Get Mystery Box with random crypto!

ETHIO BOOKS PDF

የቴሌግራም ቻናል አርማ kooblife — ETHIO BOOKS PDF E
የቴሌግራም ቻናል አርማ kooblife — ETHIO BOOKS PDF
የሰርጥ አድራሻ: @kooblife
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 10.63K
የሰርጥ መግለጫ

➥ እዚህ ቻናል ላይ የተለያዮ ተከታታይ ታሪኮች (ልቦለዶች) ና ፍልስፈና ሳይኮሎጂ የአማረኛ እና English መጽሀፍትን በ📓PDF እና ትረካዎችን እና መሳጭ ግጥሞችን ሌሎችም ጠቃሚ ነገሮች ያገኛሉ።

ለሃሳብ ና አስተያየት ለመጠየቅ @Ethio96bot

📖 ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል‼️

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-03-11 12:10:03 አምስተኛው ዙር የውድድር ማስታወቂያ

@ETHIO_BOOKS_PDF1 እንደ ሁልጊዜው
ግሩፕ ውስጥ የራስዎትን ጓደኛ ሲያስገቡ (ADD) ሲያደርጉ ብዙ ጓደኞችን ላደረጉ ሽልማት አዘጋጅተናል።

የቆይታ ጊዜ ከዛሬ ጀምሮ ለ 19 ሰአት ብቻ ይቆያል::

የሽልማት ዝርዝር

1ኛ.ለወጣ - የ 1ሺ ብር ስጦታ
2ኛ.ለወጣ - 4GB ወርሀዊ የዳታ ጥቅል
3ኛ.ለወጣ - 3GB ወርሃዊ የዳታ ጥቅል
4ኛ.ለወጣ - 2GB ወርሃዊ የዳታ ጥቅል
5ኛ.ለወጣ - 1GB ወርሃዊ የዳታ ጥቅል
6ኛ.ለወጣ - 500MB ወርሃዊ የዳታ ጥቅል
7ኛ.ለወጣ - 100 ብር ካርድ
8ኛ.ለወጣ - 50 ብር ካርድ
9ኛ.ለወጣ - 25 ብር ካርድ

የመወዳደሪያ ግሩፕ ሊንክ
@ETHIO_BOOKS_PDF1
@ETHIO_BOOKS_PDF1
@ETHIO_BOOKS_PDF1
@ETHIO_BOOKS_PDF1

ለወዳጅ ዘመድዎ ያጋሩ መልካም ዕድል
1.5K viewsedited  09:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-20 12:01:38 https://t.me/+qMTZKfzaQr5mMjY0
8.8K views09:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-27 15:59:54
አሳዛኝ መረጃ

ተወዳጁ ድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ አርፏል። ድምጻዊው ባደረበት ህመም ምክንያት ማረፉን የቅርብ ወዳጆቹ ገልጸዋል።

ድምፆዊ ማዲጎ አፈወርቅ ዘመን የሚሻገር የድንቅ ስራ ባለቤት ነው።

ነፍስህ በአፀደ ገነት ትኑር ኮከቡ


@Kooblife
@Kooblife
▬▬▬▬▬▬▬▬
1.5K views12:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-27 15:58:54 ​​ ብቸኝነቴን ..... መልሺልኝ

ክፍል አርባ አንድ (41)
.
.
.
አስቡ ይሄም ከአመታት በፊት ያለ ታሪክ ነው።
ህይወት የአንድ ወቅት ብርሀን የአንድ ወቅት ጨለማ እና መከራ ነው ። ሚካኤሌ
ከደረሰበት አደጋ ከሞት ተርፏል በሰውነቱ ላይ ተሰካክተው የነበሩት የመኪናው
የፊት መስታወት ስብርባሪ እዚሁ ባለ ህክምና ተነቃቅለው ወጥተዋል በአይኖቹ
ላይ የተሰኩት ግን መስታወቱ ቢወጡም አይኑ ማየት አልቻለም ።
አድማሱና ሰላም ሚካኤሌ ሆ/ል እያለ አብረው አድረው ጠዋት ቁርስ ስጦታም
አብራ ተቀምጣ እየበሉ ሳለ።
" ቆይ እኔ የምልህ አድማሱ " አለች ስጦታ የሁለቱን ሁኔታ ካየች በኋላ ምንም
የሚጥም ነገር በለማየቷ ።
" እሺ ስጦትዬ የኔ ቆንጆ ምን ነበር ? " አላት ፈገግ ብሎ እየተመለከታት ።
" ለምንድን ነው እዚህ ቤት ያደረከው " አለችው በጥላቻ እያየቺው ። ሁለቱም
በግርምት ተመለከቷት ።
" ምን ማለት ነው የኔ ልጅ " አለች ሰላም በመሀል በመግባት።
" እንደዚህማ አትበይ እማዬ አባቴ እቤት በሌለበት ወንድ ልጅ እንዴት ያድራል "
አለች ።
" አንቺ ልጅ እንደ ልጅ ሁኚ እንጂ ምንድን ነው እንዲህ አደኩ አደኩ የምትይው
........ እዩኝ እዩኝ የምትይው " አለች ሰላም
" ይሄ የአባቴ እና የቤተሰቤ ጉዳይ እኮ ነው " አለች ስጦት
" የኔ ልጅ እኔ እኮ የአጎቷ ልጅ እኮ ነኝ " አለ አድማሱ
" ማን ያውቃል ..... ቢሆንስ ደግሞ አባወራ በሌለበት ቤት ማንም ሁን ማደርህን
እኔ አልፈልግም " ስትል ሰላም ከተቀመጠችበት በንዴት ተነስታ ስጦታን በጥፊ
ጉንጯን አቀላቻትና በንዴት በዛቻ።
" አንቺ እርኩስ መናጢ ልጅ ...... ሂጂ ውጪና ቁርስሽን እቤትሽ ሄደሽ ብዪ
በጠዋቱ ቀኔን አትበጭብጪ .... እንደውም እዛው አዳሪ ት/ቤትሽ ወስጄ
እወረውርሻለው እሺ ያኔ ዋጋሽን ታገኚያለሽ አሁን ሂጂ ወደ እዛ " አለቻት በጥላቻ
እና በመጠየፍ ስጦታ የተመቻውን ጉንጯን እያሻሸች እና እያለቀሰች ወደ ክፍሏ
የሚወስደውን መንገድ በፍጥነት እየተራመደች ሄደች።
" ለምንድን ነው እንደዚህ መጥፎ የምትሆኚባት " አላት
" ምን አገባህ አንተ ባክህ ዝም በል .... እኔ የእሱ አለመሞት ጭራሽ አናዶኛል
አንተ እዚህ እንደገና ታናደኛለህ " አለች በቁጣ አድማሱ በግርምት አያትና።
" ታዲያ ምን ያናድድሻል " አላት
" አትሰማም እንዴ የምልህን አልሞተም እኮ ነው እያልኩሁ ያለሁት ታሾፋለህ "
አለችው
" ይሀውልሽ የኔ ቆንጆ አይሙት ጥሩ አማራጭ ነው እንደውም ተረጋጊና ቁጭ
ብለሽ ልነግርሽ እሺ " አላት
" ሌላ አማራጭ አለህ ደስ ሲል እሺ ንገረኝ " አለች በጉጉት
" ሳስበው መሞቱ ትርጉም የለውም ነበር ለአንቺም ውጣ ወረድ ነበር የሚኖረው
ስለዚህ አይኑ ጠፍቶ በህይወት መኖሩ ላይ እኛ ዳማ እንጫወትበታለን " አላት
" እንዴት እንደሆነ ንገረኝ ሌላውን ወሬ ተወውና " አለች
" ይሀውልሽ .........." አላት እና ሁሉንም ነገር ዝርዝር አድርጎ ነገራት ሰላም አፏን
ከፍታ ነበር ትሰማው የነበረው ልክ እንደጨረሰ ዘላ አቀፈችውና ደጋግማ ስማው

