 #ታላቅ የምስራች
ክርስቶስ ተንስአ እሙታን - በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤
አሠሮ ለሰይጣን - አጋአዞ ለአዳም፤
ሰላም - እምይእዜሰ፤
ኮነ - ፍስሐ ወሰላም
ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ስልጣን ከሙታን ተነሣ፤
ሰይጣንን አሰረው አዳምንም ነጻ አወጣው፤
ከሰማይ ወርዶ ሰማያዊ ቤትን የሰጠን ዝቅ ብሎ ከፍ ያደረገን ሞታችንን ሞቶ ሕይወትን የሰጠን በትንሳኤው ትንሳኤያችንን ለአበሰረን አምላክ ደግሞም በታላቅ ግርማ ሊያበስረን የሚመጣው የድንግል ማርያም ልጅ ኢየሱስ ክብር ምስጋና ይሁን!

በዓሉ የአንድነት የሰላም የፍቅር የደስታ የመተሳሰብ ያድርግልን እያልን ለታመሙት ምህረትን፣ ለአዙኑት መፅናናትን፣ ሰላም ላጡ ሰላምን፣ ለተራቡ ምግባቸውን፣ ለተቸገሩ መራራትን ያድልልን አምላካችን በምህረቱ ሁላችንንም ይጎብኘን መልካም የትንሳኤ በዓል!
ከእንግዲህም ወዲህ ፍጹም ሰላምና ደስታ ሆነ
ከአለማት ሁሉ ሠውን የመረጥክ በሞትህ ለኛ ትንሣኤ የሠጠኸን ከአምላክነት ወደ ሠውነት ያመጣህ ፍቅርህ ባይገባንም ለዚህ ክብር የፈጠርከን አምላክ ተመስገን!

#እንኳን_አደረሳችሁ
#እምነ ጽዮን መንፈሳዊ ማሕበር
87 viewsBereket Kebede, 07:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-18 17:05:58 ሕማማት
285 viewsBereket Kebede, 14:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-05 09:04:01
ዓለሙ በመላ: ጩኸት ኾኖ እያለ:
ዝም ብሎ መኖር: እንደምን ተቻለ?
.
አባ ሆይ! ዓለምን: እንደምን ቢንቋት?
ቃል እንደሌለዎ: ድምፅዎን ነፈጓት::
.
እንዴት ቢያስከፋዎ: የሰው ልጅ ጠማማ?
በአርምሞ ተለዩት: ቃልዎን ሳይሰማ::
.
ሰምቶም ላይተገብር: ንሰሐም ላይገባ:
"ቃል አላባክንም": ይመስለኛል አባ::
.
.
መርቆሬዎስ ሰማዕት: እንዴት ቢዎድዎ:
በስሙ አስጠርቶ: በዕለቱ ጠራዎ::
.
ምን እንደናፈቅነው: ድምፅዎን ባንሰማ:
ነፍስዎ በሰማይ: በአምላክ ፊት ቆማ:
ጩኸቱ ዝም እንዲል: እንዲቆም መከራ:
ትጸልይ ስለ እኛ: ትለምን አደራ::
--->
አባ ባገርዎ!
ይደር በረክትዎ
መልአኩ አላምረው(መለኛው) እንደከተበው
160 viewsBereket Kebede, 06:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-04 13:03:41 የምስራች
በአቢይ ፆም ሶስተኛ ሳምንት "ምኩራብ"
ታላቅ መንፈሳዊ ጉዞ ወደ ተአምረኛዋ ጅሩ ቅድስት አርሰማ
በቦታው ትልልቅ ተአምራቶች የሚደረጉበት ብዙዎች ለህይወታቸው ድንቅ ተአምር እየተደረገላቸው ያለ ቦታ ነው። እርሶም በዐቢይ ፆም የቅድስት አርሴማን ድንቅ ተአምር እና በረከት እናግኝ ይሎታል የምታውቁት እምነ ጽዮን መንፈሳዊ ማህበር።
በዐቢይ ፆም መልካም እንዝራ መልካም እንድናጭድ የሰማዕቷ እናታችን በስጋችን በረከት፣ ረድኤት ፣ደስታ ከእናታችን እንቀበላለን በሠማይ ደግሞ በምልጃዋ ሠማያዊ ዜግነት እናግኝ። ኑ አሁን በእጃችን ላይ ናትና የእግዚአብሔር መንግስትና የእናታችን ምልጃ! እኛስ እንሄዳለን እናንተስ ወንድሞቼ?
"እግዚአብሔርም የተቤዣቸው ይመለሳሉ እየዘመሩም ወደ ጽዮን ይመጣሉ፤ የዘላለም ደስታ በራሳቸው ላይ ይሆናል፤ ሐሤትንና ደስታን ያገኛሉ፥ ኀዘንና ትካዜም ይሸሻሉ።" ትንቢተ ኢሳይያስ 35:10
በጉዞው፦ የማታ ጉባኤ " የነፍስ ማዕድ" አዘጋጅተናል።
ዘማሪያን ጉባኤውን ያደምቁልናል።
ሌሎች አብያተቤተክርስቲያን እናያለን።
እናም ለተቸገሩት ውድ አምሳያዎቻችን ልብስ እና ሌሎችም እርዳታ የምናሰባስብ ይሆናል።
"ንጉሡም በቀኙ ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል። እናንተ የአባቴ ቡሩካን፥ ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ።  ተርቤ አብልታችሁኛልና፥ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛልና፥ እንግዳ ሆኜ ተቀብላችሁኛልና፥ ታርዤ አልብሳችሁኛልና፥
 ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፥ ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና። ጻድቃንም መልሰው ይሉታል። ጌታ ሆይ፥ ተርበህ አይተን መቼ አበላንህስ? ወይስ ተጠምተህ አይተን መቼ አጠጣንህ?  እንግዳ ሆነህስ አይተን መቼ ተቀበልንህ? ወይስ ታርዘህ አይተን መቼ አለበስንህ? ወይስ ታመህ ወይስ ታስረህ አይተን መቼ ወደ አንተ መጣን?
 ንጉሡም መልሶ። እውነት እላችኋለሁ፥ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት ይላቸዋል።"ማቴ 25፣34-40

