Get Mystery Box with random crypto!

𝐔𝐁𝐔𝐍𝐓𝐔 𝐄𝐓𝐇𝐈𝐎𝐏𝐈𝐀𝐍𝐒

የቴሌግራም ቻናል አርማ kingnan — 𝐔𝐁𝐔𝐍𝐓𝐔 𝐄𝐓𝐇𝐈𝐎𝐏𝐈𝐀𝐍𝐒 𝐔
የቴሌግራም ቻናል አርማ kingnan — 𝐔𝐁𝐔𝐍𝐓𝐔 𝐄𝐓𝐇𝐈𝐎𝐏𝐈𝐀𝐍𝐒
የሰርጥ አድራሻ: @kingnan
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.06K
የሰርጥ መግለጫ

"ኵሎ አመክሩ ወዘሠናየ አጽንዑ"
“Prove all things; hold fast that which is good.”
ሁሉን ፈትኑ መልካሙንም ያዙ፤”

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-23 02:37:41 የጥቅም ወጥመድ

አንድ ጊዜ አንድ ሰው በአንድ ፎቅ ቤት ስር ተቀምጦ በተመስጦ ስልኩን እየነካካ ሳለ በድንገት ከላይ “የአንድ ብር ሳንቲም ጭንቅላቱ ላይ ነጥራ አጠገቡ አረፈች፡፡ ይህ ሰው በጣም ስላመመው ጭንቅላቱን በማሻሸት ወደላይ በማየት የመታውን ሰው ለመሳደብ ሲቃጣው ጭንቅላቱን የመታችው የአንድ ብር ሳንቲም መሆኗን በማየቱ አንስቶ ኪሱ በመክተት ጸጥ አለ፡፡

እንደገና ተመሳሳይ ሁኔታ ሲከሰት አሁንም የለመዳት አንድ ብር በመሆኗ ቀና ብሎ ከመጮህ ይልቅ ህመሙን ታግሶ አንድ ብሯን በማንሳት ኪሱ ከተተ፡፡ ሁኔታው ለሶስተኛ ጊዜ ከተደገመ በኋላ በአራተኛው ጊዜ ጭንቅላቱ ላይ ያረፈው የለመደው የአንድ ብር ሳንቲም ሳይሆን ጠጠር ነበር፡፡

በዚያን ጊዜ ነበር፣ እጅግ በተቆጣ ድምጽ “ማን ነው የመታኝ? በማለት ወደላይ ቀና ያለው፡፡

በግል ሕይወታችንም ሆነ በማሕበራዊ ግንኑነታችን፣ “ጥቅም እስካገኘሁ ድረስ ምን ቸገረኝ” በማለት የምናልፋቸው ጎጂ ነገሮች ናቸው፡፡

እኛ ጊዜያዊ ጥቅም ስላገኘን ብቻ የተውናቸው ጥሩ ያልሆኑ ተግባሮች የእኛኑ አመለካከትና ባህሪይ እያበሰበሱ መሄዳቸው አይቀርም፡፡ በተጨማሪም፣ በእኛ ዝምታ ምክንያት ተግባሩን የሚፈጽሙት ሰዎች እርማት ስለማያገኙና፣የእነሱን አጉል ምሳሌነት በመከተል ያንኑ ተግባር ወደመፈጸም የሚሄዱ የሕብረተሰቡ ክፍሎች ስለሚበራከቱ የበሰበሰ ሕብረተሰብ መፍጠሩ አይቀርምና ሃላፊነት የሚሰማው ዜጎች እንሁን

https://t.me/kingnan
3.4K views23:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-11 23:26:08 ጠቃሚ ምክሮች

1. ከአለስፈላጊ ክርክሮች ጭቅጭቆች እና እሰጣገባዎች ራቅ።

2. ራስህን ገንቢ ሃሳብ ከሌላቸው (negative) ሰዎች አርቅ። ምክንያቱም አንተን ራሱ ሳትፈልገዉ እንደነሱ እንድታስብ ትገደድ ይሆናል፡፡