" ለዚህ ምርጥ ሀሳብህ እና እቅድህ ጥሩ አሰጣጥ ያስፈልገሀል ምርጥ ስጦታዬ
ይሆናል የኔ ቆንጆ " አለችውና ይዛው ወደ መኝታ ክፍል እየገባች በሀሳቧ " አንተ
ጅል ይሄ እቅድህ ሲፈፀም እኔ የናጠጠ ሀብታም አንተ ድሀ ትሆንና
አስወግድሀለው " እያለች እራቁታቸውን አልጋዋ ላይ ተያይዘው ወደቁ።
ሚካኤሌ አይኑን ወደ ውጭ ሄዶ እንዲሞክር ተነግሮት ከሀኪም ቤት ወጣ እናም
ወደ ቤቱ ሄደ ። አይኑ ማየት ስለማይችል ሙሉ የስራውን ሀላፊነት ለሰላም ሰጥቶ
አድማሱም እንዲረዳት አድርጓል የግድ በእሱ እጅ የሚፈረሙትን ይዛ እየመጣች
ታስፈርመው ነበር።
አንድ ቀን ሰላምም አድማሱም ወደ ድርጅቱ በሄዱበት ወቅት ከስጦታ ጋር
አብረው ቁጭ ብለው ሳለ ስጦታ።
" አባ አንድ ነገር ልነግርህ ነበር ግን እንዳላስከፋህ ፈራሁ " አለች ሚካኤሌ
እቅፍ ውስጥ እየገባች።
" አንቺ እኮ ልጄ ነሽ በአንቺ እንዴት እቀየማለው " አላት እቅፍ አርጎ እየሳማት ።
" አውቃለው አንተ የእኔ ብቻ ሳትሆን የፍቅር አባት ነህ " ስትለው ድጋሚ በደንብ
አቅፏት ሳማት ።
" እሺ በይ ንገሪኛ የኔ ልጅ "
" አንተ ሀኪም ቤት ሳለህ እሱ እዚህ ቤት ነበር የሚያድረው "
" አይ ልጄ ታዲያ ምን ችግር አለው የአጎቷ ልጅ እኮ ነው " አላት ነገሩን ቀለል
አድርጎ።
" በምን አወክ እነሱ ስለነገሩህ ብቻ እኔ ግን አባ ደስ አላለኝም እባክህ
ተጠንቀቅ " አለች ስጦታ።
" ልጄ የአጎቴ ልጅ ነው ካለች ማመን ነው ያለብን ህፃን ልጅ አይደለችም እሷን
የምንቆጣጠራት እውነት እኔንና ትዳሯን ካከበረች የትም አትሄድም ካላከበረች
የፈለገቺውን ታድርግ የእኔ ሀላፊነት ልጄ እንደ አባትነት አንቺን መውደድ ማፍቀር
ማስተማር መሰረታዊ ነገሮችሽን ሟሟላት እንደ ባል ደግሞ ትዳሬን ቤቴን
ቤተሰቤን ሚስቴን መውደድ ማክበር ታማኝ መሆንና እሷንም ማመን ነው
አይመስልሽም ልጄ " አላት
" አባቴ ስለሆንክ እኮራለው ከዛ ትምህርት በላይ የአንተ ትምህርት መንፈሴን
ይሞላዋል"አለችውና ተቃቅፈው ተሳሳሙ
ጊዜያቶች ሲሄዱ ሚካኤሌ ለአይኑ ህክምና ውጭ መሄድ ነበረበት ስለዚህ እሱ
በአጠገቧ ስለሌለ ፊርማውን እራሷ ፈርማ እንድታስተዳድር ሙሉ ሀላፊነቱን
በውክልና ሊሰጣት ሲያስብ ሰላምና አድማሱ በዚህ ወቅት አይኑ ባለማየቱ
እቅዳቸውን ለመፈፀም ዝግጅታቸውን አጠናቀቁ በአጠገቡ ስጦታ እንዳትኖርና
ውሉን እንዳታነበው አርቀው ወደ አዳሪ ት/ቤት ላኳት ። በቃ ሁሉም ነገር ለሰላም
እንደሸጠላት የሚገልፅ ውል ይዘው ወደ ቤት መጡ።.......
~ ይቀጥላል ~

@Kooblife
@Kooblife

For any comment
@Ethio96bot
1.5K views12:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-25 15:20:18 አርማጌዶን
በ ዶ.ር ጆን ኤፍ ዋልቮርድ ተፃፈ። ተርጓሚ ሰሌሞን ደጀኔ
የነዳጅ ዘይትና የመካከለኛው ምስራቅ ውዝግብ
መፅሀፍ ቅዱስ ስለ መካከለኛው ምስራቅና የምዕራብ ስልጣኔ ማብቂያ የሚነግረን ነገር
@Kooblife
@Kooblife
Join & share
546 views12:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-25 15:19:39 ብቸኝነቴን .... መልሺልኝ