ሌሎችም ፕርግራሞች ይኖራሉ
ዋጋ ምሳና እራትን ጨምሮ
400 ብር ብቻ
መነሻ ቦታ፦አዲስ አበባ በማንኛውም ቦታ
መነሻ ቀን ፦መጋቢት 3
መመለሻ፦እሁድ መጋቢት 4
"ጽዮንን ክበቧት"
ለተጨማሪ
@lovemomz
ወይንም
0901010290



ሼር አድርጉት
107 viewsኤራቅሊስ , 10:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-03 11:28:29 እግዚአብሔር እንደዚህ ያለ ማህበር ይስጠን። አሜን!
89 viewsBereket Kebede, 08:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-03 11:27:29 የዛሬ 24 ዓመት አንድ የወጣቶች መንፈሳዊ ማኅበር በቤተክርስቲያን ሥር ተመሠረተ::

ለቤተ ክርስቲያን ብዙ ሥራ የሠሩ በርካታ የጽዋ ማኅበራት : ሀገር አቀፍ ማኅበራት : የጉዞ ማኅበራት ብዙ ናቸው:: ይህ ማኅበር ግን በሀገራችን ካሉ መንፈሳውያን ማኅበራት ሁሉ ጨርሶ የተለየ ነው::

የማኅበሩ አባላት ቀን እየቆረጡ የሚሰባሰቡ : በየወሩ በየሳምንቱ የሚገናኙ ማኅበርተኞች አልነበሩም::

ማኅበርተኞቹ የወሰኑት በአንድነት አብረው ለመኖር ነበር:: ይህ ዓይነት ማኅበር የነበረው መጽሐፍ ቅዱስ ላይ በሐዋርያት ዘመን ብቻ ነው::

እነዚህ ማኅበረተኞችም የሐዋርያትን ዘመን የአንድነት ኑሮ መርሕ ለመከተል ተስማምተው የሚከተለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል የማኅበሩ የመተዳደሪያ ደንብ ለማድረግ ተስማሙ :-

"ያመኑትም ሕዝብ አንድ ልብ አንዲትም ነፍስ ነበሩአቸው፥ ገንዘባቸውም ሁሉ በአንድነት ነበረ እንጂ ካለው አንድ ነገር ስንኳ የራሱ እንደ ሆነ ማንም አልተናገረም። .... በመካከላቸው አንድ ስንኳ ችግረኛ አልነበረምና፤ መሬት ወይም ቤት ያላቸው ሁሉ እየሸጡ የተሸጠውን ዋጋ ያመጡ ነበርና"
ሐዋ. 4:32
በዚህ መሠረት ማኅበሩን ሐዋርያት በተሰበሰቡበት ቤት ስም ጽርሐ ጽዮን ብለው ሰየሙት:: ጽርሐ ጽዮን የአንድነት ኑሮ ማኅበር ብለው በጋራ መኖር ጀመሩ::

