Get Mystery Box with random crypto!

ETHIO BOOKS PDF

የቴሌግራም ቻናል አርማ kooblife — ETHIO BOOKS PDF E
የቴሌግራም ቻናል አርማ kooblife — ETHIO BOOKS PDF
የሰርጥ አድራሻ: @kooblife
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 10.63K
የሰርጥ መግለጫ

➥ እዚህ ቻናል ላይ የተለያዮ ተከታታይ ታሪኮች (ልቦለዶች) ና ፍልስፈና ሳይኮሎጂ የአማረኛ እና English መጽሀፍትን በ📓PDF እና ትረካዎችን እና መሳጭ ግጥሞችን ሌሎችም ጠቃሚ ነገሮች ያገኛሉ።

ለሃሳብ ና አስተያየት ለመጠየቅ @Ethio96bot

📖 ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል‼️

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-09-11 09:06:25 ​​ ብቸኝነቴን .... መልሺልኝ


ክፍል ሰላሳ ስድስት (36)
.
ለክርስትና እምነት ተከታዮች ለዳግማይ ተነሳይ
ለእስልምና እምነት ተከታዮች ለቅዱሱ እረመዳን ፆም መያዣ እንኳን አደረሳቹሁ
መልካም የረመዳን ወር ይሁንላቹሁ
" ወንበር አለ ተቀመጡ " አላቸው ሚካኤሌ ፍፁም ሰላማዊና በተረጋጋ ስሜት
ሆኖ አላቸው ሰላም በምን አንደበቷ ታውራ በየትኛው ሰውነቷ ትቀሳቀስ ደርቃለች
አይኖቿ ለመርገብገብ እንኳን ጊዜ ያጡ ይመስላሉ ሀይል እንደበዛበት አንፖል
ተበልቅጠው በደማቁ ከሚካኤሌ ላይ ተተክለዋል በድጋሚ እንዲቀመጡ
አዘዛቸው ።
ታረቀኝ ዘወር ብሎ ተመለከታት መደንገጧ በግልፅ ያስታውቅ ስለነበር እሱም
በመረዳት እጇን ያዘውና እንሂድ እንደማለት ሲጎትታት እሷም ከእንቅልፏ
እንደነቃች ሁሉ ብንን አለችና በደመ ነብስ እየተራመደች ወደ ወንበሩ በመሄድ
ተቀመጡ አሁንም ሰላም እንደፈዘዘች ነው።
የሚካኤሌ ቢሮ እጅግ የተዋበ በአብዛኛው ዘመናዊ እቃዎች የማይታዩበት እቃው
አይደለም ጠረኑ ለእራሱ ኢትዮጱያዊነት ነው የሚሸተው እቃዎቹ በየግድግዳው
ላይ የታሳሉ ምስሎች በአጠቃላይ ኢትዮጵያዊነት የሚሰብኩ ናቸው ከሚኪ
ከጭንቅላቱ በላይ የተሰቀለው "ባነር ሚስ አስማጪ እና ላኪ ሀላፊነቱ የተወሰነ
የግል ማህበር " የሚል ተፅፏል ይህን ሁሉ ታረቀኝ ነው በአይኑ የቃኘው ሰላም
በሚካኤሌ አይን ላይ አይኗ ተሰክቶ ቀርቷል ።
" እሺ ምን እንድረዳቹሁ ትወዳላችሁ"አለ ሚካኤሌ በፈገግታ እና በትህትና
ሁለቱንም እያፈራረቀ ከተመለከተ በኋላ ። ታረቀኝ ሰላም መልስ የምትሰጥ
መስሎት ጠበቀ እሷ ዝም በማለቷ እሱ ጉሮሮውን ጠረገና።
" ይቅርታ የመጣንበት ዋናው ምክንያት ድርጅታችን አነስተኛ ኪሳራ ስለገጠመው
........" አለና ዝም በማለት ሰላምን ተመለከታት እሷ አሁንም እንደ ደነዘዘች ነው።
" እሺ ኪሳራ ስለገጠመው ....." አለ ሚካኤሌ
" .............ከእናንተ ድርጅት ጋር በሽርክና ለመስራት ነበር የመጣነው" አለ
በፈገግታ እና በትህትና ገለፀለት ሚካኤሌም በፈገግታ አየውና።
" የትኛው ድርጅታቹሁ ?.." አለ ሚካኤሌ ታረቀኝም ሰላምን ደንግጦ ከገባችበት
አዘቅት ነቀነቃት ።
" የእኛ ድርጅት .... አይደል እንዴ ሶል ....." አላት እሷ በዝምታ እየቺው ።
" የእኛ ሳይሆን የእሷ ድርጅት በባንክ እዳ ሊወረስ ቢበዛ ሳምንት የቀረው ድርጅቱ
ምን እሱ ብቻ ቤቱም ንብረቷ ሁሉ ሊወረስ እናንተ ብልጦቹ ከእኛ ከምታገኙት
የሽርክና ጥቅም ልትከፍሉ የማይሆነውን " አለ ያቀዱትን ቀድሞ ነቅቶ።
" ምን ነገርከው ታረቀኝ " አለች ድንገት ከሄደችበት ሀሳብ ነቅታ ። ሚካኤሌ
ፈገግ አለና ።
" አይ ሰላም አንቺ ሁለ ነገሬን የቀማሽ መስሎሽ ነበር እንዴ
" እኔ ነኝ የቀማሁሽ አየሽ እኔ ደካማና የማልማር ደደብ ሰው ነኝ ለምን እንደሆነ
ባላውቅም የሰው ልጅን በጣም አምናለው ያሳዝነኛል አዝናለው ይሄ ሁኔታዬ ብዙ
ጉዳት አመጣብኝ ፈጣሪን ለመንኩት እንደሌላው ብልጥ እንዲያደረግኝ እሱም
ለሰው ማዘኔን ይሁን ማዘንህ አግባብ ነው ብሎ ሌላ ሀሳብ አመጣልኝ ድርጅቴን
ቤት ንብረቱን አስይዤ በብድሩ ገንዘብ እየተቀሳቀስኩ ትርፌን በሌላ አካውንት
እና ሁለት ድርጅት ከእኔና ከልጄ ውጪ ሌላ ማን የማያውቀው ከፍቼ መንቀሳቀስ
ጀመርጅኩ አንቺ ግን ጥሩ ሚስት መሆን ሲገባሽ ጥቅም ጎተተሽና ከዛ
ከማይረባው ውሽማ አድማሱ ጋር ቀማቹሁኝ ይሀው እዳውን መክፈል አይደለም
ኪሳራ ውስጥ ከተሽው ሊወረስ ነው ያኔ እኔ እራሴ እገዛዋለው ከዛው ከባንክ
ተበድሬ አንቺ በደመ ነፍስ እና በዚህ አፈር በሚሆነው ትል በሚበላው ውበትሽ
ከመተማመን በፈጣሪሽ እመኚ እሺ" አላት ሰላም በንዴት እና በጥላቻ ሚካኤሌን
አየቺውና ከመቀመጫዋ ፍንጥር ብላ በመነሳት ታረቀኝን እያየቺው ።
" ምን አባህ ቁጭ ብለህ ስድብ ትጠጣለህ ና ተነስ እንሂድ " አለችውና በቁጣ
ኮሌታውን አንቃ አንስታው እየጎተተች ወደ በሩ ሄዳ ልትከፍት ስትል በሩ ተከፈተና
ቶማስ ከፊታቸው ቆመ
" ከሳሼ እንዴት ነሽ እድሜ ለሚኪ በይ ልገልሽ ስመጣ እሱ ነው ተዋት ወዳ
አይደለም ሚሊየን ጋኔኖችን ተሸክማ ነው አለኝና ተውኩሽ ለካ እውነቱን ነበር
እኔንም ልታሸክሚኝ ... ለማንኛውም የአድማሱ እውነተኛ ገዳይ ፖሊሶች
ደርሰውበታል ይመጣሉ ተዘጋጂ እሺ " አላት ሰላም በብስጭት ፀጉራን ነጨች
እና ።
" እረረረ ኡኡኡኡ .... ልታሳብዱኝ ነው ተውኝ ...ተውኝ ..." ስትል ቶማስ መንገዱን
ለቀቀላት ።
" እየው የጋኔኑ ምልክት ነው እንዲህ የሚያረጋት " አላት ሚኪ ሰላም በጥላቻ
አይታው እየጮሀች ወጥታ ስትሄድ ታረቀኝ ተከትሏት በመውጣት ኮሪደሩ ላይ
እየሄዱ።
" በጣም ነው የተጫወተብሽ " ሲላት ታረቀኝ በያዘችው ቦርሳ ፊቱ ላይ በንዴት
ወርውራ ስትመታው ፊቱን ይዞ ወለሉ ላይ ተዘረገፈ ዘወር ብላ ሳታየው ሄደች ።
ሚጣ ፍዝዝ ትክዝ ብላ ተቀምጣለች እናቷ ሰርካለም እና ስጦታ ቁጭ ብለው
ያያታል።
" ምን ሆነሻል ሚጣ ?" አለቻት እናቷ ሰርካለም
" ድካሜ ልፋቴ ሁሉ መና መቅረቱ አናደደኝ " አለች
" የምን ድካም " አለች ሰርካለም ተገርማ ስጦታ ጭምር።
" እናቴ ... ሰርክዬ ሚኪ እኮ በጣም የናጠጠ ሀብታም እና የትልቅ ድርጅት
ባለቤት ነው እኮ ነው " አለቻት ሰርካለምም ደንግጣ ከተቀመጠችበት ተነስታ
ስጦታን እያየች።
" እውነት ነው ስጦታ ንገሪኝ " አለቻት።
" ምነው ግን አዎ ሀብታም ነው ሁለት ድርጅቶችም አሉት " አለች ስጦታ
ሰርካለም ጭንቅላቷን ያዘች ።
" በቃ ከእሱ ጋር የነበረኝ ህልም ሁሉ አከተመ ማለት ነው እውነቱን ነው ያቺ
ቆንጆ ሀብታም ሴት ይዞ የመጣው በቃ አክትሟል የእኔና የእሱ ጉዳይ " አለች
አይኗ እንባ አቀረረ።
" እንዴ ለምን ሀብታም ቢሆን ምን ችግር አለው"አለች ስጦት
" እንዴት እንዲህ ትያለሽ እኛ እኮ ከድህነት አዘቅት በታች ያለን የሚበላ እንኳን
የሌለን ድሀዎች ነን እሱ ግን ሀብታም " አለች ሰርካለም እያለቀሰች ።
" እንዴ ሰርኬ አላፈቅረውም እያልሺኝ አልነበር እንዴ?" አለች ሚጣ ።
" አንቺ ደግሞ .... እና በአንዴ አፈቅረሀለው ልለው ነው ሴት እኮ ነኝ መግደርደር
