Get Mystery Box with random crypto!

Kjphotoandmusic 🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ kjphotoandmusic — Kjphotoandmusic 🇪🇹 K
የቴሌግራም ቻናል አርማ kjphotoandmusic — Kjphotoandmusic 🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @kjphotoandmusic
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.48K
የሰርጥ መግለጫ

❤️@kjphotoandmusic❤️
🔥ʜʙᴅ ᴘɪᴄ😍🎂🍰🥧
🔥ᴛɪᴋ ᴛᴏᴋ ᴠɪɴᴇ🤣
🔥ᴅᴀɴᴄᴇ ᴄʜᴀʟʟᴇɴɢᴇ🕺💃
🔥ᴄᴏᴜᴘʟᴇ ᴘɪᴄs👩‍❤️‍💋‍👩
🔥ꜰʀɪᴇɴᴅsʜɪᴘ..ᴘɪᴄs👫
𝗙𝗼𝗿 𝗰𝗿𝗼𝘀𝘀👇
@tizz_bot
sᴇɴᴅ ᴜʀ ᴘɪᴄ👉 @tizz_bot
ᴊᴏɪɴ ᴜs 4 ᴍᴏʀᴇ👇👇
@kjphotoandmusic
@kjphotoandmusic🔱🌹

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-27 09:04:17 Good morning guys
347 views𝙺𝙰𝙺𝚄 𝙲𝚁𝟽, 06:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 19:37:53
ውሎ እንዴት ነበር guys?
Anonymous Poll
40%
እብድ ነው
35%
ምንም አይልም
25%
ይደብራል
68 voters426 views𝙺𝙰𝙺𝚄 𝙲𝚁𝟽, 16:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 15:44:13 ከሁሉም ይበልጥ ህመምን
የሚጨምረው ደና አለመሆንክን
እንኳ የምትነግረው እውነተኛ ወዳጅ
አለማግኘት ነው


