Get Mystery Box with random crypto!

Memhir Girma Wondimu

የቴሌግራም ቻናል አርማ memhirgirma — Memhir Girma Wondimu M
የቴሌግራም ቻናል አርማ memhirgirma — Memhir Girma Wondimu
የሰርጥ አድራሻ: @memhirgirma
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.84K
የሰርጥ መግለጫ

<< ይህም ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል >> ወደ ቲቶ 2 ፤ 12-13
ለአሰተየታችሁ
👇👇👇👇👇👇👇
@Memhirgirma2bot

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-02-04 14:56:53 የ ቲክቶክ ቻናላችንን follow በማድረግ የተለያዩ ትምህርቶችን ይከታተሉ
3.1K views11:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-04 14:53:56 https://vm.tiktok.com/ZMLFQHnA4/
3.0K views11:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-25 11:57:17
3.5K views08:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-25 11:57:16 አገልግሎታችን እንደቀጠለ ነው እግዚአብሔር ይመስገን የፊታችን እሁድ ጥር / 22 / 2014 ዓ.ም በታላቁ ካቴድራል ምስራቀ ፀሐይ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አገልግሎት ይሰጣል

እንደ ቀድሞው ፕሮግራም ህዝቡ ከመብዛቱ የተነሳ እንዳይጋፋ ቅድመ ዝግጅት አስተናጋጆች እና የቤተክርስቲያኑ አባቶች ቅድመ ዝግጅት እያደረጉ ሲሆን

የቤተክርስቲያኑ አድራሻ ፦ ከጀርመን አደባባይ አለፍ ብሎ ከምርጡለ ማርያም ህንጻ ፊት ለፊት ወይም የመዘጋጃ ቤት መቃብር አጠገብ እንደሚሆን ከወዲሁ ላሳውቃችሁ እወዳለሁ

ነገር ግን በጥምቀቱ ኃይል በመንፈስ ተወልደን፤ በዘወትር የአምልኮት መሥዋዕት በኩል በመንፈስ ቅዱስ ተይዘን ስለማንኖር፤ የኑሮአችን መድረሻ ሥጋ ብቻ እየሆነ፤ ስናስብ ለሥጋ፣ ስናቅድ ለሥጋ፣ ስንጨነቅ ለሥጋ፣ ስንደክም ለሥጋ ብቻ ሆኖ በምድራዊ እሳቦትና ጉልበት እናድርሰው የምንለው ነገር ብዙ ያስለፋናል፡፡ ሲሆን ለፍተንም ብዙ ተሰቃይተን፣ ከሰዎችም ጋር ተቀያይመን የምናገኘው ውጤት ላይ በምቀኝነት የሚያዩ ክፉዎች እያደቡበት፤ ጊዜያችን ሁሉ በይድረስ የችኮላ ጥድፊያ ተሞልቶ ስንከራተት የምንውለው አጠገባችን ላለው ለዛሬ ነገር ብቻ ሆነና ነገን የማሸነፊያ መንፈሳዊ ተስፋና ራእይ ከሕይወታችን ጠፋ፡፡ ስለዚህ፥ ዛሬ የማናውቃቸው ነገ የሚመጡ ጊዜዎች አሁን ያስጨኑቁናል፡፡ በመንፈስ ጽናት ተጎብኝተን የጀመርነውን ከፍጻሜ እንዳናደርስ አዳዲሶቹ ጊዜያት ይቀያይሩናል፡፡ ሁኔታዎች ከፍላጎታችን እየወጡ ያልፈለግነውን ያስወስኑናል፡፡ አየህ ልክ ነው፤ ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፡፡

