Get Mystery Box with random crypto!

​​. ❦የልቤ ትርታ❦ ✼አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✼ | Kjphotoandmusic 🇪🇹

​​. ❦የልቤ ትርታ❦

✼አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ✼

#ክፍል_9

... ምሽቱ በጭፈራ ቅልጥ ብሏል መቅደስ እራሷን አታውቅም ከዮናስ ጋር ታብዳለች ትጨፍራለች ትዘላለች ታቅፈዋለች ብቻ የዮናስ ጓደኞች መሸነፋቸውን አመኑ መዳኒት ጠጥታ መሆኑን ማንም አልጠረጠረም ግን ውርርዱን የሚያሸንፈው አብረው እንዳደሩ የሚያሳይ ቪዲዮ ሲያቀርብ ነው ለዚህም ቀደም ብለው ከ ወይንሸት ጋር ዝግጅት አርገዋል።

...........ከዛም አቅፎ ወዳልጋ ክፍል ወሰዳት ስልኩ ደጋግሞ ይጮሀል ግን ብዙ ወንዶች አድንቀው ያላገኙት ገላ መዳፉ ላይ መሆኑን እያሰበ ሊያነሳው ፍቃደኛ አልነበረም መቅደስ በዛ ሰአት ምንም ቢያረጋት እራሷን አታውቅም ተዘርራለች ሌላ አለም ውስጥ ነች እሱም ባንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ ማለት ይሄኔ ነው አለ ባንድ በኩል የውርርዱ ከፍተኛ ገንዘብ ሌላው አስደማሚው የመቅደስ ገላ ደስ አለው ከዛም ልብሱን ሲያወላልቅ ስልኩ ድጋሚ ጮኸ ተናዶ ሊዘጋው ሲያይ አሁን ካሰበው የውርርዱ ገንዘብ ሁለት እጥፍ የሚበልጥ ቢዝነስ ነው ዮናስ በብር ቀልድ አይወድም ሲኦል ብር አለ ቢባል እንኳ ገነትን ትቶ ሲኦል እንደሚገባ አያጠራጥርም ከዛም ይህንን ጨዋታ ለነገ ቀጠሮ ከራሱ ጋር ያዘ መቅደስንም ግቢ ድረስ አድርሷት ወደ ተጠራበት ቢዝነስ ሄደ።

.........ጠዋት ይህንን ወሬ ለወይንሸት ሲነግራት በጣም ተበሳጨች ቆይ እጅህ የገባን እድል አሻፈረኝ ብለክ ድጋሚ ትላለህ አለችው ዮናስም ከዚኛው የዛኛው ቢዝነስ ይበልጥ ነበር ስለዚህ የሚቀድመውን አስቀደምኩ አላት ወይንሸትም ታዲያ እንዴት ብዬ ነው ድጋሚ የማሳምናት በዛ ላይ ትላንትና ለምን ጥለሻት ሄድሽ ሲሉኝስ ምንድነው መልሴ ብላ ጠየቀችው እሱም ሴት ብልሀት አታጣም ይባል የለ ሴትነትሽን አንዳንዴ እንኳን ተጠቀሚበት ብሏት ሄደ።

...........የፈራችው አልቀረም ወደ ዶርም ስትገባ መቅደስ ታማ እነ ብርሀን እያስታመሙ ደረሰች ሰአዳ ልክ ስታያት ደሟ ፈልቶ ቆይ አንቺ መቼ ነው አደራሽን የምትወጪው አለቻት እሷም አይን አውጥታ ምን አረኩ አለች ይሄኔ ብርሀንም ቦግ ብላ ምን ማለት ነው የወሰድሻት እኮ ጭንቀቷን እንድትረሳ ላዝናና ብለሽ እንጂ አስክረሽ ሜዳ እንድትጥያት አይደለም።

.......ወይንሸትም ውሸቷን ጨማምራ እየውላችሁ መጀመሪያ ደና እየተዝናናን ነበር ከዛም ካልጠጣሁ ብላ አስቸገረችኝ ምንም ማረግ ስላልቻልኩ ሰጠኋት ከዛም መስከር ጀመረች ይሄን ጊዜ ዮናስን አየችው ከሱ ጋርም ካልጨፈርኩ ብላ እሪ አለችብኝ ደስታዋን ስለሆነ የምፈልገው እሺ አልኳት ከዛም ተመቻቹ መቅደስ ደንግጣ ከተኛችበት ተነሳች ምንድነው የተመቻቸነው አለቻት ወይንሸትም አስመሳይ ሳቋን በፌዝ መልክ ስቃ ማለት አንድ ላይ መደሰት መጨፈር ጀመራችሁ እሱም አብራኝ ትሁን እሸኛታለሁ ሲለኝ ያው እንደውስ ከኛ በላይ ውለታ ውሎልሽ የለ አብራችሁ እንድትሆኑ ትቼ ከፍቅረኛዬ ጋር ሌላ ጭፈራ ቤት ሄድን አለቻቸው ሁኔታው ቢያጠራጥራቸውም 50%አመኗት።

.........መቅደስ እንደበፊቱ መሆን ተስኗታል በደንብ አትበላ አትጠጣ አትማር አትተኛ ውበቷ ባይካድም ጉስቁል ብላለች።
የጌዲዮ አለመምጣት አድራሻውም መጥፋቱን ሙሉ ለሙሉ አመነች።......በዚህ ከቀጠለች ትምርቷን ማቆሟም የማይካድ ነው በርግጥ ጌዲዮ ከሄደ ሁለተኛ ሳምንቱን ያዘ

.......ወይንሸት አሁንም እኒድ እንዝናና የሚል ጥያቄ ለመቅደስ አቀረበች መቅደስም ጓደኞቿም አልተድማሙም ብንሄድ እራሱ ሁላችንም አሏት...... ፍፁም እንደትላንቱ ለማሳመን ጣረች የሚያምናት ግን አጣች።.....የዮናስም የወይንሸት እቅድ ግብ ሳይመታ ቀረ።

...........ዛሬ ደግሞ ቀኑ ሌላ ነው ለመቅደስ አፍቃሪዎች ሀዘንን አለማመንን ስቃይዋን ተረድተው ላዘኑላት እና ለራሷ ለመቅደስ ትልቅ የምስራች ቢባል ማካበድ አይሆንም...

ይቀጥላል...

ታሪኩ ቶሎ እንዲቀጥል VOTE አርጉ፡፡ክፍል 10 ከ200 ቡኃላ ይቀጥላል፡፡

❥.................. ⚘ ...................❥

ከወደዱት ሼር ያድርጉ

,,,,, ,,,,,
••●◉◉●••
Share:-@kjphotoandmusic