Get Mystery Box with random crypto!

ETHIO BOOKS PDF

የቴሌግራም ቻናል አርማ kooblife — ETHIO BOOKS PDF E
የቴሌግራም ቻናል አርማ kooblife — ETHIO BOOKS PDF
የሰርጥ አድራሻ: @kooblife
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 10.63K
የሰርጥ መግለጫ

➥ እዚህ ቻናል ላይ የተለያዮ ተከታታይ ታሪኮች (ልቦለዶች) ና ፍልስፈና ሳይኮሎጂ የአማረኛ እና English መጽሀፍትን በ📓PDF እና ትረካዎችን እና መሳጭ ግጥሞችን ሌሎችም ጠቃሚ ነገሮች ያገኛሉ።

ለሃሳብ ና አስተያየት ለመጠየቅ @Ethio96bot

📖 ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል‼️

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-07-18 17:58:23 ​​ ብቸኝነቴን መልሺልኝ

ክፍል 17

ዳኒ የወሰን ልጅ
.
.
.
ሚካኤሌ ለትንሽ ደቂቃ በሩ ላይ ቆመና ሲያያቸው ቆየና ሚጣ በመነሳት ሄዳ
እጁን ይዛ ወንበሩ ላይ አስቀመጠችው ለደቂቃ በዝምታ ቆየና ።
" መሽቷል ማክዳና ሚጢ ለምን በኮንትራት ታክሲ አትሄዱም " አላቸው ሚካኤሌ
ግን ሁለቱም ለመሄድ ፍቃደኛ አልነበሩም
" ምን እንደተባለች ለምን አትነግረንም " አለች ማክዳ
" እሺ ምንም በሽታ የለባትም " አለቸው ሚካኤሌ
" እና ምን ሆና ነው " አለችው ማክዳ
" አይምሮዋ ከአቅሟ በላይ ጫና መቋቋም ተስኖት ነው እራሷን የሳተችው ግን
በወደቀችበት የጭንቅላት አጥንቷ እና የጀርባ ተሰብሯል ሌላም የተሰበሩ
አጥንቶች እግር እጇ ላይ የተሰበሩ አሉ " አለ እና አንገቱን ወደ መሬት ደፋ።
" ሚኪ ይሄ እኮ ውድ ሆስፒታል ነው ለሜን የመንግስት አንወስዳትም አሁን እኮ
ለዚህ ህክምና በትንሹ 10 15 ሺህ ይጠይቃሉ ....."
" የመንግስት ሆስፒታል መሄዱ ምን ትሩጉም አለው እነሱ ወደ የሚያክሙበት
የግል ሆስፒታል ይልኳታል ስለዚህ እዛ መሄዷ ትርጉም የለውም " አለ ኬብሮን
ድንገት በመሀል በመግባት ።
" ሚኪ ለአልጋና ለህክምናውን ስንት ጠየቁህ በእናትህ ንገረኝ ለምን
ትደብቀኛለህ " አለች ማክዳ በልመና ።
" እነግርሻለው ማኪ ለምን እደብቅሻለው እዚህ ከ15 እስከ 20ሺህ ለጀርባ
አጥንቷ የቻይና ሆስፒታል አለ እዛ ሄዳ መታከብ አለበት " አላት ሚኪ ማክዳ እንባ
አይኗን ሞላው
" ህክምናውን ባታገኝስ ሚኪ " አለች በሚያሳዝን ቃል።
" ለምን ማኪ ? " አለ ሚኪ
" ከየት እናመጣለን ፈጣሪ በእኛ ላይ ጨክኖብናል የምንበላው ሳይኖረን በሽታ
በበሽታ አድርጎን የምንጠየቀው ብር ደግሞ ከእኛ አቅም በላይ ሆነብን ምን
አይነት ሀጢያት እንደሰራን አላወቅም ግን ጨክኖብናል " አለች እያለቀሰች
" ተይ ማኪ ፈጣሪን ማማረር ጥሩ አይደለም ለሁሉም ነገር ምክንያት አለው እሺ
