Get Mystery Box with random crypto!

Computer & ቴክኖሎጂ

የቴሌግራም ቻናል አርማ computer_technoloy — Computer & ቴክኖሎጂ C
የቴሌግራም ቻናል አርማ computer_technoloy — Computer & ቴክኖሎጂ
የሰርጥ አድራሻ: @computer_technoloy
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.00K
የሰርጥ መግለጫ

#የተማሩትን_ማስተማር_ያወቁትንማሳወቅ_ብልህነት_ነው
ለሰው መልካሙን እንጅ መጥፎውን አትመኝ በዚህ የቴሌግራም ቻናል ጥሩ ጥሩ #ቴክኖሎጅና_ኮምፒውተር_መረጃዎች_እና_እውቀቶች_ይቀላቀላሉ_ያለዎትን_እውቀት_ያሳድጋጉ
ጥያቄም ሆነ አስተያየት ካለዎት
@Kheyirbot ይጠቀሙ

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-11-20 15:11:00 ዛሬ የሚደረግ የአለም ዋንጫ የመክፈቻ ጨዋታ በነፃ ቻናሎች ይመልከቱ

   ማታ 1፡00
ኳታር ኢኳዶር

LIVE ON KAN 11 HD
               Persiana Sports HD
               ETV MEZNAGNA
               beIN Sports HD
               Qatar TV HD


-KAN 11 HD አሞስ-11036 H 6082
-Persiana,S Yah-12595 V/H 27500
-ETV MEZ ኢትዮ ሳት-11105H4500
-ቤን ስፖርት ናይል ሳት-11054 H 27500
- ቤን ስፖርት አረብ ሳት-11566 H 27500
-Alkass 1 HD ናይል ሳት-11919 H 27500
-Alkass 1 HD አረብ ሳት-11678 H 27500
-Qatar TV HD ናይል ሳት-10834 V 27500
-Qatar TV HD አረብ ሳት-10770 V 27500

https://t.me/computer_technoloy
1.0K views12:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-12 16:11:15 የእንግሊዝኛ ቋንቋን ያለምንም የበይነ መረብ ክፍያ ለመማር የሚያስችል መማሪያ ይፋ ሆነ የእንግሊዝኛ ቋንቋን ያለምንም የበይነ መረብ ክፍያ ለመማር የሚያስችል መማሪያ ይፋ ሆኗል።

https://telegra.ph/የእንግሊዝኛ-ቋንቋ-11-12
1.7K views13:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-10 21:25:47 እንዴት አድርገን የሞባይል ካርድ በCBE ሞባይል ባንኪንግ መሙላት እንችላለን?
1ኛ *889# በመጫን
~
2ኛ Welcome to CBE Mobile Banking. Press * to navigate back any time, select one
of the following options below:
1: Login
2: Exit
1ን ይጫንኑ
~
3ኛ Please enter your PIN to login: የPIN ቁጥር ያስገቡ።
~
4ኛ Welcome to CBE Mobile Banking
1: My Accounts
2: Transfer to CBEBirr Wallet
3: Make Payment to Beneficiary
4: Payment to others
5: More options
5 ይጫኑ More Options የሚለውን
~
5ኛ Welcome to CBE Mobile Banking
1: Local Money Transfer
2: Manage Beneficiaries
3: Exchange Rates
4: Utility Payment
5: Previous options
6: More options
6 ይጫኑ አሁንም More Options የሚለውን
~
7ኛ Welcome to CBE Mobile Banking
1: Buy Airtime
2: Covid-19 Donation
3: Own Account Transfer
4: My Service
5: Exit
6: Previous options
1ን ይጫኑ Buy Airtime የሚለውን
~
8ኛ Buy Airtime
1: የአካውንት አይነት - ETB -12000
1 ይጫኑ
~
9ኛ የአካውንት አይነት- ETB-12000
Request Transfer from የአካውንት አይነት- ETB
12000
Please enter Recharged Mob No
0909090909(ምሳሌ ነው ይህ ቁጥር መላክ የምትፈልጉበትን ቁጥር ያስገቡ)
10ኛ የአካውንት አይነት-ETB- 12000
Request Transfer from የአካውንት አይነት- ETB-12000
Please enter Amount
170(መሙላት የምትፈልጉትን የብር ብዛት ያያገቡ)
~
11ኛ Confirm request for የአካውንት አይነት- ETB-12000
Request Transfer from የአካውንት አይነት - ETB 12000
Recharged Mob No: 090000000(ምሳሌ ነው ካርድ የሚሞላበት ቁጥር ነው)
Amount: 170
Please Confirm
1: Yes
2: No
1 ይጫኑ ከተስማሙ ይህንን ከተጫኑ ካርድ መሙላት ቻለዋል ማለት ነው።
~
ከተመቻችሁ ለሌሎች እንዲደርሳቸው ሼር ይደረግ!
1.6K views18:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-06 21:10:16 አንጋፋው አርቲስት አሊ ቢራ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

