Get Mystery Box with random crypto!

ያልተፈታ ህልም ክፍል 15 : ......ሳሉ.....ሳሊሀ.....እባክሽን መልስ ስጪኝ.. ጥለሽኝ | Kjphotoandmusic 🇪🇹

ያልተፈታ ህልም
ክፍል 15
:
......ሳሉ.....ሳሊሀ.....እባክሽን መልስ ስጪኝ.. ጥለሽኝ አትሂጂ .......ትተሽኝ ልትሄጂ ከሆነ ለምን ቀረብሽኝ ሳሊሀ እባክሽን አቤት በይኝ...ፈገግ ብለሽ መልሽልኝ እንጂ ሳሉ..... በአላህ አቤት በይኝ ዝም አትበይ.... .... እጄ በደም ተጨማልቋል ሰው ሁሉ የምሆነውን ቆሞ በዝምታ ይመለከታል አንድም የሚረዳኝ ሰው የለም እባካችሁ እርዱኝ ..... እርዱኝ... ምን ቆማቹ ተፈጡብኛላቹ! ....ከሳሊሀ አንገት ስር የሚወርደው ደም ያለማቋረጥ ይፈሳል ማንም ሊረዳኝ ፈቃደኛ አልነበረም፡፡ በጣም ተጨነኩ ምን ላድርግ ብቻዬን ምንም ማድረግ አልቻልኩም፡፡ ሳሊሀ እጄ ላይ እንዳለች ከእንቅልፎ ደንግጬ ተነሳሁ ያ አላህ ይሄ ሁሉ ጭንቀት በህልሜ ነበር አልሀምዱ ሊላህ እንኳን ህልም ሆነ የእውነት ቢሆን ምን እንደምሆን እንጃ...... ከትምህርት እንደገባሁ ደክሞኝ ስለነበር ጋደም ባልኩበት እንቅልፍ ይዞኝ ሄዶ ነው ይሄን ሁሉ ጉድ ያየሁት፡፡ ከእንቅልፌ ስነቃ ሰአቱ 11፡15 ይላል አስር እንዳልሰገድኩ አስታውስኩ እና ከተኛሁበት ተነሳሁ ከነ ዩኒፎርሜ ስለነበር የተኛሁት ዩኒፎርሜን ቀይሬ ኡዱእ አድርጌ ሰገድኩ፡፡ ሰግጄ ስጨርስ የአጎቴ ሚስት ከኃላዬ አፏን ይዛ ቆማ እስክጨርስ እየጠበቀችኝ ነበር ጨርሼ ስነሳ "ገና ብዙ እናያለን ማነው ይሄን ያስተማረሽ ባክሽ ሰላት መስገዱንስ ተይው ሰላት የሚባል ነገርስ እንዳለ ታውቂያለሽ እንዴ? "አለችኝ እድሜ ለሳሊሀ እና ለሙአዝ የምትናገረውን እስክትጨርስ ጠብቂያት ስተጨርስ ፈገግ ብዬ የሰገድኩበትን አንስቼ ከአጠገቧ ዘወር አልኩ፡፡ የአጎቴ ሚስት ሁኔታዬ ግራ እንዳጋባት እርግጠኛ ነኝ ውስጥ ከገባሁ በኃላ "ጭራሽ እብድ መሰልኩሽ አይደል ስቀሽብኝ ሄድሽ አይደል ይሁን ግዴለም ዋጋሽን ነው የምሰጥሽ" አለችኝ፡፡ የአጎቴ ሚስት ትልቁ እኔን የማስፈራሪያ መሳሪያዋ አጎቴ ነው ማታ ከስራ ሲመለስ ቀን ያደረኩት ነገር ካለ ጨመርመር አድርጋ አስተካክላ ለቁጣ እንዲመች አድርጋ ትነግረዋለች፡፡ አንዳንዴ ሰዎች ማንኛውንም ነገር እነሱ መረዳት እንደሚፈልጉት አድርገው ይረዱታል እነሱ የሚፈልጉትን አይነት ትርጉም ይሰጡትና በተሳሳቸ መንገድ የይረዱታል፡፡ የአጎቴ ሚስትም እንደዛው ነች ለምን እንዲህ አለች ብዬ አልናደድም፡፡ በልቼ እንደጨረስኩ የግቢያችን በር ተንኳኳ በሩን ከፍቼ እዛው ቆምኩ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ሞታ እንደዛ ሳብድላት የነበረችው ልጅ አጠገቤ ቆማለች፡፡ በአግራሞት ተመለከትኳት
...እንዴት መጣሽ?
...ቤቴንስ እንዴት አወቅሽው? አልኳት ተከታትዬ
....አፈላልጌ መጣኃ ቅድም ያወራነውን ነገር እረሳሽው እንዴ? ውዴ
አለችኝ በተረጋጋ አነጋገር ምንም ላስታውስ አልቻልኩም ሳሉ ላስታውሰው አልቻልኩም እርጂኝ አልኳት ፈገግ እያለች
...እሺ ወዴ ዛሬ ነው ቁርአን የምትጀምሪው ግቢና አባያ ካለሽ ደርበሽ ነይ ሰአት ሄዷል ፍጠኚ አለችኝ (አባያ ማለት ሙስሊም ሴቶች የሚለብሱት ሰፋ ያለ ጥቁር ሙሉ ቀሚስ ነው)
