Get Mystery Box with random crypto!

♀ያልተፈታ ህልም ክፍል 14 : .....ብዙም ሳንቆይ ተደወለ ምሳ እንብላ ብለው ጥለውኝ ተነሱ | Kjphotoandmusic 🇪🇹

♀ያልተፈታ ህልም
ክፍል 14
:
.....ብዙም ሳንቆይ ተደወለ ምሳ እንብላ ብለው ጥለውኝ ተነሱ አልተከተልኳቸውም እዛው የምንቀመጥበት ቦታ ላይ ትንሽ ተቀምጬ ወደ ክፍል ገባሁ የነ ሪቾ መቀያየር ይሄን ያህል ቦታ አልሰጠሁትም አስተማሪ ከገባ በኃላ መጡ አስተማሪው የሌለ ነው የጮኸባቸው እኔ እንኳን ተርፊያለሁ አንድ መቀመጫ ላይ ሁለት ሁለት ነው የምንቀመጠው እኔ ከሪቾ ጋር ነው የምቀመጠው እንድተቀመጥ ብዬ ወደ ወደ አንዱ ጎን ተጠጋሁ ገልመጥ አድርጋኝ በሂዊ ቦታ ላይ ከሀና ጋር ተቀመጠች እኔ በቻዬን ሆንኩ ሁኔታቸው ፈገግ አደረገኝ እና አስተማሪውን መከታተል ጀመርኩ ..ወቀጣዩ ክፍለግዜ አልፎ ወደ ቤት መሄጃ ሰአት ደረሰ እንደተለመደው ሙአዝ ክፍላችን ድረስ መጣ ምንም እንዳልተፈጠረ አድርጌ ልሰናበታቸው እጄን ስዘረጋላቸው እንዳለሁ እራሱ ሳይቆጥሩኝ ወሬያቸውን እያወሩ ይስቃሉ መልስ ሳጣ ትቻቸው ሄድኩ ሙአዝ ፈገግ ብሎ ምን ነው ሙኒ ቆየሽብኝ እኮ አለኝ በሁኔታቸው ትንሽ ተናድጄባቸው ነበር ግን የሙአዝ ፈገግታ እና ሙኒ የምትለዋ ጥሪ ስሜቴን ቀየሩት ፈገግ አልኩኝ እና ዝም አልኩት ከትምህርት ቤት መውጫው በራፍ ላይ ስንደርስ እኔ ቆምኩኝ ሙአዝ ለምን ቆምሽ ምን እረሳሽ አለኝ
....ሳሊሀ ብዬ ዝም አልኩት
....ሳሊሀ ምን ሙኒ
....ሳላገኛት ወደ ቤት መሄድ አልፈልግም
.....አሁን ታዲያ የት እናገኛታለን
.....እያስተዛዘንኩ አንዴ ብቻ ክፍሏ ደርሼ ልምጣ አልኩት አጎንብሼ በአይኖቼ ሰረቅ አድርጌ እየተመለከትኩት
.....ሙአዝ ፊቱን ቋጠር እያደረገ እኔን እዚህ አቁሽ እሷ ጋር ልሂድ ስትይ አታፍሪም አለኝ
.....ይቅርታ ሙአዝ ግን የግድ ላገኛት እፈልጋለሁ እባክህ
....ሂጂ አብረሻት ነይ እኔ መሄዴ ነው
....እየከፋኝ እሺ በቃ ተወው ወደ ቤት እንሂድ
..ሙአዝ ከቆመበት ሳይንቀሳቀስ መሳቅ ጀመረ ዛሬ ምን ተገኘ የሚያስቅ ሙአዝ ብዙ ግዜ ፈገግ ሲል እንጂ እንዲህ ሲስቅ አይቼው አላውቅም
ምን ያስቅሀል?
እየሳቀ አንቺ ነሻ ሌላ ምን ሊያስቀኝ ይችላል
እኔ ምን አደረኩ የሚያስቅ ነገር አድርጊያለሁ እንዴ
የምር ወደ ቤት ልትሄጂ ነበር
አዋ እሄዳለሁ አላልከኝም
እየሳቀ እኔ እኮ እየቀለድኩ ነው ቀልድ አታውቂም እንዴ ሙኒ
እኔም እየሳኩ ሂ...ዛ
....ይሄን ያህል እንደምታከብሪኝ አላውቅም ነበር በጣም አመሰግናለሁ ሙኒ ብቻሽን ሳይሆን አብረን እንሂድ ነይ
ደስ አለኝ ወደ እነ ሳሊሀ ክፍል ሄድን አሎጣችም ነበር ከነ ሪቾ ያጣሁትን ሰላምታ እሳ ጋር እጥፍ በማድረግ አገኘሁት ሳሊሀን እንዳገኘኃት ጥምጥም አልኩባት ኸረ ቀስ አለኝ ሙአዝ እስቲ ዝም በል ላውራበት
....ሳሊሀ ሳለገኝሽ እንዳልሄድ ብዬ ነው አመጣጤ
.....እየሳቀች አቀፈችኝ እንሂድ አለች
....እሺ ብያት ወደ መውጫው አመራን ሙአዝ
....ፍቅራቹ ጨምሮዋል በዚህ አያያዝሽማ እኛም ሳንረሳ አይቀርም ሲል ሶስታችንም ሳቅን
.....ከግቢው ከወጣን በኃላ ተሰነባብተን ሳሊሀ ሄደች እኔ እና ሙአዝ አንድ ላይ ሄድን.....
.
.... ከአስፓልቱ ዳር ላይ ቆሜ የተፈጠረውን ነገር ለማየት እየተንጠራራሁ ነው ግን ምን ነገር ማየት አልቻልኩም አስፓልቱ በሰው ተሞልቶወል የሆነ አደጋ ነገር ይመስላል ወደ ሁኔታውን ለመመልከት ወደ አስፓልቱ መሀል ተጠጋሁ ብሉ ብላክ ጨርቅ ነገር ከሰዎቹ መሀል ላይ ይታያል ይበልጥ ነገሩን ለማጣራት ወደ እነሱ ቀረብኩ ሞተች እንዴ እያሉ ሲያወሩ ሰማሁ አጠገቤ የነበረውን ልጅ ምን ተፈጥሮ ነው መኪና ገጭቷት ነው ደግሞ ተማሪ ናት አለኝ ምን አልባት የእኛ ትምህርት ቤት ተማሪ ከሆነች ብዬ የተሰበሰቡ ሰዎችን እየገፋሁ ልጅቷ ወደ አለችበት ቦታ ላይ ደረስኩ ያየሁትን ማመን አልቻልኩም ሳላስበው ከምችለው በላይ ጮሁክ ሳሊሀ...... ሳሊሀ......ሳሊሀ......አቤት በይኝ እንጂ ሙና እኮ ነኝ ሳሊሀ ሳሊሀ አይንሽን ግለጪ.....

ይቀጥላል!!!!!!
Share Share Share

@kjphotoandmusic