◦◦◈◦◦◦◦
#joni

@kjphotoandmusic
@kjphotoandmusic
399 views𝙺𝙰𝙺𝚄 𝙲𝚁𝟽, 12:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 15:00:24
ታሪኩ ይቀጥል?
Anonymous Poll
80%
አው
20%
ይቅር
60 voters396 views12:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 15:59:45 ያልተፈታ ህልም
ክፍል 15
:
......ሳሉ.....ሳሊሀ.....እባክሽን መልስ ስጪኝ.. ጥለሽኝ አትሂጂ .......ትተሽኝ ልትሄጂ ከሆነ ለምን ቀረብሽኝ ሳሊሀ እባክሽን አቤት በይኝ...ፈገግ ብለሽ መልሽልኝ እንጂ ሳሉ..... በአላህ አቤት በይኝ ዝም አትበይ.... .... እጄ በደም ተጨማልቋል ሰው ሁሉ የምሆነውን ቆሞ በዝምታ ይመለከታል አንድም የሚረዳኝ ሰው የለም እባካችሁ እርዱኝ ..... እርዱኝ... ምን ቆማቹ ተፈጡብኛላቹ! ....ከሳሊሀ አንገት ስር የሚወርደው ደም ያለማቋረጥ ይፈሳል ማንም ሊረዳኝ ፈቃደኛ አልነበረም፡፡ በጣም ተጨነኩ ምን ላድርግ ብቻዬን ምንም ማድረግ አልቻልኩም፡፡ ሳሊሀ እጄ ላይ እንዳለች ከእንቅልፎ ደንግጬ ተነሳሁ ያ አላህ ይሄ ሁሉ ጭንቀት በህልሜ ነበር አልሀምዱ ሊላህ እንኳን ህልም ሆነ የእውነት ቢሆን ምን እንደምሆን እንጃ...... ከትምህርት እንደገባሁ ደክሞኝ ስለነበር ጋደም ባልኩበት እንቅልፍ ይዞኝ ሄዶ ነው ይሄን ሁሉ ጉድ ያየሁት፡፡ ከእንቅልፌ ስነቃ ሰአቱ 11፡15 ይላል አስር እንዳልሰገድኩ አስታውስኩ እና ከተኛሁበት ተነሳሁ ከነ ዩኒፎርሜ ስለነበር የተኛሁት ዩኒፎርሜን ቀይሬ ኡዱእ አድርጌ ሰገድኩ፡፡ ሰግጄ ስጨርስ የአጎቴ ሚስት ከኃላዬ አፏን ይዛ ቆማ እስክጨርስ እየጠበቀችኝ ነበር ጨርሼ ስነሳ "ገና ብዙ እናያለን ማነው ይሄን ያስተማረሽ ባክሽ ሰላት መስገዱንስ ተይው ሰላት የሚባል ነገርስ እንዳለ ታውቂያለሽ እንዴ? "አለችኝ እድሜ ለሳሊሀ እና ለሙአዝ የምትናገረውን እስክትጨርስ ጠብቂያት ስተጨርስ ፈገግ ብዬ የሰገድኩበትን አንስቼ ከአጠገቧ ዘወር አልኩ፡፡ የአጎቴ ሚስት ሁኔታዬ ግራ እንዳጋባት እርግጠኛ ነኝ ውስጥ ከገባሁ በኃላ "ጭራሽ እብድ መሰልኩሽ አይደል ስቀሽብኝ ሄድሽ አይደል ይሁን ግዴለም ዋጋሽን ነው የምሰጥሽ" አለችኝ፡፡ የአጎቴ ሚስት ትልቁ እኔን የማስፈራሪያ መሳሪያዋ አጎቴ ነው ማታ ከስራ ሲመለስ ቀን ያደረኩት ነገር ካለ ጨመርመር አድርጋ አስተካክላ ለቁጣ እንዲመች አድርጋ ትነግረዋለች፡፡ አንዳንዴ ሰዎች ማንኛውንም ነገር እነሱ መረዳት እንደሚፈልጉት አድርገው ይረዱታል እነሱ የሚፈልጉትን አይነት ትርጉም ይሰጡትና በተሳሳቸ መንገድ የይረዱታል፡፡ የአጎቴ ሚስትም እንደዛው ነች ለምን እንዲህ አለች ብዬ አልናደድም፡፡ በልቼ እንደጨረስኩ የግቢያችን በር ተንኳኳ በሩን ከፍቼ እዛው ቆምኩ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ሞታ እንደዛ ሳብድላት የነበረችው ልጅ አጠገቤ ቆማለች፡፡ በአግራሞት ተመለከትኳት
...እንዴት መጣሽ?
...ቤቴንስ እንዴት አወቅሽው? አልኳት ተከታትዬ
....አፈላልጌ መጣኃ ቅድም ያወራነውን ነገር እረሳሽው እንዴ? ውዴ
አለችኝ በተረጋጋ አነጋገር ምንም ላስታውስ አልቻልኩም ሳሉ ላስታውሰው አልቻልኩም እርጂኝ አልኳት ፈገግ እያለች
