Get Mystery Box with random crypto!

የሕይወት ትምህርት አራት ልጆች የነበሩት አንድ ሰው ነበር፡ እናም ልጆቹ በነገሮች ችኩል እንዳይሆ | 𝐔𝐁𝐔𝐍𝐓𝐔 𝐄𝐓𝐇𝐈𝐎𝐏𝐈𝐀𝐍𝐒

የሕይወት ትምህርት

አራት ልጆች የነበሩት አንድ ሰው ነበር፡ እናም ልጆቹ በነገሮች ችኩል እንዳይሆኑና ቀድመው ማደማደምን (#quick judgment) እንዳይለምዱ የሕይወት ትምህርት ያስተምራቸው ዘንድ ወደደ፡፡ ስለሆነም ከአካባቢያቸው በብዙ ርቀት የሚገኝ ዛፍን አይተው ያዩትን ነገር ይዘው እንዲመጡ ተልዕኮ ሰጥቶ አሰማራቸው፡የመጀመሪው ልጅ፡ በበጋ ሁለተኛው በበልግ ሦስተኛው በክረምት አራተኛውና የመጨሻውን በመከር ደርሰው ያዩትን ይዘው እንዲመለሱ አደረገ፡፡የመጀመሪያው ያየውን ሲያቀርብዛፉ በጣም አስጠሊታ ነው፡፡ ተጣጥፏል፣ ተሰባብሯልም አለ፡፡ ሁለተኛው ቀጠለ በአረንጓዴ ልምላሜ የተሞላ ቅርንጫፍ አውጥቷል ለወደፊትም የማፍራት ተስፍ ይታይበታል ሲል ያየውን አብራራ፡፡ ሦስተኛው በዚህ አባባል አልተስማማም እሱ ያየውን ለአባቱ ሲያቀርብም ዛፉ በአበባ ተጨናንቋል ያበቦቹ መዓዛም እጅግ ያውዳል እናም በጣም ቆንጆ ነው፡ እንደዛ አስደሳች ነገር ከዚህ በፊት በሕይዎቴ አላየሁም ሲል ባግራሞት ተናገረ፡፡የመጨረሻው ልጅ ቀዳሚዎቹ ሦስቱ ወንድሞቹ ባቀረቡት አልተስማማም፡፡ እናም እንዲህ አለ ዛፉ በበሰሉና እጅግ ባማሩ ፍሬዎች ተጨናንቋል ሕይወትንም በደስታ ይሞላል፡፡አባት የሁሉንም እይታ ካዳመጠ በኋላ ሀላችሁም ትክክል ናችሁ ምክንያቱም ያያችሁት አንድ ዛፍ ቢሆንም ያያችሁበት ወቅት ግን ለዛፉ ሕይዎት የተለያየ ትርጉም ባላበት ወቅት ነው፡፡ አስከትሎም እንዲህ አላቸው ሰውንም ሆነ ዛፍን በአንድ ወቅት ገጽታ ብቻ እንዲህ ነው ብሎ መናገር አይቻልም፡፡ሕይዎትን በችግራችን ወቀት ብቻ ከተረጎምናት፤ በበጋው ዛፉ ደርቆ እንደታየው ካየናት እንጠላታልን የበልጉን ተስፋና የክረምቱን ውበትም አናየውም፡፡ የሕይዎት ጥፍጥና የሚመዘነው በሁሉም ወቅቶች ድምር እንጅ አንደኛው ወቅት በፈጠረው ገጽታ ብቻ አይደለም ፡፡

የሕይወት ትምህርት፡

ያንድ ወቅት ችግር የቀሪ ሕይወትህን ደስታ እንዲያበላሸው አትፍቀድለት፤ሕይዎትንም ባስቸጋሪው ወቅት በነበረህ መነጸር አትያት፣ ሕይወትን በአንድ ክፉ አጋጣሚ ወክለን አንያት፣ይልቁንም በአስቸጋሪ ጊዜ ነገም ሌላ ቀን ነው ብለህ ጽና እናም የተሻለው ጊዜ እንደሚመጣ እርግጠኛ ሁን፡፡

https://t.me/kingnan