አለብኝ ቆይ ምን የሚጠላ አለው ሚኪ " አለችና እያለቀሰች ወደ መኝታ ክፍል
ሄዳ ገብታ ዘጋችው ።
ሰላም መኪናዋን ፖሊስ ጣቢያ በር ላይ አቆመች ታረቀኝ ግራ ገብቶት አያትና ።
" እዚህ ምን እንሰራለን " አላት የቀላውን አፍንጫ ይዞ።
" ሌላ ተጠርጣሪ አለኝ ብዬ ሚካኤልን አሳስረዋል በቅናት ተነሳስቶ እሱ ይሆናል
የገደለው ብዬ " አለችና ወርዳ እንዲወርድ ስትነግረው መኪና ውስጥ
እንደሚጠብቃት ሲነግራት ከመኪናው ጎትታ አውረደው ይዛው ገባች ። ውስጥ
እንደገቡ የአንዱን መርማሪ ቢሮ ከፍተው እንደገቡ መርማሪው ከተቀመጠበት
ተነስቶ ።
" እየፈለግንሽ ሳለ እራስሽ መጣሽ ወሮ ሰላም በአቶ አድማሱ ግድያ ተጠርጥረሽ
በቁጥጥር ስር ውለሻል " አላት ደነግጣ ቀኑን እረገመች።..........
~~~~ ይቀጥላል ~~~

@Kooblife
@Kooblife

For any comment
@Ethio96bot
1.1K views06:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-07 16:33:54 ​​​​ ብቸኝነቴን ..... መልሺልኝ

ክፍል ሰላሳ አምስት (35)
.
" አንተ ቆይ እራስህን እንደምን ነው የምታየው ቁልል ታደርጋለህ እንዴ? የሆንክ
......" አለችው ማክዳ ከኬብሮን ጋር ፊት ለፊት ቆመው እየተያዩ ።
" ቆይ አንቺ ምን አስፈራሽ ለምን እንደከለከልኩሽ ሁሉ ዳር ዳር ትያለሽ" አላት
ኬብሮን ፈገግ ብሎ እያያት ።
" ምንድን ነው የሚያስፈራኝ ዳር ዳር የሚያሰኘኝ " አለችው
" በሆድሽ ይዘሽ እርር ድብን ከምትይ ኬቡዬ አፈቅረሀለው ለአንተ ስል ህይወቴን
እሰጥሀለው በይኝ" አላት ማክዳ በደንብ እና በሀይል ነው የሳቀቺው ።
" እረ በናትህ እረ እሞታለው ተውኝ እኔ አንተን አፍቅሬ የሆንክ ጂግራ ነገር ምንህ
ነው ደስ የሚለው የሚፈቀረው እኔ አንተን ከማፈቅር እራሴን ባጠፋ ይሻለኛል
አሁን ውጣልኝ ላስታምምበት ከአንተ ጋር መጨቃጨቅ አልችልም " አለች
" ለምን አንቸ አትሄጂም እኔ ሚካኤሌ ልኮኝ ነው የመጣሁት "
" እኔ ተልኬ ሳይሆን ቀጥሮኝ ነው ስለዚህ ሀላፊነቱ ለእኔ ይከብዳል እሺ የኔ
አይጥ " አለችው እየተቅለሰለሰች።
" ማኪ የእኔ አይጥ አንቺ እንደውም ቀፉፊ ቅጥርተኛ ሰለሆንሽ ተባረሻል እኔ
ቤተሰብ ነኝ ተልኬ ነው የመጣሁት እና እባክሽ ትሄጂልን በትህትና እየጠየኩኝ
ነው " አላት ማክዳም ተናዳ ተያያዘችው እሱም አንቺ ውጪ እሷም አንተ ውጣ
እየተባባሉ ሆስፒታሉን በጠብ አመሱት ተያይዘው መጯጯህ ጀመሩ ተያዪዙ
ለመደባደብ ጩሀቱን የሰማች ነርስ በመምጣት በጣም ከባድ በሽተኞች ያሉበት
ስለሆነ ዝም ብለው በሽተኛቸውን እንዲያስታምሙ አስረዳቻቸው እነሱም
ተቀብለው ሁለቱም ቁጭ ብለው የጎሪጥ እየተያዩ አለፍ አለፍ ብለውም
ሲሰዳደቡ ለሊቱ በሰላም ነጋ።
በንጋታው ወደ አራት የሚጠጉ የታጠቁ ፖሊሶች ወደ ሆስፒታሉ ገቡ እና የቃል
ኪዳንን መኝታ ክፍል ከፍተው ሲገቡ ማክዳ እና ኬብሮን ተቃቅፈው ተኝተው
አገኟቸው።
ቀሰቀሷቸው ሁለቱም ደንግጠው ነቁና ከመኝታ ክፍሉ ውጪ ወጡ በሩን ዘግተው
ጠየቋቸው ፖሊሶችም ቶማስን በግድያ ወንጀል ተጠርጥሮ እንደሚፈልጉት
ተናገሩ ሁለቱም ግራ ተጋብተው ፖሊሶቹን ከተመለከቱ በኋላ ።
" በምን ወንጀል ነው የተጠረጠረው " አለ ኬብሮን
" በአቶ አድማሱ ጌታቸው ባለቤቱ የመጀመሪያ ተጠርጣሪ እሱ እንደሆነ
መስክረዋል " አለ አንደኛው ፖሊስ
" መቼ ነው ..... ስንት ሰዓት ላይ ነው ግድያው ?" አለ ኬብሮን ግራ በመጋባት
ፖሊሶቹን እየተመለከ።
" ከሁለት ወይም ከሶስት ቀን በፊት ምሽት " አለው ፖሊሱ።
" ጌታዬ ይሄ ቀልድ ነው በእርግጠኝነት የምነግራቹሁ ገዳይ በፍፁም
በእርግጠኝነት እሱ አይደለም " አለ ኬብሮን።
"እንዴት እንዲህ ትላለክ? " አለው አንዱ ፖሊስ።
" ይሀውልክ ከሶስት ቀን ባለቤቱ እኔን በመጠጥ አደንዝዛ የሆነ ነገር ልታደርግ
ስትል ሚስቱ አረመኔ እና ጨካኝ ስለሆነች ደውዬ ጠራሁት ከፈለጋቹሁ ስልኩ
እጁ ላይ ካገኛቹሁ እዩት እኔም ስልክ ላይ መደወሌን አሳያቹሀለው መጥቶ እቤት
የሚስቱን ብልግና ነግሬው ሁለቱም እንደቆሙ እኔን ሂድ ብሎኝ ሁለቱ
ሲጨቃጨቁ እራሳቸው ችግራቸውን እንዲፈቱ ብዬ ትቻቸው ወጣሁ ይህ የሆነው
ያኔ ምሽትነው " ሁሉም ፖሊሶች ደንገጠው ተያዩ እና እርግጠኛ መሆኑን ጠየቁት
እሱም በጣም እርግጠኛ እንደሆነ ነገራቸው።
" ና እሺ ወደ ፖሊስ ጣቢያ እንሂድ " አሉት ኬብሮን ሊሄድ ሲል ማክዳ ደንግጣ
ካየቻቸው በኋላ ከኬብሮን ፊት ሄዳ ቆመችና ።
" እንዴ ! የት ነው የምትወስዱብኝ በፍጹም አታስሩትም እኔ ምን ልሆን ነው
ያለእሱ ምን አደርጋለው አትውሰዱብኝ " አለች ከልቧ ፈርታ እያለቀሰች ።
ኬብሮንም ከልቧ እንደምታፈቅረው ገባው የልብ ምቱ ጨመረ ፊቷን ወደ እሱ
አዙሮ ከንፈሯን ቢጉርሰው በወደደ እሷና እና ፖሊሶቹ አትወስዱትም እንወስዳለን
እየተባባሉ እሱ ግን በእሷ ለእሱ ጠበቃነት በሀሳብ ነጉዳል በመጨረሻም ፖሊስ
ጣቢያ መጥቶ ምስክርነት እንዲሰጥ ነግረው ፖሊሶቹ እንደሄዱ ኬብሮን
ከመቀስፈት ፊቷን ወደ እሱ አዙሮ ያሰበውን ከንፈሯን የመሳም ሂደት አከናወነ
እሷም አድምቃ ከንፈሩን ጎርሳ መለሰችለት ከጥቂት ደቂቃ በኋላ ሲለቃት
የከንፈሩን ጣዕምና ወዝ ንፋስ እንዳይወስደው በምላሷ አጣጥማ ወደ ውስጥ
ካስገባች በኋላ ።
" ምን አስበህ ነው የምትስመኝ" አለችው በቁጣ።
" እንዳ አንቺ አምላካዊና ሴጣናዊ በሀሪ በሴኮንድ የሚያሳይ ሰው አላየሁም "
አላት እና ለሚካኤሌ ስለ ፖሊሶቹ እና ስለ ሁኔታው ለመናገር ስልኩን ሲያወጣ
" እንኳን እሺ " አለችው ማክዳ።
ሚካኤሌ ሙሉ ሱፍ ለብሶ ከፎቆ ቢሮ ውስጥ በመስኮት ወደ ውጭ እየተመለከተ
ኬብሮን ስለ ሁኔታው የሚነግረውን በግርምት ሲሰማ ታረቀኝ እና ሰላም ከመኪና
ወርደው ወደ ፎቁ ሲገቡ ወደ እሱ እየመጡ እንደሆነ በእርግጠኝነት ተርድቶት
ነበር ።
ታረቀኝና ሰላም ወደ ፎቁ ገብተው ደረጃውን እየወጡ ።
" እኔ የምልሽ ከነገርሺኝ ታሪክ የሚካኤሌ ጥፋት አልታየኝም " አላት እሷም ዘወር
ብላ አየችውና።
" የእሱ ጥፋትና የተቀጣበት ምክንያት ሰው መሆኑ ነው "
" ለምን ሰው መሆኑ ብቻ ታየሽ መልካም በሀሪው ለምን አልታየሽም " አላት
ደረጃውን ጨርሰው ኮሪደሩን ይዘው እየተራመዱ ።
" በእርግጥ ልክ ነህ ሁሌም የሚገርመኝ እሱን አለማፍቀሬ የማስበው ሰው
ስለሆነ ነገ እሱም ክፋት እንደሚጀምር ይሰማኝ ነበረ " አለች ቢሮ በር ላይ
ሲደርሱ በሩን አንኳኩ ከውስጥ ተሽከርካሪ ወንበር ላይ ጀርባውን ሰጥቶ ስልክ
የሚያወራ አለ በጣቱ ምልክት ሰጠ ስልኩን እስከሚጨርስ እነሱም ገብተው
በሩን ዘጉት እና ቆሙ ። ስልኩን ጨርሶ ሲዞር ሚካኤሌ ነበር የሰላም ፊት
በድንጋጤ ቀላ አንደበቷ ታሰረ አፏ ተከፈተ።
" ወሮ ወይስ ወ/ሪት ልበልሽ ብቻ ሰላም እንኳን ወደ አዲሱ ድርጅቴ በሰላም
መጣሽ " አላት ከወንበሩ ተነስቶ ለመጨበጥ እጁን ዘርግቶ በትህትና በፈገግታ
እሷ በቆመችበት ደርቃለች አይኑ ማየቱም አስደንግጧታል።....
~~~~ ይቀጥላል ~~~