3. መቀበል የምትፈልገውን ስጥ።

4. ገንቢ ያለሆኑ ጎጂ አስታያየቶችን ከመስጠት ተቆጠብ።

5. ለሰዎች ፍቅርና አክብሮት ይኑርህ።

6. ይህ መቼም በእኔ አይደርስም አትበል፣የሕይወትን አቅጣጫ ሁሌም ቢሆን ማወቅ አንችልምና።

7. የመኪና የፊት መስታወት ትልቅ ሆኖ የኋላ መመልከቻውዠ መስታወት ግን ለምን ትንሽ የሆነ ይመስልሃል....ምክንያቱም የፊቱ ካለፈው ይልቅ አስፈላጊ ስለሆነ ነው። ስለዚህም የኀላዉን ሳትዘነጋ በትልቁ የሕይወት መስታወት ወደፊት እያየህ ተጓዝ::

https://t.me/kingnan
720 views20:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-11 00:23:33 አደገኛው ስብእና/ Narcissism

አብዝተን ልንጠነቀቃቸው የሚገባ አስቸጋሪ ማንነት ያላቸው ሰዎች።

ሁል ጊዜ ጥፋተኛ እንደሆናችሁ እንድታስቡ የሚያደርጉትን። ለሚሰጧችሁ መጥፎ ምላሽ ተጠያቂው/ዋ አንተ/አንቺ ነሽ የሚሉትን።

የእነሱን ችግር እንጂ ፈፅሞ የእናንተን ማዳመጥና መረዳት የማይፈልጉትን።

ለጥፋታቸው ሀላፊነት መውሰድ የማይፈልጉ፣ ሁል ጊዜ ትክክል ነኝ ብለው የሚያስቡና ለተፈጠረው ችግር ሁሉ ምክንያቱ እናንተ እንደሆናችሁ እንዲሰማችሁ የሚያደርጉትን።

ጉራቸው ከልክ ያለፈ። ታላቅነታቸውን፣ ችሎታቸውን፣ ተፈላጊነታቸውን እና የበላይነታቸውን ሁሌ የሚናገሩትን። ከእናንተ የወሰዱትን ሀሳብ ጭምር የራሳቸው አድርገው የሚነግሯችሁን።

የሰውን ትኩረት ለመሳብ የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም። በእያንዳንዱ ንግግራቸው እኔ....እኔ....እኔ የሚሉትን።

ለሌላ ሰው ችሎታ እውቅና የማይሰጡና የሚቀብሩትን።

ሌሎችን በጣም የሚያሳንሱ። የእነሱ ትልቅነት የሚጎላው የሌላውን ውድቀት፣ ድክመትና አለመሳካት ሲያወሩ የሚመስላቸውን።

ፈፅሞ አክብሮት የላቸውም። ተሳስቻለሁ....ይቅርታ የሚባል ነገር አይታሰብም። ለጥፋታቸው ሌላውን ተጠያቂ በማድረግ የሚያሸማቅቁትን።

እነሱ የሚፈልጉትን ሀሳብ እንድትቀበሉና በነሱ ቁጥጥር ስር እንድትሆኑ የሚያደርጉትን።

ምንም አይነት ፍቅርና ርህራሄ የሌላቸውን።

ክፋታቸውን ነቅታችሁ ስትርቋቸው ስማችሁን የሚያጠፉ። ሚስጥርና ድክመታችሁን ለሰው የሚያወሩተን። በሚችሉት ሁሉ ሊጎዷችሁ የሚሞክሩትን።

ይህንን ካነበቡ በኋላ ግንኙነቶችዎን ደግመው ይመርምሩ። ለሌሎችም እንዲጠቅም ሼር ያድርጉ

በመአዛ መንክር - ክሊኒካል ሳይኮሎጂስት

https://t.me/kingnan
650 views21:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-07 01:16:18 እስቲ አፍቅሩ !

