Get Mystery Box with random crypto!

አገልግሎታችን እንደቀጠለ ነው እግዚአብሔር ይመስገን የፊታችን እሁድ ጥር / 22 / 2014 ዓ.ም | Memhir Girma Wondimu

አገልግሎታችን እንደቀጠለ ነው እግዚአብሔር ይመስገን የፊታችን እሁድ ጥር / 22 / 2014 ዓ.ም በታላቁ ካቴድራል ምስራቀ ፀሐይ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አገልግሎት ይሰጣል

እንደ ቀድሞው ፕሮግራም ህዝቡ ከመብዛቱ የተነሳ እንዳይጋፋ ቅድመ ዝግጅት አስተናጋጆች እና የቤተክርስቲያኑ አባቶች ቅድመ ዝግጅት እያደረጉ ሲሆን

የቤተክርስቲያኑ አድራሻ ፦ ከጀርመን አደባባይ አለፍ ብሎ ከምርጡለ ማርያም ህንጻ ፊት ለፊት ወይም የመዘጋጃ ቤት መቃብር አጠገብ እንደሚሆን ከወዲሁ ላሳውቃችሁ እወዳለሁ

ነገር ግን በጥምቀቱ ኃይል በመንፈስ ተወልደን፤ በዘወትር የአምልኮት መሥዋዕት በኩል በመንፈስ ቅዱስ ተይዘን ስለማንኖር፤ የኑሮአችን መድረሻ ሥጋ ብቻ እየሆነ፤ ስናስብ ለሥጋ፣ ስናቅድ ለሥጋ፣ ስንጨነቅ ለሥጋ፣ ስንደክም ለሥጋ ብቻ ሆኖ በምድራዊ እሳቦትና ጉልበት እናድርሰው የምንለው ነገር ብዙ ያስለፋናል፡፡ ሲሆን ለፍተንም ብዙ ተሰቃይተን፣ ከሰዎችም ጋር ተቀያይመን የምናገኘው ውጤት ላይ በምቀኝነት የሚያዩ ክፉዎች እያደቡበት፤ ጊዜያችን ሁሉ በይድረስ የችኮላ ጥድፊያ ተሞልቶ ስንከራተት የምንውለው አጠገባችን ላለው ለዛሬ ነገር ብቻ ሆነና ነገን የማሸነፊያ መንፈሳዊ ተስፋና ራእይ ከሕይወታችን ጠፋ፡፡ ስለዚህ፥ ዛሬ የማናውቃቸው ነገ የሚመጡ ጊዜዎች አሁን ያስጨኑቁናል፡፡ በመንፈስ ጽናት ተጎብኝተን የጀመርነውን ከፍጻሜ እንዳናደርስ አዳዲሶቹ ጊዜያት ይቀያይሩናል፡፡ ሁኔታዎች ከፍላጎታችን እየወጡ ያልፈለግነውን ያስወስኑናል፡፡ አየህ ልክ ነው፤ ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፡፡

ይሻሉናል ያዋጡናል ብለን የተከተልናቸው የሥጋ ጥበቦችና የርዕዮተ ዓለም መንገዶች፤ የመንፈሳዊነታችንን ጉዞ ቆም ብለን ከማየት የከለከሉን ብዙዎች እንሆናለን፡፡ ይባሱኑ በተገኘንበት በዚህ ክ/ዘመን ላይ ደግሞ፤ መንፈሳዊ ምሪትንና ኃይልን እንደጅልነት፣ የዋህነት፣ አላዋቂነት፣ ኋላ ቀርነት፣ ባሕላዊነት፣ ታሪክ ናፋቂነት ቆጥረነው፤ በሥጋ የተማርናቸው ዕውቀቶች፣ በሥጋ ያመጣናቸው ውጤቶች፣ በሥጋ የጀመርናቸው አካሄዶች፣ በሥጋ የቀረጽናቸው መርሆች፣ በሥጋ ያወጣናቸውና የምንከተላቸው ንድፈ ሀሳቦች እንዲሁም የምንመርጣቸው የኑሮ ዘይቤዎች በሙሉ፤ በፍልስፍናና ሥነ አመክንድ መስመሮች ተጉዘንባቸው፤ የሃይማኖትን እውነታ ከወግና ከልምድ ማሳለፍ አቅቶን፤ ዘመናዊ ነን ያልነው ትውልዶች የዘመን መጫወቻ ሆነን እንገኛለን፡፡
@Memhirgirma