Get Mystery Box with random crypto!

Kjphotoandmusic 🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ kjphotoandmusic — Kjphotoandmusic 🇪🇹 K
የቴሌግራም ቻናል አርማ kjphotoandmusic — Kjphotoandmusic 🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @kjphotoandmusic
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.48K
የሰርጥ መግለጫ

❤️@kjphotoandmusic❤️
🔥ʜʙᴅ ᴘɪᴄ😍🎂🍰🥧
🔥ᴛɪᴋ ᴛᴏᴋ ᴠɪɴᴇ🤣
🔥ᴅᴀɴᴄᴇ ᴄʜᴀʟʟᴇɴɢᴇ🕺💃
🔥ᴄᴏᴜᴘʟᴇ ᴘɪᴄs👩‍❤️‍💋‍👩
🔥ꜰʀɪᴇɴᴅsʜɪᴘ..ᴘɪᴄs👫
𝗙𝗼𝗿 𝗰𝗿𝗼𝘀𝘀👇
@tizz_bot
sᴇɴᴅ ᴜʀ ᴘɪᴄ👉 @tizz_bot
ᴊᴏɪɴ ᴜs 4 ᴍᴏʀᴇ👇👇
@kjphotoandmusic
@kjphotoandmusic🔱🌹

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-08-22 19:13:57
ውሎ እንዴት ነበር guys?
Anonymous Poll
47%
እብድ ነው
38%
ምንም አይልም
15%
ይደብራል
53 voters452 views16:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 10:41:27 ክፍል 12
:
.....እንዴት እወድሻለሁ ይላል ወረቀቱን ይዤ ተቀመጥኩ ደጋግሜ አነበብኩት በጣም እወድሻለሁ እንዴት ወረቀቱን አስቀምጬ የተጠቀለለውን እቃ መፍታት ጀመርኩ ዩኒፎርም ቀሚስ ነው ደስ አለኝ ምክንያቱም ግዙልኝ ብል ማንም ሊገዛልኝ አይችልም ቀሚሱን ለብሼ አየሁት ልኬ ሆነ ልኬን ማወቁ ጎበዝ ነው ግን ወረቀቱ..... እኔም በጣም እወደዋለሁ ግን ደግሞ እኔ የምወደው እንደፈቅረኛ ሳይሆን እንደ ታላቅ ወንድም ነው ሁሌም ቢሆን ታላቅ ወንድም እንዲኖረኝ እመኝ ስለነበር እሱ ለእኔ እንደታላቅ ወንድም ነው ግንኙነታችንን የማይሆን ስም ሰይመንለት ወንድምነቱን ማጣት አልፈልግም እሱ እንደ እኔ ያስብ አያስብ አላውቅም.....
ወረቀቱን በድጋሚ አንስቼ አነበብኩት ወረቀቱን ገልበጥ አድርጌ ሳየው
"ሳይሽ በጣም ደስ ትይኛለሽ እንዲሁ በጣም እወድሻለሁ ጓደኛሽ መሆን እፈልጋለሁ ይሄን ቀሚስ የሰጠሁሽ እንደውለታ እንድትቆጥሪው አይደለም የግድ ስለሚያስፈልግሽ ነው ከአንድ ከቤተሰብ አባልሽ እንደተሰጠሽ ቁጠሪው ወላሂ ለ አላህ ብዬ እወድሻለሁ "
ይላል ማን ነው እኔን እንዲህ የሚወደኝ እንዲህ የምወደድ ሰው ነኝ እንዴ ወረቀቱ መጨረሻ ላይ "ሳሊሀ" ይላል ይህን እኔ ማመን አልችልም ወላሂ እኔም በጣም ወድጄሻለሁ ለምን ለእኔ እንዲህ ታደርግልኛለች ያ አላህ ሰው እንዴት የማያውቀውን ሰው እንዲህ ይወዳል በደስታ ሰከርኩ የምሆነው ጠፋኝ ጥርሴ ሳይዘጋ እቆማለሁ እቀጣለሁ እሄዳለው ፅሁፋን ደጋግሜ አነባለሁ ለመጀመሪያ ግዜ እወድሻለሁ ተባልኩኝ ለዛውም በሴት ደስ ሲል ቅድም ለምን ሙአዝና ሳሊሀ ብቻቸውን እንዳወሩ ገባኝ....
.
....ሂዊን ከመስጅድ ስመለስ አላገኘኃትም ከነ ሪቾ ጋርም አልነበረችም ስጠይቃቸው አላየናትም አሉ ዞር ዞር ብዬ ፈለኳት የለችም እነሪቾ ቀዝቀዝ ብለውብኛል ጠዋት ከሂዊ ጋር ስለነበርኩ ይመስለኛል ታዲያ እንዴት ብቻዋን ልተዋት ምሳ ከበላን በኃላ አናግሪያቸው ነበር ከደገመችው እኔም እተዋታለሁ አሁን ግን ቢያንስ እንድትስተካከል አንድ እድል እንስጣት አልኳቸው ከሪቾ በስተቀር ሁሉም ተስማሙ ወደ ክፍል ስገባም አላገኘኃትም ነበር ወደ እቤት ሄዳ ይሆናል ብዬ ተውኩት......
.
.....የሚነጋ አልመሰለኝም ነበር ሳሊሀን እስካገኛት በጣም ቸኮልኩ ያለመደብኝን የንጋት ሰላትንም ሰግጄ ቁጭ አልኩ.... ድንገት ባለፈው የሰማሁት ቁርአን አስታወስኩ እኔ ለምን አልሞክርም ብዬ ከቸቀመጥኩበት ተነስቼ ቀርአን አመጣሁ ቁርአኑኑ ከፍቼ ለመቅራት (ለማንበብ) ሞከርኩ ግን ምንም ስለማላውቅ ምን ብዬ ልቅራ ዝም ብዬ በተመስጦ እመለከተው ነበር መቅራት እፈልጋለሁ ግን.....
.
አዲሱን ቀሚስ ለብሽ ቁርሴን ነካ ነካ አድርጌ ወጣሁ ሙአዝ የሚጠብቀኝ ቦታ ላይ ቆሞዋል ከእሩቅ እያየኝ የመጀመሪያ ቀን ያሳየኝን አይነት ፈገግታ አሳየኝ እኔም እየፈገግኩ ሙአዝ ወደ ቆመበት ቦታ ሄድኩ አጠገቡ ስደርስ ሙኒ አንቺ ነሽ አለኝ እንደመሽኮርመም እየሰራራኝ አጎነበስኩ ወላሂ ሙኒ በጣም ነው ያማረብሽ አለኝ ፈገግ ብዬ መራመድ ጀመርን ዛሬም ሳንጨባበጥ መንገዳችንን ቀጠልን ጊዜው የመጀመሪያ ሲሜስተር ማብቂያ ነበር እና የፋይናል ፈተና እየደረሰ ነው ሙኒ ፈተና እኮ እየደረሰ ነው ለምን ማጥናት አትጀምሪም አለኝ የእስከዛሬውን ትምህርት አዳምጬ አላውቅም ገና ትላንት ብቻ ነው በቅጡ እንኳ ያዳመጥኩት እንዴት ነው የማጠናው አልኩት ሙአዝ ፈገግ እያለ አንቺ ለማጥናት ተዘጋጂ እንጂ ሌላውን በእኔ ጣይው አለኝ እንደተስማማሁ ገለፅኩለት ትምህርት ቤት ደረስን አርፍደን ነበር የመጣነው ቀስ እያል ስለነበር የምንሄደው እረፈደ ተማሪ ሁሉ ገብቶ ነበር እኛ ብቻ ነበርን በፍጥነት እየተራመድን እኔም ወደ ክፍሌ ሙአዝም ወደ ክፍሉ ሄድን ደግነቱ እኛ ክፍል መምህሩ አልገባም ነበር ገና ወደ ክፍል ከመግባቴ ነበር ሪቾ እእእእእእእምንድ ነው አለችኝ
....ምኑ ሪቾ አልኳት ደንግጬ
......ቀሚሱ
.....ምን ሆነ
..... ሲ.....ያ.....ም......ር.....ብ....ሽ አለችኝ
የደስታ ሳቅ ሰኩኝ የምርም ያምርብኛል ማለት ነው እያልኩ ኩራት ተሰማኝ ሁለም እንደሚያምርብኝ ሲነግሩኝ በጣም ደስ አለኝ የምሳ ሰአት ደርሶ ወደ መስገጃው ቦታ ሄድን እንደገባሁ ሳሊሀን በአይኔ መፈለግ ጀመርኩ አላገኘኃትም ቅር እያለኝ ኡዱእ አደረኩኝ ኡዱእ አድርጌ ስጨርስ ሳሊሀ ስትገባ ተመለከትኳት ከነበርኩበት ተነስቼ አጠገቧ እንደሄድኩ እንጃ ብቻ አጠገቧ ቆምኩ ለረጅም ግዜ እንደተለያየ ሰው ተቃቅፈን ሰላም ተባባልን ሳሊሀ በስስት እየተመለከተች ረጅም ቀሚስ እንዲህ ያምርብሻል አለችኝ ፈገግ አልኩላት ወደ መስገጃው ቦታ ገብተን ሰገድን.....
፡
ይቀጥላል!!!!!!