ክፍል አርባ (40)
.
.
.
ወደ ኋላ ከዕረዥም አመታት በፊት።
እንደ እውነቱ ፍቅር የልብ ጤንነት የአጥንት ጥንካሬ የመንፈስ እርካታ የስሜት
ደስታ ነበር እንደ እባብ በመሬት እየዳሀየች ተስባ ነክሳ መርዟን በሰውነቱ
እረጭታ በደም ስሩ እንዲሰራጭ በማረግ ካለ እሷ እንዳይቀሳቀስ እንዳይተነፍስ
አርጋ አስራና ወታትባ ሰለ እሷ ሀብት ንብረቱን አይደለም ሁለመናውን ሊሰጣት
ግድ ያሰኘው አንድኔ አንድ ምክንያቱ ፍቅርና ፍቅር ብቻ ነው።
ዕለት በዕለት የሚካኤሌ እና የሰላም የንግግር ቋንቋ ተለዋውጦ ፍቅር
በሚረጭበት አንደበት ሰላም የራሷ ለሚካኤሌ ያላት ግምት ግራ አጋብቷት።
ታፍቅረው ወይም አታፍቅረው አታውቅም ግን ሚኪን ሀብቱን ለመቀማት
አድማሱን ደግሞ የሰጠችውን ንፁሁ ፍቅር እና ገላዋን እንደ ምራቁ ሀክ ቱ ብሎ
ተፍቶት ብር እና ሀብት በመመኘቱ ሁለቱንም ለመቅጣት ዝግጁ ነች ። ይህን
የምታደርገው ደግሞ ውበቷንና የወሲብ ጥማታቸውን ለሀለቱም እየሰጠች
ገላዋን በደስታ የሰጠች እያስመሰለች በውሸት ደስታና ፈገግታ መስጠት
ያለበትን ሁሉ መስጠት።
አንድ ቀን ሴራቸው አድማሱና ሰላም እየሸረቡበት ሳለ ሚካኤል ድንገት መጣ
ሁለቱም ደነገጡ ። ሚካኤሌ ሁለቱንም ሰላምታ እንዳቀረበላቸው እሷ ድንገት
አፏ ላይ የመጣውን ጊዜያዊ ምክንያት ተነፈሰችለት እሷ በጊዜያዊነት የዘላለም
አሪፍ ምክንያት ሆኖ አድማሱ ከእዛ ቤት እንዳይወጣ አደረገው ።
" አይገርምህም ሚኪ ጠፋ ያሉኩሁ የአጎቴ ልጅ ነው ለካ አጎቴም ሞቷል እሱ
የአጎቴ የመጀመሪያም የመጨረሻም ልጅ ነው ..... ስላገኘሁት በጣም ነው ደስ
ያለኝ " አለች ደስ ያላት በማስመሰል ማስመሰሉ ከእሷ ውጪ ማን ተክኖበት ።
ሚካኤሌ ስለ አጎቷ በመስማቷ የደስደስ በማለት ልብስ እንድትቀይርና እራት
እንደሚጋብዛቸው ነገራቸው ቀጥሎም ወደ መኝታ ክፍሉ ገባ ።
ከትንሽ ቆይታ በኋላ ከመኝታ ክፍሉ ሲወጣ ሰላም እጅግ ተውባ እና አምሮባት
ተመለከተ በአድናቆት አፍን ከፈተው ።
ወደ አንድ እሬስቶራንት እራት ለመብላት ተያይዘው ተጓዙ ከታረቀኝ ጋር
ትውውቃቸውም በዚህ ወቅት ነበር ትውውቃቸውም እጇን ለመታጠብ ከሚኪ ጋር
ሄደው እሱ ለውሀ ሽንት መፀዳጃ ቤት ሲገባ እና እሷ እጇን በመታጠብ ላይ ሳለች
ግን መልኩ ስላስጠላት አቋሻው ነው ያባረረችው ከዛ በኋላ ሁሌም አቋሿው
ነበር የምታባርረው እሱ ግን አንድ ቀን ብሎ በተስፋ ይጠብቃት ነበር ።
እናም እቺ ቀን የብዙ ነገሮች መፈጠሪያ ሆናለች እራት ከበሉ በኋላ መጠጥ
ጀምረው ሰላም እራሷን እስክትስት ያረገችውን አለማወቅ ድረስ ነበር የሰከረቺው
በዚህ ወቅት ከአድማሱ ጋር ተጠቃቅሳ ሽንት ቤት ብለው በመሄድ በጓሮ የዕነ
ቶሎ ቶሎ ቤት የሆነ ወሲብ ፈፀሙ ምስኪኑ ሚኪ ከአጎቷ ልጅ ጋር ነው የሄደችው
ብሎ ቁጭ ብሎ ይጠብቃል።
ለሊቱ አጋማሽ ላይ በበቃኝ ከሬስቶራንቱ ወጥተው ወደ ቤታቸው ሲሄዱ አድማሱ
መንገድ ላይ ወረደ እነሱም ወደ ቤታቸው ሄዱ ። እቤት ከደረሱ በኋላ ግን
ተነጣጥለው መተኛት አላስፈለጋቸውም ወደ እሱ መኝታ ክፍል ተያይዘው ገቡ
ሁሌም ሚኪ ከሰላም ጋር ወሲብ ሲፈፅሙ መከላከያ ይጠቀም ነበር ዛሬ ግን
ያንን ለማረግ አቅሙም ሆነ ብቃቱ አልነበረውም ዝም ብሎ ነበር የፈፀመው
የስጦታ ትክክለኛ አባት ማን እንደሆነ እራሷ ሰላም ግራ የገባት ለዚህ ነው
ማስታወስም አልቻለችም ከስካሯ አንፃር በዚህ ላይ ለስጦታ ምንም የእናትነት
እና የልጅነት ፍቅር በሁለቱም ውስጥ ምንም ፍቅር የለም ። ስጦት ወደ
ማደሪያው ት/ቤት ከመግባቷ በፊት ዲ ኤን ኤ ተመርምራ የአድማሱ ልጅ
እንደሆነች ማረጋገጫ አጊተዋል ሰጦት ግን ደሜ የሚለኝ የሚኪ እንጂ የአድማሱ
አይደለም ትላለች እና መቀበል አቅቷታል በፍፁም አትፈልጋቸውም ።
በወቅቱ ሚካኤሌ በሰማኒያ ሊያገባት የተስማማውም ስጦታ መፀነሷን
ስትነግረው ነበር ተጋብተው ጥሩ ሚስት ሆና የኖረችው ከዛ በኋላ ሚስት ሳትሆን
መከራ እና ስቃይ ሆና ፍዳውን ስታሳየው የኖረችው ። ይሄ ድርጊቷ የአድማሱ
እቅድ ነበር ተሰላችቶ እንዲፈታት ነበር አልተሳካም።
ስጦት ካደገች በኋላ አድማሱ የመጨረሻ ሚካኤሌን ለመግደል እቅድ አወጡ
የመኪናውን ፍሬዬን በጥሰው ገደል ለመክተት እንዳሰቡትም ፍሬዬኑን በጠሱት ።
ሚካኤሌ ሀገር ሰላም ብሎ ጠዋት ወደ ስራ ለመሄድ መኪናውን አስነስቶ
እየበረረ ወደ ድርጅቱ በመሄድ ላይ ሳለ መሀል መንገድ ላይ ፍሬዬኑ እንቢ አለው
በመጨረሻ ማድረግ ያለበት በሰው ላይ አደጋ በማይፈጥር ቦታ ላይ አጋጭቶ
ማቆም እንዳለበት ወስኖ ከአንድ ግንብ ግቢ ላይ አጋጨው መኪናው ጭርምት
ከማለቱ የፊቱ መስታወት እረግፎ በሚካኤሌ ሰውነት ላይ እና አይኑ ላይ ተሰካካ
።..........
~ ይቀጥላል ~

