Get Mystery Box with random crypto!

የፊታችን እሁድ ጥር 15 /2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 3ሰዓት ጀምሮ በሰሚት ዋሻ መካነ ሕይወት ቅዱስ ገ | Memhir Girma Wondimu

የፊታችን እሁድ ጥር 15 /2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 3ሰዓት ጀምሮ በሰሚት ዋሻ መካነ ሕይወት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የመልአከ መንክራት መምህር ግርማ ወንድሙ የወንጌል እና የፈውስ አገልግሎት ይከናወናል

የቤተክርስቲያኑ አድራሻ ፤ ሳሚት ኮንዶሚኒየም 2ተኛ በር ወረድ ብሎ ከኢትዮ ቻይና ት/ቤት በታች እንደሆነ ልናሳውቃችሁ እንወዳለን

ሰማያዊ ሰው መሆንን [ብናውቅም] ስለማናውቅ፤ መንፈሳዊ እውነትን ለመረዳትና የእምነት ግንዛቤ ይኖረን ዘንድ ማስተዋል ጠፍቶን ዝም ብለን በሥጋ እንገላወዳለን፡፡ ታዲያ ይሄ ማስተዋል ማጣት የሃይማኖትን ትምህርት በሥጋ ዕውቀትና ድካም ለመገንዘብ ጥረት እንድናደርግ መንስኤ ሆኖ፤ 'የተጠመቁ አህዛቦች' እንድንሆን አመለካከታችን በተደበቀ መንፈስ ሲመራ፤ ዛሬ በሀገራችን ያሉት በጎጥ መከፋፈል፣ በልዩነት ተተንርሶ ጥፋት ማድረስ፣ እንደ ወገን መተሳሰብ ቀርቶ እርስ በእርስ መበላላት የጋራ ምልክቶቻችን ሆነው ሁሉም ተሳዳቢና አሽሟጣጭ እስከሆነበት ጥግ ድረስ የጥፋት ልጆች በመሆን፤ የሚብሰውና የሚከፋውን ጊዜ ይበልጡኑ እያባስነውና እያከፋነው፤ የነፍስም የሥጋ ብልሹዎች ሆነን መቅሠፍትን እየጠራን ወደ ፍርድ ዘመን የምናደርገውን ግስጋሴ ለማፍጠን ዕለታችንን በሥጋ ጀምረን በሥጋ እንጨርሳለን፡፡

አብዛኞቻችን በሥጋ ዕድሜ የአካልና የአእምሮ ዕድገት አሳይተን "ይሄን ያህል ዓመቴ ነው" ስንል፤ በእምነት ዕድሜ ግን መንፈሳዊ ዕድገትና ሰማያዊ ከፍታ የሌለን ፍጡሮች ሆነናል፡፡ አዎ.. ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፥ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነው፡፡
@Memhirgirma