ጥቅምት 27/2015 (ዋልታ) አንጋፋው አርቲስት አሊ ቢራ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን የኦሮሚያ ኮሙዩኒኬሽን አስታወቀ።

አርቲስት አሊ ቢራ ባጋጠመው የጤና እክል ምክንያት በአዳማ ጄነራል ሆስፒታል ለሳምንታት የሕክምና ክትትል ሲደረግለት መቆየቱ ታውቋል።

አርቲስቱ በ72 አመቱ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው ሲሆን በኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢንደስትሪ ውስጥ ከ50 ኣመታት በላይ አገልግሏል፡፡
1.6K views18:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-02 23:54:53
ዛሬ የተፈረመው ስምምነት ምን ዝርዝር ጉዳዮችን ይዟል?

(ማምሻውን ካገኘሁት ባለ 10 ገፅ ዶክመንት ተቀንጭቦ የተወሰደ)

The Permanent Cessation of Hostilities:
- ሁሉም አካላት አስቸኳይ የተቃርኖ አካሄዶችን እና ውጊያዎችን እንዲያቆሙ (ከውጭ ሀይሎች ጋር ማበር፣ የአየር ጥቃቶችን መፈፀም፣ ፈንጂዎችን መትከል፣ ድንገተኛ ጥቃቶችን መፈፀም ወዘተ እንዲያቆሙ)
- ይህ አካሄድ በትግራይ ክልል ህገመንግስታዊ ስርአት እንዲመለስ እና የፖለቲካ ውይይት እንዲጀመር እንዲያስችል
- የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊትን ጨምሮ የፌደራል ስልጣን ወደ መቀሌ ከተማ እንዲመለስ እና አስፈላጊው ህዝባዊ አገልግሎት እንዲቀጥል ማስቻል

Disarmament, Demobilization and Reintegration:
- ኢትዮጵያ አንድ መከላከያ ሰራዊት ብቻ እንዳላት ግንዛቤ ተወስዶ ለህወሀት ታጣቂዎች ትጥቅ ፍቺ፣ ብተና እና መልሶ ማቋቋም (DDR) በህገ-መንግስቱ መሰረት እንዲከናወን
- ስምምነቱ በተፈፀመ በ24 ሰአት ውስጥ በሁለቱም ወታደራዊ ኮማንደሮች መሀል ግንኙነት እንዲፈጠር፣ በ5 ቀናት ውስጥ ደግሞ ውይይት እንዲያደርጉ
- የትጥቅ አፈታቱ ሂደት ለከባድ መሳርያዎች ቅድሚያ ተሰጥቶት እንዲከናወን፣ ሂደቱም ኮማንደሮቹ ከተገናኙ በሗላ በ10 ቀን እንዲጠናቀቅ፣ ትንንሽ መሳርያዎችን ጨምሮ ሁሉም ትጥቅ አፈታት በ30 ቀን እንዲጠናቀቅ
- የትጥቅ አፈታት ሂደቱ በትግራይ ክልል ያለውን የህግ እና ፀጥታ ሁኔታ ታሳቢ ባደረገ መልኩ እንዲከናወን

TPLF Shall:
- ህወሀት የፌደራል መንግስቱን ስልጣን እንዲያከብር፣ የፌደራል ንብረቶችን፣ ተቋማትን እና አለም አቀፍ ድንበር እንዲቆጣጠር ማስቻል
- ህወሀት በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል የሚገኙ ተፃራሪ ቡድኖችን መደገፍ እንዲያቆም
- ፀረ-ህገ መንግስታዊ የስርዐት ለውጥ እንዲመጣ ከማድረግ ጥረት እንዲቆጠብ... ወዘተ

The Government of the FDRE Shall:
- መንግስት የህወሀት ተፋላሚዎች ላይ ያተኮረ ወታደራዊ ጥቃት እንዲያቆም
- በስምምነቱ መሰረት ትግራይ ክልል ውስጥ አስፈላጊ የህዝብ አገልግሎቶች እንዲጀምሩ ማስቻል
- ህወሀት የተጣለበት የሽብርተኝነት ስያሜ እንዲነሳለት ማስቻል... ወዘተ

Restoration of Federal Authority in the Tigray Region:
- የፌደራል ስልጣን በትግራይ ክልል እንዲቀጥል (የፌደራል ተቋማትን መቆጣጠር ጨምሮ)፣
- የፌደራል መንግስት ደግሞ የትግራይ ክልል በፌደራል መንግስት ተቋማት እንዲወከል ማስቻል አለበት (ህዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች ጨምሮ)

