Get Mystery Box with random crypto!

የስኬት ሚስጢር

የቴሌግራም ቻናል አርማ keyofsuccesse — የስኬት ሚስጢር
የቴሌግራም ቻናል አርማ keyofsuccesse — የስኬት ሚስጢር
የሰርጥ አድራሻ: @keyofsuccesse
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.15K
የሰርጥ መግለጫ

✍በህይወትዎ ምን ማሳከት ይፈልጋሉ? ቀንዎን በስኬት እና በውጤት ለማሳለፍ።
ውጤታማ የቢዝነስ እና የሽያጭ ሰው ለመሆን።
. የሰራ ፈጠራ ስልጠና
. ለግል ህይወት እና የስብዕና ግንባታ ስልጠና
. የራሰን አቅም በሚገባ ለማወቅ
. ስለ ህልምዎ ፤ ስለ ራዕይዎ ፤ ስለ የህይወት ግብዎ ለማወቅ።
. አነቃቂ እና አስተማሪ የስኬታማ ሰዎች ታሪክ
. በየትኛውም የህይወት ዘርፍ ስኬታማ እና ውጤታማ ለመሆን።

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-08-03 06:48:52 1. ከሰዎች ጋር ለመስራት ስትፈልግ ሶስት ነገሮቻቸውን ተመልከት፦ ብልህነት (intelligence)፣ ጉልበት (energy) እና ታማኝነት (integrity)፡፡ እና የመጨረሻው ከሌላቸው ስለ መጀመሪያዎቹ ሁለት ስብእናዎች አትጨነቅ!
☞ ምክንያቱም በእውነት (truth)፣ በሐቀኝነት (honesty) እና በስነ-ምግባር (ethics) ልኬቶች ውስጥ የሚሰሩ ሰዎች ማንም ባይመለከታቸው እንኳ ልባቸውን ያዳምጣሉ፣ ትክክለኛውን ነገርም ያደርጋሉ ፡፡

2. ስኬታማ በሆኑና ያልተሳካላቸው ሰዎች መካከል ያለው ልዩነት ስኬታማ ሰዎች በማያስፈልጉ ነገሮች ላይ 'ምንጊዜም 'አይሆንም' (no) ስለሚሉ ነው።
☞ በየቀኑ ወደ እኛ አቅጣጫ ለሚመጡ አስፈላጊ ላልሆኑ ነገሮች ደግመን ደጋግመን 'አይሆንም' (no) ማለት እና አስፈላጊ ለሆኑ ጥቂት ነገሮች ትኩረት በመስጠት 'እሽ' ማለት አለብን።
ይህን መርህ በየትኛውም ነባራዊ ሁኔታ፣ በዕለት ተዕለት የውሳኔ አሰጣጥ መንታ መንገድ ላይ ስትደርስ ልትጠቀምበት ትችላለህ። ይህን ካደረክ ህይወትህን ማቅለል ትችላለህ።

3. ከአንተ የተሻሉ ሰዎች ጋር ጊዜህን አሳልፍ!
☞ በባህሪያቸው ከአንተ የተሻሉ ጓደኞችን መምረጥ ከቻልክና ከእነሱ ጋር ጊዜህን ካሳለፍክ አንተም ወደዚያ አቅጣጫ መጓዝ ትችላለህ፡፡
ዕድሜህም ሆነ ያለህበት ደረጃ ምንም ይሁን ምን እንደ መሪ፣ የንግድ ሰው ፣ ሠራተኛ እና ሰብዓዊ ፍጡር ከፍ የሚያደርግህን ጥበብ ፣ ልምድ እና ባህርይ የበለጠ ስኬታማ ከሆኑ ሰዎች መማር አስፈላጊ ነው፡፡
.
4. ሀብታም ብትሆን ወይም የገንዘብ ነጻነት ቢኖርህ ልትሰራው የምትችለውን ስራ ለመስራት ወስን!
☞ ይህን ስታደርግ የምትወደውን እና የምትጓጓለትን ነገር መፈለግና ያንን የህይወትህ ዋና ተግባር እንድታደርገው ይረዳሃል።
ይህ ማለት በየቀኑ ልትሰራው የምትጓጓለት ስራ ስላለህ ከአልጋህ ዘለህ ትነሳለህ፣ ምንጊዜም አንድ ነገር ትማራለህ ይህም ደስታን ይሰጥሃል።