...እሺ ወዴ ዛሬ ነው ቁርአን የምትጀምሪው ግቢና አባያ ካለሽ ደርበሽ ነይ ሰአት ሄዷል ፍጠኚ አለችኝ (አባያ ማለት ሙስሊም ሴቶች የሚለብሱት ሰፋ ያለ ጥቁር ሙሉ ቀሚስ ነው)
በጣም ደስ አለኝ መማር እፈልጋለሁ እነደዛኛው ልጅ መቅራት እፈልጋለሁ፡፡
....እሺ ሳሉ ወደ ግቢ ግቢና ጠብቂኝ በራፍ ላይ ከምትቆሚ
....አይ እዚሁ እሆናለሁ ባይሆን ቶሎ ነይ
እሺ ብያት ወደ ውስጥ ገብቼ የበላሁበትን አነሳስቼ አባያ ለብሼ ወጣሁ ስወጣ የ አጎቴ ሚስት አላየችኝም ነበር ከ ሳሊሀ ጋር ወደ ቁርአን ቤቱ ሄድን፡፡ ወደ ቁርአን ቤቱ ገባን ቁርአን ቤቱ ሰፈራችን ያለው መስጅድ ውስጥ ነበር፡፡ ሳሊሀ ገና ከመቀመጧ ነበር የሚቀሩ ተማሪዎች የከበቧት ምንድን ነው ግራገባኝ "አሰላሙ አለይኩም" አለቻቸው ሁሉም በህብረት "ወአለይኩም ሰላም" ብለው መለሱላት "እንዳረፈድኩ አውቃለሁ አፉ በሉኝ" አለች፡፡ እኔ ከሳሊሀ አጠገብ ተቀመጥኩ በዙሪያችን ከተቀመጡ ልጆች መካከል አንዷ ለሳሊሀ ቁርአን ሰጠቻት ሳሊሀም ተቀበለቻት እና ልቀጥል አለቻት አንገቷን በመነቅነቅ እንድትቀጥል ምልክት ሰጠቻት ልጅቷ መቅራት ጀመረች ሳሊሀ በመሀል አይደለም እያለች ልጅቷ ስትታሳት እያረመቻት ታዳምጣታለች፡፡ እኔ ምንም አልልም የሚቀሩ ልጆችን አይን አይን እየተቁለጨለጭኩ አያቸዋለሁ፡፡ ከእኔ በእድሜ በጣም የሚያንሱ ልጆች ቁርአንን አቀላጥፈው ሲቀሩ ቀናሁ ቅናቱ ከክፋት የመጣ ሳይሆን ምነው እኔም እንደ እነሱ ቀርቼ በሆነ አይነት ነገር ነው፡፡ በራሴም አዘንኩ ሳሊሀን የከበቧት ልጆች ቀስ በቀስ ተነሱ ሁሉንም አስቀርታ ስትጨርስ እኔን ማስቀራት ጀመረች ከ አሊፍ ጀምራ ደጋግማ አስቀራችኝ ጥሩነት እኔ ማንኛውንም ነገር ቶሎ የመቀበል አቅም አለኝ፡፡ እነዚህን የተወሰነ ቅሪና ወደ ቀጣዩ እናልፋለን አለችኝ እሺ አልኳት ሳሊሀ ለመናገር ጉሮሮዋን ስትጠራርግ ሁሉም ተማሪዎች ወደ እሷ ዞሩ ቦታው ፀጥ አለ ሳሊሀ መናገር ጀመረች "ዛሬ አዲስ ተማሪ ይዤላችሁ መጥቻለሁ ስሟ ሙና ይባላል ከዛሬ ጀምሮ የዚህ ቁርአን ቤት ቀሪ ትሆናለች "ብላ ንግግሯን ጨረሰች "አሰላሙ አለይኩም እንኳን ደህና መጣሽ እህታችን" አሉኝ በህብረት ደስ ሲሉ "ወአለይኩም ሰላም" ብዬ መለስኩላቸው የመግሪብ ሰላት አዛን ተአዘነ ሁሉም መውጣት ጀመሩ አንዷ ልጅ ብቻ ወደ እኛ መጣች "ኡስታዝ ነገ አልመጣም" ለምን አለቻት ሳሊሀ የሆነ የገጠመኝ ነገር አለ አለቻት እሺ ግን ነገን ብቻ ነው የተፈቀደልሽ አለቻት ሳሊሀ ፈገግ እያለች እሺ ኡስታዝ ብላት ወጣች ሳሊሀ ኡስታዝ ናት ማለት ነው ይገርማል እንዴት አላወኩም ኡስታዝ ማለት መምህር እንደማለት ነው፡፡ ሰግደን እንድንሄድ ሳሊሀ ጠየቀችኝ እሺ ብያት የመግሪብን ሰላት ሰግደን ወጣን ቤታችን ከመስጅዱ ብዙም አይርቅም ቶሎ ደረስኩ ሳሊሀ እኔን ለመሸኘት ብላ አብረኝ መጣች የእሷ ቤት ይርቃል እንደሚመሽባት እያወቀች እኔን ለመሸኘት መጣች የኔ ሚስኪን እቤት ስደርስ አቅፌ ሳምኳትና ተለያየን ሳሊሀ ትንሽ ከሄደች በኃላ ተመለሰች ሙኒ ብላ ጠርታ አስቆመችኝ ወዬ ሳሉ ለ አላህ ብዬ በጣም እወድሻለሁ አለችኝ ሳሉ እኔም በጣም እወድሻለሁ አልኳትና በድጋሚ ሳምኳት እሺ ወዴ ብላኝ ሄደች ከአይኔ እስክትጠፋ በአይኔ ሸኘኃት እና ወደ ቤት ለመግባት በሩን ማንኳኳት ጀመርኩ ለካ የአጎቴ ሚስት እንደወጣሁ አላወቀችም በዛ ለይ የቅድሙ አለ ዛሬ በቃ አለቀልኝ ምን እንሚሉኝ ምን እንደ ሚያደርጉኝ እንጃ.......