Share @kjphotoandmusic
454 views07:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 18:56:36 ♀ያልተፈታ ህልም
ክፍል11
፡
.....ድስ እያለኝ ተማርኩኝ ከልቤ እያዳመጥኳቸው ትምህርቶቹን ጨርሰን የምሳ ሰአት ተደወሎ ወጣን ሙአዝ እኛ ክፍልጋር ቆሞ አገኘሁት እንሂድ አለኝ እሺ ብዬው ለነ ሪቾ ልሄድ ነው ብያቸው ተመለስኩ ኮሊደሩን ጨርሰን ደረጃውን ስኖርድ ቆምኩኝ "ሙኒ ምነው ለምን ቆምሽ" አለኝ መሄድ አልችልም ሙአዝ አንተ ሂድ
.....ለምን እሄዳለሁ ብለሽኝ ነበር እኮ ሙኒ አሁን ምን ተፈጠረ
ምን ልበለው ሙአዝ በቃ አንተ ሂድ አልኩሀ እኔ ነገ እሄዳለሁ.... ሙአዝ ፊቱ ቋጠር አድርጎ ምክንያትሽን ንገሪኝና እሄዳለሁ...
ሙአዝም መኮሳተር ይችላል እንዴ ይገርማል ተኮሳትሮ ሳየው ዛሬ የመጀመሪያዬ ነው
....ሙ....አ......ዝ አንተ ልክ ነበርክ ግን አልሰማሁክም ሳስተካክል እሄዳለሁ
.....አሁን ምን አበላሸሽ አለኝ
.....ምክርህንአልሰማሁም
.....እየሰማሽኝ እኮ ነው ሙኒ ሌላ ነገር ካለ ንገራኝ...... አንገቴን አቀርቅሬ በለሰለሰ ድምፅ.....ቀሚሴ
አልኩት ሙአዝ ፈገግ ብሎ እና ለዚህ ነው በይ ነይ ብሎ ደረጃውን መውረድ ጀመረ ሙአዝ እኔ አልሄድም ድጋሚ መሸማቀቅ አልፈልግም ብዬው እዛው ቆምኩ ሙአዝ የወረደውን ደረጃ በድጋሚ ወጣው ሙኒ ቀስ በቀስ ታስተካክይዋለሽ ለምን በአንድ ቀን ሁሉም ነጠር ለምን አልሆነም አይባልም ሁሉም ነገር ደረጃ በደረጃ ነው የሚሆነው ስለዚህ ከዚህ ቦሀላም ብዙ ቀናቶች አሉሽ ታስተካከይዋለሽ ነገር ግን ለ እሱ ብለሽ ዛሬ ከቀረሽ ምክንያት ይሆንሽና ጭራሽ መሄዱን ታቆሚዋለሽ አሁን እንሂድ እሺ ብዬ ተከተልኩት ሁለታችንም ገባን እንደ ገባሁ ጅልባቢስቷን አገኘኃት በድጋሚ ሰላም ብላኝ የኡዱእ ውሀ ሰጠችኝ ኡዱእ አድርጌ ወደ መስገጃው ለመግባት በራፋ ላይ እንደቆምኩ ጅልባቢስቷ አጠገቤ መጥታ ፈገግ እያለችልኝ ነይ ወደ እዚህ ብላ ምልክት ሰጠችኝ መግባቴን ትቼ ወደ እሷ አጠገብ ሄድኩ አቤት አልኳት እኔም ፈገግ ብዬ ባለፈው ከግዴታ ሰላት ውጪ ስገጂ ስልሽ ለምን ብለሽኝ ነበር እዛ ሆኜ ማስረዳት ስላልቻልኩ ነው አለችኝ ፈገግ እያለች ነው የምታወራው ፈገግታዋ አላዋቂነቴ እንዳያሸማቅቀኝ አድርጎኛል በሙሉ ልብ አው ብዬሽ ነበር አልኳት እሺ መስጂድ ከሆነ የገባሽው ከመቀመጥሽ በፊት ሁለት ረካእ ይሰገዳል የሰላቱም ስም (ታህያተል መስጀድ) ይባላል ካልሆነ ግን ከዝሁር ሰላት (በምሳ ሰአት የሚሰገደው ስግደት) በፊት ግዴታ ያልሆነ ግን ብትሰግጂው ምንዳ የሚያስገኝ(ሱና) ሰላት አለ እሱም ሁለት ረካእ ነው አለችኝ ፈገግ ብላ እንግባ ቡላኝ ቀደመችኝ እሷን ተከትዬ ገባሁ ጅልባቢስቷ ለእኔ ብላ አዘጋጅታው ይሁን አይሁን አላውቅም የለበሰችውን አይነት ጅልባብ ሰጠችኝ አጄም እግሬም ክፍት ነበር አላህ ይስጦልኝ ብዬ ተቀበልኳት ቃሉ ደስ ሲል...... ዛሬም እንዳለፈው ግዜ ፀጥታው የሰዎቹ ሁኔታ ደስ ይላል ይሄ ቦታው ምድር ላይ ካሉ ቦታዎች ለብቻው ተነጥሎ የተሰራ ነው የሚመስለው ምድር ላይ እንደዚህ ሰላም ያለው ቦታአይቼ አላውቅም ይኖራል ብዬም አላስብም ጅልባቢስቷ እንደነገረችኝ አድርጌ ሰገድኩ የፈጠረኝ አካል እንዳለ አምኜ ለክብሩ ወድጄና ፈቅጄ መስገድ ምን ያህል እንደሚያስደስት መግለፅ ይከብዳል የጌታዬ እዝነት ልቤ ውስጥ ጠብ ሲል ታወቀኝ የሰገድኩበት ቦታ ላይ አቀረቀርኩ ውስጤ ተላወሰ ሳላስበው አለቀስኩ እንባዬ መንታ መንታ መውረድ ጀመረ ለምን እንደማለቅስ አላውቅም ፊቴን በጅልባቡ ሸፍኜ አለቅስኩ ከልቤ ተንሰቅስቄ አለቀስኩ ያ... አላህ....