@Kooblife
@Kooblife

For any comment
@Ethio96bot
1.2K views13:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-07 16:33:54 ​​ ብቸኝነቴን ...... መልሺልኝ

ክፍል ሰላሳ አራት (34)
.

".......በቃ በለቅሶ ብዛት እንባዬ ደረቀ አይኔ ማየት አልችል አለኝ ዙሪዬን አየሁ
ማንም ከአጠገቤ የለም በእርሀብ የተነሳ ሆዴና ጀርባዬ ተጣበቁ በየምግቤቱ
እየሄድኩ ምግብ እየበሉ ያሉ ሰዎችን እባካቹሁ ከምትበሉት አንዴ አጉርሱኝ አልኩ
እንኳን ሊያጎርሱኝ ጠግበው የሚመልሱትን ምግብ እንኳን ለእኔ ሳይሆን ለውሻ
ነበር የሚሰጡት ግራ ገባኝ ለሰው ልጅ ያለኝ ጥላቻ በረከተ እሬት እሬት አለኝ
በመጨረሻ ከቆሻሻ ውስጥ ነጭ ነጭ ያወጣ እንጀራም ዳቦም አጊቼ በላው እና
ቤተ ክርስቲያን በር ሄጄ ተኛሁ በንጋታው በጣም ታመምኩ ተሰቃየሁ አንድ
ጎልማሳ ሴት አገኙኝ ወስደው አሳከሙኝ በዛው ቤታቸው ወሰዱኝ መሀን ነበሩ
ባልም ልጅም የላቸውም ቤታቸው ጠላ ይሸጣሉ ለካ የወሰዱኝ ለእኔ አስበው
ሳይሆን ጠላ እንዳሻሽጥ ነው ። ምግብ በስርአቱ አልበላ አሻሮ፣ እንኩሮ፣ የጠላ
ቂጣ፣ ምን አለፋህ ጠላው በእኔ ጉልበት ሆነ የሚጠመቀው ጠጪዎቹ ለሚሉኝ
ነገር ለሚጠይቁኝ ሁሉ እሺ ማለት አለብኝ አለበለዚያ ሴትየዋ ቆዳዬ እስኪተላ
ትገርፈኛለች ። በቃ እሺ ብዬ ከመቀመጥ ውጪ ቆንጆ ልጅ ነች ይሏታል በእኔ
የተነሳ አያሌ ወንዶች ይጎርፍ ነበር ሳስበው ይገርመኛል አንድ አንዴ ስሜታቸው
እጃቸው ላይ ይመስለኛል ብሆን የአንድ ሰው ነው አንድ ሺህ ወንድ የመኘኛል
የሚያናድዱት ባለ ትዳሮቹ ነበሩ ከሚስቱ የተለየ ነገር እኔ እንዳለ ሲጠይቁኝ።
ከዛ የስራው ድካም የምግብ መጥፋቱ በየቀኑ ከእኔ ጋር የሚወጡት ወንዶች
እሬት እሬት ማለቱ በቃ ሴትየዋን ብገላት ደስተኛ ነኝ ግን አልችልም ከዚህ ቤት
በሆነ ምክንያት መውጣት እንዳለብኝ ተሰማኝ የሚገርምህ ከጎሮቤት ጋር እንኳን
አትስማማም ሰላምታ የላትም።
ከሚጠጡት መሀል በቅርቡ የመጣ አንድ በጣም ቆንጅዬ ልጅ ነበር እሱን ከልቤ
አፈቀርኩት እሱም አፈቅርሻለው ላግባሽ አለኝ አይኔን አላሸሁም አላገረገርኩም
ቤቱ ወሰደኝ ለ15 ቀን ነበር ጥሩነቱን ያሳየኝ ከዛ እየሰከረ እየመጣ በፊልም ላይ
ያየውን በእኔ ላይ መፈፀም ያምራዋል እንቢ ስል መደብደብ ሲለው ማንም ያጣ
የነጣ ጭቅቅታም ጠላ ጠጪ ሲጫወትብሽ እኮ ነው አንስቼ ሰው ያረኩሽ
ይለኛል ሲለው ከቡና ቤት ሌላ ሴት ይዞ እየመጣ መሬት አስተኝቶኝ እያስረገጠኝ
ከሴቷ ጋር ያደርጋል ሲለው ጓደኞቹን ልኮ እንዲጫወቱብኝ ያረገኛል ። መራራ
ህይወት ይሄ ህዝብ ቁጭ ብሎ ለመፍረድ ማንም አይቀድመው ። ከዛ ጊዜ በኋላ
ነው ታሪኬ የተቀየረው ለዚህ ሰው የሚባል ፍጡር ያለ እርህራሄ ጨካኝ ገዳይ
መሆን ።
ያቺ ጠላ ሻጭ በጠና መታመሟን ሰማሁ ማታ ልጠይቃት መስዬ ሄጄ አፍኜ
ገደልኳት ይሄን ደግሞ ማታ ሰክሮ ሲወላገድ መንገድ ላይ ጠብቄ ብልቱን
ቆረጥኩለት ማንነቴን ሳያውቅ አሁን እያማረው ይቀራታል ማዘን እርህራሄ ተወኩ
" አለች ሰላም ፊቷ ላይ በቀል ስሜት የሚቀለቀል እሳት ይታይባታል።
" .... የአለምን ሰው የተባለ ፍጡር ሁሉ ብጨርስ የምረካ አይመስለኝም ሰው
በጣም እጠላለው " አለች በጥላቻ እየተርገፈገፈች ።
" ይህን ሁሉ ለምን ለእኔ ነገር ነገረሺኝ ታዲያ?" አላት እሱም ሰው ነውና ለእሱም
እንደማትመለስ እየተረዳው በፍርሀት እየተርበደበደ።
" ትንፍስ እድል ውስጤ ለብቻዬ ይዤው ተቀምጬ ጨነቀኝ ቆጠቆጠኝ
ላራግፍበት የምችለው ሰው አንተ ስለሆንክ "
" ማመንሽ ገርሞኝ ነው ለፖሊስ ሄጄ ብከስሽስ?" አላት
" መብትህ ነው ማስረጃ ካለህ .... አየህ ለእኔም ለዚህ ሁሉ ለተፈፀመብኝ ግፍ
ማስረጃ ተብዬ ነው አንተም መጠየቅህ አይቀርም ከዛ ስትወጣ ያቺ ቀን
የመጨረሻ የምታያት ቀን ሆነች ማለት ነው እገልሀለው " አለችው ደንግጦ
ከተቀመጠበት ተነሳ አየቺው እና በጩሀት " ቁጭ በል!! " አለችው ደንግጦ
ተቀመጠ !"... የአንዱ ታሪክ ይቀርሀል የሞኙ ባሌ ሚካኤሌ " አለችው እየፈራ
እየተቀጠቀጠ በእሺታ ጭንቅላቱን ነቀነቀ።
በሆስፒታል መኝታ ክፍል ውስጥ ፅጌሬዳ በሰው ሰሰው ሰራሽ መሳሪያ
እየተደገፈች ህይወቷን ለማስቀጠል ሙከራ እየተደረገላት ነው ። ከበሽተኞች
አልጋ ላይ በጀርባዋ ተኝታለች አየሩ ፀጥ ብሎ በአፍጫዋ የተከተተው አመዳማ
ቢጫ ጎማ አኮስጅን እየሰጣት የእሱ ድምፅ ነው የሚሰማው ሽሽሽሽሽ ሽሿሿሿ
የሚል ።
ከአልጋው አጠገብ ማክዳ ተቀምጣ አይን አይኗን ትመለከታለች ሀሳቧ ግን
ኬብሮን ጋር ነበር በጣም ናፈቀችው ለደቂቃ ከጎና በታጣው በወደደች ፈጣሪዋን
በሆነ ታምር እንዲያመጣላት ለመነችው። ብዙም ሳይቆይ በሩ በእርጋታ ተንኳኳና
ተከፈተ ዘወር ብላ ስታይ ኬብሮን ነበር ደነገጠች አላመነች በህልሟ መሰላት
ቃልን አይታ እንደገና ስታየው ቆሟል ብድግ ሄደችና እየገፋቺው ወጥታ በሩን
ዘጋቺውና።
" አንተ ምን አባህ ልትሰራ መጣህ ? ለምንድን ነው የምትከታተለኝ ነገሩሁ እኮ
በጣም ነው የምታስጠላኝ " አለች
" ሰምቼሻለው አንቺ መኖርሽን ባውቅ አልመጣም እራስሽን አይተሽዋል እንዴት
እንደምታስጠይ " አላት ማክዳ ተናደደች አበደች መስታወተ ፍለጋ አይኗ
ተንከራተተ።.......

~ ይቀጥላል ~~~~

@Kooblife
@Kooblife

For any comment
@Ethio96bot
815 views13:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-07 16:33:54 ​​ ብቸኝነቴን ... መልሺልኝ

ክፍል ሰላሳ ሶስት (33)
.
.
" ......አይኔን ገና በልጅነት ስገልጥ ከብርሀን ፍጥነት እኩል የዚች ዓለም በእኔ
መምጣት የዕልልታዋ ድምፅ ሞቃት እና ድምቀቷን አየሁ ተበረቅራቂ ፀአድዋ
በአይኖቼ ታተሙ እጇን ዘርግታ ፍንክንክ ብላ ተቀበለቺኝ።.....
..ስወለድ በሀብት በተደላቀቀ ቤት ውስጥ ነው የተወለድኩት እስክራች የበዛበት
ሀይ ላይት ይታየኛል ( ብዙም ትዝ በማይላት ) አባቴ ለእኔ እንዴት እንደሚሆንልኝ
ይታወሰኛል እናቴም እንደ አባቴ ባይሆንም ፍቅሯን ስትገልፅልኝ ብቻ ...
አባቴ ነፍስ ሳላውቅ በምን እንደሞተ ብዙም ባላውቀውም ሞተ ሌላው ሀይላይቴ
( ትውስታዬ ) አባቴ ሲሞት የነበረኝን ሁኔታ ነበር ብዙም ሳንቆይ እናቴ ሌላ ባል
አገባች የዚህች አለም ቆሻሻነቷ የረከሰች የገማች የጠነባች መሆኗን የተረዳሁት
ያኔ በእልልታ እጇን ዘርግታ በእልልታ ነተቀበለቺኝ ሁሉ ውሸት ደማቅ የመሰለችው
ዓለም በጨለማ ድባብ የተመታች እንደሆነች ያኔ ነው ያወኳት..." አለች ሰላም
ማስታወስ ባትፈልግም በግድ ወደ ህሊናዋ እየመጣ እያደማት የሚያስነባት
ትዝታ ።
" ከዛስ ምን ሆነ " አላት ታረቀኝ አይን አይኗን ሲያያት ቆይቶ።
" ...... እእእ እንጀራ አባቴ የእናቴን የገላ ጠረን ከገላው ሳያስለቅቅ እየመጣ እኔን
እያስገደደ ይደፍረኝ ነበር በየቀኑ ከምችለው በላይ ይገናኘኝ ነበር ለእናቴ ነገርኳት
አልቻልኩም አልኳት እሷ ግን ለእኔ ከመከላከል ይልቅ ቻይው አለችኝ በምን
አቅሜ ልቻለው ማን ጋር ልሂድ መሄጃ አጣሁ ። የሆነ ቀን አሜሪካ ፊልም ሳይ
አንድ ሀሳብ መጣልኝ ። ከቤት ጠፍቼ ወጣሁ 4 ቀን ያህል የት እንዳለሁ ማንም
አያቅም እኔ ግን እዛው ግራንድ (ምድር ቤት) ነበር የተደበኩት እቤት እያለው
ውሀ ምግቤን አስገብቼ ነበር እናም በ 5 ኛው ቀን ምሽት ላይ ወጣሁ ቀስ ብዬ
ተደብቄ የሲሊደሩን ጋዝ ለቀኩት እና ሳሎን ቤት እሳት ለቅቄ ወጣሁ ሀብት ንበረቱ
እስከነዛ አረመኔዎች ነዶ አመድ ሆነ። እናት ተብየዋ አንድ ብር የሌላት ድሀ
ነበረች አባቴን ያገባችው ሀብቱን ለመውረስ ከእንጀራ አባቴ ጋር ተመሳጥራ ነው
ያገባቺው ሳስበው ታዲያ የገደለትም እነሱ ይመስሉኛል ። እንኳን ባዶ እጅህን
ኖሮህም የማትመች እቺ ዓለም በሰው እርሃብና ስቃይ በሚዝናና በዚህ