ይቀጥላል!!!!!!
Share Share Share
ከወደዱት ሼር ያድርጉ

@kjphotoandmusic
462 views12:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 23:19:00 ሞት ተፈርዶበት አንገቱ ውስጥ ገመድ ገብቶ የመጨረሻ ቃል ተናገር ተባለ፤ ከዛ ኮስተር ብሎ "ይብላኝ ለእናንተ እኔስ ትምህርት ወስጃለው" አለ አሉ።

ስለዚህ ከትናንሽ ስህተቶችህ ቶሎ ካልተማርክ ባለቀ ሰዓት ከነቃህ ትርፉ ቁጭት ነው፤ ከነቃህ አይቀር አታርፍድ ወዳጄ!

መልካም ምሽት

Share
@kjphotoandmusic
439 views20:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 20:35:33 ሁሉም ሰው ሊወድክ አይችልም ምክኒያቱም አንተ ብር አይደለክም። ነገር ግን ያለ ምክንያት የወደደክን አምላክህ አስታውስ።

@kaku_cr7

Share @kjphotoandmusic
453 views17:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 23:36:48 ይቅርታ አድርግ ሰውንም ተረዳ ነገር ግን ሞኝ አትሁን

Share
@kjphotoandmusic
473 views20:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 20:45:09 ♀ያልተፈታ ህልም
ክፍል 14
:
.....ብዙም ሳንቆይ ተደወለ ምሳ እንብላ ብለው ጥለውኝ ተነሱ አልተከተልኳቸውም እዛው የምንቀመጥበት ቦታ ላይ ትንሽ ተቀምጬ ወደ ክፍል ገባሁ የነ ሪቾ መቀያየር ይሄን ያህል ቦታ አልሰጠሁትም አስተማሪ ከገባ በኃላ መጡ አስተማሪው የሌለ ነው የጮኸባቸው እኔ እንኳን ተርፊያለሁ አንድ መቀመጫ ላይ ሁለት ሁለት ነው የምንቀመጠው እኔ ከሪቾ ጋር ነው የምቀመጠው እንድተቀመጥ ብዬ ወደ ወደ አንዱ ጎን ተጠጋሁ ገልመጥ አድርጋኝ በሂዊ ቦታ ላይ ከሀና ጋር ተቀመጠች እኔ በቻዬን ሆንኩ ሁኔታቸው ፈገግ አደረገኝ እና አስተማሪውን መከታተል ጀመርኩ ..ወቀጣዩ ክፍለግዜ አልፎ ወደ ቤት መሄጃ ሰአት ደረሰ እንደተለመደው ሙአዝ ክፍላችን ድረስ መጣ ምንም እንዳልተፈጠረ አድርጌ ልሰናበታቸው እጄን ስዘረጋላቸው እንዳለሁ እራሱ ሳይቆጥሩኝ ወሬያቸውን እያወሩ ይስቃሉ መልስ ሳጣ ትቻቸው ሄድኩ ሙአዝ ፈገግ ብሎ ምን ነው ሙኒ ቆየሽብኝ እኮ አለኝ በሁኔታቸው ትንሽ ተናድጄባቸው ነበር ግን የሙአዝ ፈገግታ እና ሙኒ የምትለዋ ጥሪ ስሜቴን ቀየሩት ፈገግ አልኩኝ እና ዝም አልኩት ከትምህርት ቤት መውጫው በራፍ ላይ ስንደርስ እኔ ቆምኩኝ ሙአዝ ለምን ቆምሽ ምን እረሳሽ አለኝ