.
....በህብረት ለማሰገደው ሰላት ጥሪ ተደርጎ ሁሉም ተሰብስቦ ቆመ እኔም አብሪያቸው ቆምኩ ወንዶቹን ተከትለን ነበር እየሰገድ የነበረው ከወንዶቹ በኩል አላሁ አክበር(አላህ ትልቅ ነው) የሚለውን ድምፅ ስሰማ ከቁጥጥሬ ውጪ በሆነ መልኩ እንባዬ ይወርድ ጀመር እንዴት ላስቁም ከ አቅሜ በላይ ሆነብኝ አላሁ አክበር የሚለውን ድምፅ ስሰማ ለቅሶዬ ይጨምራል በከንቱ ያሳለፍኳቸውን ጊዜያት በጣም ፀፀተኝ ለምን ጌታዬን አልተዋወኩትም ይሄን ሁሉ አመት ለምን በዚህ ሁኔታ ለምን አልሰገድኩለትም ሰላቱን ጨርሰን ተቀመጥን ጌታዬን ለመለመን እጄ አነሳሁ ጌታዬን እንዲምረኝ ተማፀንኩ ጌታ ሆይ ምህረትህን ለግሰኝ እየደጋገምኩ ጌታዬ ሆይ ምህረትህን ከልቤ እለቀስኩ ጌታዬ ምህረቱን ጠየኩ ዱአ እንደሚደረግ ማን ነገረኝ እኔ እንጃ ጅልባቢስቷ አይይታኝ ነው መሰለኝ ዱአዬን (ፀሎቴን) ስጨርስ አጠገቤ መጥታ አቀፈችኝ ጭራሽ ባሰብኝ እሷም አብራኝ አለቀሰች እንደምንም ለቅሶችንን አቀመን ወጣን ጅልባብ እዛው የሚቀመጥ ነው እንደ እኔ አይነቷ ስትመጣ የሚሰጣት ነው ግቢውን ለቀን ወጣን ከጅልባቢስቷ ጋር ነኝ ሙአዝ ወደ እኛ መጣ ምን ሆና ነው አላት ፈገግ ብላ ምንም አለችው ለካ በጌታዬ ፊት ማልቀስ እንደዚህ ልብን ያረጋጋል እኔ ለሙአዝ መልስ አልሰጠሁትም ጅልባቢስቷ ትምህርት ቤት ድረስ አብራን ሄደች ግቢ ከገባን በኃላ አብሽሪ እሺ አለችኝ ፈገግ አልኩላት ስማኝ ልትሄድ ስትል ግን ስምሽን አልነገርሽኝም እኮ አልኳት ፈገግ እያለች ሳሊሀ እባላለሁ አለችኝ ሙና እባላለሁ አልኳት እሺ ደግሞ ጓደኛሽ ነኝ እሺ ከፈለግሽኝ ብላ ክፍሏን ነግራኝ እዛ ነይ እሺ አለችኝ ደስ አለኝ እየፈገግኩ እሺ አልኳት ሰአትእረፍዶ ስለነበር ተደወለ ምሳ በልተን ወደ ክፍል ገባን ያለመደብኝን ፃፍኩ ማስታወሻ መያዝ ጀመርኩ ተመስጬ ተማርኩ የዛሬን ትምህርት በሚገርም ሁኔታ ተማርኩኝ ትምህርት ስንጨርስ እንደተለመደው ከሙአዝ ጋር ወደ ሰፈር ሄድን ሙአዝ በፌስታል የሆነ ነገር ይዞ ነበር ግን ምንድን ነው ብዬ አልጠየኩትም ሰፈር ስንደርስ ሙኒ አለኝ አቤት አልኩት ይሄን ፌስታል እቤት ስተደርሺ ከፍተሽ እይው ብሎ ሰጠኝ ለእኔ ነው አልኩት አይደለም ለሙና ነው ብሎ አሳቀኝ እሺ ብዬ ተቀበልኩት ምን ይሁን እሰካየው ድረስ በጣም ቸኮልኩ ሙአዝ ትንሽ ራቅ ብሎ ቆሞ ነገ በጠዋት እሺ ብሎኝ ሄደ ለምን አልጨበጠኝም ብዬ አልከፋኝም እሺ ብዬው ወደ እቤት ገባሁ ጊቢ ውስጥ የ አጎቴ ሚስት ነበረች ደግሞ ምን ይዘሽ መጣሽ አለችኝ ሳልመልስላት ወደ ውስጥ ገብቼ ፌስታሉን ከፈትኩኝ በስጦታ መጠቅለያ የተጠቀለለ ነገር አለው ከተጠቀለለው እቃ ላይ ትንሽዬ ወረቀት አለ አነሳሁት በጣም እወድሻለሁ ሙኒ ይላል ደነገጥኩ ሙአዝ ለእኔ እንዴት.....
፡
ይቀጥላል!!!!!!

