Get Mystery Box with random crypto!

​​ ብቸኝነቴን ...... መልሺልኝ ክፍል ሰላሳ አራት (34) . '.......በቃ በለቅሶ | ETHIO BOOKS PDF

​​ ብቸኝነቴን ...... መልሺልኝ

ክፍል ሰላሳ አራት (34)
.

".......በቃ በለቅሶ ብዛት እንባዬ ደረቀ አይኔ ማየት አልችል አለኝ ዙሪዬን አየሁ
ማንም ከአጠገቤ የለም በእርሀብ የተነሳ ሆዴና ጀርባዬ ተጣበቁ በየምግቤቱ
እየሄድኩ ምግብ እየበሉ ያሉ ሰዎችን እባካቹሁ ከምትበሉት አንዴ አጉርሱኝ አልኩ
እንኳን ሊያጎርሱኝ ጠግበው የሚመልሱትን ምግብ እንኳን ለእኔ ሳይሆን ለውሻ
ነበር የሚሰጡት ግራ ገባኝ ለሰው ልጅ ያለኝ ጥላቻ በረከተ እሬት እሬት አለኝ
በመጨረሻ ከቆሻሻ ውስጥ ነጭ ነጭ ያወጣ እንጀራም ዳቦም አጊቼ በላው እና
ቤተ ክርስቲያን በር ሄጄ ተኛሁ በንጋታው በጣም ታመምኩ ተሰቃየሁ አንድ
ጎልማሳ ሴት አገኙኝ ወስደው አሳከሙኝ በዛው ቤታቸው ወሰዱኝ መሀን ነበሩ
ባልም ልጅም የላቸውም ቤታቸው ጠላ ይሸጣሉ ለካ የወሰዱኝ ለእኔ አስበው
ሳይሆን ጠላ እንዳሻሽጥ ነው ። ምግብ በስርአቱ አልበላ አሻሮ፣ እንኩሮ፣ የጠላ
ቂጣ፣ ምን አለፋህ ጠላው በእኔ ጉልበት ሆነ የሚጠመቀው ጠጪዎቹ ለሚሉኝ
ነገር ለሚጠይቁኝ ሁሉ እሺ ማለት አለብኝ አለበለዚያ ሴትየዋ ቆዳዬ እስኪተላ
ትገርፈኛለች ። በቃ እሺ ብዬ ከመቀመጥ ውጪ ቆንጆ ልጅ ነች ይሏታል በእኔ
የተነሳ አያሌ ወንዶች ይጎርፍ ነበር ሳስበው ይገርመኛል አንድ አንዴ ስሜታቸው
እጃቸው ላይ ይመስለኛል ብሆን የአንድ ሰው ነው አንድ ሺህ ወንድ የመኘኛል
የሚያናድዱት ባለ ትዳሮቹ ነበሩ ከሚስቱ የተለየ ነገር እኔ እንዳለ ሲጠይቁኝ።
ከዛ የስራው ድካም የምግብ መጥፋቱ በየቀኑ ከእኔ ጋር የሚወጡት ወንዶች
እሬት እሬት ማለቱ በቃ ሴትየዋን ብገላት ደስተኛ ነኝ ግን አልችልም ከዚህ ቤት
በሆነ ምክንያት መውጣት እንዳለብኝ ተሰማኝ የሚገርምህ ከጎሮቤት ጋር እንኳን
አትስማማም ሰላምታ የላትም።
ከሚጠጡት መሀል በቅርቡ የመጣ አንድ በጣም ቆንጅዬ ልጅ ነበር እሱን ከልቤ
አፈቀርኩት እሱም አፈቅርሻለው ላግባሽ አለኝ አይኔን አላሸሁም አላገረገርኩም
ቤቱ ወሰደኝ ለ15 ቀን ነበር ጥሩነቱን ያሳየኝ ከዛ እየሰከረ እየመጣ በፊልም ላይ
ያየውን በእኔ ላይ መፈፀም ያምራዋል እንቢ ስል መደብደብ ሲለው ማንም ያጣ
የነጣ ጭቅቅታም ጠላ ጠጪ ሲጫወትብሽ እኮ ነው አንስቼ ሰው ያረኩሽ
ይለኛል ሲለው ከቡና ቤት ሌላ ሴት ይዞ እየመጣ መሬት አስተኝቶኝ እያስረገጠኝ
ከሴቷ ጋር ያደርጋል ሲለው ጓደኞቹን ልኮ እንዲጫወቱብኝ ያረገኛል ። መራራ
ህይወት ይሄ ህዝብ ቁጭ ብሎ ለመፍረድ ማንም አይቀድመው ። ከዛ ጊዜ በኋላ