ይሻሉናል ያዋጡናል ብለን የተከተልናቸው የሥጋ ጥበቦችና የርዕዮተ ዓለም መንገዶች፤ የመንፈሳዊነታችንን ጉዞ ቆም ብለን ከማየት የከለከሉን ብዙዎች እንሆናለን፡፡ ይባሱኑ በተገኘንበት በዚህ ክ/ዘመን ላይ ደግሞ፤ መንፈሳዊ ምሪትንና ኃይልን እንደጅልነት፣ የዋህነት፣ አላዋቂነት፣ ኋላ ቀርነት፣ ባሕላዊነት፣ ታሪክ ናፋቂነት ቆጥረነው፤ በሥጋ የተማርናቸው ዕውቀቶች፣ በሥጋ ያመጣናቸው ውጤቶች፣ በሥጋ የጀመርናቸው አካሄዶች፣ በሥጋ የቀረጽናቸው መርሆች፣ በሥጋ ያወጣናቸውና የምንከተላቸው ንድፈ ሀሳቦች እንዲሁም የምንመርጣቸው የኑሮ ዘይቤዎች በሙሉ፤ በፍልስፍናና ሥነ አመክንድ መስመሮች ተጉዘንባቸው፤ የሃይማኖትን እውነታ ከወግና ከልምድ ማሳለፍ አቅቶን፤ ዘመናዊ ነን ያልነው ትውልዶች የዘመን መጫወቻ ሆነን እንገኛለን፡፡
@Memhirgirma
3.3K viewsedited  08:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-21 10:27:05
3.0K views07:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-21 10:27:05 የፊታችን እሁድ ጥር 15 /2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 3ሰዓት ጀምሮ በሰሚት ዋሻ መካነ ሕይወት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የመልአከ መንክራት መምህር ግርማ ወንድሙ የወንጌል እና የፈውስ አገልግሎት ይከናወናል

የቤተክርስቲያኑ አድራሻ ፤ ሳሚት ኮንዶሚኒየም 2ተኛ በር ወረድ ብሎ ከኢትዮ ቻይና ት/ቤት በታች እንደሆነ ልናሳውቃችሁ እንወዳለን

ሰማያዊ ሰው መሆንን [ብናውቅም] ስለማናውቅ፤ መንፈሳዊ እውነትን ለመረዳትና የእምነት ግንዛቤ ይኖረን ዘንድ ማስተዋል ጠፍቶን ዝም ብለን በሥጋ እንገላወዳለን፡፡ ታዲያ ይሄ ማስተዋል ማጣት የሃይማኖትን ትምህርት በሥጋ ዕውቀትና ድካም ለመገንዘብ ጥረት እንድናደርግ መንስኤ ሆኖ፤ 'የተጠመቁ አህዛቦች' እንድንሆን አመለካከታችን በተደበቀ መንፈስ ሲመራ፤ ዛሬ በሀገራችን ያሉት በጎጥ መከፋፈል፣ በልዩነት ተተንርሶ ጥፋት ማድረስ፣ እንደ ወገን መተሳሰብ ቀርቶ እርስ በእርስ መበላላት የጋራ ምልክቶቻችን ሆነው ሁሉም ተሳዳቢና አሽሟጣጭ እስከሆነበት ጥግ ድረስ የጥፋት ልጆች በመሆን፤ የሚብሰውና የሚከፋውን ጊዜ ይበልጡኑ እያባስነውና እያከፋነው፤ የነፍስም የሥጋ ብልሹዎች ሆነን መቅሠፍትን እየጠራን ወደ ፍርድ ዘመን የምናደርገውን ግስጋሴ ለማፍጠን ዕለታችንን በሥጋ ጀምረን በሥጋ እንጨርሳለን፡፡

አብዛኞቻችን በሥጋ ዕድሜ የአካልና የአእምሮ ዕድገት አሳይተን "ይሄን ያህል ዓመቴ ነው" ስንል፤ በእምነት ዕድሜ ግን መንፈሳዊ ዕድገትና ሰማያዊ ከፍታ የሌለን ፍጡሮች ሆነናል፡፡ አዎ.. ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፥ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነው፡፡
@Memhirgirma
3.1K viewsedited  07:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-21 10:27:05

2.1K views07:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-21 10:27:05 እኛ በፊቴ ገበታን አዘጋጀህልኝ ብለን ስለማናመሰግን የምንበላው ሁሉ ከሥጋችን ውፍረት በቀር አልሆን አለ፡፡
2.0K views07:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-21 10:27:05 እግዚአብሔር ይመስገን ጥር / 8 / 2014 ዓ.ም በታላቁ ካቴድራል ምስራቀ ፀሐይ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የመልአከ መንክራት መምህር ግርማ ወንድሙ አገልግሎት በደማቅ ሁኔታተከናውኟል
እግዚአብሔር ከብሯል ዲያቢሎስ ተዋርዷል!