share @kjphotoandmusic
468 views15:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 14:47:32 . ❦የልቤ ትርታ❦

✼አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✼

#ክፍል_11

... ዋዉ የትላንትናው ምሽት ዛሬ ቀኑን ልዩ አርጎታል መቅደስማ ሌላ ሰው ሆናለች ገና ከእንቅልፏ ስትነቃ ፊቷ በሀሴት ያበራ ነበር ሁሉም ጓደኞቿ ጨራርሰው ወደክላስ ሲሄዱ እሷ እረጋ ብላ ለሳምንታት የረሳችውን መዋቢያዋን አንስታ ትቀባባ ጀመር ሲላት እየዘለለች ሲላት ብቻዋን እየሳቀች ደስታዋ ልክ አጥቶ ነበር።
......ልክ ከዶርም ስትወጣ ጌዲዮን አገኘችው ድጋሚ እንዳዲስ ተፈራሩ እሱም ኩስትር አለ እሷም እንደበፊቱ በመርበትበት ሰላም አደርክ ብላ ጠየቀችው እሱም ፈጣሪ ይመስገን ብሏት ወሬ ሳይጨምር መንገዱን ቀጠለ እሷም ይህን ቃሉን ስለነበር የናፈቀችው ደስታዋ ጨምሮ እየዘለለች ወደ ክፍል ሄደች አስተማሪው መምህር ያሬድ ነበረ ትንሽ ደቂቃዎችም ሆኖታል ትምርት ከተጀመረ መቅደስ ምንም ሳትል ቀጥታ ገባች ያሬድም እልህ ስለነበረበት እስካሁን የት ነበርሽ ብሎ ተቆጣት እሷም የምትለው ሲጠፋባት ከጌዲዮ ጋር ነበርኩ ልትል አስባ ገና ጌዲዮ የሚለው ቃል ካፏ ሳይወጣ ያሬድ በንዴት ጌዲዮ ጌዲዮ ታዲያ ምን ይጠበስ የሚያዋጣሽ ትምርቱ ነው ያ በሽተኛ ነው ብሎ ጮኸባት ባንዴ ደስታዋን ከፊቷ አጠፋው።
......መቅደስም ይቅርታ ቲቸር መናገር ካለብህ እኔን ተናገረኝ በተረፈ ጌዲን እንድትናገረው አልፈቅድልህም ብላ መሬቱን እየደበደበች ሄዳ ወንበሯ ላይ ቁጭ አለች
........ዮናስ ጌዲን ማስፈራራት ፈልጎ ስለነበር ከጓደኞቹ ጋር መንገዱ ላይ ቆሞ ጠበቀው አጠገባቸውም ሲደርስ ና አለው ጌዲዮም አንገት እንደደፋ እኔን ነው አላቸው በተኮሳተረ ድምፅ አዎ አንተን ነው ና ጌዲዮም ያለምንም ፍራቻ አጠገባቸው ሄዶ ምን ፈለጋችሁ አላቸው ዮናስም ከት ብሎ ስቆ ወገኛ ከንዳንተ አይነቱ በሽተኝ ደሞ ምን ይፈለጋል ሲለው ጌዲያ ቆጣ ብሎ ታዲያ ለምን አስቆማችሁኝ አለ ዮናስም ላስጠነቅቅህ ስማ ከመቅደስ ስር ስር እላለሁ ብትል እደፋሀለሁ ታቃለህ እደፋሀለሁ ጌዲዮም በፌዝ መልክ እያየው ውይ ታዲያ ብትንቀኝም ከኔ ትልቅ ነገር ፈልገሀል እኔም አንድ ነገር ልንገርህ ጀግና ፊትለፊት ተዋግቶ ድል ያደርጋል እንጂ እንዳንተ ኋላ ኋላ ብሎ አይደለም እሺ መቅደስን የግልህ ማድረግ ካለብህ በፍቅር ነው የሚያስፈልጓትን የምትፈልጋቸውን ነገሮች በማጥፋት አይደለም እንደው በዚ መንገድ የግልህ ብታረጋት እንኳን መሰረት የሌለው ቤት አይቆምም እና እውነቱን ያወቀች ቀን የውሸት ማንነትህ ገደል ይዞህ እንደሚገባ አትጠራጠር አለው ዮናስም ደሙ ፈልቶ ስማ አንተ ደነዝ እንድትመክረኝ ሳይሆን እንድትጠነቀቅ ነው ያስቆምኩህ አሻፈረኝ ካልክ ግን በነብስህ ፍረድ ሲለው ጌዲዮ ከበፊቱም በላይ በመኮሳተር
........አንተ የፍቅር ትርጉሙ አልገባህም መኖር ካለብኝ ለፍቅር ነው ፍቅር ማለት ደግሞ ስለሌላ መኖር ነው አየህ በዚች ምድር ላይ ለሁለት ነገሮች ነው የምኖረው አንድ ለናቴ ዛሬ ደግሞ ለሁለተኛዋ እናቴ ለፍቅሬ በነዚ ሁለት ነገሮች ለመጣብኝ ከነብስ በላይም ካለ አሳልፌ ለመስጠት ዝግጁ ነኝ ዙሪያ ጥምጥም ከምትሄድ ፊትለፊት ሞክረኝ ደግሞ አትርሳ መቅዲ የማታውቃቸው ያንተ ድብቅ ሚስጥሮች እንዳሉ እናም ወንድም ከኔ በላይ አንተ ፍራ እሺ ብሎት እየተውረገረገ መንገዱን ቀጠለ ዮናስ በጓደኞቹ ፊት አፈረ እነሱም እሱን ለማባበል ይሄ በሽተኛ ፋራ ቆይ እንሰራለታለን ይሄ ገገማ እያሉ የስድብ ናዳ አወረዱበት።
.......አሁን ጌዲዮ አንድ ነገር ገባው መቅደስና ዮናስ የፍቅር ግንኙነት እንደሌላቸው የባለፈው ውሳኔውም ትክክል እንዳልነበር ተረዳ ግን አሁንም መቅደስ እሱን እንደምታፈቅረው ማወቅ ቢፈልግም ግልፅ አልሆነለትም
.......መቅደስና ጓደኞቿ ከመመገቢያ ክፍል እየወጡ ሳለ ጌዲ ደግሞ ገና ሊበላ እየገባ ፊትለፊት ተገናኙ መቼስ ጅብ በቀደደው ውሻ ይሾልክበታል ነው ውሻ በቀደደው ጅብ ይሾልክበታል የሚባለው ብቻ የሆነው ሆኖ እንደተገናኙ ብርሀን ሀይ ጌዲ ሰላም ነው አለችው ከዛም መቅደስ በከፈተችው መንገድ ሁሉም ሰላም አሉት የሚሄድበትን እያዩ የሚያወሩት ሲያጡ የት እየሄድክ ነው ብለው ጠየቁት እሱም ምሳ ልበላ አላቸው እሺ መልካም ምሳ ብለውት ከመለያየታቸው ጌዲዮ አዙሮ ጣለው መቅደስ እየሮጠች ወደሱ መጣች በጣም እየተወራጨ ነበር እንደምንም ብላ አረጋጋችው ከግማሽ ሰአት ቡሀላ እግሮቿ ላይ አስተኝታ ባፍ ባፍንጫው የደፈቀውን አረፋ በገዛ ልብሷ እየጠረገችለት ነቃ ገና ከመንቃቱም አናግሯት የማያውቀውን ከግሮቿ ሳይነሳ መቅዲ አላት እሷም እራሱን እየደባበሰች ወዬ ጌዲ አለችው
የእውነት ፈተንሽኝ ታውቂያለሽ ከዚ በፊት ወድቄ ስነቃ አለሜ ጨልማ ሂወት ጠቁራብኝ ተስፋዬ ተሟጦ ነበር አሁን ግን እንዲህ ሲላት ታይቶ የማይታወቅ ምንም እንኳ ባይስቅ ፈገግታ ፊቱ ላይ ይነበብ ነበር አሁን ግን ምን አለችው መልሱን ለመስማት ጓጉታ ባንቺ የተነሳ ጭራሽ መውደቄን ወደድኩ ምን ብዬ እንደማመሰግንሽ አላቅም ለውለታሽ የሚመጥን ቃል የለኝም እውነት ግን እግዚአብሔር አንቺን ሲፈጥር ብዙ ጥበቡን አፍስሶብሻል አላት
መቅደስ ይህንን የተስፋ ቃል በመስማቷ ቀኑን ሙሉ በደስታ ጮቤ ስትረግጥ ዋለች...