ህብረተሰብ ውስጥ ምንም ማንም ሳይኖረኝ ገባሁ ከዛ ይህ ሰው የሚባል አውሬ
ያሳየኝ ስቃይ ..........ተወዉ .... ተወው ..." አለቾና አነባች በጣም እያለቀሰች
ታረቀኝ ወደ ደረቱ አስጠግቶ አባበላት ".....ማን እኮ ያኔ በለጋ እድሜዬ እንዲህ
አላባበለኝም እንደ ቆሻሻ ነው የጣሉኝ ....... ሰው ....ሰው .. አንድ ቀን ስልጣን
ባገኝ እራሴን ጨምሮ ......" አለቀሰች ከፊቷ ያለውን ጠረጴዛ እየደበደበች።
ምሽት ላይ በሚካኤሌ ቤት እሱና ልዕልና ከፊታቸወ ኮፒተር ከፍተው ሶፋ ወንበር
እየተመለከቱ ነው ከፊታቸው ባለ ሶፋ ላይ ሚጣ እና ሚስጥረ በንዴት
የእጃቸውን ክንድ ጉልበታቸው ላይ መዳፋቸውን አገጮቻቸው ላይ አድርገው
ከወገባቸው ጎንበስ ብለው ፍጥጥ ብለው ያያቸዋል ሚካኤሌም ልዕልናም ግራ
ገብቷቸው ያየዋቸዋል።
" ምን ሆናቹሁ ነው ልጆቼ ?" አለ ግራ ገብቶት
" ምንም " አሉ ሁለቱም በአንድ ላይ
" አስተያያቹሁ እኮ ያስፈራል " አላቸው መልስ አልሰጡትም ዝም ብለው ያዩታል
በድጋሚ ሲያያቸው እያያቸው።
" እረ በፈጣሪ ልጆች ምን ሆናቹሁ?" አለ ግራ ገብቶት።
" ምንም " አሉት በድጋሚ ። እሱም ዝም ብሎ አያቸውና።
" እሺ ስራ እየሰራን ነው እስከ ምንጨርስ ለምን ዕነ ሰርካለም ጋር ሄዳቹሁ
አትጫወቱም " አላቸው
" አንሄድም እዚህ ነው የምንፈልገው " አሉት ሁለቱም አንድ ላይ ተገርሞ ፈገግ
ብሎ አያቸው።
" እንዴ ዛሬ ምን ነክቶቹሀል ?" አለ
"ምንም " አሉት። አንዴ እነሱን ሌላ ጊዜ እነሱን ሌላ ጊዜ ልዕልናን ሲያያት ።
ልዕልና የሆነ ነገር ገባት ቦርሳዋን ይዛ ተነሳች ሚካኤሌ ቀና ብሎ ሲያያት።
" ልጆችህ የእኔን መምጣት የወደዱት አይመስለኝም በቃ ልሂድ አይመስልህም "
አለችው
" አዎ አልተመቸንም በቃ ትሂድ " ሲሉ ደንግጦ አያቸው ልዕልና ስትራመድ
ኮፒተሩን ዘግቶ ያዘውና እቤቷ እንድታየው እየሰጣት ተከታትለው ወጡ ። እነሱ
እንደወጡ ሚጣ እና ስጦት በደስታ ተጨባብጠው በደስታ ሲጨፍሩ ሚካኤሌ
ሸኝቷት መጣና።
" ቆይ ምን ሆናቹሁ ነው አዋረዳቹሁኝ እኮ " አለቸው ፈገግ ብሎ እነሱም
ተጠቃቀሱና።
" አባታችን ቀድመን ባነንብህ እቅድህን አሰናከልንብህ " አሉት ሚካኤሌ አሁን ገና
ገባው ከልዕልና ጋር ሌላ ነገር የሚያረግ መስሏቸው ነገሩን ማበላሸታቸው ነበር
። እየሳቀ ሁለቱንም አቅፏቸው ከሶፋው ላይ ወድቀው ይላፍ ጀመር።...
~ ይቀጥላል ~

@Kooblife
@Kooblife

For any comment
@Ethio96bot
1.1K views13:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 15:32:02 ​​ ብቸኝነቴን ..... መልሺልኝ

ክፍል ሰላሳ ሁለት (32)
.
.
ማክዳ የመዓዛን መምጣት ስትመለከት እንደ ኤሌትሪክ ነዘራት ተያዩ ወደ
ኬብሮን ተመለከተችና።
" አንተም ሰው ሆነህ... ምን አባትህ ደስ የሚል ነገር ኖሮህ ነው ይሄ ሁሉ ሴት
የሚጋጋልህ አልገባኝም ..... በጣም ነው እኮ የምታስጠላው ስትታይ እጅ እጅ
የምትለው "የምትለው ብላ ወጥታ ልትሄድ ስትል
" ከአንቺ ውጪ ማንም አልወደደኝም እናም ምኔን አይተሽ እንደወደድሺኝ
እራስሽን ጠይቂ " አላት ፈገግ ብሎ በንዴት ዘወር ብላ ወገቧን ይዛ ማኪ።
" ሞኝ .... ደደብ ሞኝ እኮ ነህ እኔ አንተን ልወድህማሰብህ እራሱ ይገርማል
እፍረተ ቢስ ..... ለማንኛውም የእኔ እህት ወደመጣሽበት ጉዳይ ግቢ " ብላ
ወጥታ ስትሄድ
" ይቅረታ ማኪ ወደ መጣችበት ጉዳይ ለመግባት በር ተከፍቶ አይኬድም በሩን
አንዴ በደንብ ዘግተሽ ትቆልፊልናለሽ " አላት ማክዳን አውቆ ለማበሳጨት
የተናገረው ነበር ። ማኪም በንዴት እንደ በሬ ጮሀ አየችውና መዓዛ እንደገባች
በሩን ወርውራ የዘጋችው። ያልተግባቡ ያልተዋወቁ አፍቃሪዎች ናቸው ለብቻ
ለብቻ ሲሆኑ ፍቅር ያስቆዝማቸዋል ሲገናኙ እንደማይዋደዱ እንደሚጠላሉ
ከስድብ ጋር ይነጋገራሉ ብቸኝነቱን የሚመርጡ ይመስላሉ። ሁለቱም ያሳዝናሉ።
" ደግሞ አሁን ምን ፈልገሽ መጣሽ ልትተዪኝ አትችይም " አለ
" ለእውነቱ አሁን የመጣሁት ይቅርታ ልጠይቅህ ነው" አለች መአዛ ፍፁም
ትህትና በተሞላበት በጨዋ ደንብ።
" እየቀለድሽ ነው " አላት ተገርሞ እያያት።
" ከምሬ ነው ባለቤቴ ውጭ እየጠበቀኝ ነው ። አየህ እኔ ከባለቤቴ ያጣሁት ነገር
ስሜቴን አለመጠበቁ ነው ሌላ ሁሉንም በደስታ ሰጥቶኛል አንተን በገንዘብ
አስሬህ ይህንን ስሜቴን እንድትፈፅምልኝ ነበር ገንዘብ እየሰጠሁሁ በውለታ
ያሰርኩሁ " አለችው መዓዛ በፍፁም ተለውጣ በትህትና።
" ታዲያ ሞልቶ ከተትረፈረ ወንድ እኔን በምን አየሺኝ "
" ከተትረፈረፍት አንተ ተገኘህ እና እኔ ምን ላርግ " አለች
" ምን ታደርጊ መሰለሽ በተቻለ መጠን ከባለቤትሽ ጋር ተስማሚና እኔን ተይኝ
አየሻት የአሁኗን ማኪ ፍቅር ነው እንደዚህ የሚያንጨረጭራት እኔም የእሷ ፍቅር
ነው የሚያንተከትከኝ እባካቹሁ በመሀል እየገባቹሁ አታቃጥሉን"
" በቃ እኔ ከባሌ ጋር ያለኝን ችግር በንግግር ፈትቻለው ተስማምተናል
መጀመሪያም ያንን ነበር ማድረግ የነበረብኝ ባለመነጋገር ብዙ ነገር ተበለሽቷል
እሱን አስተካክላለወ ... ልጅህ ያልሆነውንም ፅንስ የአንተ ነው ማለቴ ይቅርታ
ከዚህ በኋላ ምርጥ እህትህ ነኝ የምረዳህ ነገር ካለ ደውል ቻው " ብላው
ልትወጣ በሩን ስትከፍት።
" እንዴ ለሰባበርሻቸውስ የፊት አጥቶቼ " አላት ፈገግ ብላ አይታው በሩን ዘግታ
ሄደች ። ከትንሽ ቆይታ በኋላ በደስታ ጮሀ ትንሽ ቆይቶ ሚጣናስጦታ በሩን
ከፍተው እየሮጡ ገቡ።
" ምን ሆናቹሁ ነው ?" አላቸው ሁለቱንም እያያቸው ።
ስጦታ " ስትጮህ ማኪ ምን ሆኖ እንደሆነ ሂዱና እዩት ብላን ነው " አለችው ።
የሆነ ነገር ገባው ከመአዛ ጋር ወሲብ እየፈፀመ ከሆነ ለማስቆም ልጆቹን
እንደላከች ቅናት ወይም ንዴት ፈገግ አለና ።
" ትሄዱና እንዲህ በሉልኝ እወዳቹሁ የለ ..... ከሆነች ልጅ ጋር መኝታ ቤት ውስጥ
ሆኖ አልከፍትም አለን በሉልኝ" አላቸው
" ኬቡ አይደብርህም እንዴ እኛ እራሱ ሁለት ገገሞችን ለማጣበስ ስራ
በዝቶብናል እንደገና እናንተንም እናጣብስ እንዴ ?" አለችው በፈገግታ አዎ አላት
ኬቡ።
" ምን አርገህ መጣህ ሚኪዬ " አለች ልዕልና ሚካኤሌ የቢሮዋን በር አንኳኩቶ
ከፍቶ እንደገባ ወንበር ይዞ ተቀመጠና።
" ከዚህ በኋላ እንደ ድርጅቱ ባለቤት ሳይሆን የምታይኝ ቅጥር ሰራተኛ እንደሆኩ
አስቢና ማዘዝ ያለብሽን እዘዢኝ ... ቶማስን ሆ/ል ሚስቱን ሲያስታምም አጊቼው
ሁሉንም ነገር ነግሬው እንዲደበቅ አርጌዋለው ነገሮች እስኪሰተካከሉ እኔ ጋ
የሆነች ልጅ አለች እሷን እቀጥራታለው አይሻልም " አላት
" እረ በጣም ጥሩ አርገሀል .... እና ስለ ድርጅቱ ያወጣሀው እቅድ " አለችው
ልዕልና በቻፒስትክ ውበት ተጨማሪ ውበት ያገኙትን ከንፈር ገለጥ አድርጋ አጫ
በረዶ የመሰሉ ጥርሶቿን አብለጭልጫ እያሳየች።
" ይቅርታና ባለቤትሽ ፍቃደኛ ከሆነ ነገሩ ከእኔ ጋርም ይሁን ከሌላ ሰው ጋር በስራ
ጉዳይ ሁሌም ስለሚያምንሽ ፍቃደኛ ነው የትም ብትሆኚ እንቢ አይልም ? ብቻ
ንገሪውና በኋላ እኔ ቤት እንሄድና እናየዋለን ሳይመሽ ትመለሺያለሽ " አላት
ተስማሙና ሌላ ነገር ትዝ አለው ".....ሌላው ልዕል የድርጅቱ ስያሜ እንዲቀየር
እፈልጋለው በሁለቱ ሴት ልጆቼ ሚጣ እና ስጦታ የመጀመሪያዎቹን ፊደል ወስደን
ሚስ ተብሎ እንዲጠራ " አላት። ልዕልና ሁለት ልጆቼ ሲላት ገርሟት አየቺው።
አመሻሽ ላይ ልዕልናም በእራሷ እሱም በእራሱ መኪና መጥተው ከኮደሚኒየሙ
በር ላይ አቆሙና ወረዱ ቅድሚያ ሚኪ ደውሎ እንግዳ ይዞ እንደሚመጣና ቤቱን
እንዲያስተካክ ነግሮት ነበር። እናም ደረጃውን ወጥተው ኮሪደሩ ላይ ሲወጣ
ሚጣ ስጦታ እና ሰርካለም ቁጭ ብለው ዘወር ብለው አዩትና አኮረፍ እሱ ፈገግ
ብሎ መጥቶ ሰላም ሲላቸው እጃቸውን አጣምረው ዝም አሉት ግራ ገብቶት ቆሞ
አያቸው ፊታቸውን አዞሩበት።............

