Get Mystery Box with random crypto!

ዜና አርሰናል (Arsenal news)

የቴሌግራም ቻናል አርማ arsenal754 — ዜና አርሰናል (Arsenal news)
የቴሌግራም ቻናል አርማ arsenal754 — ዜና አርሰናል (Arsenal news)
የሰርጥ አድራሻ: @arsenal754
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.03K
የሰርጥ መግለጫ

Arsenal

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-03-05 13:35:06 አርቴታ ከ ስካይ ስፓርትስ ጋርም ረዘም ያለ ቃለ ምልልስ አድርጎ ነበር።

አንዳንድ ነጥቦች

ስለ ዝውውር
~> አጥቂ ማስፈረም ተቀዳሚ አላማቸው መሆኑን፤
~>ጥራት እንጂ ቁጥር ላይ እንደሚያተኩሩ፤
~> አዲስ የሚመጡ ተጫዋቾች ለጨዋታ ዘይቤው የሚመቹ እንደሚሆኑ፥ ለተጫዋቹ ሲባል የጨዋታ ሲስተም መቀየር እንዳይኖርበት ተጠንቅቀው እንደሚያስፈርሙ፤
~> አሁን ወጣቶች ላይ ብቻ እንደሚያተኩሩ፤
~> ቀጣዪ የዝውውር መስኮት ካለፈው በላይ ወሳኝ እንደሚሆን፤
~> የሚፈረመው አጥቂ በርካታ ጎሎችን የሚያስቆጥር እንደሚሆን፤ ወሳኝ አጥቂ የሌለው ቡድን ትልቅ ለመሆን እንደሚቸገር ተናግሯል።


ስለ ላካዜት
ላካዜት አብረውት ለሚጫወቱ ተጫዋች እንደሚመች እና የተሻለ እዲጫወቱ ስለሚረዳ ወሳኝ ተጫዋቾች መሆኑን ገልጿል።


ስለ ሳካ
~> የተወሰኑ ጨዋታዎች ላይ ጥሩ መጫወትን ብዙ ተጫዋቾች ሊያደርጉት ይችላሉ ሆኖም እንደ ሳካ በሁሉም ጨዋታ ምርጥ አቋም ማሳየት አስቸጋሪ መሆኑን፤

~> ከአካዳሚ ባያድግ እና በ70 ሚሊዮን ፓውንድ ቢያስፈርመው የበለጠ ታዋቂ ሊሆን እንደሚችል ገልፆ፤ ለምን ስለ ሳካ ብዙ እንደማታወሩ አያይገባኝም ሲል ጋዜጠኛው በመጠየቅ አጠናቅቋል።



ስካይ ዘርዘር ያለ ዘገባ ይዟል፤ በዚህ ሊንክ ማግኘት ትችላላችሁ።

https://www.skysports.com/football/news/11670/12557127/mikel-arteta-exclusive-interview-arsenal-boss-on-emirates-stadium-connection-pierre-emerick-aubameyang-exit-and-why-this-summer-is-so-important
6.2K viewsedited  10:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-05 13:11:35 አርሰናል ከ ዋትፎርድ

አርቴታ ትላንት በጋዜጣዊ መግለጫው ካነሳቸው ነጥቦች መካከል፤

ስለ ጉዳት
~> #ከቶሚያሱ(አጠራጣሪ ነው) ውጭ ሁሉም ሙሉ ጤንነት ላይ ይገኛሉ።

ስለ ቶፕ 4
አርሰናል አሁን የሻንፒየንስ ሊግ ቦታ ይዞ ለመጨረስ ቅድሚያ ግምት እያገኘ መምጣቱን ተጠይቆ
"አውንታዊ ነገር ቢሆንም አሁን 6ኛ ነን አላማችን የነገን ጨዋታ ማሸነፍ ነው" ሲል ጫና ለማቅለል ሞክሯል።

ስለ ፓርቴ
~> ከጥቃቅን ነገሮች ጀምሮ እጅግ መሻሻሉን፤
~> ለጨዋታ ብቁነቱ (fitness ) ከመቸውም ጊዜ የተሻለ መሆኑን፤
~> ልምምድ ላይ ማመን የሚከብዱ ጎሎችን እንደሚያስቆጥር እና በቅርቡ ጨዋታዎች ላይም ጎል ያገባል ብሎ እንደሚጠበቅ ገልጿል።


ስለቡድኑ አልሸነፍ ባይነት
በራስ ከመተማመን እንደሚጀምር ገልፆ፤ የምናስበው ለመተግበር መትጋት፣ አንዱ ለሌላው መጫወት፤ ችግሮች ሲመጡ እንዴት መፍታት እንዳለብን ልምድ መውሰድ በቀላሉ ላለመሸነፍ ወሳኝ ነው ብሏል።