በምድር ላይ ያልባከነ ምርጥ ጊዜ ማለት በፍቅር ያሳለፋችኋቸው ደይቃዎች ናቸው … እስቲ አፍቅሩ …መልካችሁ ምንም ይሁን አፍቅሩ …እድሚያችሁ ምንም ይሁን አፍቅሩ … ኑሮ ቢከብዳችሁ ራሱ ኑሮ ከከበደው ጋር ተፋቀሩ …ፍቅር ተያይዞ ማደግ ብቻ አይደለም ተያይዞ መውደቅም ነው ! በጥላቻና በድርቅና ከመቆም ለፍቅር መውደቅ ተለማመዱ !

``አገር፣ህዝብ ፣ፖለቲካ በሚል ግዙፍ ነገር ውስጥ እየዳከራችሁ የጤፍ ቅንጣት አክላችሁ አትሙቱ … ፍቅር የሚባል እጅግ ረቂቅ አየር ወደውስጥ ሳቡና አገር አክሉ ! የማታፈቅሩበት አገር ምን ያደርግላችኋል? ገብስ ልታመርቱበት ነው? …የማታፈቀሩበት ህዝብ ምን ያደርግላችኋል ቀብራችሁን እንዲያደምቅ ነው …?የማታፈቅሩበት ፖለቲካ ምን ያደርግላችኋል? ፓርላማ ልተሰየሙበት ነው? …የማታፈቅሩበት ህገ መንግስት ምን ያደርግላችኋል ሲጀመር ይልተጣመራችሁትን መገንጠል እንዲፈቅድላችሁ ነው? …

ተያዩ ተነጋገሩ ትዝብት ጥርጣሬ ፍርሃትን ወደዛ ጣሉና በፈገግታ በተሞላ ፊታችሁ የወደዳችኋትን ወደእናተ ሳቡ የወደድሽውን ወደራስሽ ጋብዥ ! ተቃቀፉ …አብራችሁ ቡና ጠጡ … ተደዋወሉ ‹ቴክስት› ተላላኩ ! በሚወዷችሁ ሰዎች እቅፍ ውስጥ ስጋችሁ ይድላው !ነፍሳችሁም ደስ ይበለው !ተሳሳሙ …ለመጨረሻ ጊዜ በፍቅር ከተሳማችሁ ስንት ቀን ስንት ወር ስንት ዓመት ሆናችሁ … ኪሳራ !

ህግ ስርዓትና አሉባልታ አትፍሩ …ደግሞ አትንቀዠቀዡ! ብቻ ማፍቀርም መፈቀርም ፈልጉ ..ራሳችሁን ብቻ ቀለል አድርጉት አየሩ ራሱ ወደየት እንደሚወስዳችሁ ያውቃል !…ለምርጫችሁ ብዙ መስፈርት አታስቀምጡለት ….ፈልጉ ተፈላለጉ ያለምንም ወሰን በነፍስም በስጋም ወደፍቅር ድንበር ቅረቡ ….ፀብ አትፍሩ መለያየት አያስጨንቃችሁ …ዘላለማዊ ጥላቻም ሆነ ጊዚያዊ ፍቅር ብሎ ነገር የለም ! አልፎ ሂያጅ ፍቅር የሚባል ነገር የለም ፍቅር ወደየትም አያልፍም …ፍቅር ራሱ መንገዱ ነው ! ተራመዱበት ፍጠኑበት …ብቻ አትቁሙ ! መንገድ ላይ በቆማችሁ ቁጥር ለሌላው እንቅፋት ትሆናላችሁ !