~ ይቀጥላል ~

@Kooblife
@Kooblife

For any comment
@Ethio96bot
4.8K views12:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 15:32:02 ​​ ብቸኝነቴን..... መልሺልኝ

ክፍል ሰላሳ አንድ (31)
.
ሚካኤሌ አንድ የሚያምር ዘመናዊ መኪና በመያዝ ከአንድ ፎቅ ስር አቆመው
በቀጥታ ከመኪናው ወርዶ ወደ ውስጥ ገባ አንድ ቢሮ አንኳኩቶ ገባ ።አንዲት
የምታምር ወጣት ሴት ተቀምጣለች በሚያምር ፈገግታ ተቀበለችው ።
" እኔ አላምንም ሚኪዬ " አለች ፍፅም ሰላማዊ ደስታ ከውስጥ የመነጨ ደስታ
እና እርካታ።
" ልእልት እንዴት ነሽ " አላትና አቅፎ ሳማት።
" የአይንህ ጉዳይ ዲም ላይት መሰለኝ አንዴ ብርት አንዴ ጥፍት የሚለው......
ለማንኛው አረፍ በልልኝ " አለችና በእጆቿ ወንበሩን ጠቆመችው ።
" ያኔ ለህክምና ውጭ ሄጄ ስመለስ አይኔ በርቷል ያልነገርኩሽ አንድ ሚስጥር
ከአንድ ሰው ከዘለለ ሚስጥርነቱ አበቃ ማለት ነው አሁንም አዲት ህፃን ስላየቺኝ
ሚስጥርነቱ አበቃ ብዬ እራሴን ያጋለጥኩት ።" ሲላት በፈገግታ አያትና
" ሲጀመር የአንቸን ሚስት ሳስባት ሴት መሆኔን እጠላለሁ ለእሷ ስም አጣለው
ጨካኝ አረመኔ ብቻ የሚለው ቃል ብቻ በቂ አይደለም " አለችው ፈገግ አለና
ተመለከታት።
" አሁን እሷን ፊት ለፊት ተጋፍጬ የማንኮታኩታት ጊዜ መጥቷል እስከ ዛሬ ለእሷ
አስቤላት ነበር አእምሮዋ እንዳይጎዳ ብዬ ነበር ግን ብልግናዋ ከምችለው በላይ
ሆነብኝ " አላት ሚካኤሌ ልእልና ፈገግ ብላ አየቺው እና።
" እንዲህ ጎድታህ ከውሽማዋ ጋር ተሰባጥራ በአድጋ አስመስላ አይንህን አጥፍታ
ሀብት ንብረትህን ቀምታህ አሁንም ግን ስለ እሷ እንዳትጎዳ ትመኛለህ አሁንም
ታፈቅራታለህ ማለት ነው ?" አለችው
" ሰለማፈቅራት አይደለም ሰው ስለሆነች መጉዳት ያልፈለኩት የሰው ልጅ ያለ
ምክንያት መጥፎ አይሆንም እሷ ሌላ ሰው ጎድቷት እኔን ጎዳቺኝ እኔም እሷ
ስለጎዳቺኝ መጉዳት ከጀመርኩ ሰንሰለት ሆነ ማለት ያ ማለት ነገሮች ይከብዳሉ
ለዚህ ነበር ዳግመኛ እንዳትጎዳ ያሰብኩላት ግን የእሷ ጭካኔ ስለበረታ
ላስቆማት ይገባል " አላት እሷ በእሺታ ጭንቅላቷን ነቀነቀችና በፈገግታ ስታየው
ቆይታ ።
" እና አሁን ድርጅትህን ያስተዳደሩን ስራ ልትነጥቀኝ ነው ማለት ነው " አለችው
በጨዋታ መልክ በፈገግታ።
" እንዴ ምን ሆነሽ ነው እኔ ከአንቺ በታች ሆኜ ነው የምሰራው እዚህ ካደረሺው
ድርጅት ላፈናቅልሽ አላደርገው?"
" ትቀልዳለህ በእራስህ ድርጅት የእኔ የበታች ሆነህ ልትታዘዝ ነው " አለችው
በእሺታ ጭንቅላቱን ነቀነቀ። ልዕልና የሆነ ነገር ትዝ አላትና ። "........ ሚኪ
እረስቼው ቶማስን እባክህ አድነው ፖሊስ በጣም እየፈለገው ነው " አለችው
ሚካኤሌ ደንግጦ አያትና ።
" ምን አድርጎ " አላት በድንጋጤ እያያት።
ሰላም ከታረቀኝ ጋር በቢሮው ውስጥ ተቀምጠው ያወራሉ።
" ሶል ምን ሆነሽ ነው እንዲህ ጨካኝ የሆንሺው "አላት ታረቀኝ
" አንተ ከውጪ እምታውቀኝ ውስጤን ታውቀዋለህ አታቀኝም አንተ ያፈቀርከኝ
ውጬን አይተህ ነው እኔ በህይወቴ መቼም ለሰው ልጅ ጥሩ ሆኜ አላውቅም
በሰው ልጅ ስቃይ ይመደሰት የምዝናና በሰላምና በፍቅር ሲኖሩ በሽታ ይሆንበኛል
ስለዚህ በጭካኔ የሰውን ደስታ መንጠቅ..."
" እረ በፈጣሪ ስም .... ሶል አንቺም እኮ የሰው ልጅ ነሽ " አላት በግርምት
በድንጋጤ እያያት።
" በህይወቴ ሰው ሆኜ እንደመፈጠሬ የምጠላውም የምናደድበትም ነገር የለኝም
ምነው አውሬ ሆኜ በተፈጠርኩ በቃ የሆነ እንሰሳ ብሆን ብዬ አስባለው" አለች
በፀፀት
" ይቅርታ እስከዚህ ድረስ ሰው መሆንሽን ለምን ጠላሺው "
" ሰው መሆን ምን ደስ የሚል ነገር አለ ? እ ንገረኝ ዓለም የምትበጠበጠው
በእንሰሳት ነው በጦርነት፣ በአሸባሪነት ፣ በምቀኝነት ፣ በራስ ወዳድነት ፣
በጥቅመኝነት ፣ ሴት በመድፈር ፣ ዓለም ከዚህ በላይ የምትታመሰው ሰላም
ያጣችው እኮ በሰው ልጅ ነው እኔን ፊት ለፊት ስለማረግ ጨካኝ አረመኔ ተባልኩ
አንተ ኪስ ውስጥ ብር አለ ወደ ውጭ አንድ ሰው መጥቶ እርቦኛል ብር ሰጠኝ
ቢልህ ላትሰጠው ትችላለህ አንተ ዘወር ስትል ልጁ ቢሞት አንተም ገዳይ ነህ
ልዩነቱ ፊት ለፊት መሆኑ እና መደበቁ ነው አንተ ቪላ ውስጥ እያደርክ ስንቱ
ብርድ ይመተዋል አስበኋቸው ታውቃለህ አንተ ጠግበህ ትራፊህን ለውሻ
ስትሰጥ ሌላው ተርቦ ሆዱን አቅፎ ይተኛል ...... እስቲ ተወኝ " አለች ሰላም
" በቃ ይሄ ነው ምክንያትሽ ?" አላት
" አነሰብህ አይደል .... ከበቂ በላይ ነው ..... ወሻን እንተወው ለምን ያበላውን
እጅ አይነክስም ይሞትለታል እንጂ የሰው ልጅ ግን አብሮ ጠጥቶ በልቶ የእኔ ዘር
አይደለህም መሬቴን ልቀቅ ብሎ አንገት ይቆርጣል እሺ ሌላ ምሳሌ አንበሳ ሲበላ
ከሁሉም ጋር ይበላል ሊያጠቃው የመጣ ሌላ አካል አንድ ላይ ሆኖ ያጠቃል ሰው
እርስ በእርሱ ይገዳደላል። .... እኔ ሰው በመሆኔ ኑሮዬ ስቃይ መከራ ችግር
የበዛበት ነበር በዚህ አመኔ ጨካኝ ሰው በሚባል ፍጡር ጌታም ሰውን መፍጠሩ
የፀፀተው እውነቱን ነበር።." አለችና አንገቷን ደፍታ አለቀሰች።
ኬቡ እቤቱ ማንም ሳይኖር ለብቻው ጫት ይቅማል ሚካኤሌ ስጦታ ስላለች
ከተቻለ እቤት ባይቅም ከቃመ ከልጆቹ ደብቆ እንዲቅም ሲጋራ ቤት ውስጥ
መሳብ ፈፅሞ እንዳያስብ ነግሮታል ስለዚህ ደብቆ ይቅማል ድረሰት ለመፃፍ
ወረቀት ከምሯል ግን መፃፍ አልቻለም ሀሳቡ ሁሉ ማክዳ ጋር ነበር ። ድንገት በሩ
በሀይል ሲከፈት ደነገጠ ማክዳ ነበረች መጣችና ሁለቴ በጥፊ አጮለችው እና
" ከዚህ በኋላ ሁለተኛ እንዳታየኝ እሺ ሄደህ ያቺን እያት " አለችው ። ደንግጦ
ጉንጩን እያሻሸ ።
" መቼ አየሁሽ ..... አየሀኝ የምትይኝ ?" አላት
" ይሄ ቅጠልህን ይዘህ ስትመጣ ነዋ ወደ ቤታችን የተመለከትከው " አለች
" እና ቤቱን ማየት አንቺን ማየት ነው ?"
" አዎ.... በቃ... አትይ አትይ ነው!! " ብላ ልትወጣ ስትል መዓዛ በር ላይ
ቆማለች። .........
~ ይቀጥላል ~