ወደዚህ ማኅበር የገቡ ሰዎች የተለያየ የኑሮ ደረጃና የሀብት መጠን ቢኖራቸውም ሁሉም ያላቸውን ገንዘብ : የቤት ካርታቸውን : መኪናቸውን : የሚከራይ ንብረታቸውን ወዘተ ለማኅበሩ አስረክበው ጠቅልለው ገቡ:: በማኅበሩ ውስጥ ሲኖሩም ሁሉም የሚበሉት የሚለብሱት እኩል ሆነ:: ድሃና ሀብታም የሚባል በመካከላቸው አልነበረም:: ልጆቻቸውንም አብረው ያበላሉ አብረው ያሳድጋሉ::

ይህ በዚህ ክፉ ዘመን ይደረጋል ተብሎ የማይገመተው የሐዋርያት ዘመን አኗኗር በእነዚህ ወጣቶች እውን ሆኖ ሃያ አራት ዓመት ቆየ:: የዚያን ጊዜ ወጣቶች ዛሬ ጎልማሶችና ጥቂቶቹም አረጋውያን ሆነዋል::

ልጆቻቸውም አድገው ለቁም ነገር ደርሰዋል:: ለልጆቻቸው ምንም ሀብት እንደማያወርሱና የጋራ ንብረታቸው ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ብቻ እንደሚውል ነግረው አሳድገዋቸዋልና አንድም ልጅ ስለ ወራሽነት አያስብም::

ማኅበርተኞቹ አብረው እንደ ሐዋርያት ዘመን መኖር ብቻ ሳይሆን ላለፉት 24 ዓመታት የሐዋርያትን ሥራም ሠርተዋል:: በዚህም መሠረት በሃያ አራት ቋንቋዎች ከየብሔረሰቡ ሌላው ቀርቶ ከኬንያ ጭምር ወጣቶችን በማምጣትና ሰባኪያን እንዲሆኑ በማሠልጠን 1779 መምህራንን ለስብከተ ወንጌል አሰማርቶአል::

"ለገጠሪቱ ቤተ ክርስቲያን ዕጣንና ጧፍ ብቻ ሳይሆን ሰውም እንሥጥ" በሚል መርሕ የተነሣው ይህ አገልግሎትም በርካታ ዲያቆናትን ቀሳውስትንና ሰባክያንን በየጠረፉ ላሉ ምእመናን አድርሶአል::
ይህንን ስልጠና ለ33 ዙር ሲያካሒዱ ተማሪዎቹን ወደ አንድነት መኖሪያቸው በማምጣት እዚያው እያደሩ ከእነርሱ ጋር እየበሉ እየጠጡ እንዲያድሩ በማድረግ ነው:: ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቀውን ይህንን ሥራ ወስነው በገቡበት የሐዋርያት ዘመን አገልግሎት በመጽናት እዚህ ድረስ አድርሰውታል::

በቀጣይ አገልግሎቱን በተሻለ መንገድ ለማከናወን
ጽርሐ ጽዮን የአንድነት ኑሮ ማኅበር አብራችሁን ባትኖሩም አብራችሁን ሥሩ የሚል ዕድል ለሁላችን አቅርቦአል:: የፊታችን እሑድ የካቲት 27 በሶር አምባ ሆቴል የገቢ ማሰባሰቢያ 1000 ብር ለጥንዶች 1300 ብር የመግቢያ ትኬት እየተሸጠ ነው::
(በትናንትናው ዕለት ለቅበላ አንድ ኪሎ ሥጋ በ1000 እንደተሸጠ ይታወሳል)

ቤተ ክርስቲያንን የምንወድ ሁላችን ከቻልን በሥፍራው እንገኝ:: ባንችል እንኩዋን ማኅበሩን በሚከተለው የባንክ ቁጥር እንርዳና እነሱ ለ24 ዓመታት የሰበሰቡትን በረከት በጥቂቱ እንካፈል::

COMMERCIAL BANK OF ETHIOPIA BURAYU E/O/T/B/K/YE/T/T/Z
Account፡ 1000102969972
87 viewsBereket Kebede, 08:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