በጣም ደስ አለኝ መማር እፈልጋለሁ እነደዛኛው ልጅ መቅራት እፈልጋለሁ፡፡
....እሺ ሳሉ ወደ ግቢ ግቢና ጠብቂኝ በራፍ ላይ ከምትቆሚ
....አይ እዚሁ እሆናለሁ ባይሆን ቶሎ ነይ
እሺ ብያት ወደ ውስጥ ገብቼ የበላሁበትን አነሳስቼ አባያ ለብሼ ወጣሁ ስወጣ የ አጎቴ ሚስት አላየችኝም ነበር ከ ሳሊሀ ጋር ወደ ቁርአን ቤቱ ሄድን፡፡ ወደ ቁርአን ቤቱ ገባን ቁርአን ቤቱ ሰፈራችን ያለው መስጅድ ውስጥ ነበር፡፡ ሳሊሀ ገና ከመቀመጧ ነበር የሚቀሩ ተማሪዎች የከበቧት ምንድን ነው ግራገባኝ "አሰላሙ አለይኩም" አለቻቸው ሁሉም በህብረት "ወአለይኩም ሰላም" ብለው መለሱላት "እንዳረፈድኩ አውቃለሁ አፉ በሉኝ" አለች፡፡ እኔ ከሳሊሀ አጠገብ ተቀመጥኩ በዙሪያችን ከተቀመጡ ልጆች መካከል አንዷ ለሳሊሀ ቁርአን ሰጠቻት ሳሊሀም ተቀበለቻት እና ልቀጥል አለቻት አንገቷን በመነቅነቅ እንድትቀጥል ምልክት ሰጠቻት ልጅቷ መቅራት ጀመረች ሳሊሀ በመሀል አይደለም እያለች ልጅቷ ስትታሳት እያረመቻት ታዳምጣታለች፡፡ እኔ ምንም አልልም የሚቀሩ ልጆችን አይን አይን እየተቁለጨለጭኩ አያቸዋለሁ፡፡ ከእኔ በእድሜ በጣም የሚያንሱ ልጆች ቁርአንን አቀላጥፈው ሲቀሩ ቀናሁ ቅናቱ ከክፋት የመጣ ሳይሆን ምነው እኔም እንደ እነሱ ቀርቼ በሆነ አይነት ነገር ነው፡፡ በራሴም አዘንኩ ሳሊሀን የከበቧት ልጆች ቀስ በቀስ ተነሱ ሁሉንም አስቀርታ ስትጨርስ እኔን ማስቀራት ጀመረች ከ አሊፍ ጀምራ ደጋግማ አስቀራችኝ ጥሩነት እኔ ማንኛውንም ነገር ቶሎ የመቀበል አቅም አለኝ፡፡ እነዚህን የተወሰነ ቅሪና ወደ ቀጣዩ እናልፋለን አለችኝ እሺ አልኳት ሳሊሀ ለመናገር ጉሮሮዋን ስትጠራርግ ሁሉም ተማሪዎች ወደ እሷ ዞሩ ቦታው ፀጥ አለ ሳሊሀ መናገር ጀመረች "ዛሬ አዲስ ተማሪ ይዤላችሁ መጥቻለሁ ስሟ ሙና ይባላል ከዛሬ ጀምሮ የዚህ ቁርአን ቤት ቀሪ ትሆናለች "ብላ ንግግሯን ጨረሰች "አሰላሙ አለይኩም እንኳን ደህና መጣሽ እህታችን" አሉኝ በህብረት ደስ ሲሉ "ወአለይኩም ሰላም" ብዬ መለስኩላቸው የመግሪብ ሰላት አዛን ተአዘነ ሁሉም መውጣት ጀመሩ አንዷ ልጅ ብቻ ወደ እኛ መጣች "ኡስታዝ ነገ አልመጣም" ለምን አለቻት ሳሊሀ የሆነ የገጠመኝ ነገር አለ አለቻት እሺ ግን ነገን ብቻ ነው የተፈቀደልሽ አለቻት ሳሊሀ ፈገግ እያለች እሺ ኡስታዝ ብላት ወጣች ሳሊሀ ኡስታዝ ናት ማለት ነው ይገርማል እንዴት አላወኩም ኡስታዝ ማለት መምህር እንደማለት ነው፡፡ ሰግደን እንድንሄድ ሳሊሀ ጠየቀችኝ እሺ ብያት የመግሪብን ሰላት ሰግደን ወጣን ቤታችን ከመስጅዱ ብዙም አይርቅም ቶሎ ደረስኩ ሳሊሀ እኔን ለመሸኘት ብላ አብረኝ መጣች የእሷ ቤት ይርቃል እንደሚመሽባት እያወቀች እኔን ለመሸኘት መጣች የኔ ሚስኪን እቤት ስደርስ አቅፌ ሳምኳትና ተለያየን ሳሊሀ ትንሽ ከሄደች በኃላ ተመለሰች ሙኒ ብላ ጠርታ አስቆመችኝ ወዬ ሳሉ ለ አላህ ብዬ በጣም እወድሻለሁ አለችኝ ሳሉ እኔም በጣም እወድሻለሁ አልኳትና በድጋሚ ሳምኳት እሺ ወዴ ብላኝ ሄደች ከአይኔ እስክትጠፋ በአይኔ ሸኘኃት እና ወደ ቤት ለመግባት በሩን ማንኳኳት ጀመርኩ ለካ የአጎቴ ሚስት እንደወጣሁ አላወቀችም በዛ ለይ የቅድሙ አለ ዛሬ በቃ አለቀልኝ ምን እንሚሉኝ ምን እንደ ሚያደርጉኝ እንጃ.......

ይቀጥላል!!!!!!
Share Share Share
ከወደዱት ሼር ያድርጉ

@kjphotoandmusic