2022-02-14 17:11:54
ጥሩ ዛፍ ከተጠጋህ ጥሩ ጥላ ታገኛለህ 1)ጥሩ ዛፍ ከተጠጋህ ጥሩ ጥላ ታገኛለህ
ጥሩ ጓደኛ ከተጠጋህ መልካም ነገር ትማራለህ
2)ምቀኞች መብዛታቸው በስኬት መንገድ ላይ የመሆንህ ምልክት ነው
3)ወንድ ልጅ እናቱ በሕይወት እስካለች ድረስ ሕፃን ነው..ለእናቱ
4)በፈተና ላይ አለመታገስ ሌላ ፈተና ነው
ፈገግታ ቃላት የሌለው መልካም ንግግር ነው
5ካንተ የባሰ አለና አመስግን ፈገግ በል
6) በኃላህ የሚወጋህ ካለ አንተ ወደፊት የምትራመድ ነህ ማለት ነው
7) የተዋበ ንግግር ግልፅ የሆነን እውነት ሊሸፍን ይችላል
8) ለሌሎች ጥሩ ጓደኛ ሰትሆን ጥሩ ጓደኛ ታገኛለህ
9) ረዥም ምላስ አለው ማለት አጭር እጅ እንዳለው ያመላክታል
10) ሁለት ወፍ የሚያባርር ሁለቱንም ያጣል
11) የበጎች መንጋ ውስጥ መሪ ከምትሆን ከመንጋው የተነጠለ አንበሳ ብትሆን ይሻላል
12) ትንሽን ለመስጠት አትፈር ምንም አለመስጠት ከሱ የባሰ ነውና
13) የተሸናፊዉ ፈገግታ ያሸናፊውን ደስታ ይቀንሳል
14) የሁሉን ሰው ውዴታ ማግኘት ሊደረስበት የማይቻል ግብ ነው
15) ነፍስ በኩራት ስትሞላ ጎደሎ የመሆኗ መገለጫ ነው
16) ኩራተኛ ሰው ተራራ ጫፍ ላይ ሆኖ ሌሎችን ትንሽ አድርጎ እንደሚያይ ነው ነገርግን እሱንም ትንሽ አድርገው እንደሚያዩት አያውቅም
17) ብዙ ጊዜ በጉጉት ከምንጠብቀው ይልቅ ድንገት የምናገኛቸው ነገሮች ውብ ናቸው እኛ ከለፋነው ጌታ የፃፈው መልካም ነውና
18) ግኡዝ የሆኑት ውሃና አፈር ለእፅዋት አግልጋይ ናቸው ፤
እፅዋቶች ደግሞ ለእንስሳት ያገለግላሉ
እንስሳት ፣እፅዋትና ግኡዛን ደግሞ የሰውን ልጅ ያገለግላሉ ... በተቃራኒው
የሰው ልጅ ወደታች ወርዶ ለግኡዛን አገልጋይ (አምላኪ) መሆን ከጀመረ ያኔ ከነሱ የባሰ ይሆናል።
19) ሰውን ዛሬ ባየሁ ሁኔታው የነገውን አትናገር ነብያት በግ ጠብቀው ከዛ የሰዎች መሪ ሆነዋል
20) ለአንድ ጌታ ሲሰገድ፦ ፊት ወደመሬት ቢወርድም እውነታው ግን ወደ ሰማይ መውጣት ነው
21) የሰው ልጅ ለዘለዓለም እንደሚኖር ሆኖ ይለፋል አንድ ቀን የኖረ ሳይመስለው ይሞታል፨
https://t.me/kingnan
6.3K views14:11