" አላት ሚካኤል
" ምን ምክንያት አለው ሚጣንም እግዚአብሔር ይስጠውና ዶክተሩ ከፈለልን
አሁን ማን ይከፍለዋል ?" አለች ማክዳ
" እረ ማኪ ዶክተሩ እኮ አይደለም የከፈለልኝ ሚኪ ነው የከፈለው እኮ " አለች
ሚጣ ሁሉም ደንግጠው ተመለከቷት የሚኪ ድንጋጤ እንዴት አወቀች የሚለውና
ማንም እንዲያውቅ ባለመፈለጉ ነው ማክዳ አንዴ ሚጣን ሌላ ጊዜ ሚኪን
አየችና።
" አንቺ እንዴት አወቅሽ ግን " አለቻት ማክዳ ግራ ተጋብታ
" እራሴን ስቼ በነበረ ጊዜ እሰማ ነበር ዶክተር ማን ይከፍላል ሲሉ ሚኪ ደግሞ
እኔ እከፍላለው ግን ማንም እንዳያውቅ ሲል ሰምቼያለው " አለች ሚጣ ማክዳ
በድንጋጤ ሚካኤሌን ስታየው እሱ አንገቱን ደፍቶ መሬት መሬት እያየ ነበር።
ቃልኪዳን የሆቴሉን መኝታ ክፍል በር ላይ ቆማ ተመለከተቻቸው ሁለቱም
ከወገባቸው በላይ እራቁታቸውን ነበሩ የሰላምን ፈገግታ አየችና እሷም ፈገግ
ብላ።
" በጣም የምወድህ እና የማምንህ ባሌ መጣሁልህ " አለችው እሱም ፈገግ
ብሎ ሰላምን ለቆ ወደ ሚስቱ በመሄድ ተቃቅፈው ከንፈሯን ሲስም ሰላም ደንግጣ
ስታይ።
" አንቺ አንድ ሺህ ዲያቢሎስ አንቺን ሴራ ቀድሞ ታማኙ ባለቤቴ ነግሮኛል አንቺ
የእኛን ትዳር ለማፍረስ ያሴርሽ መስሎሻል ግን እኛ ነን በአንቺ ያሴርነው ... ነይ
ውጪ ዛሬ ውርደትሽን ትቀምሺያለሽ ... " አለችና ከባሏ ጋር በመሄድ እራቁቷን
እንዳለች ከአልጋ ጎትተው አውረደዋት መሬት ለመሬት እያፏቀቁ ወደ ዋናው
መዝናኛ በርካታ ህዝብ ወደ ተሰበሰበበት ወስደዋት በሁሉም ሰው ፊት እራቁቷን
እንዳለች አቁመዋት ሴራዋን ያደረገችውን ሁሉ ህዝቡ ግማሹ የሚጠጣውን
ሲደፍባት ሌላው በጠርሙስና በጫማ ሊመቷት ሲሉ ከለከሉና ድራፍቱ ሲደፍባት
መሬት ላይ እጥፍጥፍ ብላ በመቀመጥ እንዴት መበቀል እንደምትችል ታሴር
ነበር።
ኬብሮን ከፍራሹ ላይ ተቀምጦ ጫቱን ሲቅም ማክዳ አጠገቡ ቁጭ ብላ
እያየቺው ።
" መቃም እኔም እፈልጋለው" አለች ማክዳ
" እኔን ለማናደድ ነው ወይስ ..." አለና ዝም ብሎ ሲያያት እሷም ሆስፒታል
እንደምታድር ተናግራ ብዙ ቢከራከሩም እንቢ አላት መጨረሻ ላይ የቤቱ በር
ተንኳኳ ማክዳ ሄዳ ከፈተች አታውቃትም ግን መአዛ ነበረች ገፈተረቻትና
በመግባት ከኬብሮን ፊት ስትቆም እሱ ደንግጦ ተነሳ እሷ በንዴት ስታየው
ቆይታ።
" አንተ ብስብስ ወረዳ እቺ ደግሞ ማን ነች ... እኔን አስረግዘህ ከሌላ ሴት ጋር
አሸሼ ገዳሜ....." ስትለው ኬብሮን ብድንጋጤ ከተቀመጠበት ተነስቶ እያያት
" ምን?.... አስረግዘህ ነው ያልሺው " አለ ሰውነቱ እየተቀጠቀጠ.........

ይቀጥላል

@Kooblife
@Kooblife

For any comment
@Ethio96bot
9.2K views14:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