እግዚአብሔር እረኛዬ ነው
ምን ያልጠወለገብን አለ በአኗኗራችን? ኢትዮጵያውያን በአምላክ የቅድስናው ኃይልና ጥበብ እንዳልተጎበኘን ፣ የአባቶቻችን ሞገስና ጽድቅ በዓለም ፊት እንዳልተነበበ ፣ የእምነት ምሪትና የበረከት ጉዞ እንዳልነበረን ሁሉ፤ በቃ ሙልጭ ብለን ጠፋንና የክህደትን ዘመን አንድ ጊዜ አበቀልነው፤ ከዛ በኃላ ትውልድ ጋሸበ፡፡ መውጫ መግቢያው ሁሉ የተምታታ ፤ ምኑን ከምኑ ማድረግ እንደምንችል የጠፋን ፤ እንደው ግራ ግብት ያለን ፍጡሮች ሆነን ቁጭ አልን፡፡
ለምን?
የለመለመው መስክ ጠፍቶናላ፡፡ ስለማንጸልይና ስለማንሰግድ፣ ለእውነት የምንቆምበትን መንፈሳዊ ድፍረትንም ስላጣን፣ ጊዜያችንን ገንዘብና ተድላ ይጨርሰው ብለን ስለወሰንበት፤ የምናድረው ሁሉ በጠወለገ መስክ ላይ ሆነ፡፡ የጠወለገ ጊዜ፣ የጠወለገ ዓመት፣ የጠወለገም ሰዓትና ወቅት ላይ ተገኘንና የምናየው፣ የምንሰማው፣ የምናደርገው ሁሉ በሰይጣን ስሩ የደረቀ፤ የዓለም ሙቀት ያበላሸው፤ መስመር የጠፋው ድንግዝግዙ የወጣ ነገር ሆነ፡፡ ዳዊት ያለው ግን እንደዚህ ነበረ፡፡
' በለመለመ መስክ ያሳድረኛል ፥ በዕረፍት ውኃ ዘንድ ይመራኛል '

በዕረፍት ውኃ ዘንድ #ይመራኛል እኮ ነው እናንተ፡፡ እኛን አሁን የሚመራን ምንድነው? ገንዘብ ነው፡፡ ጥቅም ነው፡፡ ሥልጣን ነው፡፡ ዝና ነው፡፡ እግዚአብሔር አንተ አትመራም ሰው ይምራን ብለን የሆነ የ60'ዎቹ ዘመን ላይ ተደጋገፍንና አንድጋ የክህደትን ድምጽ ጮኽን፤ በኃላም የአፋችንን ፍሬ ተከትሎ ሰው ላይ የወደቀ ትውልድ፣ ሰው ላይ የወደቀ ዘመን፣ ሰው ላይ የወደቀም ኑሮ ላይ ተገኘን፡፡ አሁን ባለጊዜውም እንደፈለገ ይመረሃል፡፡ ባለመብት ነኝ፣ እኔም ዜጋ ነኝ፣ እኔም እውነት አለኝ ብትል ባለጊዜዎቹ አያደምጡህም፡፡ ወይ ትገዛላቸዋለህ ወይ ያጠፉሃል፡፡ በኃላዬ ተከተሉኝ ያለውን መድኃኔዓለምን አይ አታስፈልገንም ብለን ስንተወው እየጎተቱ የሚገዙን መጡ፡፡
'በዕረፍት ውኃ ዘንድ ይመረኛል'
አያችሁ
እግዚአብሔር ደሞ የሚመራው በዕረፍቱ ውኃ ላይ ነው፡፡ እፎይ በምትልበት፡፡ ጎንህን በምታሳርፍበት፡፡ ምንም የውስጥ ጭንቀት በማትጨነቅበት፡፡ ሰላምህ ወዳለበት፡፡ ሁሌ ወድምትታጠብበት፡፡ በዕረፍት ውኃ ነዋ የሚመራው፡፡
የዘመናችን ውኃ ደግሞ በኤልሳዕ ዘመን እንደነበረው ክፉው ፣ አጨንጋፊውና ሞት የሚጠራው ውኃ ሆኗል፡፡ ይኸው ታዲያ በሃገራችን ሲሆን የምናየው ሁሉ ምንድነው? የክፉ ውኃ ባለቤት የሆኑ ትውልዶች የሚኖሯቸው ምልክቶች በሙሉ አሉን፡፡ እርስ በእርስ በጎጥ መጠላላት ፣ መጨፋጨፍ ፣ ደምን በግፍ ማፍሰስ ፣ አመጻ ፣ ክፋት ፣ ምቀኝነት ፣ ቁጣ ፣ እልህ ፣ ስድብ ፣ ማባረር ፣ መንቀፍ ፣ በሌላው ችግር የራስን ምቾት መጠበቅና ወዘተ.. የኛ ትውልድ የክፉ ውኃ ባለቤትነታችን መገለጫዎች ናቸው፡፡ እናንተ በጸሎት ቤታችሁ የምትኖሩ ግን 'በዕረፍት ውኃ ዘንድ ይመራኛል' ስትሉ ከዚህ የግርግርና የችግር ዓመትና ጊዜ አውጥቶ በሚያሳርፈው ውኃ ላይ ያኖራችኀል፡፡

