Get Mystery Box with random crypto!

ከነባሩ የመውጣት ፈተና ነገር በምሳሌ ጠጅ በብርሌ ይሰምራልና ለውጥን በመተግበርና በማስተግበር አ | 𝐔𝐁𝐔𝐍𝐓𝐔 𝐄𝐓𝐇𝐈𝐎𝐏𝐈𝐀𝐍𝐒

ከነባሩ የመውጣት ፈተና

ነገር በምሳሌ ጠጅ በብርሌ ይሰምራልና ለውጥን በመተግበርና በማስተግበር አንድ ጥሩ ማሳያ ሊሆን የሚችል ምሳሌ ልጠቁማችሁ በተለይ አሁን እየኖርንበት ያለው ሁናቴ ባንወደውም እንዴት ከዚህ መውጣት እንደማንሻ ያመላክተናል፡

ከዓመታት በፊት ሳይቲስቶች አንድ ኤክስፐርምንት አደረጉ፡፡ እሱም ምንድን ነው በአንድ ብረት ድስት መሰል ሳህን ላይ ውሃ በመጨመር በከፍተኛ ሙቀት እንዲፈላ ካደረጉ በኋላ አንዲት እንቁራሪት በማምጣት በፈላው ውሃ ላይ ጨመሯት፡፡ እንቁራሪቷ ሙሉ ኃይኋን ተጠቅማ ከመቅጽበት ተስፈንጥራ ወጣች፡ ሳይንቲስቶች በመቀጠል ያደረኩት እንቁራሪቷን ቀዝቃዛ ውሃ በያዘ ሳህን ውስጥ አስቀመጧት፡፡ ቀዝቃዛውን ውሃ እንቁራሪቷ የወደደችው በመሆኑ የመውጣት ሙከራ አላደረገችም፡፡ ከዛም ሳህኑን በዝቅተኛ ሙቀት ማሞቅ ሲጀምሩ እቁራሪቷ ምቾት እየተሰማት ተደላድላ ተቀመጠች፡ የሙቀት መጠኑ ቀስ በቀስ እጨመረ ሂዶ ከፍተኛ ደረጃውን በመያዙ እንቁራሪቷ የማምለጥ ሙከራ ሳታደርግ እዛው አረረች፡፡ ከለመዱት የመውጣት ፈተና እያረሩም ቢሆን በዛው ማዝገምን ያስመርጣል፡፡

እውነታው እሚነግረን ብዙዎቻችን እንደ እንቁራሪቷ እንደሚሰማን ነው፡፡ አሁን ካለንበት የማንወደው ግን ምቾት የሰጠን አድርገን ከምንወስደው ከባቢ ሁኔታ መላቀቅ አንወድም፡፡ ወይም ደግሞ የተሻለው ለውጥ የሚጠይቀንን ዋጋ ለመክፈል ዝግጁ አይደለንም፡፡ ይኸን የሚያጠናክር አባባልም አለን፡ ካለመዱት መልአክ የለመዱት ሰይጣን የሚል፡፡ በሕይወት ውስጥ ምርጫው ሁለት ነው ወይ ከነበሩበት ብሶ መበስበስ ወይም ደግሞ ወደ አዲስ መሻገር፡ ባሉበት መቀጠል የሚባል ሦስተኛ አማራጭ የለም፡፡ There is no permanent thing except change እንዲልሳይንሱ፡ ስለሆነም ወይ ወደፊት ወይም ደግሞ ወደኋላ ማለት የተፈጥሮ ግዴታ ነው፡፡ ምርጫችን ወደፊት እንዲሆን ሳንወደው ከተመቸን ከባቢ ሁኔታ መንቃት ይጠይቀናል፡

ምንጭ፦ Frog in the Beaker
https://t.me/kingnan