@Kooblife
@Kooblife

For any comment
@Ethio96bot
4.6K views12:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 13:27:45 ​​​​ከጭኔ ገብቶ የሚወዘውዘኝ ሰው ነው በጣም
ተርቤያለው "አለችው ።ታረቀኝ በምን ያህል በፍጥነት ልብሱን እንዳወላለቀ
አላወቀም ባዶ እራቁቱን ሆኖ ዘሎ ወጣባት ስሜቱ አልጋ ጋር እስኪደርሱ ጊዜ
አልሰጠውም መሬቱ ላይ ተያይዘው ወደቁ ጭኖቿን በሀይል ከፈተው ለምንም
እድል አልሰጠም ጭኗ ወስጥ ገባ።
" ምነው ገና በቁምህ ጨርሰሀል እንዴ?" አለችው።
ምሽቱ እንዲህ አልፎ ነው የነጋው።
" ምን ፈልገህ መጣህ ?" አለችው ማክዳ በጥላቻ እያየቺው
" ማለት አልገባኝም " አላት ግራ በገባው ሁኔታ ኬብሮን። ለረዥም ደቂቃዎች
ሲተያዩ ቆይተው።
" ማታ አብረሀት እየተዝናናህ አብራህ ካደረቺው ጋር እዛው አትሆንም እኔ ድሀዋ
ምንም የሌለኝ ጋር ምን አመጣህ?" አለች ኬብሮን ገርሞት እየሳቀ።
" የሆነ ማድረግ የነበረብኝ ነገር ነበር አደረኩ ከዛ ግን አብሬ አላደርኩም ለሊት
ትቼያት ወጣሁ " አላት
" እሱን እኮ ነው ያልኩሁ .... እኔ የአንተ አለመፈለግ እንጂ እኔ ከልክዬሀለው እቢ
ብዬህ ነበር ?.... ውጣልኝ እንደውም " አለች በጩሀት እያለቀሰች።
" ማኪ አንቺ እንዳሰብሺው አይደለም ምንም አለረኳትም እምልልሻለው " አላትና
አጠገቧ ሄዶ አልጋ ላይ ተቀምጦ አቅፎ ሊስማት ሲል በንዴት ከተኛችበት ተነስታ
በጥፊ ጉንጩን አቅልታው እንዲወጣላት ነገረቺው በዚህ ጊዜ ተናደደ
አመነጫጨቀችው።
" እረ ቆይ ቢሆንስ ባደርግስ አንቺ ምኔ ነሽ የምፀፀተው የማዝነው ካደረኩም በቃ
እንኳን አደረኩ አያገበሻም " አላትና ወጥቶ ሄደ እሷም እሱም በየቤታቸው
ማልቀስ ጀመሩ ።
ሰላም ፖሊስ ጣቢያ ሄዳ ለረዥም ጊዜ ፍቅረኛዋ የሆነውን ጓደኛዋን ከትላንት
ጀምሮ እንዳላገኘችው እናም አንድ ሰው ሚስቴን ገሏል እገለዋለው እያለ
እንደነበርና ለእሷም መጥቶ እንደዛተ ተናግራ የተጠርጣሪው ስም ስዩም የሚባል
እንደሆነ አመልክታ በሄደች በጥቂት ሰአታት ውስጥ የአድማሱ አስክሬን
እንደተገኘ እሷንም ጠርተው ሲያሳያት እሱ እንደሆነና ገዳዩም ስዩም እንደሚሆን
ተናግራ ሄደች። ወዲያው የስዩም ፎቶ ተበትኖ በሀገሪቱ ተፈልጎ እንዲያዝ ትዕዛዝ
ተላለፈ።..........
~~~~ ይቀጥላል ~~~

@Kooblife
@Kooblife

For any comment
@Ethio96bot
10.6K views10:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 13:27:45 ሲሆን ልጆች አንደኛውን መርጠው ለሌላኛው ለሌኛው ብዙ ስሜት
ላይኖራቸው ይችላሉ እንደ ስጦታ።
" ስለ ሁሉም ነገር እኮ ሚኪ እንደ ትልቅ ሰው ቁጭ አርጎ ነግሮኛል .....
የሚያሳዝነኝ ምን እንደሆነ ታውቂያለሽ በዚህ ወቅት ምግብ በላስቲክ ገዝቶ
መጥቶ ሲበላ አያሳዝንም " አለቻት ሚጣ ስጦትን እያየቻት ።
" በጣም እንጂ ለዚህ ሁሉ ተጠያቂዋ እርኩሷ እናቴ ነች አሁን ግን እኔ አለሁለት
በደንብ እከባከበዋለው አዳሪ ት/ቤት አልሄድም ማንም ቢጠራኝ ከእሱ ውጪ
የትም አልቀሳቀስም" አለች ስጦት የሚጣ ፍላጎት ይሄ አልነበረም በአይሆንም
እራሷን ነቀነቀችና ።
" አንቺ ተማሪ ነሽ አባትሽን ትከባከቢያለሽ ወይስ ትምህርት ትማሪያለሽ እሱም
እሺ አይልሽም እኔ ግን ሌላ ሀሳብ አለኝ"
" ምን " አለች ሰጦታ በጉጉት።
" እኔ አሁን ብቸኛ ነኝ አንቺም ብቸኛ ነሽ አይደል ? እኔ እህት ብትኖረኝ ደስ
ይለኛል አንቺስ ደስ ይልሻል ? " አለቻት በጉጉት መልሷን እየጠበቀች ።
" እንዴ በጣም ነው ደስ የሚለኝ ሁሌም እህትና ወንድም ወንድማማቾች ወይም
እህታማቾች ሳይ እኔ መቼ ይሆን የሚኖረኝ እላለው " አለቻት በሰመመን በህልም
ዓለም እየዋኘች እየበረች እየተሳፈፈች።
" የእኔ እናት እኮ እንደ ሚኪ ባይሆንም ጥሩ እና ውስጧ ምንም የሌላት ምስኪን
ነች ደግሞ አንቺን ሳይሽ እህቴ በሆነች ብዬ ተመኘሁ ሚኪ እና ሰርኬን
እናጋባቸው " አለች
" አውቄ ብሻለው ባክሽ ዳር ዳር ስትይኝ ...... እኔም ወድጄሻለው .......
ለአባቴም አስባለው .....ከዛሬ ጀምሮ ወደ ማጣበስ ስራችን እንሂድ .." በደስታ
ተጨባበጡ ተሳሳሙ።
አድማሱና ኬብሮን ቆመው ለትንሽ ተያዩ ፍጥጥ ተባብለው ሲተያዩ ቆዩና
አድማሱ እራቁቷን ያለቺውን ሰላምን አያት በጣም ተናዷል ሰላም ዝም ብላ
ታወራለች።
" አንተ አህያ ሚስቴ እኮ ነች " አለው ተቆጥቶ
" እኔ የምታልብህ ነች መቼ አልኩ " አለው ፈገግ ካለ በኋላ
" እንዴት ሚስቴን ታወጣታለህ?" አለው ወደ እሱ እየተጠጋ በጩሀት ።
" ታሾፋለህ እኔ እሷን ላወጣት .... በምን አቅሜ ስታየኝ እሷን እችላታለው ....
ትረማለህ እሷ ልታወጣኝ ስትል ለምን ለባልሽ ታማኝ ሁኚ ስላት እሱ ልክስክስ
ግማታም ነው በጣም ይሸታል ካልሲው ብብቱማ ለብቻው የሞተ ይመስለኛል
በጣም ይሸታል አፍ አይጥ የሞተበት ይመስላል ከእሱ ጋር የምተኛው እንደ ውሻ
አድርግ ያልኩቱን ስለሚያረግልኝ ነው እንጂ አንድ ደቂቃ ከእሱ ጋር አይተኛም
ስትለኝ ለባልሽ ታማኝ ሁኚለት ብያት ልሄድ ስል ያገኘሁሁ " አለው የውሸቱን
" እሷ ነች ይህን ያለችህ " አለውና ጫማውን አውልቆ አሸተተው ወደ ኬብሮን
አፍንጫ ሲወስደው ኬቡ እንዲተው ነገረው ቀጠለና ብብቱን.......
" አድሜ ውሸቱን ነው እውነት አላልኩትም " አለች እያለቀሰች
" አንቺ ቆይ በጨረፍታ እኮ ስለመግባት ስታወሩ ሰምቼያለው አንተ ሂድ እኔና እሷ
እንጨርሳለን " አለው ኬቡም ሀሳብ ሳይቀይርበት አመስግኖት ሲወጣ እየጮሀ
እየሰደባት ወደ እሷ ተጠጋና በቦክስ መታት ወደቀች በአፏ ደም እየፈሰሰ።
" አድማሱ በቃ አለቀልህ አንተም ኬብሮንም ትሞታላቹሁ " አለች እየሳቀች ።
እሱም እሱ እንደሚገላት ተናግሮ ዘወር ሲል ግንባሩ ላይ ሽጉጥ ተደቀነና ተተኮሰ
ግንባሩን በሳው ፈገግ አለች።
በንጋታው ጠዋት ለሊቱ ለሊት ሲይመስላት አዳሯን በለቅሶ ነው ያደረቺው
የኬብሮን ከሰላም ጋር መሆኑ አናዶታል ከልቧ ነበር የምታፈቅረው ማታ ሚካኤሌ
ሊያፅናናት ሊያግባባት ምን እንዳላደረገ ሊያሳምናት ሞክሯል ግን አልሆነለትም
ከዚህ በኋላ በትገለው ኬብሮንን በወደደች አይኑን እንኳን ማየት አትፈልግም ።
በዚህ ወቅት የመኝታ ቤት በር ተንኳኳ ከዚህ ቀደም ሳሎን ውስጥ ፍራሽ አጥንፋ
ከሚጣ ጋር ነበር የምትተኛው አሁን ሳሎን ሶፋ ላይ ሰርካለም ስለተኛች
በሰርካለም መኝታ ቤት ከሚጣጋ ነበር የተኛቺው እሷ ከእንቅልፋ ተነስታ ወጥታ
ሄዳለች ኮደሚኒየሙም በለ አንድ መኝታ ክፍል ነው። የተንኳኳው በር ተከፍቶ
ኬብሮን ገባ ዘወር ብላ በጥላቻ አየቺው እሱ በፈገግታ ..........
~~~~ ይቀጥላል ~~~~