....ሳሊሀ ብዬ ዝም አልኩት
....ሳሊሀ ምን ሙኒ
....ሳላገኛት ወደ ቤት መሄድ አልፈልግም
.....አሁን ታዲያ የት እናገኛታለን
.....እያስተዛዘንኩ አንዴ ብቻ ክፍሏ ደርሼ ልምጣ አልኩት አጎንብሼ በአይኖቼ ሰረቅ አድርጌ እየተመለከትኩት
.....ሙአዝ ፊቱን ቋጠር እያደረገ እኔን እዚህ አቁሽ እሷ ጋር ልሂድ ስትይ አታፍሪም አለኝ
.....ይቅርታ ሙአዝ ግን የግድ ላገኛት እፈልጋለሁ እባክህ
....ሂጂ አብረሻት ነይ እኔ መሄዴ ነው
....እየከፋኝ እሺ በቃ ተወው ወደ ቤት እንሂድ
..ሙአዝ ከቆመበት ሳይንቀሳቀስ መሳቅ ጀመረ ዛሬ ምን ተገኘ የሚያስቅ ሙአዝ ብዙ ግዜ ፈገግ ሲል እንጂ እንዲህ ሲስቅ አይቼው አላውቅም
ምን ያስቅሀል?
እየሳቀ አንቺ ነሻ ሌላ ምን ሊያስቀኝ ይችላል
እኔ ምን አደረኩ የሚያስቅ ነገር አድርጊያለሁ እንዴ
የምር ወደ ቤት ልትሄጂ ነበር
አዋ እሄዳለሁ አላልከኝም
እየሳቀ እኔ እኮ እየቀለድኩ ነው ቀልድ አታውቂም እንዴ ሙኒ
እኔም እየሳኩ ሂ...ዛ
....ይሄን ያህል እንደምታከብሪኝ አላውቅም ነበር በጣም አመሰግናለሁ ሙኒ ብቻሽን ሳይሆን አብረን እንሂድ ነይ
ደስ አለኝ ወደ እነ ሳሊሀ ክፍል ሄድን አሎጣችም ነበር ከነ ሪቾ ያጣሁትን ሰላምታ እሳ ጋር እጥፍ በማድረግ አገኘሁት ሳሊሀን እንዳገኘኃት ጥምጥም አልኩባት ኸረ ቀስ አለኝ ሙአዝ እስቲ ዝም በል ላውራበት
....ሳሊሀ ሳለገኝሽ እንዳልሄድ ብዬ ነው አመጣጤ
.....እየሳቀች አቀፈችኝ እንሂድ አለች
....እሺ ብያት ወደ መውጫው አመራን ሙአዝ
....ፍቅራቹ ጨምሮዋል በዚህ አያያዝሽማ እኛም ሳንረሳ አይቀርም ሲል ሶስታችንም ሳቅን
.....ከግቢው ከወጣን በኃላ ተሰነባብተን ሳሊሀ ሄደች እኔ እና ሙአዝ አንድ ላይ ሄድን.....
.
.... ከአስፓልቱ ዳር ላይ ቆሜ የተፈጠረውን ነገር ለማየት እየተንጠራራሁ ነው ግን ምን ነገር ማየት አልቻልኩም አስፓልቱ በሰው ተሞልቶወል የሆነ አደጋ ነገር ይመስላል ወደ ሁኔታውን ለመመልከት ወደ አስፓልቱ መሀል ተጠጋሁ ብሉ ብላክ ጨርቅ ነገር ከሰዎቹ መሀል ላይ ይታያል ይበልጥ ነገሩን ለማጣራት ወደ እነሱ ቀረብኩ ሞተች እንዴ እያሉ ሲያወሩ ሰማሁ አጠገቤ የነበረውን ልጅ ምን ተፈጥሮ ነው መኪና ገጭቷት ነው ደግሞ ተማሪ ናት አለኝ ምን አልባት የእኛ ትምህርት ቤት ተማሪ ከሆነች ብዬ የተሰበሰቡ ሰዎችን እየገፋሁ ልጅቷ ወደ አለችበት ቦታ ላይ ደረስኩ ያየሁትን ማመን አልቻልኩም ሳላስበው ከምችለው በላይ ጮሁክ ሳሊሀ...... ሳሊሀ......ሳሊሀ......አቤት በይኝ እንጂ ሙና እኮ ነኝ ሳሊሀ ሳሊሀ አይንሽን ግለጪ.....