5. ዝናን ለመገንባት 20 ዓመት ሊወስድ ይችላል ይህን ለማበላሸት ግን አምስት ደቂቃዎችን ብቻ ይወስዳል ፡፡ ይህን ማስብ ከቻልክ ነገሮችን በተለየ መንገድ ማድረግ ትችላለህ።
☞ የማንኛውም ሰው ዝና ወይም እውቅና በአሸዋ እንደተገነባ ቤት በፍጥነት ሊወድቅ ይችላል። ስለሆነም በህይወት ጉዞህ የምትመራበትን ታማኝነት (integrity) በውስጣዊ የጂፒኤስ ስርዓትህ ውስጥ ሳትገነባ ከቀረህ መውደቅህ የማይቀር ነገር ነው፡፡

መልካም ቀን!
272 views03:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 06:48:52
258 views03:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-01 13:45:16 የህይወት መዳረሻችንን ዲዛይን የምናደርገው እኛው ነን፣ ደራሲው እኛ ነን፤ ታሪኩን የምንፅፈው እኛው ነን። የመፃፊያ ብዕሩ በእጃችን ነው፤ በህይወታችን የምናገኘውም ነገር ምርጫችንን ነው! የሊዛ ኒኮልስ አባባል ነው በራሷ አባባል ያለችውን ልንገራችሁ 'You are the designer of your destiny. You are the author. You write the story. The pen is in your hand, and the outcome is whatever you choose.'
ታዲያ አሁን ያለንበት ሁኔታ የመረጥነው ነው? ደስተኛ ነን? ካልሆንን መጀመሪያ ምርጫችን ምን እንሆነ አስበን እንወስን...በህይወት ከሚንፈተንባቸው ነገሮች አንዱ ማመንታት ነው...ላድርገው አላድርገው፣ ልጀምረው አልጀምረው እያልን ማመንታት የሁልጊዜ ልማዳችን ከሆነ ለመወሰን አሁኑኑ በቁርጠኝነት ይነሱ/ይወስኑ!!!!
205 views10:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 20:24:34 ብዙ ነገሮች የሚወለዱት ከሀሳብ ነው።
የሁሉም ነገር መነሻ " ሀሳብ " ነው።

ስኬትም ውድቀትም የውልደት ማህፀናቸው " ሀሳብ " ነው።

አሁን እያሰብክ ያለው ምንም ይሁን ምን የነገ ህይዎትህ አንድ አካል ይሆናል።

ስለዚህ ነገን ማሳመር ስትፈልግ "ሀሳብህን " አሳምረው።

"ስኬት ፣ አድስ ዓመትና የአድስ ዓመት አዳዲስ ዕቅዶችን" በተመለከተ
314 views17:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-29 20:50:44 ለመስነፍ አልተፈጠርክም!

የመጀመሪያው ጠንክሮ የመስራት ሸክም ነው፤ ሁለተኛው የፀፀት ሸክም ነው። ጠንክሮ መስራት ምናልባት 1 ኪሎ ግራም ቢመዝን ነው፤ ፀፀት ግን 100 ኪሎ ግራም ተሸክሞ እንደመዞር ነው። የቱ እንደሚሻልህ አንተው ምረጥ!

ሁላችንም አሁን ካለንበት የተሻለ ነገር እንፈልጋለን፤ በከንቱ ቀንህ ያለፈ ጊዜ "በቃ አይኔ እያየ ምንም ሳልሰራበት ቀኑ አለፈ?" እያልክ ራስህን የወቀስክበትን ጊዜ አስብ፤ አየህ ወዳጄ ጠንክረህ የምትሰራው ከፍ እንድትል ብቻ አይደለም ሁሌም ከራስህ ጋር እንድትስማማ ነው።

ግሩም ምሽት ተመኘንላችሁ

የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
522 views17:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-28 09:15:55 ሳይንሳዊ ምርምር፡- 42 የማሰላሰል እና የማሰብ ጥቅሞች