ማህበረሰቡ የሰከነ... ረጋ ያለ... ቁም ነገር …ሁነኛ ሰው… የማይሆን ሰው…የሚሆን ሰው… እያለ ከጫነባችሁ የጉልት ሂሳብ ውጡና እብደታችሁ በሰፈረላችሁ ልክ ከዚህ ነዝናዛ አዕምሮ ተላቃችሁ በልባችሁ ደስታ ኑሩ ! ካለፈ ታሪካችሁ ውጡ …ካለፈ ህመማችሁ አገግሙ … በዘፈን ስም ሙሾ ከሚያስወርዱ ሙዚቃዎች ራቁ ….እንዴ…! …እንዳሰባችሁና እንደተመኛችሁ እስከመቸ ትኖራላችሁ ?! ባለፈ ጥላቻችሁ ከሬዲዮና ከምናምን በተለቃቀመ የመካካድና ተጎዳሁ ተሰበርኩ ታሪክ (ያውም እንደዛም ብለው ማፍቀር ላያቆሙ) በፍርሃት ተሸማቃችሀ ትኖራላችሁ እንዴ ?!

አንዳንዴማ ልብሳችሁን ጣሉ …እራቁታችሁን መኖር ተለማመዱ …እራቁታችሁን ከሆናችሁ ልብስ አይኖራችሁም… ልብስ ከሌላችሁ ኪስ አይኖራችሁም ….ኪስ ከሌላችሁ በኪስ ከሚያዙ ነገሮች ሁሉ ነፃ ናችሁ … ምንም ነገር ልትይዙ የምትችሉት ብቸኛ ነገር ልባችሁ ብቻ ይሆናል … እንደልባችሁ ኑሩ ! የነፍሶቻችሁ ባሉን ላይ የተቋጠሩ ክሮችን ከራሳችሁ የፍርሃት እጅም ይሁን ከሌሎች ሰዎች የቁጥጥር እጅ ላይ አላቁና ወደሰፊው ህዋ ልቀቋቸው በአየሩ ላይ ይንሳፈፉ !

አሌክስ አብርሃም

https://t.me/kingnan
633 views22:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-30 13:50:50
ንስር ወጀብ ከመምጣቱ ብዙ አስቀድሞ ማወቅ ይችላል። እንዳወቀም ከፍታ ቦታ ለይ ይቀመጥና ንፋሱን ይጠብቃል። ወጀቡ ሲመጣ ከተቀመጠበት በመብረር ንፋሱ አግዞት ከወጀቡ በላይ እንዲበር ያደርገዋል። ወጀቡ ከታች ያለውን ዓለም ሲያተራምሰው፣ ንስሩ ከወጀቡ በላይ ይንሳፈፋል። እዚህ ላይ አንድ ነገር ልብ እንበል። ንስሩ ወጀቡን አላመለጠውም ፤ ተጠቀመበት እንጅ!!

የሕይወት ወጀብ ወደ እኛ ሲመጣ፣ ልክ እንደ ንስሩ ከወጀቡ በላይ መብረር እንችላለን፤ በሽታን፣ አደጋን፣ ውድቀትን፣ እና ሃዘንን ወደ ሕይወታችን የሚያመጣውን ንፋስ ለከፍታችን መወጣጫ ልናደርገውው እንችላለን።

(ከዩቲዩብ ቪዲዮ ላይ ታይቶ የተተረጎመ)

https://t.me/kingnan
4.6K views10:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-24 22:35:36 ሽመላዊ ትምህርት

ሽመላ በመባል የሚታወቁት አዋፋት ወቅትን መሰረት ያደረግ ምቹ መኖሪያ ፍለጋ ከቦታ ቦታ ዝውውር ያደርጋሉ፡ በጉዟቸውም ልብ ብለን አስተውለናቸው እንደሆነ የ “V” ፊደልን ቅርጽ ሰርተው ነው የሚበሩት፡፡ ከተፈጥሮ ለመማር ንቁ የሆነ ለምን ይህንን አይነት ቅርጽ ሰርተው መብረርን መረጡ የሚለውን መጠየቅ ይችላል፡፡ ሳይንስ የደረሰበት እውነታ ሽመላዎች በአንድነት ሲበሩ የሚኖረውን የአየር ግፍት ለብቻቸው ሲበሩ ከሚፈጥርባቸው የአየር ግፊት በእጅጉ ስለሚቀንስ ነው፡፡ ብቻ ለብቻ ከሚበሩት ይልቅ የ “V” ፊደልን ቅርጽ ሰርተው በአንድነት ሁነው ሲበሩ የመብረር ፍጥነታቸውም በ71% ይጨምራል፡፡ ይህንን በመረዳታቸው ነው ሽመላዎች የ “V” ፊደልን ቅርጽ ሰርተው መብረራቸው፡፡