ብቸኝነቴን .... መልሺልኝ

ክፍል ሰላሳ (30)
.
.
.
" እስከ አሁን ምን አስቆየህ ቶሎ ና አይደል ያልኩል " አለች ሰላም ከፊቷ
ጭንቅላቱ በጥይት ተበስቶ የሞተውን አድማሱን እና ገዳዩን በእጁ ሽጉጥ ይዞ
የቆመውን ታረቀኝን እየተመለከተች።
ታረቀኝ ማለት የዛሬ ወዳጇ አይደለም የቆየ ነው እረዥም ጊዜ በእሷ ፍቅር
የሚሰቃይ ወጣት ነው እሷ ግን በጣም ስለምትጠላው ገና ስታየው እብድ
እንዳየች ትሸሸዋለች ። ከእሱ ጋር ሰው ፊት መቅረብ አይቻልም መልኩ የሰው
አይመስልም የጎማሬ እንጂ ትላለች ነገር አለባበሱ እና በጣም እራሱን መጠበቁ
የናጠጠ ሀብታም ያስመስለዋል ብራድ እና ውድ ልብሶች ነው የሚለብሰው እሱ
በአንድ የውጭ የእርዳታ ድርጅት ሹፌር እንደሆነ ነግሯታል ስታስበው ደመወዙን
ለዚህ ጉዳይ ለልብሱ ነው የሚጨርሰው ብላ ታስባለች የማያምረውንም
መልኩን በውድ ልብሶቹ ነው የሚሸፍነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ሰራተኞቹ
ሲሸሿት ድርጅቱንም መምራት ሲከብዳት ለአድማሱ ማስታወቂያ ለጥፍና ሰራተኛ
ቅጠር ስትለው እሱ መጥቶ ተወዳድሮ ነበር ያቀረበው መረጃ ደግሞ በአንድ
የግል ድርጅት ብቃት ያለው ስራ አስኪያጅ እንደ ነበረ የሚያሳይ ነው ። ስለዚህ
ም/ስራ አስኪያጅ አድርጋው ሙሉ ለሙሉ ስራውን ለእሱ ትታዋለች። ወደ ቢሮ
በሄደች ቁጥር እያያት አይኑ እንደሚከራተት ከቀሚሷ እና ከፓንቷ ስር በሀሳብ
እየገባ እራሱን እንደሚያዝናና ስለተረዳቺው አንድ ቀን እንደሚጠቅማት ስታስብ
ነበር ይሀው ዛሬ ጠቀማት ። ለሚካኤሌ ፎቶውን በላከቺበት ቅፅፈት ለእሱም
መልእክት "ልሞትልህ ነው ና ቶሎ ድረስልኝ " ብላ ፅፋለት ነው የመጣው
" እንዴ ይሄ እኮ ባልሽ ነው ገደልኩት " አላት በድንጋጤ
" ሁሌም ለአንቺ ህይወቴን እሰጣለው ትለኝ አልነበር " አለች
" አሁንም እሰጣለው መቼም ቢሆን " አላት
" አየህ ይሄ ሆዳምና የገንዘብ ሰው ነው የድሮ ፍቅረኛውን ከፎቅ ወርውሮ ገሏት
ነው የመጣው አሁን እኔንም ገሎ ሀብትና ንብረቴን ሊወርስ ነበር አንተ
ባትደርስልኝ " ብላ ከተቀመጠችበት በመነሳት ወደ እሷ ሄዳ አቀፈቺው እናም
አለቀሰች ። እሱ አሁን የተረዳው ነገር ከፓንት ውጪ ምንም እንዳላደረገች ትዝ
ሲለው ሰውነቱ ነዘረው አቀፋት ቀጥሎ አፅናናት እና ሁሌም ከእሷ ጋር መሆኑን
ነገራት እሷ ግን ከጀርባው ሆና እያላገጠችበት ነበር ። ከእቅፍ ወጣችና ወደ
ጀርባው ሄደች እሱ ደግሞ የአድማሱን አስከሬን እያየ ቁጢጥ አለና ።
" አሁን ሶልዬ ይሄን ምን እናርገው " አላት ወደ አስክሬኑ እያየ
" እኔ የምልህ የትኛው ይሻልሀል " አለችው ዞሮ አላያትም።
" አስክሬኑን ቅድሚያ ከማንሳትና ወይም ከዚህ..." አለችው። ቀስ ብሎ ዘወር
በማለት ተመለከታት አሁን ፓንቷም ወልቋል አይኑ ፈጠጠ አፍን ከፈተ
የሚከድነው ደጋግሞ እየመጣበት ያለውን ምራቅ ለመዋጥ ነው ከተቀመጠበት
ተነስቶ ቆመ እንጆሪ የመሰሉ ከንፈሮቿን ቀጠለ የጠነከሩ የመሰሉ ጡቶቿን
ቀጥሎ እንብርቷን ሲያይ አለጋ በመሰሉት የእጆቿ ጣቶች እየተራመደች ወደ ታች
ስትወረድ ተመለከተና ከጣቷ ቀድሞ ያንን ተመለከተ የሚያምሩት ጭኖቿን
እግሮቿን አየና የመጨረሻውን ምራቅ ውጦ ።
".......እእ ..... እእ ..... ማ ..... ለቴ .... ምን እናረገው ....... " አላት ውብ ገላዋ
እና የወሲብ ጥማቱ አንደበቱን ቆልፈውት። እሷ ደግሞ ቁልቁል ወደ ሱሪው
ተመለከተች ድንኳን የሰራውን የሱሪውን ዚፕ አካባቢ አየችና።
" እኔን ያሳሰበኝ እሱ ሳይሆን
7.9K views10:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 13:27:45 ብቸኝነቴን...... መልሺልኝ