Transitional Measures:
- የምርጫ ቦርድ የአካባቢ እና ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚደረግ ምርጫ እስከሚከናወን አካታች የሆነ ግዜያዊ አስተዳደር በክልሉ እንዲኖር ማስቻል
- የሽብርተኝነት ስያሜው በተነሳ በሳምንቱ ሁለቱ አካላት የፖለቲካ ውይይት እንዲጀምሩ እና ለፖለቲካ ልዩነታቸውን መፍትሄ እንዲያበጁ
- ሁለቱም አካላት የአካባቢ ይገባኛል ጥያቄዎችን በኢፌዴሪ ህገመንግስት መሰረት እልባት እንዲሰጡ።

መልካም ምሽት።
2.0K views20:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-30 02:09:57
በጅማ ከተማ ሚስቱን የገድለዉ ግለሰብ በሕግ ቁጥጥር ስር ውሏል።

በኦሮሚያ ክልል ጅማ ከተማ አቶ ተማም አብዱላሂ የተባለ ግለሰብ ባለቤቱን ወ/ሮ ሷሊሃ መሀመድን በዛሬው እለት ከረፋዱ 5 ሰዓት አካባቢ ገድሎ ተሰውሮ ነበር።

አቶ ተማም አብዱላሂ በጅማ ዩኒቨርስቲ መምህር መሆኑ የተነገረ ሲሆን ትዳራቸዉ ከተመሰረተ ገና 1 አመት እንደሆነና ወንጀሉን በጅማ ዞም ፈጽሞ በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን በወልቂጤ ከተማ ሲንቀሳቀስ በሕዝብና በመንግስት ትብብር በቁጥጥር ስር ውሏል።

እንዲህ አይነት የግድያ ወንጀሎች በማህበረሰባችን ውስጥ በተደጋጋሚ እየተፈጸመ በመሆኑ ሕዝቡ በስነ ምግባር የሚታነጽባቸዉን ማዕከላት በየአከባቢው ትኩረት ሰጥቶ መገንባትና በዚህ ወንጀልም የተሳተፉ ግለሰቦች ላይ አስተማሪ፣ ተመጣጣኝና ፈጣን ሕጋዊ ውሳኔ እንዲሰጥ እንጠይቃለን።

@
1.9K views23:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-22 19:14:35 በ2022 ምርጥ የካሜራ ጥራት አላቸው ተብለው የተመረጡ ስማርት ስልኮች የትኞቹ ናቸው…ʔ

ስማርት ስልኮችን ተመራጭ ከሚያደርጋው ውስጥ የካሜራ ጥራት አንዱ ነው። የስማርት ስልክ አምራቾች ለካሜራ ጥራት ትኩረት ሰጥው እየሰሩ ይገኛሉ።
https://am.al-ain.com/article/the-best-camera-phone-for-2022?utm_source=paid+twitter&utm_medium=paid+social&utm_campaign=amharic+always+on
2.2K views16:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-12 17:22:28 #አንዲት_ሀገር_እንዴት_ማጥፋት_ይቻላል

በደቡብ አፍሪካ በሚገኝ አንድ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ በር ላይ የሚከተለው መልእክት ተጽፎ ታገኙታላችሁ ፦
"ማንኛውንም ሀገር ማፍረስ የአቶሚክ ቦንብ መጠቀምም ሆነ የረዥም ርቀት ተምዘግዛጊ ሚሳኤሎችን መጠቀምን አያስፈልግም...የትምህርት ጥራትን ዝቅ ማድረግ እና በተማሪዎች ፈተና ኩረጃን መፍቀድ ብቻ ነው የሚፈልገው... ታማሚዎች ኮርጀው ባለፉ ዶክተሮች እጅ ይሞታሉ ... በኮራጅ መሐንዲሶች እጅ የተሰሩ ሕንፃዎች ይወድቃሉ ... ኮርጀው ባለፉ ኢኮኖሚስቶች እና የሂሳብ ባለሙያዎች እጅ ገንዘብ ይጠፋል ... የሰው ልጅ የሚሞተው በእንደዚህ አይነት የፈጣሪ ትዕዛዝን በሚተላለፉ የሀይማኖት ሊቃውንት እጅ ነው... ፍትህ እንደዚህ ባሉ ዳኞች እጅ ይዛነፋል... "የትምህርት ውድቀት የሀገር ውድቀት ነው። "

ለተፈታኞች መልካም ፈተና እንዲሆንላቸው ተመኝተናል

ከfb
2.6K viewsedited  14:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-03 06:48:48 TrueCaller Pro v9.14.7