ሌላው ሊደንቀን የሚገባው ባሕሪያቸው በሆነ ምክንያት (በጉዳትም ሊሆንይችላል) አንድ ሽመላ ተነጥሎ ከዚህ ቅርጽ ከወጣ የተወሰኑት ተነጥለው በመቅረት በግራና በቀኝ በመሆን የሚደርስበትን የአየሩን ግፊት በማገዝ ወደ መንጋው እንዲቀላቀል ያግዙታል እንጅ ጥለውት አይሄዱም፡፡ እገዛቸውም የሚዘልቀው አገግሞ ከመንጋው እስኪቀላቀል ድረስ ወይም ደግሞ ለይቶለት እስኪሞት ድረስ የሚቀይ ነው፡፡

ሽመላዎች የሚያደርጉትን እረዥም ጉዞ ይመራ የነበረው ሽመላ በደከመው ጊዜ የመሪነት ሚናውን ለአንደኛው ያስረክብና ከኋላ በመሆን እረፍት ያደርጋል፡ ሽመላዎች በሚጓዙበት ወቅት ቋቅቋቅ የሚል ድምፅ ያስተጋባሉ፡፡ ይህም በገጠሩ የሀገራችን ክፍል እንደሚደረገው የደቦ ሥራ ሽለላ ጎዞውን ተበረታታው በነቃ መንፈስ እንዲጓዙት ለማድረግ የማነቃቂያ ስራ ነው፡፡ በተለይም ደግሞ ፊት ሆኖ መንጋውን ለሚመራው፡፡

ግብረገባዊ ትምህርት

ተፈጥሮ በራሷ ይንን ይረዱት ዘንድ ለሽመላዎች ጥበብ ሰጣቸዋለች፡፡ እኛም ከእነሱ ተምረን በአንድነት መስራት የሚያስገኘውን ጥቅም፣ በጋራ ሲሆኑ የሚፈጠረውን ተጨማሪ ጉልበት ማጤንና አንድነትን ማጠንከር እንዳለብን ያሳስበናል፡፡ አንድነት ኃይል ነው፡፡ በአንድነት በመሆናችን ለየብቻ ከነበረን የበለጠ ተደማሪ ኃይል ማግኘት እንችላለን፡፡

ትምህርት አንድ፡

የጋራ መዳረሻን በእምነት ከያዝንና እንደ አንድ ልብ መካሪ ሁነን በአንድነት መስራት ከቻልን በፍጥነት ከአሰብንበት እንደርሳለን፡፡ የላቀ ውጤትም እናስመዘግባለን፡፡

ትምህርት ሁለት፡

የመሪነት ሚናን ለመጋራት በመካከላችን መከባበርና መተማመን ሊኖር ይገባል፡፡ ሥራዎችንና ችግሮችን ስንጋራ ያለንን ብቃት በአንድነት አስተባብረን ስንጠቀምበት በአጭር ጊዜና በትንሽ ጥረት ብዙ ውጤት ማስመዝገብ አንችላለን፡ የመሪነት ቦታ ዕርስት አደለም!

ትምህርት ሦስት፡

ወቅቱን የጠበቀ ማበረታቻ ስንለዋወጥ እርምጃችን ፈጣን ይሆናል፡፡

ትምህርት አራት፡

ልዩነታችንን አድንቀን ተቀብለን ለጋራ ችግራችን በጋራ እንነሳ በተለይም ደግሞ በአስቸጋሪና በፈታኝ ጊዜ አንድነታችንን እንጠብቅ፣ እናጥብቅ፡፡