ይቀጥላል...

❥.................. ⚘ ...................❥

ከወደዱት ሼር ያድርጉ

,,,,, ,,,,,

Share:-@kjphotoandmusic
37 views🅚🅐🅚🅤 7, 11:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 10:42:33 ​​. ❦የልቤ ትርታ❦

✼አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✼

#ክፍል_10

...ነገሩ አስገራሚም አስደንጋጭም ነው አስደንጋጩ ጌዲዮ አይመጣም ብለው ለደመደሙት ነው አስገራሚው ክስተት ደግሞ የመቅደስ ህልም እውን መሆኑ ነው።
.
....ለካ ነገሮች ሲዘበራረቁ ቦታ ቦታቸውን ሊይዙ ነው የሚባለው እውነት ነው።ጌዲዮ ካመጣችው ባጃጅ ሲወርድ እውን እሱ አይመስልም በጣም ከስቶ ፊቱ ጠቁሯል ምግብ አሳይተው እንደነሱት ህፃን ብብት ብሏል ፀጉሩ ተበጥሮ የሚያውቅ አይመስልም ልብሱም ዝርክርክ ብሏል ብቻ ባጭሩ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ሳይሆን የጎዳና ተዳዳሪ መስሏል ተማሪው ተገርሞ ለወሬ ከመቸኮሉ የተነሳ ቀስ ብለው ፎቶ አንስተውት በሚሴጅ መቀባበል ጀመሩ ባንዴ ግቢው ተዳረሰ ደስ ያላቸው እንዳያቅፉት እንኳን ደና መጣህ እንዳይሉት ይፈሩታል በመምጣቱ የተበሳጩት ደግሞ ቢችሉ መልሰው ቢያባርሩት ደስታቸው ነበር።.......
በዚህ ሰአት መቅደስ እራሷን አሟት ተኝታ ነበር እነሰአዳም አሉ። የመቅደስ ስልክ ሲጮህ ዝም አለችው ከዛም ሚሴጅ ገባ ብርሀንም ለምን አታዪውም አለቻት መቅደስም እራሷን ይዛ እንዳቃታት አመልክታ አንቺ እዪው አለቻት ከዛም ስትከፍተው ጌዲዮ የመምጣቱ ዜና ነው ብርሀን ሳታስበው በደስታ ጮኸች እነሱም ደንግጠው ምን ሆንሽ አሏት እሷም ነገረቻቸው ግን አላመኗትም ከዛም ፈጠን ብላ ፎቶውን አሳየቻቸው መቅደስ ከማየቷ ከመኝታዋ ወርዳ በለሊት ልብሷ ጫማ እንኳን ሳታደርግ በረረች እነሱም ተከተሏት...
.......ወይ ፍቅር
......ዞር ብላ ግራ ቀኝም አላየችም ቀጥታ እንዳየችው በራ ዘላ ተጠመጠመችበት እራስ ምታት የተባለ ተረሳ ጌዲዮ ትርታው ጨመረ ለማንም ተሰምቶት የማያውቅ ስሜት ለሷ ስለሚሰማው እንደማግኔት ስቦት እሱም አቀፋት ብዙ ተማሪ በሁኔታቸው አለቀሰ ብርሀንና ሰአዳማ ተቃቅፈው ነው ያለቀሱት ጓደኛ መታደል ልክ እንደነሱ ነው ደስታዋ ደስታቸው ሀዘኗ ሀዘናቸው። ሌሎቹም ፎቶ እያነሱ በ ፌስቡክ ይለጥፏቸው ጀመር ግን አዎ ተቃቅፈው ላያቸው እውነት ያጓጓሉ እናም ለደቂቃም ቢሆን ናፍቆታቸውን አስታገሱ ሁለቱም የደስታ እንባ ተናነቃቸው ግን ልትለቀው ስታስብ ፈራች ከዛ እየተቅበጠበጠች ደስታዋን ለመደበቅ እየሞከረች ካንገቱ ስትላቀቅ በሳቅ ተሞልታ አይናይኑን እያየች ውይ ጌዴ ይሄን ያክል ጊዜ የት ሄደህ ነው አለችው።
.....እሱም በስስት እያያት ዝም አላት ቀጠለች በመምጣትህ ደስ ብሎኛል እንኳን ደህና መጣህ አለችው እሱም አመስግኗት ቦርሳውን ይዞ ወደ ማደሪያው ሄደ።
........ጌዲዮ እንዲህ ጉስቁል ያለው በናፍቄቷ በፍቅሯ ነው ከሄደበት ቀን ጀምሮ ካንድ ቤት ወጥቶ አያውቅም ከሷ ሌላ ምንም አይታየውም ነበር በርግጥ በፊትም ማንንም ባያናግርም እሷን ሲለይ ግን ብሶበት አንድ ክፍል ውስጥ ማልቀስ ባለቀሰና እራሱን ባስጨነቀ ቁጥር በሽታው እየተነሳበት ከመቅደስ በላይ ጌዲዮ ተጎድቷል ትላንት ግን እራሱን መቆጣጠር ሲያቅተው የመጣው ቢመጣ የማንም ብትሆን አይኗን ባይ ይሻለኛል ብሎ ነው ገና በለሊት ጅማን የረገጠው።
......በውነቱ መቅደስ ስታቅፈው በህልም አለም ውስጥ ያለ ነበር የመሰለው ነገር ግን ሲለያት በውኑ መሆኑም ሲታወቀው ታፍቅረው አታፍቅረው ባይገባውም ደስታውን መቆጣጠር አቅቶ አለቀሰ።
........መቅደስም ስለቷ ሰመረ እሷም እንደሱ ማፍቀሩን ባታውቅም በደስታ ሰከረች።
.....ይሄንን የሰሙት መምህር ያሬድ ወይንሸት ዮናስም በንዴት የሚይዙት የሚጨብጡት አጡ።
.....የጅማ ዩንቨርስቲ እሁድም ስለሆነ ገና በጠዋቱ ድምቅምቅ አለ።
.......የመቅደስንና የጌዲዮን ደግሞ የመገናኘት ደስታ እነብርሀን ባንድ ለማድረግ አሰቡ በመቀጠልም ከጌዲዮ የዶርም ጓደኞች ጋር በመነጋገር ገንዘብ አዋጡ ብርሀን የሀብታም ልጅ ስለሆነች ከሴቶች ከፍተኛውን ወጪ የሸፍነችው እሷ ነች ከወንዶች ደግሞ በለጠው ወይንሸትን ሲነግሯት በጣም ስለተቃጠለች ግን እንዲያውቁባትም ስለፈለገች ብሩን አዋጣለሁ ፓርቲው ላይ ግን አልገኝም ሌላ ቀጠሮ አለኝ አለቻቸው ሰአዳም አረ ብር በሽ ነው አንፈልግም አለቻት።
......በርግጥ ለብዙ ጊዜ አብረውት ሲማሩ በዝምታውና በበሽታው የተነሳ ለማናገር ቢፈሩትም ዛሬ ግን ደፍረው ከማናገርም አልፈው ወስደው ፀጉሩን አስቆርጠው በራሳቸው ምርጫ አልብሰው አስጌጡት ጌዲዮ መጀመሪያ ሲነግሩት ውስጡ ደስተኛ አልነበረም ምክንያቱም ብዙ ጫጫታና ወከባ ያለበት ቦታ አይመቸውም ቡሀላ ግን መቅደስ እንደምትኖር ሲነግሩት እሷ ካለች የትም ይመቸኛል በሚል ሀሳብ ፍቃደኛ ሆነ።
.
.....መቅደስም ሲነግሯት ደስታዋ እጥፍ ሆነ እሷንም እንደሱ አስዋቧት
......ከዛም የሚገርም ፓርቲ ሆነላቸው በርግጥ አንድ ላይ ባይሆኑም ግን ባይን እየተሰራረቁ አንዳንዴ ደግሞ ደፍራ እየሄደች እያናገረችው ምሽቱን ቦረቁበት ግን ጌዲዮ ያመዋል ብለው ሰግተው ነበር እሱ ግን እንኳን ሊያመው የህመም ስሜትም አልተሰማውም ሁሉንም ያዝናና ዋው የሚያስብል ምርጥ ምሽት አብረው አሳለፉ...