@Kooblife
@Kooblife

For any comment
@Ethio96bot
505 views12:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-25 15:19:39 ብቸኝነቴን ...... መልሺልኝ

ክፍል ሰላሳ ዘጠኝ (39)
.
.
.
እስቲ እኔ ወደ ኋላ ልመልሳችሁ ሰላምና ሚካኤሌ እንዴት ተገናኙ የፍቅር
ህይወታቸው እና የትዳር ጉዞቸው እንዴት ነበር ስጦታስ እውነት የማን ልጅ ነች?
ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ይሆናቹሁ ታሪኮቹን ይዘን ወደ ከ13 ከ14 አመታት
በፊት ወደ አለ ታሪክ ወደ ኋላ ተመለሰን
አስቡ ወደ ኋላ እየተመለስን ነው
በአሁኑ የሰላም በበፊቱ በሚካኤሌ የድርጅት በስብሰባ አዳራሽ ውስጥ
ተሰብስበው ሚካኤሌ በሚያምር ግርማ መጎስ ተቀምጦ ከመላው ሰራተኞች ጋር
ስለ ድርጅቱ ሁኔታ ያስረዳችዋል ሰራተኞች የመሰላቸውን ሀሳብ ይተነፍሳሉ
በእርጋታ በወድማማዊ ሁኔታ ተነጋግረው ስብሰባው እንደተጠናቀቀ ሚካኤሌ
የመጨረሻ ሀሳቡን ተናገረ ።
" ወንድሞቼ እና እህቶቼ እናንተም ደመወዝ የሚከፈላቹሁ እናንተም ስራውን
በአግባቡ ስትሰሩ እኔም ትርፋማ ስሆን ነው ይሄ ድርጅት ከተዘጋ የሁላችንም
ጉሮሮ ተዘጋ ማለት ነው እና እባካቹሁ በአንድ ልብ ሆናቹሁ ስሩ ዛሬ የተዘናጋቹሁ
ስራቹሁንም በአግባቡ ያላከናወናቹሁ በሚቀጥለው የአፈፃፀም ግምገማ ላይ
የተሻለ አፈፃፀም ይዛቹሁ እንደምትመጡ አምናለሁ በተረፈ አሁን ወደየስራቹሁ
እሺ አመሰግናለው " አላቸው ሁሉም እየመጡ በወድማዊ ፍቅር እያቀፍት
እየሳሙት ተሰናበቱት ።
ከዚህ ድርጅት ትንሽ እራቅ በሚል አንድ ካፌ ደግሞ አድማሱ ከሰላም ጋር
ተቀምጦ ሴራውን ይጎነጉን ነበር። እሷ አሁንም ባለመስማማት ውስጥ ሆና ግን
ተስማማች ፎቶውን መኪናውን በፎቶ አሳይቷት መልካም እድል ተመኝቶላት
ተለያዩ።
ሚካኤሌ መኪናውን አስነስቶ ከድርጅቱ እየወጣ ሳለ ቶማስ ደወለለት በሞባይሉ
አንስቶት ማናገር ጀመረ ቶማስ ድርጅቱ ኪሳራ እንደገጠመው እና ግማሽ ሼሩን
እንዲገዛው ጠየቀው ምንም ችግር እንደሌለው እና አንዲት ልጅ እንደሚልክ
በእሷ ስም እንደምትገዛው ነገረው በዚህ ተስማምቶ ስልኩን ዘግቶ ለተባለችው
ልጅ ስልክ ሊደውል ቁጥር ለማውጣት ሲነካካ ሰላም ጉስቁል ያለ ልብስ ለብሳ
ፀጉራ ተሞነጫጭሮ ትክዝ ብላ መንገዱን ልታቋርጥ በቀስታ ስትራመድ
ሚካኤሌ ድንገት ቀና ብሎ ወደ መንገዱ ሲመለከት እና ሲገጫት እኩል ሆነ
ደንግጦ ፍሬን ያዘ።
ከገጫት በኋላ ሀኪም ቤት ወስዷት አሳከሟት እሷም ወደ 10 ቀን ተኝታ
ከታከመች በኋላ ዶ/ሩ መውጣት እንዳለባት ለሚኪ ነገረው። ሚኪም ወደ እሷ
ሄዶ ።
" የኔ እህት አሁን እዚህ ህክምናሽን ጨርሰሻል ወደ ቤትሽ ወይም ወደ ቤተሰብሽ
መሄድ ትችያለሽ " አላት ሚካኤሌ
" የትም መሄጃ የለኝም " አለችና አለቀሰች ።
" እንዴት መሄጃ የለሽም ...... እስከ ዛሬ የት ነበርሽ ?" አላት ደንገጥ ብሎ
እያያት።
" ክ/ ሀገር ከእናቴ ጋር ነበር የምኖረው እናቴ አሁን ሞታለች ልትሞት ስትል
አዲስ አበባ አጎት አለሽ ብቸኝነት እንዳይሰማሽ እሱን ሄደሽ ፈልጊው አለችኝ
መጣሁ ወር አለፈኝ አጣሁት የያስኩትን ገንዘብ ጨረስኩ ቤተ ክርስቲያን በር ላይ
ነበር የምተኛው አንተ ስትገጨኝ በጣም እርቦኝ ከበላሁ ሁለት ቀን ነበር ......"
አለችና አለቀሰች ሚካኤሌ በጣም አዘነ ። በቃ ማልቀስ እንደሌለባት ነግሮዋት
ብቻውን እንደሚኖርና ሰራተኛውም ፍቃድ እንደወጣች ነግሯት ወደ ቤቱ
እየወሰዳት ቅያሪ ልብስና የለሊት ልብስ ገዛላት ።
እቤቱ ከወሰዳት በኋላ እራቱን ምሳውን ምግብ እየሰራችለት ማታ ቤቱን ቡና
አፍልታ አጫጭሳ ነበር የምትጠብቀው እሱም ባዶ እጁን አይመጣም የሆነ
ልብስ እየገዛላት ነበር የሚገባው ስለሚያዝንለት ሁሌም ምሽት መኝታ ክፍል
ውስጥ ለሆነ ሰአታት በኮፒተሩ አልጋ ላይ ተቀምጦ አንድ አንድ የቢዝነስ እቅድ
ያወጣል።
የሆነ ወቅት ቀን ሚካኤሌ ስራ ሆኖ አድማሱ መጣ ።
" አንቺ ተመቻችተሽ ተቀመጪ አልኩሽ እንዴ?" አላት
" እና ምን ላርግ " አለች በጭንቀት
" በዚህ ውበትሽ አማልይው እና አብረሺው ተኚ" አላት
" ከአንተ ውጪ እንዴት የሌላ ሰው ገላ ......." አለች
" አፍሺን ዝጊ በጥፊ አይንሽን በጀርባሽ ነው የማዞርልሽ ብር እኮ ነው ይሄ
ሀብትና ብር ላይ ቆመሽ ታላግጪያለሽ " አላት
" እሺ አንተ ከፈለክ ምንም አደርጋለው " አለች በሀዘኔታ
" ሰውነትሽን የሚያሳይ ነጭ ቢጃማሽን አድርገሽ በአይኑ ጎምለል ጎምለል
በይበት " አላት በእሺታ ጭንቅላቷን ነቀነቀች ።
የሴራቸው ሁኔታን ከጨረሱ በኋላ በለችበት ሁኔታ የተቀሰቀሰው ስሜቱ አናቱ ላይ
ወጥቶ ቢፈታተነው እዛው ጠረጴዛ ላይ ስሜቱን አርክቶባት አስጠንቅቋት ወጣ።
ከዛ ጊዜ በኋላ በለሊት ልብስ ገላዋን በሚያሳይ ለሚኪ ሻይ ቡና ይዛለት
ትገባለች መጀመሪያ ላይ ቀና ብሎ ሊያያት እንኳን አልፈቀደም ነበር ። ከሆኑ
ቀናታን በኋላ በጨረፍታ ያያት ጀመር ከረጅም አመታት በኋላ የወንድነት ስሜቱ
ይፈታተነው ጀመር እሷም ሁኔታውን ታይ ነበር እና አንድ ውሳኔ ላይ ለእራሷ
ወሰነች።
"... ፍቅር የማይገባው የሰው ልጅ ብቻ ነው ከዚህ በኋላ በህይወቴ ፍቅር
አይገባኝም አረመኔያዊነት በሀሪዬ ይሆናል ይሄም ጅል እኔን ሊያወጣኝ ይፈልጋል
አስደስተዋለው ሳልቆጥብ እሰጠዋለው ግን የምቀጣው እሱንም አድማሱንም
ይሆናል" አለች ። ከዚህ ውሳኔዋ በኋላ እንደለመደችው ቡና ይዛለት ገባ ቀና ብሎ
አያት ተውባለች አምራለች አተነፋፈሱ ተለየ ቡናውን አስቀምጣ አየቺውና የለሊት
ልብሷን ከፍ አርጋ ጭኖቿን እያሳየች ከጎኑ ሄዳ አልጋው ላይ ተንበረከከችና
ጡቶቿ ፊቱን እንዲዳበሱ አረገችው ስሜቱ እየተወጠረ እጠነከረ ሲሄድ ተሰማው
ጭኖቿን አይቶ ቀና ብሎ ሊያያት ሲሞክር ጡቷ ሳያስበው የተከፈተው አፍ
ውስጥ ገባ።...........
~ ይቀጥላል

@Kooblife
@Kooblife

For any comment
@Ethio96bot
639 views12:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-17 16:26:34 ​​ ብቸኝነቴን ..... መልሺልኝ