ሲጠቃለል በመሪነት ቦታ መቀመጥ ርስት መውረስ አይደለም

ምንጭ: FLIGHT OF SWANS

https://t.me/kingnan
4.6K views19:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-21 22:52:48 ፍቅርና ጊዜ

ሁሉም አይነት ስሜቶች የሚኖሩበት አንድ ደሴት ነበር፡፡ የደስታ ስሜት፣የመከፋት ስሜት፣ እውቀት እና ሌሎቹ ስሜቶች ፍቅርን ጨምሮ፡፡ አንድ ቀን ታዲያ ደሴቱ ሊሰምጥ እንደሆነና ሁላቸውም ስሜቶች ሊያመልጡ የሚችሉበትን ጀልባ መስራት እንዲችሉ አዋጅ ተነገረ፡፡ በዚህም መሠረት ሁሉም ስሜቶች ጀልባቸውን ሲሰሩ ፍቅር ግን ደሴቱ እስኪ ሰምጥ ድረስ ጀልባ አልሰራም ነበርና ከሊሎቹ ስሜቶች እገዛ ለመጠየቅ ወሰነ፡፡

ሀብታምነት የሚባለው ስሜት በፍቅር በኩል ሲያልፍ “ሀብታም ሆይ ከአንተ ጋ ይዘኸኝ ልትሻገር ትችላለህ?” አለው ፍቅር፡ “አይሆንም፡፡ አልችልም በጀልባየ ውስጥ በርካታ ወርቅና መዳብ የያዝኩ በመሆኑ ለአንተ የሚሆን ቦታ የለኝም” ሲል ጥሎት ሄደ፡፡ ፍቅር አቶ ስግብግብን ሲያልፍ ተመለከተውና እንዲረዳው ጠየቀው፡፡ “አልችልም አቶ ፍቅር ጀልባየን ታበላሽብኛለህ አይሆንም ብሎ” ትቶት ሄደ፡፡ አቶ መከፋትን በቅርብ አገኘውና አሁንም ፍቅር አብሮ እንዲያሻግረው ጠየቀው፡፡ “ኦው! ፍቅር አዝናለሁ እኔ ብቻየን ነው መሆን የምፈልገው፡፡” ብሎ አሰናበተው፡፡ ደስታም ፍቅርን አልፎት እየሄደ በጣም በፈንጠዝያ ደስታ ላይ ስለነበር ፍቅር ሲጠራውም መስማት አልቻለም፡፡ ባጋጣሚ “ፍቅር ና እኔ እወስድሃለሁ” የሚል ድምጽ ሰምቶ ሲዞር የተባረከ አዛወንት ነበር፡፡ “ጊዜው ነው” ወዳጀ ፍቅር ሲል እውቀት የተባለው ስሜት መለሰ፡፡ “ጊዜ ማለት!?” ፍቅር በመደነቅ ጠየቀው “ነገር ግን ለምን ጊዜው ሊረዳኝ ቻለ?” እውቀት ፈገግ እያለ ምክንያቱም “የፍቅርን ዋጋ መረዳት የሚችለው ጊዜ ነው፡፡” ሲል መልስ ሰጠው፡፡

ምንጭ፡ 100 moral stories

https://t.me/kingnan
1.0K views19:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-20 19:43:01 አሁኑኑ አቁም