➌• ነፍሴንም መለሳት፥ ስለ ስሙም በጽድቅ መንገድ መራኝ።

ድንቅ ቃል ነው፡፡ ነፍሴንም መለሳት፡፡ ይሕንን ቃል የሚናገር ጽህፈት በሐዲስ ኪዳንም ውስጥ እናገኛለን፡፡
" ነፍሴን በሲኦል አትተዋትምና፥ ቅዱስህንም መበስበስን ያይ ዘንድ አትሰጠውም።"
(የሐዋርያት ሥራ 2:27)
ነፍሴንም መለሳት፡፡ ይሕንን የነቃ ሰው ሁሉ ይለዋል፡፡ ነፍሴንም መለሳት፡፡ ነፍስህ ካልተመለሰ ምንም ነገርህ ቢመለስ ዋጋ የለውም፡፡
" ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል?"
(የማቴዎስ ወንጌል 16:26)
ደግሞ ይቀጥልና ስለ ስሙም በጽድቅ መንገድ መራኝ ይላል፡፡ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን፡፡ አያችሁ የቸርነቱን ጥግ? ምን አለ ዳዊት..
'ነፍሴንም መለሳት ፥ ስለ ስሙም በጽድቅ መንገድ መራኝ'
ስለ ስሙ እኮ ነው የሚገርማችሁ፡፡ በስሙ ብቻ ኃይልን እንጨብጣለን፡፡ በስሙ ብቻ በረከትን እናገኛለን፡፡ በስሙም ኃይል የከበብን ሁሉ ጥሰን እናልፋለን፡፡ መቁጠሪያ ለምን አጋንንትን እንደሚያነድ ገባችሁ? በስሙ ነዋ፡፡ መቁጠሪያ አትያዙ ለሚሏችሁ ባህላዊ አማኞች ንገሯቸው፡፡ በስሙ የተባረከውና የተወደደው ሁሉ ወደ ጽድቁ መንገድ የሚመራው ነው በሏቸው፡፡ በስመ መለኮቱ አጋንንትን ስትቀጠቅጥ እጅ እግሩ የሚታሰረው ስለ ስሙ ነው፡፡ ቤተክርስቲያን የምትቆመው በስሙ ነው፡፡ ታቦት የሚቀረጸው በስሙ ነው፡፡ የምንቆርበው በስሙ ነው፡፡ የምንሰግደውም በስሙ ነው፡፡ የምንጸልየው በስሙ ነው፡፡ በእንባ የምንነግረውም በስሙ ነው፡፡ የምንባ'ረከውም የምንባርከውም በስሙ ነው፡፡ በቃ ይኸውላችሁ በስሙ፡፡ ሲም ካርድ አውጥተህ በስምህ ባለቤት እንደምትሆነው የጽድቅም መንገድ የባለቤትነት ይዞታው የኖረው በስሙ ነው፡፡ እንዲህ አለ፡፡ 'ነፍሴንም መለሳት ፥ ስለ ስሙም በጽድቅ መንገድ መራኝ'"