ክፍል ሰላሳ ስምንት (38)
.
.
.
ሚካኤሌ ሆ/ል ቶማስን አስቀምጦ እሱ ወደ ቤቱ መጥቷል። እናም መካናውን
አቁሞ ደረጃውን በመውጣት ወደ ቤቱ የዕነ ሰርካለም ቤት ሰላም በማለት
ሊያልፍ ሲል ሚጣ እና ስጦታ ወደ ቤቱ እንዳይገባ እሮጠው ሄደው ያዙትና
" ሚክ አባቴ የሆነ ሽታ አይሸትህም " አለችው ስጦታ ሚካኤሌ በአፍንጫው
አየሩን ዛቅ ዛቅ አርጎ ወደ አፍንጫው ሞጀረው ግን ምንም አዲስ ሽታ
አልሸተተውም ።
" እረ ምንም የለም ልጆቼ " አለ ግራ ተጋብቶ
" አይ ፋዘር በቃ አራድነት ትንሽ ይጎልሀል " አለች ሚስጥረ።
" እረ ምን አራድነት ብልጥነትም ጭምር ሞቅ ያለ ፈራም ነው እንጂ ...... እረ
ፕሊስ አታዋርደን " አለች ሚጣም ሚካኤሌ ግራ ተጋብቶ የሆነ ጨዋታ
ሊጫወቱበት እንደሆነ ገብቶታል ። ያላወቀው ምን እንደሆነ ነው ግራ የገባው ።
" ይሀውልህ እዚህ አንተ ቤት ጥሩ የፍቅር ጠረን እየነፈሰ ነው እዚህ እኛ ጋር ግን
መጥፎ አየር ነው የሚነፍሰው " አለች ሚጣ እንደማዘን ብላ።
" የዚህኛው የእኛ ቤቱ ገብቶኛል ያልገባኝ ይሄኛው ነው ቤት ነው ሁለተኛው ቤቴ "
አለ ማክዳን የላካት አሞታል ብሎ ከኬብሮን ጋር ተመሳጥሮ ነው የዕነ ሰርካለም
ቤት ግን አልገባውም ምን እንደተፈጠረ።
" ይሄኛው እንኳን ሁለተኛው ቤትህ የአንተ መሆኑ ያጠራጥራል ለምን መሰለህ
ሰርኬ ከዚህ በኋላ እንዳይመጣብኝ ላየው አልፈልግም ብላ ከጠዋት ጀምሮ በሩን
ዘግታ ስቅስቅ እያለች እያለቀሰች ብኗኳኳ ብኗኳኳ የሚከፍትልን አጣን እንቢ
አለች " አለች ስጦታ።
" ምን አረኳት ምን በድያት " አለ እየደነገጠ ።
" የበደልካት አንተ ሳትሆን ሀብትህ የድርጅት ባለቤት መሆንህ ነው " አለች
ሚጣ።
" እና እሱ ከእሷ ጋር ምን ግንኙነት አለው " አላቸው ።
" አለው እኔ አባቴ እንድትሆን የተመኘሁት እን እኛ ምስኪን ድሀ መስለሀኝ ነው
ሚኪ እኛ የመነጠቅን የምንበላው እንኳን የሌለን ድሀዎች አንተ የተከበርከት
የትልልቅ ድርጅቶች ካፓኒዎች ባለቤት የእኔ እናት አንተን ብታገባ ተፋቅረው ተጋቡ
ሳይሆን ሴት ልጅ ብር ትወዳለች የሚሉ የአንዳንድ ሰዎች አመለካከትን እኛ ላይ
አገኙት ማለት ነው " አለች ስጦታ።
" እንዴ ምን ማለት ነው ይሄ ሰው ምንም ቢሆን ወሬ አያጣም ስለ ሰው ብለን
የራሳችንን ህይወት እንበጥብጥ መተው ካለብኝ ሀብት ንብረቴን ጥዬ አገባትና
ለእሷ ስል ከሀ እጀምራለሁ እሺ የት ነው ያለችው " አለና ወደ ቤት ተከታትለው
ገቡ።
" አንተ ውጣልኝ .......ውጣልኝ ....." አለች ሰላም በጩሀት ሶፋ ላይ ተቀምጣ
ከፊቷ ካለው ጠረጴዛ ላይ ከተቀመጠው ውስኪ እየቀዳች በደረቁ እንደ ውሀ ወደ
ጉሮሮዋ እያንቆረቆረች ፊቷ እና አይኗ ቀልቶ ደም መስሏል በግንባሯ ላይ
በተለያየ አቅጣጫ ተገታትረዋል አንድ ለእናቱ የሆነው የአ.አ ጎተራው የብሄር
ቤሄረሰብ ቀለበት መንገድ ይመስል ተጠላልፏል። ታረቀኝ የሰላም ሁኔታ
አስፈርቶታል ለዕዛ ሲል ጥሏት ለመሄድ አልፈለገም እሷ ግን ብቻዋን መሆን
እንደምትፈልግና እንዲሄድላት በጩሀት ደጋግማ ተናገረችው