★ ነፍስህን መዋሸት አቁም

★ ከችግርህ መሸሽ አቁም

★ ትምህርት ከማትወስድባቸው ሰዎች ጋር ጊዜ ማጥፋትን አቁም


★ እሳሳታለው በሚል ጥሩ ስራ ከመስራት መቆጠብን አቁም ስላለፈው ጊዜ በመጨነቅ ያለህበትን ጊዜ ማበላሸት አቁም

★ውስጣዊ ደስታን በቁሳዊ ነገሮች ለመገዛት መሞከርን አቁም እኔ ውስጣዊ ደስታ ማግኘት አልችልም ብሎ ማሰብን አቁም

★ከችግርህ በላይ ሌላ ችግር እንዳትፈጥር በችግርህ ላይ ከመጠን በላይ ማሰብን

አቁም

ሁልጊዜ ለሰዎች ስሞታ ማሰማትን አቁም

ወደ ምቅኝነት እንዳይቀይር ከሰዎች ላይ ባለ ነገር ሁሉ መቅናትን አቁም

በፈፀምከው ስህተት ምክንያት ሌሎችን. መውቀስን አቁም

ከምታደረገው ነገር ላይ ከሰዎች ምስጋና መጠበቅን አቁም

በአንተና በሌሎቹ መካከል በተፈጠረ ግጭት ይቅርታን ከሌሎች መጠበቅን አቁም እርግጠኛ የሆንክበትን ነገር ትተህ የሚያጠራጥርህን ነገር መስራትን አቁም።

join us

https://t.me/kingnan
3.8K views16:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-18 16:27:46 ከነባሩ የመውጣት ፈተና

ነገር በምሳሌ ጠጅ በብርሌ ይሰምራልና ለውጥን በመተግበርና በማስተግበር አንድ ጥሩ ማሳያ ሊሆን የሚችል ምሳሌ ልጠቁማችሁ በተለይ አሁን እየኖርንበት ያለው ሁናቴ ባንወደውም እንዴት ከዚህ መውጣት እንደማንሻ ያመላክተናል፡

ከዓመታት በፊት ሳይቲስቶች አንድ ኤክስፐርምንት አደረጉ፡፡ እሱም ምንድን ነው በአንድ ብረት ድስት መሰል ሳህን ላይ ውሃ በመጨመር በከፍተኛ ሙቀት እንዲፈላ ካደረጉ በኋላ አንዲት እንቁራሪት በማምጣት በፈላው ውሃ ላይ ጨመሯት፡፡ እንቁራሪቷ ሙሉ ኃይኋን ተጠቅማ ከመቅጽበት ተስፈንጥራ ወጣች፡ ሳይንቲስቶች በመቀጠል ያደረኩት እንቁራሪቷን ቀዝቃዛ ውሃ በያዘ ሳህን ውስጥ አስቀመጧት፡፡ ቀዝቃዛውን ውሃ እንቁራሪቷ የወደደችው በመሆኑ የመውጣት ሙከራ አላደረገችም፡፡ ከዛም ሳህኑን በዝቅተኛ ሙቀት ማሞቅ ሲጀምሩ እቁራሪቷ ምቾት እየተሰማት ተደላድላ ተቀመጠች፡ የሙቀት መጠኑ ቀስ በቀስ እጨመረ ሂዶ ከፍተኛ ደረጃውን በመያዙ እንቁራሪቷ የማምለጥ ሙከራ ሳታደርግ እዛው አረረች፡፡ ከለመዱት የመውጣት ፈተና እያረሩም ቢሆን በዛው ማዝገምን ያስመርጣል፡፡

እውነታው እሚነግረን ብዙዎቻችን እንደ እንቁራሪቷ እንደሚሰማን ነው፡፡ አሁን ካለንበት የማንወደው ግን ምቾት የሰጠን አድርገን ከምንወስደው ከባቢ ሁኔታ መላቀቅ አንወድም፡፡ ወይም ደግሞ የተሻለው ለውጥ የሚጠይቀንን ዋጋ ለመክፈል ዝግጁ አይደለንም፡፡ ይኸን የሚያጠናክር አባባልም አለን፡ ካለመዱት መልአክ የለመዱት ሰይጣን የሚል፡፡ በሕይወት ውስጥ ምርጫው ሁለት ነው ወይ ከነበሩበት ብሶ መበስበስ ወይም ደግሞ ወደ አዲስ መሻገር፡ ባሉበት መቀጠል የሚባል ሦስተኛ አማራጭ የለም፡፡ There is no permanent thing except change እንዲልሳይንሱ፡ ስለሆነም ወይ ወደፊት ወይም ደግሞ ወደኋላ ማለት የተፈጥሮ ግዴታ ነው፡፡ ምርጫችን ወደፊት እንዲሆን ሳንወደው ከተመቸን ከባቢ ሁኔታ መንቃት ይጠይቀናል፡