ክፍል ሀያ ስምንት (28)
.
.
ሚካኤሌ ልጁን ስጦታ እቅፍ አርጎ የሚስማት ቦታ እስኪያጣ ድረስ እሷም
በተመሳሳይ አቅፋው አጠገቡ ቁጭ ብላለች አይን አይኑን ታየዋለች።
" ቆይ በዚህ ምሽት ከየት መጣሽ የአዳሩ ትምህርትሽስ ?" አላት ሚካኤሌ ።
" በቃ ስትናፍቀኝ ድንገት ልምጣ ብዬ አድማሱን ደውዬ ጠራሁትና ውሰደኝ
ስለው እንቢ ብሎኝ በስንት ጭቅጭቅ ነው እዚህ አድርሶኝ የተመለሰው።"
አለቺው ሁሉም በግርምት እያያት ነው።
" እንዴ እናትሽንም ሳታያት ነው ወደ እዚህ ቀጥታ የመጣሺው ?" አላት ሚካኤሌ
በፍቅር እያያት
" አባ ለእኔ አንተ ነህ እናቴም አባቴም ከአንተ ውጪ ማንንም አላውቅም እሺ"
አለች ስጦታ።
" የኔ ፍቅር እንዲህማ አይባልም ውዴ የምናውቀውና የተነጋገርነው እሱ እንዳለ
ሀቅ ነው እሺ" አላት እየሳማት ።
" ታስገድደኛለህ አንተ እኔን አትፈልገኝም አትወደኝም እኔ የምፈልገው ጥሩ
እናትና አባት አለሽ እንድባል እንጂ መጥፎ እራስ ወዳድ እናትና አባት አሉሽ
እንድባል አልፈልግም "
" የኔ ልጅ እርግጠኛ ሁኚ በዚህ ከፈጣሪ በታች ህይወቱን የሚሰጥልሽ ሰው
ቢኖር እኔ ነኝ ግን...." አላት ሳይጨርስ
" በቃ እሱን አውቃለው ለእኔ አንተ በቂ ነህ ..... ሌላ ምንንም አልፈልግም
ሁለቱንም አልወዳቸውም በጣም በጣም ያስጠሉኛል አዳሪ ት/ቤት የገባሁትም
ከእነሱ ጋር ላለመኖር እኮ ነው ከአንተ መራቅ ፈልጌ አይደለም " አለችው
እያለቀሰች
" እናቴ አታልቅሺብኝ እኔ እኮ....." ሚጣ አላስጨረሰቺውም በመሀል ገባችና ።
" እንዴ መብቷ እኮ ነው ..... ለምን ታጨናንቃታለህ ከፈለገቺው ጋር ትኑር እኔም
ብሆን ምርጫዬ እንደ እሷ ነው ደግሞ እኔም ቆንጅዬ እህት አገኘሁ ማለት ነው።
" ስትል ስጦታን ጨምሮ ሁሉም በድንጋጤ ሲያያት ሰርካለም ግን ተናደደች።
ኬቡ ከወገቡ በላይ እራቁቱን ሆኖ በሁለት እጆቹ ወደ ኋላ ተደግፎ አልጋ ላይ
ቁጭ ብሎ ከፓንት ውጪ ምንም ያላረገቺው ሰላምን ያያታል እሷ ሙዚቃ ከፍታ
እየደነሰችለት በእጇ ውስኪ ይዛ የጠጣች እየመሰለች ከግራና ከቀኝ በከፈሮቿ
ጥግ እና ጥግ እየፈሰሰ ወደ ጡቶቿ ከዛ ቁልቁል ወደ እንብርቷ ከዛም እየፈሰሰ
ከዛም ...... ከዛም..... ወደ ታች ወረደ እሷም በእርጋታ ወደ እሱ ተጠጋች ወደ
ኋላ በጀርባው አንጋለለቺው ከወደ እንብርቱ መሳም ጀመራ ወደ ላይ ወጣች
ጡቶቸን አገጩን ስማው ከንፈሩን ልትስመው ስትል አሸሸባት መሳም
ከጀመረችበት ጀምሮ ፎቶ እያነሳቺው ነው ከንፈሩን ማሸሹ ምንም አልመሰላትም
ወደ ጆሮው ሄዳ ትንሽ ከሳመቺው በኋላ ወደ ከንፈሩ ሄዳ ጫፍ ላይ ስትደርስ
ኬብሮን አስቆማትና ከሰላዩ ላይ ገፋ እያደረጋት ።
" እፕፕፕፕ ምንድን ነው የሚሸተው በጣም የሚሸት አለ " አላት እንደ በፊቱ
የስካሩ ሙድ የለቀቀው በሚመስል።
" እኔ ምንም አልሸተተኝም .... ምን ይሸታል ?" አለች ግራ በማጋባት ስሜት
እያየቺው።
" የሚሸት ነገርማ አለ እእእእ .... ነው ከኋላ አስተነፈሽ እንዴ"
" ሄይ ... መቀለድህ ነው ቀልድ አያምርብክም " አለች ፈገግ ብላ እያየቺው እሱ
ግን ከላዩ ላይ ገፍትሮ አስነሳትና እሱ ቆሞ እሷ በጀርባዋ እንደተኛች ።
" እውነቱን ልንገርሽ ሽታ ሳይሆን ግማት ነው በጣም የሚገማ የሳንባ ምች
የሚያሲዝ ግማት ነው ያለው " አላት በመጠየፍ ስሜት።
" አንተ የምርህን ነው እንዴ ? " አለችው ከተኛችበት ብድግ በማለት ተቀምጣ
ቀንዴትና በቁጣ።
" ከምሬ ነው አንቺ ነሽ የምትሸቺው ቤቱን ሙሉ ነው ያገማሺው ከአሁን አሁን
ይለቃል ብዬ ነበር ግን ጭራሽ እየባሰ መተንፈስ አቃተኝ እጅግ እጅግ አንቺ
ትገሚያለሽ መቼ ነው የታጠብሺው ውሀ ቤትሽ የለም ውይይይይ .... አንድ ወር
በቦቲ ጫማ ሳይታጠብ የተደረገ ካልሲ እንኳን እንደ አንቺ አይሸትም " አላት
ሰላም በንዴት ጨሳ እና በግና ከአልጋው ተፈናጥራ ሄዳ በጥፊ ልታጮለው
ስትል እጇን ያዘውና በጥላቻ እና በንቀት እያያት።
" ትገሚያለሽ እያልኩሽ ወደ እኔ ትመጪያለሽ እንዴ? ስታስጠይ .............በዚህ
ግማት እንዴት ነው ሰው ፊት የምትቀርቢው በብርሽ ስለፈሩሽ ይሆናል መቼም
ዝም ያሉሽ" አላት ። እውነት ንዴቷን መቋቋም አልቻለች ።
" አንተ ውሻ እኔን ትገሚያለሽ ትላለህ " አለችና ግራ እጇን ሰደደች ለጥፊ
እሱንም ያዘውና ፊት ለፊት እየተያዩ።
" እንደምትገሚ ደጋግሜ ነግሬሻለው ውሻ ላልሺው በሴስኝነቱ ከሆነ አንቺ ነሽ
ውሻዋ በታማኝነቱ ከሆነ ልክ ነሽ እኔ ነኝ ሰለ ሚኪ ሰልልኝ ብለሽ የምትሰጪኝ
ብር ሰልዬልሽ አላውቅም ለሚኪ እውነቱን ነግሬው እየተጠቀምንብሽ ነበር እሺ
ጨርሰናል እውነቱን እወቂ አልሰከርኩም ነበር የአንቺን ጨዋታ ለመጫወት ነው
ደራሲ ነኝ ብር የማይገዛው እውቀት አለኝ እሺ አንድ ነገር ልበል የቆዳ የገላ
ግማት እና ሽታ በውሀ ይጠራል የውስጥ ግማት ግን ንሰሀ ካልገባሽ በምንም
አይፀዳም እንደገማሽ ትኖሪያለሽ " አለና እጇን ወርውሮ ወጥቶ ሊሄድ ሲል ከፊቱ
አድማሱ በንዴት ቆሞ እያያቸው አየውና ደንግጦ ቆመ።
ሚካኤሌ ስጦታ እና የሰርካለም ቤተሰቦች ተሰብስበው ተቀምጠው ሳለ ሚጣ
ወደ ሚኪ በመሄድ ስጦታን ይዛ እሱ ቤት እንድትሄድ ጠየቀቺው ሚኪም
የሚፈለገው ነገር ስለነበር ፈቀደላት ቁልፍ ተቀብላ ከስጦታ ጋር ተያይዘው
ሲወጡ እነሱን ተመለከተና።
" ምን ያህል አውሬ እና ጨካኝ እናት ብትሆን ነው በልጅ እንደዚህ የምትጠላው
ከዚህ በኋላ አሪፍ ጨዋታ እጫወትባታለው ጥሩነቴን አይታለች መጥፎነቴን
ደግሞ በትንሹ ላሳየት ለልጄ ብዬ ነበር እስከአሁንም ለልጄ ስል ነበር ...." እያለ
እያወራ አክስትየውን አየ ። ወዲያው ግን ሞባይሉ መልዕክት እንደገባ ድምፅ
አሰማ ከኪሱ ሲያወጣ።
" ሚኪ ቆይ እኔ ልይልህ " አለቺውና ማክዳ አጠገቡ ተቀምጣ ከፈተቺው አየቺው
ሰላም ነበረች የላከቺው ከኬብሮን ጋር ስትስመው የተነሳውን ፎቶ እያየቺው
በድንጋጤ አይኗ ፈጠጠ እንባዋ እረገፈ።.........
~~~~ ይቀጥላል ~


ብቸኝነቴን .... መልሺልኝ

ክፍል ሀያ ዘጠኝ (29)
.
.
.
" የእኔ ስም ሚስጥር ነው የአንቺን ግን አላወኩትም" አለች ሚስጥረ ከሚጣ ጋር
በሚካኤሌ ቤት ሶፋ ላይ እግራቸውንም ሶፋ ላይ አድርገው እጥፍ ጥፍ ብለው
ተቀምጠው።
" የእኔ ሚጣ ነው ..... ወይኔ ግን ሚስጥር እድለኛ ነሽ ሚኪን የመሰለ አባት
ከየትም ማንም አያገኝም " አለቻት ሚጣ መንፈሳዊ ቅናት እያደረባት ።
" እውነቱ ምን አለበት ጥቂት እንኳን የሚኪ ደም ባለብኝ እላለው ደስ የሚለኝ
ደግሞ አይኔን ስገልጥ ጀምሮ አጠገቤ ሆኖ መልካምነትን ፍቅርን እየሰበከ
ያሳደገኝ እሱ ነው ... እናቴን አልወዳትም ጭካኔ አረመኔነት እራስ ወዳድነትን
ነበር የምትሰብከኝ በቃ በጣም ነው የምታስጠላኝ ከእሷ ምንም ነገር መውረስ
አልፈልግም መኖርም ጭምር " አለች ለሰላም እጅግ የበዛ ጥላቻ እንዳላት
በሚያስታውቅ የምሬት ድምፅ ለእውነትም የልጆች በሀሪ የአካባቢና የቤተሰብ
ድምር ውጤት ነው ። ብዙ ጊዜ በጥሩ ቤተሰብ የኑሮ ደረጃ ላይ ያደጉ ልጆች
ከቤተሰብ ብዙውን በሀሪ ይወስዳሉ ። እናትም አባትም መጥፎ ከሆኑ ብዙውን
ጊዜ ልጆቹም መጥፎ ሆነው ያድጋሉ ነገር ግን እንደ ሰላምና ሚካኤሌ አይነት
በሀሪ
4.7K views10:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 13:27:45 ​​ ብቸኝነቴን ......መልሺልኝ

ክፍል ሀያ ሰባት (27)
.
ሰላም ዛሬ ብርሀን ሆኖ እንደዋለው ቀን ምሽቷን ብርሀን ለማድረግ አስባ
ለኬብሮን ብዙ ብር አውጥታ ገላውን ፍልውሀ ገብቶ በንድብ እንዲታጠብ
አድርጋ ልብስ ገዝታለን እጅግ ውብ አድርጋው ለሚካኤሌ የደወለቺው እሱ ግን
ጭራሽ ስቆ እሷን አናደዳት በህይወቷ እንደ እሱ አይነት ወንድ አልገጠማትም
የእሱን ንዴት ለማየት ስትደክም እረ እሱ ምን በወጣው ጭራሽ እሷን ያናድዳታል
በዚህ ካልተናደደ ችግር የለም ሁለተኛውን ጥይቴን እተኩሳለው።
" ምነው ሳክ ደስ አለህ እንዴ " አለችው ሰላም።
"በጣም እንጂ ካረገ ከመቆየቱ የተነሳ ቦታ ሁሉ ሳይጠፋው አይቀርም አንቺ
ደግሞ እንደምታስደስቺው ቦታውን እንደምታሳይው አምናለው መልካም አዳር "
አላት እየሳቀ
" ቆይ እንዳትዘጋው ...... ምን እያልክ ነው" አለች ተናዳ።
" ገብቶሻል ምነው ተገረምሽ ..... መልካም ምኞቴን ነው የገለፅኩልሽ እሺ "
አላት ሰላም አለመናደዱ ጭስስ እርር ድብን ነው ያረጋት እውነቱ ግን ለእሷ
ያልተናደደ ይምሰል እንጂ ከእሷ በበለጠ እርሱ ውስጥ አንጀቱ ከስሏል ግን ምን
ማረግ ይችላል እሷ ሰውን ለማሳበድ ለማናደድ ስትጥር ተናዶ እሷን ከማስደሰት
የሆድን በሆድ ይዞ ለሰው ያሰበችውን ለእሷ ማድረግ ይሄ ነው ምርጡ ሀሳብ
ቀድሞ የተዘጋጀበት።
" አንድ አንዴ ሳስበው እብድ ትመስለኛለህ የድሮ ባለቤቴ " አለች ሰላም ዳግም
ስሜቱን ለመረዳት።
" አይይ የድሮ ሚስቴ ምን አንድ አንዴ ነው ሁሌም ነው እንጂ ምን ታረጊዋለሽ
አብዳ የምታሳብድ ሚስት ለጥቂት ጊዜ አግብቼ ነበር ለዛ ነው " አላት እና ከት
ብሎ ደጋግሞ ሳቀ ሰላም አናቷ የነደደ መሰላት ፀጉሮቿ ቀጥ ብለው እንደ ስልክ
እንጨት ቆሙ።
" ቆይ አንተ ምንድን ነው የሚያስገለፍጥህ ግልፍጥ ...." አለችው በጣም ተናዳ
እሱ እንደገና ሳቀ ንግግሯን ቀጠለች።
" ..... የጓደኛህ የቶማስ ሚስት ቃልኪዳን መሞቷን እእ መገደሏን ሰማህ?..."
አለችው ሚኪ ሳቁን አቆመ ክው ብሎ ቀረ ዝምምም ጭጭጭጭ ለደቂቃዎች
አይምሮው የተናጋ መሰለው አይኑ ፈዞ በአንድ ቦታ ተተክሎ ቀረ።
" የት ሄድክ አሀን በደንብ ደነገጥክ አይደል " አለችው ሰላም በእርካታ በደስታ
ተውጣ።
" አዎ ደንገጬያለው ሰላም ..... የደነገጥኩት ለአንቺ ነው ቶማስ በሚስቱ
ሚስቱም በእሱ የመጣባቸውን ሰው አይምሩም ይገልሻል እውነቴን ነው አትሞኚ
ፍቅር እና ትዳር ለአንቺ ነው ጥቅም ለአንቺ ነው እቃቃ ጨዋታ ለአንቺ ነው
ሴሰኝነት ለእንደ ዕነ ቶማስ አይነቱ ዓለም ነው ህይወት ነው ፀጋና በረከት
የሞላበት ነው ተጠንቀቂ ይገልሻል" አላት የደነገጠው ግን ለእሷ አልነበረም
ለቃልኪዳን ለቶማስም ነው የነገራትም ነገር ይገልሻል ያላት እውነት ነው። እሷ
ከት ብላ ስትስቅ እሱ ልክ እሷ ስልኩን ስትዘጋው እሱ በጣም ተናዶ በሀይል
ጮሆ ስልኩን ከኮሪደሩ ጋር ፈጠፈጠው በጩሀቱ ሁሉም ሰምተውት ነበረና ከቤት
ከሰርካለም ውጪ ሁሉም እየሮጡ ወጡ ሲያይት መሬት ላይ ተንበርክኮ ሲያለቅስ
ተመለከቱት ሚጣ እየሮጠች ሄደችና አቀፈቺውና ምን እንደሆነ ጠየቀቺው እሷም
እያለቀሰች ወደቤት ይዘውት ገቡ።
ኬብሮን ፅድት ብሎ በጣም ሰክሮ ሶፋ ወንበር ተቀምጦ እየጠጣ ሲጋራ እየሳበ
ቆየ የሚያጨሰውን ሲጋራ ልክ እንዳጠፋው ሰላም በነጭ የለሊት ልብስ
(በቢጃማ ) ካለ ጡት ማስያዣ ያለውን ጡቷን እና ፓንቷን እያሳየች መጣች
ኬብሮን ልክ እንዳያት አይኑ ፈጠጠ እና አፍን ከፈተ።
" አሁን የትኛውን እንቀጥል መጠጡ ወይስ ይሄ ውብ ሰውነት" አለችው ሰላም
ፈገግ ብላ ውብ ሰውነቷን ገልፃ እያሳየቺው እሱም ፈገግ ብሎ እየተገዳገደ
በመሄድ ጉንጯን ሳማትና ።
" በሾህ የታጠረው ፅጌሬዳ አበባ አይሻለኝም " አላት ፈገግ ብለው ወደ መኝታ
ክፍል ገቡ።
" በጣም የምወደው ልጅ ነው ታማኝ ባልና ሚስት ናቸው ግን ምን ያደርጋል
በመሀል ሴጣን ገባ አልሳካ ሲለው ገደላት የምታሳዝን ታማኝ አፍቃሪ ትዳሯን
ባሏን አክባሪ ነበረች " እያለ ሚኪ አለቀሰ ሚጣ አጠገቡ ሆና አቅፋው
እያፅናናችው።
" ሴጣን ይመጣል እንዴ ?" አለችው ሁሉም አያት ።
" አዎ ሚጣዬ የድሮ ሚስቴ ሴጣን ነች እሷ ነች የገደለቻት ... አሁን ግን ባሏ
ይገላታል ከገደላት ደግሞ ሁለት ልጆቹን ጥሎ እስር ቤት ይገባል ከዛ ልጆቹ ......
ሄጄ ላስቆመው ይገባል አዎ ልሂድና ላስቁመው " ብሎ ወደ በሩ ከሚጣ ጋር
ሲሄድ ሰርካለም አየችውና ጠራችው ቆም ሲል ።
" ሚኪ እኔንም እንደዚህ ያረገችኝ እሷ ናት " አለችው ሁሉም ደንግጠው ወደ
ሰርካለም ሲመለከቱ በሩ ተንኳኳ ሚጣ እሮጣ ሄዳ ከፈተች አንዲት ቆንጅዬ
የእሷ እድሜ እኩያ በር ላይ ቆማለች ተያዩ።
" ይቅርታ እዚህ ቤት የሚኖረው የት ሄዶ ነው?" አለች ወደ ዕነ ሚኪ ቤት እያሳየች
በዚህ ወቅት ውስጥ ስታየው "....የኔ አባት ናፍቀሀኝ ነበር " ብላ እሮጣ
አቀፈቺው እሱም እቅፍ አረጋትና።
" ልጄ ወዴ ፍቅሬ በዚህ ምሽት ከየት ተገኘሺልኝ " አላት አቅፎ በፍቅር እየሳማት
ሰርካለም በቅናት አንጀቷ ሲያር ሚጣ ተደሰተች አክስቷ እና ማክዳ በድንጋጤ
እንቆቅልሽ ሆኖባቸው ያያሉ።...........
:~~~~~~~~~ ይቀጥላል ~~~~

@Kooblife
@Kooblife

For any comment
@Ethio96bot
5.0K views10:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