Get Mystery Box with random crypto!

#ታላቅ የምስራች ክርስቶስ ተንስአ እሙታን - በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤ አሠሮ ለሰይጣን - አጋአዞ | እምነ ጽዮን መንፈሳዊ ማህበር

#ታላቅ የምስራች
ክርስቶስ ተንስአ እሙታን - በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤
አሠሮ ለሰይጣን - አጋአዞ ለአዳም፤
ሰላም - እምይእዜሰ፤
ኮነ - ፍስሐ ወሰላም
ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ስልጣን ከሙታን ተነሣ፤
ሰይጣንን አሰረው አዳምንም ነጻ አወጣው፤
ከሰማይ ወርዶ ሰማያዊ ቤትን የሰጠን ዝቅ ብሎ ከፍ ያደረገን ሞታችንን ሞቶ ሕይወትን የሰጠን በትንሳኤው ትንሳኤያችንን ለአበሰረን አምላክ ደግሞም በታላቅ ግርማ ሊያበስረን የሚመጣው የድንግል ማርያም ልጅ ኢየሱስ ክብር ምስጋና ይሁን!

በዓሉ የአንድነት የሰላም የፍቅር የደስታ የመተሳሰብ ያድርግልን እያልን ለታመሙት ምህረትን፣ ለአዙኑት መፅናናትን፣ ሰላም ላጡ ሰላምን፣ ለተራቡ ምግባቸውን፣ ለተቸገሩ መራራትን ያድልልን አምላካችን በምህረቱ ሁላችንንም ይጎብኘን መልካም የትንሳኤ በዓል!
ከእንግዲህም ወዲህ ፍጹም ሰላምና ደስታ ሆነ
ከአለማት ሁሉ ሠውን የመረጥክ በሞትህ ለኛ ትንሣኤ የሠጠኸን ከአምላክነት ወደ ሠውነት ያመጣህ ፍቅርህ ባይገባንም ለዚህ ክብር የፈጠርከን አምላክ ተመስገን!

#እንኳን_አደረሳችሁ
#እምነ ጽዮን መንፈሳዊ ማሕበር