" ....... ምንድን ነው ጀርባዬ ላይ ያለ መዥገር የምትሆንብኝ በጥይት ግንባርህን
ብዬ ልድፋህ ወይስ ከዚህ ቤት ትወጣልኛለህ .... የሆንክ አጋስስ " አለችው ።
ታረቀኝም እንዳመረረች ስለገባው ተነስቶ ወጣ የሄደ መስሎ በሩ ላይ መሬት ላይ
ቁጭ ብሎ ይጠብቃት ያዘ።
ሰላም ውስኪውን ትጨልጣለች ትስቃለች እንደገና ታለቅሳለች ግራ የገባው
ህይወት።
" ቆይ ለእኔ እንደዚህ መሆን ማን ነው ተጠያቂ እኔ እራሴው ነኝ ወይስ ፍቅር
እንዳይገባኝ ያደረጉኝ ለልጄ ፍቅር መስጠት እንዳልችል እና እንድጠላት ያደረጉኝ
እናቴ እንጀራ አባቴ እና የሰው ልጅ ወይስ ከፍቅር ገንዘብ እንደሚበልጥ ለገንዘብ
ስል መግደል እንዳለብኝ ያስረዳኝ አድማሱ ነው ?..... እሱን እኮ ከልቤ አፍቅሬው
ነበር እሱ ግን...." አለችና በሀሳብ ተጓዘች።
ከዓመታት በፊት ወደ ኋላ እንመለስ
በአንድ ሆቴል አድማሱና ሰላም አብረው እራት እየበሉ እሷን የብዙ ወንዶች አይን
አርፎባታል በጣም ተውባ ነበር አድማሱ የሚካኤሌን ሀብት እና ንብረት እንዴት
መቀማት እንደሚችል ያስባል እሷ ደግሞ የአድማሱን ፍቅርና እሱን ብቻ ነው
የምታስበው።
" እና ያልኩሽን አሰብሽበት ከአንተ ውጪ ሌላ ገላ ሌላ ምናምን እንዳትይኝ ብቸኛ
እና ትዳር የሌለው ምስኪን ሰው ነው በቀላሉ ሊታለል የሚችል " አላት
" ሰውዬው ምስኪን ስለሆነ ለምን እንቀማዋለን የራሳቾንን ኑሮ ለምን አንኖርም
ባለን ነገር " አለችው በልመና።
" ምን ፃድቅ ፃድቅ ያረግሻል አንቺ ባትሰሪው ሌላ አሰራለው ስንት ሀብታም
መሆን የሚፈልግ አለ ወስኚ አሁን " አላት ግራ ገባት ለእራሷም በዚህ ምድር
ጥሩ ሰው እንደሌለ አሰበች በቃ እሷም ተመሳስላ መጥፎ መሆን ከብዙ ክርክር
በኋላ ተስማማች።
ከሀሳብ ስንመለስ
" ..... እስቲ ወገተኛ ካልሆናቹሁ መልሱልኝ ለእኔ እንዲህ መሆን ማን ነው
ጥፋተኛ ?" አለች
ስጦታ እና ሚጣ በሳሎን ውስጥ ቁጭ ብለው በጩሀት ለመግባባት የከበዳቸው
የሚመስሉትን የሚካኤሌን እና የሰርካለምን ክርክር የሰማሉ ድምፅ አነስ
ሲልባቸው ሄደው በር ስር ተለጥፈው ይሰማሉ በመጨረሻ ከብዙ ጭቅጭቅ
በኋላ ተስማሙ ዕነ ሚጣም በእፎይታ ተነፈሱ ሲሳሳሙ ሰሙና በደስታ
ተጨባብጠው ተሳሳሙ። እቺን ዕቅድ አቅደው ሚጣ እናቷ ሀብታም ወንድ
አለመውደዷን ስጦታ ሚኪ ለአመነበት ነገር ግትር እንደሆነ ተናገረች በዚህ
ጉዳይ አውርተው ሁለቱን ለማገናኘት አቀዱ እቅዳቸውም ተሳካ።
ሚኪና ሰርኬ ከመኝታ ክፍሉ ተቃቅፈው በደስታ ፈገግ ብለው ወደ ሳሎን ሲመጡ
ሁለቱም ህፃናት ቆመው እጃቸውን ዘርግተው ጠበቋቸው አያቸውና ግራ ሲጋቡ።
" እናንተን ዕነ ኬቡን ለማጣበስ ያየነው መከራ ስቃይ ኡሁሁ ገገማ ፋራዎች ናቹሁ
ዕቅድ ስናወጣ ስታፈርሱ አደከማቹሁን አሁን አጣብሰን ስራችን አልቋል ሂሳብ
ይከፈለን "አለች ሚጣ
" የቀረ በዝምድና አንሰራም ሌላው የልጆችiን መብት ወደ ኋላ ጥላቹሁ መኝታ
ክፍል ከመሳሳም ባለፈ በልጅ አፍ የማይነገር ነገር ሳታፍሩን በማረጋቹሁ ሳንከስ
ሂሳብ ካሳ ይሰጠን " አለች ስጦታ ኮስተር ብላ ዕነ ሚኪ እየተያዩ ሳቁ።......
ይቀጥላል