ይቀጥላል...

ታሪኩ ቶሎ እንዲቀጥል VOTE አርጉ፡፡ክፍል 11 ከ20 ቡኃላ ይቀጥላል፡፡

❥.................. ⚘ ...................❥

ከወደዱት ሼር ያድርጉ

,,,,, ,,,,,
••●◉◉●••
Share:-@kjphotoandmusic
220 views🅚🅐🅚🅤 7, 07:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 20:09:41 ትዕግስት የታላቅነት ድል ነው!!
የሰው ልጅ መልካምን ነገር ሁሉ የሚያገኘው የተወሰኑ ሰአታትን በመታገሱ ነው።

ፈንዲሻ እንዴት አማረብሽ ቢሏት እሳቱን ስለታገስኩ ነው አለች።የምትሰጠው ነገር ብዙም ይሁን ትንሽ ፈገግታ ጨምርበት።
Share:-@kjphotoandmusic
269 views niha , 17:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 20:04:04
ታሪኩ ይቀጥል?
Anonymous Poll
89%
አው
11%
ይቅር
47 voters260 views🅚🅐🅚🅤 7, 17:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 09:47:41 ​​. ❦የልቤ ትርታ❦

✼አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✼

#ክፍል_9

... ምሽቱ በጭፈራ ቅልጥ ብሏል መቅደስ እራሷን አታውቅም ከዮናስ ጋር ታብዳለች ትጨፍራለች ትዘላለች ታቅፈዋለች ብቻ የዮናስ ጓደኞች መሸነፋቸውን አመኑ መዳኒት ጠጥታ መሆኑን ማንም አልጠረጠረም ግን ውርርዱን የሚያሸንፈው አብረው እንዳደሩ የሚያሳይ ቪዲዮ ሲያቀርብ ነው ለዚህም ቀደም ብለው ከ ወይንሸት ጋር ዝግጅት አርገዋል።

...........ከዛም አቅፎ ወዳልጋ ክፍል ወሰዳት ስልኩ ደጋግሞ ይጮሀል ግን ብዙ ወንዶች አድንቀው ያላገኙት ገላ መዳፉ ላይ መሆኑን እያሰበ ሊያነሳው ፍቃደኛ አልነበረም መቅደስ በዛ ሰአት ምንም ቢያረጋት እራሷን አታውቅም ተዘርራለች ሌላ አለም ውስጥ ነች እሱም ባንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ ማለት ይሄኔ ነው አለ ባንድ በኩል የውርርዱ ከፍተኛ ገንዘብ ሌላው አስደማሚው የመቅደስ ገላ ደስ አለው ከዛም ልብሱን ሲያወላልቅ ስልኩ ድጋሚ ጮኸ ተናዶ ሊዘጋው ሲያይ አሁን ካሰበው የውርርዱ ገንዘብ ሁለት እጥፍ የሚበልጥ ቢዝነስ ነው ዮናስ በብር ቀልድ አይወድም ሲኦል ብር አለ ቢባል እንኳ ገነትን ትቶ ሲኦል እንደሚገባ አያጠራጥርም ከዛም ይህንን ጨዋታ ለነገ ቀጠሮ ከራሱ ጋር ያዘ መቅደስንም ግቢ ድረስ አድርሷት ወደ ተጠራበት ቢዝነስ ሄደ።

.........ጠዋት ይህንን ወሬ ለወይንሸት ሲነግራት በጣም ተበሳጨች ቆይ እጅህ የገባን እድል አሻፈረኝ ብለክ ድጋሚ ትላለህ አለችው ዮናስም ከዚኛው የዛኛው ቢዝነስ ይበልጥ ነበር ስለዚህ የሚቀድመውን አስቀደምኩ አላት ወይንሸትም ታዲያ እንዴት ብዬ ነው ድጋሚ የማሳምናት በዛ ላይ ትላንትና ለምን ጥለሻት ሄድሽ ሲሉኝስ ምንድነው መልሴ ብላ ጠየቀችው እሱም ሴት ብልሀት አታጣም ይባል የለ ሴትነትሽን አንዳንዴ እንኳን ተጠቀሚበት ብሏት ሄደ።