ስለ ቤን ዋይት
ምርጥ የውድድር አመት እያሳለፈ እንደሚገኝ፣ ወደ አዲስ ክለብ መጥቶ፣ የለበሰው የማልያ ቁጥር፣ የወጣበት ዋጋ... ይህን ሁሉ ተቋቁሞ እያሳየ ያለው አቋም እንዳስደነቀው ገልጿል።


ስለ ዋትፎርድ
የሮይ ሆጅሰን ቡድን ሁሌም የተደራጀ እና ለማሸነፍ ፈታኝ እንደሚሆን ተናግሯል።

ዘርዘር ያለ ቃለ ምልልስ ያደረገ ሲሆን በቀጣዩ ሊንክ ሙሉ ቃለ ምልልሱን ማግኘት ትችላላችሁ።


https://www.football.london/arsenal-fc/fixtures-results/mikel-arteta-tomiyasu-injury-referee-23291182
4.9K views10:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-15 17:52:45 #ኢማኑኤል_ኤቡዬ
"በ2007 @ቤኪንግሃም ቤተመንግሥት በንግስቷ ግብዣ ሄድን፤ #ሄነሪ (Henry ) ጠራኝ እና 'ኤቡዬ እባክህ ይህ የንግስት ቤት ነው ምንም እንዳትነካ፤ ምንም እንዳታደርግ አለኝ'፥ ችግር የለም አታስብ አልኩት።"

" ንግስቷ የሁሉንም እጅ ጨብጣ እንጨረሰች፤ 'ማም'፥ 'ማም' ብየ ተጣራሁ፤ 'አቤት ደህና ነህ' አለችኝ። አዎ ደህና ነኝ፥ ግን ከዚህ በኋላ ኳስ መጫወት አልፈልግም፥ ውሻዎችን ልንከባከብ፤ ብቻ ከዚህ ቤት መውጣት አልፈልግም።"
4.9K views14:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-14 14:47:29
አርሰናል በጥር የዝውውር መስኮት ከ#ፒኤስጂ #ኦባምያንግን በ #ማውሮ_ኢካርዲ እንቀይራችሁ የሚል ጥያቄ ውድቅ አድርጓል። አርሰናል ዋና ኢላማዎቻቸውን የማያገኙ ከሆኑ ምንም አይነት ተጫዋች ሳያስፈርሙ እስከ ክረምት የዝውውር መስኮት ለመቆየት ቀደም ብለው ወስነው ነበር።

#ኢካርዲ ድንቅ ተጫዋች ቢሆንም በዲሲፕሊን ምክንያት ክለቦችን በመበጥበጥ ይታወቃል፤ በዚህም ምክንያት ያለውን ሙሉ አቅም/ችሎታ ሳይጠቀምበት 28 አመቱ ላይ ደርሷል። በዚሁ አስቸጋሪ ፀባዪ (በተለይ ከሴቶች ጋር በተያያዘ ) የአርጀንቲና ብሄራዊ ቡድን አባልም አይደለም።

#ዘአትሌቲክ
4.6K viewsedited  11:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-14 08:12:30
አርሰናል #የአርማንዶ_ብሮጃን ሁኔታ በቅርበት እየተከታተለው ይገኛል። ተጫዋቹ የቼልሲ ንብረት ሲሆን በውሰት ለሳውዝሃምፕተን ድንቅ ብቃቱን በማሳየት ላይ ይገኛል። አርቴታ የተጫዋቹ አድናቂ ሲሆን ከአርሰናል የአጥቂ ዝርዝር ውስጥ ገብቷል።

#ክሪስ_ዊትለይ

ጋዜጠኛው አያይዞ እንደዘገበው #ማርቲኔሊ በአርሰናል የልምምድ ሜዳ የአጥቂ ሚናን በመለማመድ ላይ ይገኛል።
4.1K viewsedited  05:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-13 22:46:43
በዚህ ሳምንት ያለንበት ሁኔታ
3.7K views19:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-13 22:44:34
ሌላ ጥሩ ዜና #ቶሚያሱ ወደ ልምምድ ተመልሷል።
3.2K views19:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-13 22:43:11
ይህ ሳምንት ከመየትኛም የዚህ አመት የውድድር ጊዜ የተሻለ ለአርሰናል ወደ ሻምፒዮንስ ሊግ ለመመለስ ተስፋ የሰጠ ወቅት የለም።
3.1K views19:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-12 17:25:44
2.9K views14:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-11 00:44:38 ለሻምፒዮንስ ሊግ ቦታ አምርረው እንደሚጫወቱ አሳይተዋል።

ዎልቭስ 0: 1 አርሰናል
3.0K views21:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