ምንጭ፦ Frog in the Beaker
https://t.me/kingnan
3.6K views13:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-16 01:28:05 የሕይወት ትምህርት

አራት ልጆች የነበሩት አንድ ሰው ነበር፡ እናም ልጆቹ በነገሮች ችኩል እንዳይሆኑና ቀድመው ማደማደምን (#quick judgment) እንዳይለምዱ የሕይወት ትምህርት ያስተምራቸው ዘንድ ወደደ፡፡ ስለሆነም ከአካባቢያቸው በብዙ ርቀት የሚገኝ ዛፍን አይተው ያዩትን ነገር ይዘው እንዲመጡ ተልዕኮ ሰጥቶ አሰማራቸው፡የመጀመሪው ልጅ፡ በበጋ ሁለተኛው በበልግ ሦስተኛው በክረምት አራተኛውና የመጨሻውን በመከር ደርሰው ያዩትን ይዘው እንዲመለሱ አደረገ፡፡የመጀመሪያው ያየውን ሲያቀርብዛፉ በጣም አስጠሊታ ነው፡፡ ተጣጥፏል፣ ተሰባብሯልም አለ፡፡ ሁለተኛው ቀጠለ በአረንጓዴ ልምላሜ የተሞላ ቅርንጫፍ አውጥቷል ለወደፊትም የማፍራት ተስፍ ይታይበታል ሲል ያየውን አብራራ፡፡ ሦስተኛው በዚህ አባባል አልተስማማም እሱ ያየውን ለአባቱ ሲያቀርብም ዛፉ በአበባ ተጨናንቋል ያበቦቹ መዓዛም እጅግ ያውዳል እናም በጣም ቆንጆ ነው፡ እንደዛ አስደሳች ነገር ከዚህ በፊት በሕይዎቴ አላየሁም ሲል ባግራሞት ተናገረ፡፡የመጨረሻው ልጅ ቀዳሚዎቹ ሦስቱ ወንድሞቹ ባቀረቡት አልተስማማም፡፡ እናም እንዲህ አለ ዛፉ በበሰሉና እጅግ ባማሩ ፍሬዎች ተጨናንቋል ሕይወትንም በደስታ ይሞላል፡፡አባት የሁሉንም እይታ ካዳመጠ በኋላ ሀላችሁም ትክክል ናችሁ ምክንያቱም ያያችሁት አንድ ዛፍ ቢሆንም ያያችሁበት ወቅት ግን ለዛፉ ሕይዎት የተለያየ ትርጉም ባላበት ወቅት ነው፡፡ አስከትሎም እንዲህ አላቸው ሰውንም ሆነ ዛፍን በአንድ ወቅት ገጽታ ብቻ እንዲህ ነው ብሎ መናገር አይቻልም፡፡ሕይዎትን በችግራችን ወቀት ብቻ ከተረጎምናት፤ በበጋው ዛፉ ደርቆ እንደታየው ካየናት እንጠላታልን የበልጉን ተስፋና የክረምቱን ውበትም አናየውም፡፡ የሕይዎት ጥፍጥና የሚመዘነው በሁሉም ወቅቶች ድምር እንጅ አንደኛው ወቅት በፈጠረው ገጽታ ብቻ አይደለም ፡፡

የሕይወት ትምህርት፡

ያንድ ወቅት ችግር የቀሪ ሕይወትህን ደስታ እንዲያበላሸው አትፍቀድለት፤ሕይዎትንም ባስቸጋሪው ወቅት በነበረህ መነጸር አትያት፣ ሕይወትን በአንድ ክፉ አጋጣሚ ወክለን አንያት፣ይልቁንም በአስቸጋሪ ጊዜ ነገም ሌላ ቀን ነው ብለህ ጽና እናም የተሻለው ጊዜ እንደሚመጣ እርግጠኛ ሁን፡፡

https://t.me/kingnan
3.7K views22:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