...........የፈራችው አልቀረም ወደ ዶርም ስትገባ መቅደስ ታማ እነ ብርሀን እያስታመሙ ደረሰች ሰአዳ ልክ ስታያት ደሟ ፈልቶ ቆይ አንቺ መቼ ነው አደራሽን የምትወጪው አለቻት እሷም አይን አውጥታ ምን አረኩ አለች ይሄኔ ብርሀንም ቦግ ብላ ምን ማለት ነው የወሰድሻት እኮ ጭንቀቷን እንድትረሳ ላዝናና ብለሽ እንጂ አስክረሽ ሜዳ እንድትጥያት አይደለም።

.......ወይንሸትም ውሸቷን ጨማምራ እየውላችሁ መጀመሪያ ደና እየተዝናናን ነበር ከዛም ካልጠጣሁ ብላ አስቸገረችኝ ምንም ማረግ ስላልቻልኩ ሰጠኋት ከዛም መስከር ጀመረች ይሄን ጊዜ ዮናስን አየችው ከሱ ጋርም ካልጨፈርኩ ብላ እሪ አለችብኝ ደስታዋን ስለሆነ የምፈልገው እሺ አልኳት ከዛም ተመቻቹ መቅደስ ደንግጣ ከተኛችበት ተነሳች ምንድነው የተመቻቸነው አለቻት ወይንሸትም አስመሳይ ሳቋን በፌዝ መልክ ስቃ ማለት አንድ ላይ መደሰት መጨፈር ጀመራችሁ እሱም አብራኝ ትሁን እሸኛታለሁ ሲለኝ ያው እንደውስ ከኛ በላይ ውለታ ውሎልሽ የለ አብራችሁ እንድትሆኑ ትቼ ከፍቅረኛዬ ጋር ሌላ ጭፈራ ቤት ሄድን አለቻቸው ሁኔታው ቢያጠራጥራቸውም 50%አመኗት።

.........መቅደስ እንደበፊቱ መሆን ተስኗታል በደንብ አትበላ አትጠጣ አትማር አትተኛ ውበቷ ባይካድም ጉስቁል ብላለች።
የጌዲዮ አለመምጣት አድራሻውም መጥፋቱን ሙሉ ለሙሉ አመነች።......በዚህ ከቀጠለች ትምርቷን ማቆሟም የማይካድ ነው በርግጥ ጌዲዮ ከሄደ ሁለተኛ ሳምንቱን ያዘ

.......ወይንሸት አሁንም እኒድ እንዝናና የሚል ጥያቄ ለመቅደስ አቀረበች መቅደስም ጓደኞቿም አልተድማሙም ብንሄድ እራሱ ሁላችንም አሏት...... ፍፁም እንደትላንቱ ለማሳመን ጣረች የሚያምናት ግን አጣች።.....የዮናስም የወይንሸት እቅድ ግብ ሳይመታ ቀረ።

...........ዛሬ ደግሞ ቀኑ ሌላ ነው ለመቅደስ አፍቃሪዎች ሀዘንን አለማመንን ስቃይዋን ተረድተው ላዘኑላት እና ለራሷ ለመቅደስ ትልቅ የምስራች ቢባል ማካበድ አይሆንም...

ይቀጥላል...

ታሪኩ ቶሎ እንዲቀጥል VOTE አርጉ፡፡ክፍል 10 ከ200 ቡኃላ ይቀጥላል፡፡

❥.................. ⚘ ...................❥

ከወደዱት ሼር ያድርጉ

,,,,, ,,,,,
••●◉◉●••
Share:-@kjphotoandmusic
323 views🅚🅐🅚🅤 7, 06:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 11:01:16 ​​. ❦የልቤ ትርታ❦

✼አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✼

#ክፍል_8

... መቅደስና ሰአዳ የጌዲዮን አድራሻ ለመጠየቅ ወደ ቢሮ ሄዱ ቢሮውን ሲያንኳኩ ይግቡ የሚል ድምፅ ሰሙ ከፍተውም ገቡ ሲገቡም ያጋጠማቸው አስተናጋጅ የመቅደስ አፍቃሪ መምህር ያሬድ ነው።መቅደስ በሰአቱ አልደነገጠችም ባለፈው በንዴት ተማሪ መሀል መቅደስ የሰደበችውን አስታውሳ ሰአዳ ግን ክው ነው ያለችው። መምህር ያሬድ መቅደስን ሲያይ እየተቅለሰለሰ እንዲቀመጡ ጋበዛቸው ተቀመጡ ምን ልርዳችሁ አላቸው በትህትና እነሱም የጌዲዮን አድራሻ ፈልገው እንደሆነ አስረዱት መምህር ያሬድ በጌዲዮ የተነሳ በሚያፈቅራት ሴት አንደበት ተሰድቧል በሷ ሳይሆን በሱ ቂም ይዟል እሱ ከሌለ የግሌ አደርጋታለሁ ብሎም አሰበ በውስጡም እንኳን ከዚ ግቢ ከምድረ ገፅም ይጥፋ ብሎ ተመኘ በመቀጠልም ነገ ፈልጎ እንደሚጠብቃቸው ነግሮ ልክ በዚህ ሰአት መጥተው እንዲወስዱ ቀጠራቸው መቅደስ ፈፅሞ ቂም ይዟል ብላ ስላላሰበች አመስግነውት ሄዱ።.......ልክ እንደሄዱለትም በርብሮ ፈልጎ ወዲያው አገኘው ከዛም ከሌላ ሰውም እንዳያገኙት አርጎ የጌዲዮን አድራሻ ሰነድ አርቆ ደበቀው።

..........በነጋታውም ክላሱዋን አቋርጣ ባላት ሰአት ቢሮው ሄደች በለሰለሰ ድምጿ ስጠኝ ብላ ጠየቀችው መምህር ያሬድም መቅዲ የእውነት በጣም አዝናለሁ ከትላንት ጀምሮ ሌላ ስራ አልሰራሁም ማለት ይቻላል ስፈልግ ግን ላገኘው አልቻልኩም መቅደስም ሙሉ ተስፋዋ ተሟጦ አላገኘሁትም ማለት አለችው እሱም መቅዲ የቻልኩትን ሞክሪያለሁ ግን ላገኘው አልቻልኩም ምንም ማድረግ አልችልም ሲላት እንባዎቿ ካይኗ እንደጅረት ያለማቋረጥ ይፈሱ ጀመር መምህር ያሬድም ከወንበሩ ተነስቶ አጠገቧ ሄዶ አቅፎ ባስመሳይ አንደበቱ አባበላት።.....ከቢሮ ስትወጣ ላያት ከለቅሶ ቤት ተመላሽ ነው የምትመስለው............