@Kooblife
@Kooblife

For any comment
@Ethio96bot
6.6K views13:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-17 16:26:34 ብቸኝነቴን ..... መልሺልኝ

ክፍል ሰላሳ ሰባት (37)
.
ሚካኤሌ መኪናው ከሆስፒታል ግቢ ውስጥ አቁሞ ወደ መኝታ ክፍሉ መግቢያ
በር ላይ አቁሞ ወደ ሆ/ሉ መኝታ ክፍል ገባ አንገቱን ደፍቷል ያኮረፈ ይመስላል
በቀጥታ በኮሪደሩ በመሄድ በሩን እንኳኩቶ ገባ ማክዳ ብቻዋን ተቀምጣለች ቃል
ኪዳን ኦክስጅኑ ተነቅሎላት በእራሷ አቅም በመተንፈስ ላይ ነች ። እንዴት
እንደሆነች ጠየቃት ጥሩ ለውጥ እንዳመጣችና ደህና መሆኗን ነገረችው እሱም
ቁጭ አለ ትክዝ ብሏል ማክዳ ደጋግማ ዘወር ብላ ተመለከተቺው
" ምን ሆነሀል ሚኪ ጥሩ አይደለህም " አለችው ዘወር ብሎ ተመለከታት ለደቂቃ
ፍዝዝ ብሎ።
" አንቺና ኬብሮን እዚህ ተጣልታችሁ ነበር እንዴ?" አላት
" አዎ ...ዝም ብሎ እራሱን እየቆለለ ታፈቅሪኝለሽ እውነቱን ንገሪኝ እያለ
ሲጨቀጭቀኝ አናደደኝና ተናገርኩት ሰደብኩት "
" እና እውነት አንቺ እሱን አታፈቅሪውም " አላት ጠንከር ብሎ
" ማ .... እኔ እሱን ላፈቅረው እንዴ ትቀልዳለህ ድፍረታቹሁ በምን ሂሳብ ነው
እሱን የማፈቅር የሚመስላቹሁ?" አለችው
" ፍቅር የሚመስልና የማይመስል ነገር አይደለም ........... ለማንኛውም እኔ
እዚህ እቆያለው ወደ ቤት ከሄድሽ በዛው አየት እያረግሽው ብቻውን ስለሆነ ጥሩ
አይደለም ።" አላት
" እንዴ ምን ሆነ ደግሞ ?" አለች ደንገጥ ብላ
" መንገድ ላይ ወድቆ ልቡንና ጭንቅላቱን አሞት ተኝቷል" አላት እሷ ደንግጣ
ከተቀመጠችበት በመነሳት አይን አይኑን ስታየው እሱም ተገርሞ አያት።
" በእኔ ነው እንደዚህ የሆነው ..... እሱ ቀልድ አያውቅም እንዴ እንዴት እንዲህ
ያመራል ምን ዓይነቱ ልጅ ነው በፈጣሪ"
" ታፈቅሪዋለሽ ማለት ነው?" አላት እሷ ደንገጥ አለችና።
" እሺ አሁን የት ነው ያለው ?........ ተወው ለካ እቤት ነው ብለሀኛል ..... በቃ እኔ
ሄጃለው " አለችውና ቻው ሳትለው እየሮጠች ሄደች።
በፖሊስ ጣቢያ የምርመራ ቢሮ ውስጥ መርማሪው ከሰላም ጋር ፊት ለፊት
እየተያዩ በምርመራ አጣድፏታል እሷ ግን ካለ ምንም ጭንቀት በአግባቡና
በተረጋጋ ስሜት ውስጥ ሆና ትመልሳለች ።
" ቆይ ያኔ ምሽት እኔጋ እንደነበረ ማን ነው የተናገረው" አለች
" ምን ይሰራልሻል ማወቁ ግን የሙያ ግዴታችንም አይፈቅድም መናገር
አንችልም ግን አንቺ እውነቱን ብትነግሪን ይሻላል " አላት መርማሪው ።
" እንግዲያውስ ምንም የምነግርህ ነገር የለም እኔ አልገደልኩም ነፍሰ ገዳይም
አይደለሁም " አለች በተረጋጋ ስሜት ። መርማሪው በግርምት ፍጥጥ ብሎ
ተመለከታት ።
" በጣም ግራ ያጋባል በዛች ደቂቃ ከአንቺ ጋር ከነበረ ከዛ በኋላ ወጥቶ በሌላ
ሰው መገደሉ አስገረመኝ " አላት።
" እኔ ....... እኔጋ ነበር ያን ምሽት አልኩሁ እንዴ?" አለችው
" አንቺማ አላልሺም ነገር ግን ያን ምሽት አንቺ ጋር እንደነበረ አሳማኝ ማስረጃ
አለ" አላት መርመሪው በአትኩሮት እየተመለከታት ።
" በቃህ ሌላስ የለህም ...... ትሰማኛለህ ባልተረጋገጠ መረጃ አንድ ግለሰብ
በቂም ተነሳስቶ ይሁን በሌላ ሳታውቅ ከመሬት ተነስተህ ይሄን ያህል ሰዓት
በማጉላላትህ በህግ እጠይቀሀለው እኔ ንፁሁ ኢትዮጵያዊ ዜጋ እንጂ ገዳይ እና
ባለጌ ሰው አይደለሁም ገላለች ወይም ስትገል አይቻታለው የሚል ምስክር ካለህ