ይቀጥላል!!!!!!
Share Share Share

@kjphotoandmusic
480 views17:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 00:03:03 ♀ያልተፈታ ህልም
ክፍል 13
:
....ሰግደን ስንጨርስ ቦታውን ለቀን ወጣን ሳሊሀ እኔ ከምገምተው በላይ ስለ እኔ ታውቃለች በጣም ገርሞኛል እኔ ግን ስለሷ ምንም የማውቀው ነገር የለም ስሟን እራሱ ከእሷ ጠይቄ ነው ያወኳት የሆነው ሆኖ ስለ ተለያዩ ነገሮች እያነሳን አወራን ስለትምህርትም አውርተን ነበር እና አብሪያ እንዳጠና ጠየቀችኝ ደስ እያለኝ እሺታዬን ገለፅኩላት ሳሊሀ ሁሌም ፈገግ እንዳለች ነው እኔም ላይ ሳታጋባብኝ አይቀርም በቅርቡ እንዳወኳት ሳይሆን እየተሸማኝ ያለው ከረጅም አመታት በፊት እንደምንተዋወቅ ነው የሚሰማኝ......
.
....ሂዊ ዛሬ ትምህርት ቤት መታለች ወላጅ አምጥታ ነበር በጣም ነው ያሳዘነችኝ አባቷ ነበር የመጡት ምን ብላ ነግራቸው እንደመጡላት እንጃ ከእርእሰ መምህሩ ቢሮ ትንሽ ራቅ ብለን ሁኔታውን እየተመለከትን ነበር መምህሩ ያደረገችውን ነግሯቸው ነው መሰለኝ አባቷ ከተቀመጡበት ብድግ ብለው ተነስተው ቆሙ ሂዊም እነሱ ሲቆሙ አብራቸው ቆመች የሂዊ አባት መካከለኛ ቁመት ያላቸው ወፈር ያሉ ናቸው እንደ ሂዊ ቀይ ናቸው እና ድንገት ሂዊን በጥፊ አዞሩባት ሂዊ የእጃቸውን ግፊት መቋቋም አቅቷት ወደቀች አጠገቧ ሆኜ አይዞሽ እኔ አለልሽ ብላት ምንኛ ደስ ባለኝ እሷ ለተመታችው እኔን አመመኝ ግን አባቷ ምን ሆነው ነው የሚቀጧት ከሆነ እቤት ነው እንጂ ወጪ ላይ ለዛውም ትምህርተ ቤት ውስጥ የምር ያስጠላል ለነገሩ አጎቴ ቢሆን በጥፊ አይደለም ቀበቶውን ፈቶ በቀበቶም ሊመታኝ ይችል ነበር እሱ እንደሆነ አያደርገውም አይባልም የሂዊ አባት ከቢሮ ሂዊን ይዘዋት ወጡ ወደ እኛ ተመጣለች ብለን ስንጠብቅ ይዘዋት ወደ ቤታቸው ሄዱ እዚህ ሆነው እንደዚህ ከመቷት ቤት ወስደው ምን እንደሚያደርጓት ፈጣሪ ነው የሚያውቀው ዛሬ እነ ሪቾም አዘኑላት ግን የገረመኝ ነገር ዳዊትም አምጥቶዋል እንዴት ሁለቱም በ አንድ ቀን ሊያመጡ ቻሉ እንጃ
.....ዛሬ ሳሊሀ ወደ መስገጃ ቦታው አብራን ነው የመጣችው ሁሌም አብራን ብትሆን ደስ ይለኛል ሰግደን ከወጣን በኃላም ሶስታችንም አንድ ላይ እየተመለስን ሳለን ሙአዝ እኔ የምልሽ ሳሊሀ ለምን አንቺ የምትቀሪበት ቦታ ለምን ሙኒንም አታስገቢያትም አላት ጥያቄው እኔም አእምሮ ውስጥ ነበር ግን ሙአዝ ቀድሞ ተናገረልኝ የኔ አሳቢ የሳሊሀን መልስ እየጠበቅን ነው ሳሊሀ ፈገግ እያለች ደስ ይለኛል ግን ሙኒ ትፈልጊያለሽ አለችኝ አዎንታዬን አንገቴን በመነቅነቅ ገለፅኩላት ትምህርት ቤት ስንደርስ ሳሊሀ ወደ ክፍሏ ለመሄድ ልትስመኝ መጣች ቅር አለኝ ልትሄጂ ነው አልኳት እየሳቀች አይ ለመሄድ ካልሆነ አንቺን መሳም አልችልም ማለት ነው አለችኝና አቅፋ ስማኝ ከሙአዝ ጋር እንደቆምን ትታን ሄደች በአይኔ ሸኘኃት ሙአዝ ፈገግ እያለ ሄድሽ እኮ አብረሻት አለኝ አይኔን ወደ መአዝ እየሠለስኩ ቀናህ አንተንም እንዲህ ልይህ እንዴ....
....ኸረ አልፈልግም
....አው ብትለኝም አላይህም አላይህም እሺ
....ከሙአዝ ጋር እየተቀላለድን የምንቀመጥበት ቦታ ላይ ደረስን ገና እንዳዩን ፊታቸው ተቀያየረ ነገረ ስራቸው ግራ እየገባኝ ነው ምንድን ነው እንደዚህ መቀያየር ከሂዊ ጋር ለምን ሆንሽ ከሆነ ትላንት ነግሪያቸዋለሁ ከዚህ ወጪ ምን አደረኩ ታዲያ ኸረ አሁንስ አበዙት መአዝ እኔ ልሂድ ሙኒ ብሎኝ ሄደ አሁን እንግዲ ብቻዬን ነኝ ሂዊም ሆነ ሙአዝ የሉም ምን እነደምሆን እንጃ....


ይቀጥላል!!!!!!
459 views21:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