...ከዛም እየተመላለሽ ጠይቂኝ ስላላት እየተመላለሰች ወደቢሮው ትሄዳለች እያለቀሰች ትመለሳለች አንድ ቀንም እንዲሁ እያነባች ወደ ክፍል ስትገባ እነ ብርሀን ቁጭ ብለው እያጠኑ ነበር ምንም ሳታናግራቸው ተጠቅልላ ተኛች ብርሀን ግን ቀሰቀሰቻት እና ይህ ቆይ የያሬድ ተንኮልስ ቢሆን አለቻቸው ሰአዳም እኔም ጠርጥሪያለሁ አለች መቅደስም ተነስታ ቁጭ አለች ወይን እሸት ግን ምንም መናገር አልፈለገችም ግን እውነት ቢሆንስ ብላ ለማጣጣል እንዴ ምን ልሁን ብሎ ይህንን ነውር ይፈፅማል ስትል ወዲያው መቅደስ ባለፈው ይቅርታ ስላልጠየኩት አለች እነብርሀንም አዎ የሚል መልስ ሰጧት ከዚያም ያሬድ በማይኖርበት ሰአት ሄደው ሌላ መምህር ጠየቁ ያው ያሬድ ስለደበቀው ፈልገው ቢያስፈልጉትም ሊያገኙት አልቻሉም ወይንሸት ደስ አላት ሰአዳና ብርሀን ግን ከመቅደስ ጋር አብረው አዘኑ።

.........ወይንሸት እና ዮናስ ጌዲዮ ስለጠፋ መቅደስን እንዳሰቡት የጌሙ መሀል ላይ ማቆም አልቻሉም አሁን እሷ ማንንም ማግኘት አትፈልግም ልክ እንደጌዲዮ ብቸኝነትን መርጣለች ይሁን እንጂ ሙከራቸውን አላቆሙም ባለፈው ወይንሸት ማሳመን እንደከበዳት ለዮናስ ስትነግረው ቅድሚያ ብር ስለሰጣት ዝቶባታል እሷም ከዮናስ ከተጣላች ብዙ ገቢ እንደምታጣ ስለምታቅ ሙከራዋን አጠንክራ ቀጥላለች።

መቅደስ ጌዲዮን በብዛት የምታይበት ቦታ እየሄደች በተስፋና በናፍቆት ትጠብቀዋለች የወንዶች ዶርም መግቢያውን ከሩቅ ሆና ድንገት የምታየው እየመሰላት በስስት ትጠብቀዋለች ወድቆ የምታቅፈውን ታስታውሳለች እውነት ላያት ታስለቅሳለች ለካ ፍቅር እውነትም ሀያል ነው ማለትም የማይቀር ነው።....ፍቅርን ስላልፈለጉት አይለቅም ስለፈለጉትም አይዝም በቃ በፍቅር ወጥመድ ውስጥ መውደቅ ወደድንም ጠላንም የተፈጥሮ ህግ ነው ከዚ በፊት መቅደስ ካይስኩል ጓደኛዋ ፍቅር እንዲይዛት ትፈልግ ነበር ምክንያቱም ለሷ ከማንም በላይ ብዙ ነገር ሆኖላታል ብዙ ብዙ በቃላት የማይገለፅ ፍቅርን ሰቷታል ግን ፍቅር እንዲይዛት ስለፈለገች አልያዛትም ይኸው ዛሬ ግን ተራው ደርሷት በጌዲዮ ፍቅር እንዲህ እየታመመች ነው።.............ከሩቅ ሆነው ሲያዩዋት የነበሩ የግቢው ቦዘኔ ተማሪዎች ሊያስደነግጧት ተነጋገሩና አንድኛው ተማሪ ልክ እንደጌዲዮ አጎንብሶ ወደወንዶቹ ዶርም መግቢያ ሄደ መቅደስም በተስፋ ስትመለከተው የነበረው መግቢያ ጌዲዮን ያመጣው መሰላት ልጁም ልክ እንደጌዲዮ ተንፈራፍሮ ወደቀ መቅደስም ጨርቋን ጥላ ወደሱ እሮጠች ልክ ስትደርስም ልጁ በሳቅ ወደቀ ሌሎቹም እራሷን እስክትይዝ ሳቁባት እያለቀሰች ወደማደሪያዋ ሄደች አብዛኛው ተማሪ ግን አዘነላት እነዛ ቦዘኔ ተማሪዎች በሰሩት አሳፋሪ ስራ ተበሳጩ እውነት ግን የፍቅር አምላክ ጌዲዮን ያመጣላት ይሆን???????????

........ዶርም ስትገባ ብርሀንና ሰአዳ ሁኔታዋ አንጀታቸውን በልቶት አብረዋት አለቀሱ ወይንሸትም አሁን ተንኮል ለመስራት አመቺ ግዜ ላይ እንዳለች አስባ ብርሀንን እና ሰአዳን መቅደስን ማዝናናት እንደምትፈልግ ነግራ እነሱም እንዳይከተሏት አሳመነቻቸው ከዛም በስንት ልመና መቅደስን ላዝናና በሚል ፓርቲ ወሰደቻት ሀሳቧ ግን ማዝናናት ሳይሆን በመዳኒት አደንዝዛ ከ ዮናስ ጋር አንሶላ እንዲጋፈፉ ማድረግ ነው።ከዛም እንዳሰበችው ቀኑ ሄዶ ጨለማው ሲተካ የቀረበላት ለስላሳ ላይ መዳኒት ጨመረች እራሷንም ስትስት መጨፈር ማበድ ስትጀምርላት ፈረሱም ሜዳውም ያው ብላ ለዮናስ አስረክባ ከሹገር ዳዲ ጋር ተቃቅፋ ወጣች...

ይቀጥላል...

ታሪኩ ቶሎ እንዲቀጥል VOTE አርጉ፡፡

❥.................. ⚘ ...................❥

ከወደዱት ሼር ያድርጉ

,,,,, ,,,,,
••●◉◉●••

Share:-@kjphotoandmusic
339 views🅚🅐🅚🅤 7, 08:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 17:00:18 ሃሳብ ሲደጋገም…….ስሜት ይሆናል!
ስሜት ሲደጋገም…….ተግባር ይሆናል!
ተግባር ሲደጋገም…….ልምድ ይሆናል!
ልምድ ሲደጋገም…….ህይወት ይሆናል!

ህይወት የሚጀምረው ከማሰብ ነው ስለዚህ ሃሳባችንን የምንፈልገው ላይ ብቻ እናድርግ።

ምን ደጋግማችሁ ታስባላችሁ?
Share:-@kjphotoandmusic
345 views🅚🅐🅚🅤 7, 14:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