እሰረኝ እሺ " አለች በጩሀት
" ልታስፈራሪኝ እየሞከርሽ ነው " አላት በግርምት እያያት ።
" ለምን አስፈራራሀለው እውነታውን መናገሬ ነው ስገል ያየኝ ምስክር ካለህ
እሰረኝ አለበለዚያ ግን ስራዬን አታስተጓጉልብኝ እሺ መርማሪ " አለች ቆፍጠን
ባለ ንግግር ።
" ጥሩ ነው በእራስ መተማመንሽ " አላት
" ታውቃለህ ከልጅነት ጀምሮ አንድ ቀን ደስታየን ማየት ለነፈቃት ምስኪን ሴት
እስር ቤት መግባት ለእሷ ምንም ማለት አይደለም ........ ቆይ አንተ ዛሬ እኔን
አስቀምጠህ ህግ ምናምን የምትለኝ እኔ ዘላለሜን በሰው ልጅ ስሳቃይ የት
ነበራቹሁ ህግ ለእኔ የታሰረ ለሌላው የተፈታ ነው እኔ በህግ ፊት በተደጋጋሚ
ቆሜ ለምኛለው ማን ሰማኝ አሳማኝ ማስረጃ አምጪ እንጂ የተባልኩት ስለዚህ
ተውኝ እሺ ..... መሄድ እችላለው የምትለኝ ከሌለ" አለችው
" ትችያለሽ ሂጂ አሁን ማንም ሳይሆን ተጠርጣሪው አንቺ ነሽ ማስረጃውን
በመያዝ ዳግም እንደምንገናኝ ተስፋ አረጋለው "
" ካገኘህ የእዛ ሰው ይበለን .... ይቅናህ " ብላው ገልምጣው በሩን ከፍታ
ከታረቀኝ ጋር ወጣች ።
" እንዴት እና ምን ብለሽ አመለጥሽ " አለ ታረቀኝ በጣም ከመፍራቱ የተነሳ ላብ
በላብ ሆኖ ሰውነቱ እየተቀጠቀጠ ።
" እኔ እንደ አንተ ላባም ቀጥቃጣ አይደለሁም ለእያንዳንዱ ውሳኔ መልስ ምት
እያዘጋጀው ነው አሁን ምንም አያመጡም አትፍራ እሺ " አለችው ታረቀኝ በደስታ
ዘሎ አቀፋት እና ሲስማት ከሰውነቷ እራቅ አረገቺውና " .... ባክህ ልቀቀኝ
ልጅነትህን አልጨረስክም እኔ ፊጥጥ ብለህ መታዘል የምትፈልገው " አለችና
ተያይዘው ወደ መኪናቸው ሄደው በመግባት መብረር ጀመሩ ።
ማክዳ የኮዶሚኒየውን ደረጃ በፍጥነት በመውጣት ቁና ቁና እየተነፈሰች ኮሪደሩን
ቤቷን እንኳን ዘወር ብላ ሳታይ አልፋ የዕነ ሚኪን በር ከፍታ ዘላ ገባች ። ኬብሮን
ጀርባውን ለበሩ ሰጥቶ ተኝቶ ያቃስት ነበር ደንግጣ ሄደች ተንበርክካ እያለቀሰች

" አሳመምኩሁ አይደል እኔ እኮ ደደብ ጨካኝ የማረባ ነኝ ይቅርታ አድርግልኝ
እባክህ .... እስቲ ቆይ ምንህን ነው ዘወር ብለህ እየኛ ....." አለች እያለቀሰች ዕነ
ሚጣ ከጀርባዋ ሆነው እያያት ሲሳሳቁ ቆዩና ተነስተው ሊወጡ ሲሉ አየቻቸው እና
ነገሬም ሳትል ዘወር ብላ ወደ እሷ ገለበጠችውና ግንባሩን እየሳመችው
ጠየቀችው ልቡንና ጭንቅላቱን አሳያት ።
" እሺ ተነስ ና ሀኪም ቤት እንሄዳለን ተነስ ዶ/ር ይይህ " አለች
" እእእ ....አልሄድም " አላት ለምን እያለች ስተጨቀጭቀው
" ... ምክንያቱም በሽታዬም ዶክተሬም አንቺ ስለሆነሽ" አላት እና ጣቶቹን ፀጉራ
ውስጥ ሰክቶ ጭንቅላቷን ጉቱቶ ከንፈሯን ከንፈሩ ላይ ለጠፈው አፏ ተግደረደረ
ግን ልቧ አሸነፈ አንዱን እጁን ይዛ ከጡቶቿ ውስጥ ከተተችው የፈለገውን
እንዲነካካ ፈቀደችለት ልብስ ለማውለቅ ደቂቃ አልፈጀባቸውም።......

@Kooblife
@Kooblife

For any comment
@Ethio96bot
6.0K views13:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-11 09:06:39
እንኳን ለ 2015 የ አዲስ አመት በዓል አደረሳቹ ዓመቱ ያሰብነዉን የምናሳካበት ፣ የሰላም ፣ የደስታ ፣ የፍቅር ፣ የአንድነት እንዲሆንልን ከልብ እንመኛለን እናመሰግናለን ።

@Kooblife
@Kooblife
1.0K views06:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