Category: #Utility
Hack:
Premium Unlocked
Feedback: 7.916.749 4.5
Price: Free

#share
#አዲስ ቁጥር ሲደወልላችሁ የቁጥሩን ባለቤት የሚነግራችሁ አፕ እንዴት ይሰራል???
#True_caller android app
የሚሰራበት ሃሳብ በጣም ቀላል በሆነ መንገድ ነው።

አፑን መጀመሪያ ስትጭኑት የሚጠይቃችሁ ዋናው ከስልካችሁ የሚፈልገው ፈቃድ phone book or contact list ለማንበብ ነው ልክ ፈቃድዱን ሥትሰጡት ስልካችሁ ላይ ያለውን ስልክ ቁጥሮች በሙሉ ከነ ስማቸው ወደራሱ central database server (ማእከላዊ መረጃ ማጠርቀሚያ ሰርቨር) በመላክ ይመዘግበዋል።

በተመሳሳይ ሁኔታ በአለም ላይ ያሉ ሰዎች ይህን አፕ በጫኑት ቁጥር ስልካቸው ላይ ያሉትን ስልክ ቁጥሮች በሙሉ ወደ መረጃ ማጠራቀሚያው ይልከዋል።
ከዛ አዲስ ቁጥር ሲደወልላችሁ ወዲያውኑ ስልክ ቁጥሩን ከራሱ database ይፈልገዋል እና ያለውን መረጃ ያመጣላችኋል።

አስራሩ ባጨሩ ሲገለጽ: ሰጥቶ መቀበል እንደማለት ነው ። እናንተ ስልካችሁ ላይ ያሉትን ስልክ ቁጥሮች በሙሉ እንዲወስድ ትፈቅዱለታላችሁ እሱ ደሞ የማታውቁት ስልክ ሲደወልላችሁ የስልኩ ባለቤት ማን እንደሆነ ይነግራችኋል።

ሌላኛው መንገድ Facebook ን በመጠቀም ነው አፑ ሌላ የsignup (መመዝገቢያ መንገድ አለው) ይህም በፌስቡክ signup ማድረግ ነው። በፌስቡክ login ስትሉ የፌአቡክ አካውንታችሁን መረጃ የማንበብ አቅም አለው ይህም የፌስቡክ ጓደኞቻችሁን እንዲያነብ ፈቃድ ይኖረዋል አልዚህ በተመሳሳይ መንገድ የጓደኞቻችሁን ስልክ፣ ፎቶ ስም እና ሌሎች ተጨማሪ መረጃዎችን መሰብሰብ ይችላል።
2.9K views03:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-28 20:36:20 የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማሻሻያ ተደረገ

የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማሻሻያ መደረጉን የንግድ እና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር ለኢቢሲ በላከው መግለጫ አስታወቀ።

በዚሁ መሠረት ከመስከረም 18 ቀን 2015 ዓ.ም እኩለ ሌሊት 6:00 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ የሚከተለው እንዲሆን ተወስኗል።

1. ቤንዚን በሊትር - 57 ብር ከ05 ሣንቲም
2. ነጭ ናፍጣ በሊትር - 59 ብር ከ90 ሣንቲም
3. ኬሮሲን በሊትር - 59 ብር ከ90 ሣንቲም ሲሆን

4. በሥራ ላይ የነበረው ዋጋቸው ባለበት የሚቀጥል የነዳጅ ውጤቶች

4.1. የአውሮፕላን ነዳጅ በሊትር - 76 ብር ከ87 ሣንቲም

4.2. ቀላል ጥቁር ናፍጣ በሊትር - 43 ብር ከ89 ሣንቲም

4.3. ከባድ ጥቁር ናፍጣ በሊትር - 43 ብር ከ06 ሣንቲም እንዲሆን ተወስኗል።

በሌላ በኩል አነስተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ በተረዘጋው የታለመ ድጎማ አሠራር ታቅፈው ሕዝቡን እንዲያገለግሉ የተመረጡት የሕዝብ ትራንስፖርት ተሽክርካሪዎች በሚጠቀሙት ነዳጅ ላይ በሁለተኛው ምዕራፍ ምንም ዓይነት የዋጋ ጭማሪ አልተደገረም።

እነዚህ ተሽከሪዎች በሐምሌ ወር በተወሰነላቸው ዋጋ ቤንዚን በብር 41.26 በሊትር እንዲሁም ነጭ ናፍጣን በብር 40.86 በሊትር እየገዙ እንዲቀጥሉ ብቻ ሳይሆን ከእጥፍ በላይ ያደገ ድጎማ ከመንግሥት እንዲያገኙ የተደረገ ስለሆነ በሚቀጥው ጊዜ ዋጋ እስኪሻሻል ድረስ በሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ ምንም ዓይነት ጭማሪ አይደረግም ሲል ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ገልጿል።
2.3K views17:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