ነው ታሪኬ የተቀየረው ለዚህ ሰው የሚባል ፍጡር ያለ እርህራሄ ጨካኝ ገዳይ
መሆን ።
ያቺ ጠላ ሻጭ በጠና መታመሟን ሰማሁ ማታ ልጠይቃት መስዬ ሄጄ አፍኜ
ገደልኳት ይሄን ደግሞ ማታ ሰክሮ ሲወላገድ መንገድ ላይ ጠብቄ ብልቱን
ቆረጥኩለት ማንነቴን ሳያውቅ አሁን እያማረው ይቀራታል ማዘን እርህራሄ ተወኩ
" አለች ሰላም ፊቷ ላይ በቀል ስሜት የሚቀለቀል እሳት ይታይባታል።
" .... የአለምን ሰው የተባለ ፍጡር ሁሉ ብጨርስ የምረካ አይመስለኝም ሰው
በጣም እጠላለው " አለች በጥላቻ እየተርገፈገፈች ።
" ይህን ሁሉ ለምን ለእኔ ነገር ነገረሺኝ ታዲያ?" አላት እሱም ሰው ነውና ለእሱም
እንደማትመለስ እየተረዳው በፍርሀት እየተርበደበደ።
" ትንፍስ እድል ውስጤ ለብቻዬ ይዤው ተቀምጬ ጨነቀኝ ቆጠቆጠኝ
ላራግፍበት የምችለው ሰው አንተ ስለሆንክ "
" ማመንሽ ገርሞኝ ነው ለፖሊስ ሄጄ ብከስሽስ?" አላት
" መብትህ ነው ማስረጃ ካለህ .... አየህ ለእኔም ለዚህ ሁሉ ለተፈፀመብኝ ግፍ
ማስረጃ ተብዬ ነው አንተም መጠየቅህ አይቀርም ከዛ ስትወጣ ያቺ ቀን
የመጨረሻ የምታያት ቀን ሆነች ማለት ነው እገልሀለው " አለችው ደንግጦ
ከተቀመጠበት ተነሳ አየቺው እና በጩሀት " ቁጭ በል!! " አለችው ደንግጦ
ተቀመጠ !"... የአንዱ ታሪክ ይቀርሀል የሞኙ ባሌ ሚካኤሌ " አለችው እየፈራ
እየተቀጠቀጠ በእሺታ ጭንቅላቱን ነቀነቀ።
በሆስፒታል መኝታ ክፍል ውስጥ ፅጌሬዳ በሰው ሰሰው ሰራሽ መሳሪያ
እየተደገፈች ህይወቷን ለማስቀጠል ሙከራ እየተደረገላት ነው ። ከበሽተኞች
አልጋ ላይ በጀርባዋ ተኝታለች አየሩ ፀጥ ብሎ በአፍጫዋ የተከተተው አመዳማ
ቢጫ ጎማ አኮስጅን እየሰጣት የእሱ ድምፅ ነው የሚሰማው ሽሽሽሽሽ ሽሿሿሿ
የሚል ።
ከአልጋው አጠገብ ማክዳ ተቀምጣ አይን አይኗን ትመለከታለች ሀሳቧ ግን
ኬብሮን ጋር ነበር በጣም ናፈቀችው ለደቂቃ ከጎና በታጣው በወደደች ፈጣሪዋን
በሆነ ታምር እንዲያመጣላት ለመነችው። ብዙም ሳይቆይ በሩ በእርጋታ ተንኳኳና
ተከፈተ ዘወር ብላ ስታይ ኬብሮን ነበር ደነገጠች አላመነች በህልሟ መሰላት
ቃልን አይታ እንደገና ስታየው ቆሟል ብድግ ሄደችና እየገፋቺው ወጥታ በሩን
ዘጋቺውና።
" አንተ ምን አባህ ልትሰራ መጣህ ? ለምንድን ነው የምትከታተለኝ ነገሩሁ እኮ
በጣም ነው የምታስጠላኝ " አለች
" ሰምቼሻለው አንቺ መኖርሽን ባውቅ አልመጣም እራስሽን አይተሽዋል እንዴት
እንደምታስጠይ " አላት ማክዳ ተናደደች አበደች መስታወተ ፍለጋ አይኗ
ተንከራተተ።.......

~ ይቀጥላል ~~~~

@Kooblife
@Kooblife

For any comment
@Ethio96bot