➍• በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም፤ በትርህና ምርኵዝህ እነርሱ ያጸናኑኛል።

አቤት አቤት፡፡ ይሕ ቃለ ደግሞ ይደንቃል፡፡ ፊት ለፊት ነው ያስቀመጠው ይኸውልክ እይ፡፡ በሞት ጥላ መካከል እንኳን ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም፡፡
" እንግዲህ ስለዚህ ነገር ምን እንላለን? እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል?"
(ወደ ሮሜ ሰዎች 8:31)

" ሥጋንም የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ፤ ይልቅስ ነፍስንም ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ።"
(የማቴዎስ ወንጌል 10:28)

" በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን።"
(ወደ ሮሜ ሰዎች 8:37)

ይሕንን ሁሉ የቃልኪዳን ቃል ይዘን ነው እንግዲህ የምንጨነቀው፡፡ በሞት ጥላ መካከል እንኳን ብሄድ አንተ እኮ አለህና ክፉን አልፈራም ነው እኮ፡፡ ልብ በሉ የቃሉ ባለቤት ልበ አምላክ ነብዩ ዳዊት በዘመነ ፍዳ ሆኖ ነው ይሕንን የተስፋ ቃል በኃይል የተናገረው፡፡ እኛ ግን ያለነው ዓመተ ምሕረት ላይ ነው፡፡ አማኑኤል በሥጋ ባለበት ዘመን፡፡ ዳዊት አንተ ከእኔ ጋር ነህና አልፈራም ያለው በተስፋው መሠረት ነው፡፡ እኛ እኮ አማኑኤል ብለን እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ ያልንበት ክፍለ ዘመን ላይ ነው የምንገኘው፡፡ ታዲያ አማኑኤልን በጸሎት ቤታችን በስግደትና በጸሎት ዘወትር ይዘን በሞት ጥላ መካከል እንኳን ቢያስገቡን ማንን ክፉ ነው የምንፈራው? በወደደን በእርሱ #ከአሸናፊዎች እንበልጣለን እኮ ነው፡፡ በክፋት ካሸነፉ ፣ በተንኮል ካሸነፉ ፣ በሥልጣን ከፍ ካሉ ፣ ገንዘብ ከፍ ካረጋቸው ፣ ጊዜ ከሰቀላቸው ከሁሉ እኮ ነው፡፡
የዳዊት መዝሙርን በቃል ያዙ!!

➎• በፊቴ ገበታን አዘጋጀህልኝ በጠላቶቼ ፊት ለፊት ራሴን በዘይት ቀባህ፥ ጽዋዬም የተረፈ ነው።

በፊቴም ገበታን አዘጋጀህልኝ ደግሞ አለ፡፡ አሁን ቆይ በምትሰሩት ብቻ የምትመገቡ ይመስላችኃል? እግዚአብሔር በተፈጥሮ አንጾና ቀርጾ ያዘጋጀውን ነው'ኮ በገንዘብ ከሌላ ባለጊዜ ላይ ገዝተህ የምትበላው፡፡ ሻጩ ከየት ያመጣዋል ብላችሁ ነው?
" ወደ ሰማይ ወፎች ተመልከቱ፤ አይዘሩም አያጭዱምም በጎተራም አይከቱም፥ የሰማዩ አባታችሁም ይመግባቸዋል፤ እናንተ ከእነርሱ እጅግ አትበልጡምን?"
(የማቴዎስ ወንጌል 6:26)
2.1K views07:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-21 10:27:05
1.7K views07:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