1-የማሰብ ልምምዶች የመንፈስ ጭንቀትን ይቀንሳል
2-የአእምሮ ማሰላሰል እናቶች የመንፈስ ጭንቀትን ለማከም ይረዳል
3-የሜዲቴሽን ልምምዶች ስሜትን እና ጭንቀትን ለመቆጣጠር ይረዳሉ
4-ሜዲቴሽን በአጠቃላይ ጭንቀትንና ጭንቀትን ይቀንሳል
5-ሜዲቴሽን የፓኒክ ዲስኦርደር ምልክቶችን ለመቀነስ ይረዳል
6-ማሰላሰል በአንጎል ውስጥ የግራጫ ቁስ ትኩረትን ይጨምራል
7- ማሰላሰል የስነ-ልቦና ንቃትን በእጅጉ ያሻሽላል እና የእንቅልፍ ፍላጎትን ሊቀንስ ይችላል።
8- የረዥም ጊዜ ማሰላሰል በአንጎል ውስጥ የጋማ ሞገዶችን የመፍጠር ችሎታን ያሻሽላል
9-ሜዲቴሽን አልኮልን እና እፅን አላግባብ መጠቀምን ይቀንሳል
10-ሜዲቴሽን የእርስዎን ትኩረት፣ ትኩረት እና በጭንቀት ውስጥ የመስራት ችሎታን ያሻሽላል
11-ሜዲቴሽን የመረጃ አያያዝን እና ውሳኔን ያሻሽላል
12- ማሰላሰል የአዕምሮ ጥንካሬን፣ ጽናትን እና ስሜታዊ እውቀትን ይሰጥሃል
13- ማሰላሰል ከህመም የበለጠ ጠንካራ ያደርግሃል
14-ሜዲቴሽን ከሞርፊን በተሻለ ህመምን ያስታግሳል
15-ሜዲቴሽን ADHD (ትኩረት ማጣት ሃይፐርአክቲቪቲ ዲስኦርደር)ን ለመቆጣጠር ይረዳል።
16- ማሰላሰል ትኩረትን የሚከፋፍሉ ነገሮች ቢኖሩም ትኩረትን የመጠበቅ ችሎታን ይጨምራል
17-ማሰላሰል መማርን ፣ማስታወስን እና ራስን ማወቅን ያሻሽላል
18-የአእምሮ ማሰላሰል ፈጣን የማስታወስ ትውስታን ያሻሽላል
19-ማሰላሰል ስሜትዎን እና ስነ ልቦናዊ ደህንነትዎን ያሻሽላል
20- ማሰላሰል ብዙ ጊዜ በተግባራት ወጥመድ ውስጥ እንዳትወድቅ ይከላከላል።

21-ሜዲቴሽን ውስን የአንጎል ሀብቶችን እንድንመድብ ይረዳናል።
22-ሜዲቴሽን ቪዥኦስፓሻል ሂደትን እና የስራ ማህደረ ትውስታን ያሻሽላል
23- ሜዲቴሽን አስጨናቂ ሁኔታዎችን ለመቋቋም ያዘጋጅሃል
24-የማሰብ ችሎታ ማሰላሰል ፈጠራን ያበረታታል።
25-ሜዲቴሽን ለልብ ህመም እና ለስትሮክ ተጋላጭነትን ይቀንሳል
26-ሜዲቴሽን ጭንቀትን እና በሽታ የመከላከል አቅምን የሚቆጣጠሩ ጂኖችን ይጎዳል።
27-ሜዲቴሽን የደም ግፊትን ይቀንሳል
28-የአስተሳሰብ ስልጠና የእብጠት መታወክን ይቀንሳል
29-የአእምሮ ማሰላሰል ሴሉላር ደረጃ እብጠትን ይቀንሳል
30-የማስታወስ ልምምድ አስምን፣ ሩማቶይድ አርትራይተስን እና የአንጀት እብጠት በሽታን ይከላከላል።
31-የማሰላሰል እና የማሰላሰል ጸሎት የቅድመ የወር አበባ ሲንድሮም እና ማረጥ ምልክቶችን ለማከም ይረዳል
32-የአእምሮ ማሰላሰል የአልዛይመርን እና ያለጊዜው የመሞት እድልን ይቀንሳል
33-የአእምሮ ማጎልበት ስልጠና በፋይብሮማያልጂያ ለተያዙ ታካሚዎች ጠቃሚ ነው።
34-ሜዲቴሽን የልብ ምትን እና የአተነፋፈስን መጠን ለመቆጣጠር ይረዳል
35-የአእምሮ ማሰላሰል ኤችአይቪን ለማከም ሊረዳ ይችላል።
36- ማሰላሰል ረጅም ዕድሜ ሊሰጥህ ይችላል።
37- Transcendental Meditation የጤና ጥቅሞች
38-ፍቅር-ደግነት ማሰላሰል መተሳሰብን እና አዎንታዊ ግንኙነቶችን ያሻሽላል
39-የፍቅር ደግነት ማሰላሰል ማህበራዊ መገለልንም ይቀንሳል
40- ማሰላሰል የርህራሄ ስሜትን ይጨምራል እና ጭንቀትን ይቀንሳል
41-የማሰብ ማሰላሰል የብቸኝነት ስሜትን ይቀንሳል
42- ማሰላሰል ስሜታዊ ምግብን ይቀንሳል
715 views06:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-23 03:41:27 ተመስገን በል!

የዛሬ ሳምንት እንደምትሞት ቢነገርህ አሁን ያስጨነቀህ ነገር ሁሉ ተራ እንደሆነ ይገባሀል! ከጎደለህ ይልቅ የተደረገልህ ይበልጣል! ስለዚህ ተመስገን በል ወዳጄ!

የምስጋና ምሽት ተመኘንላችሁ
131 views00:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 09:20:03 #ብስለት

"ብስለት ማለት ዕድሜ አይደለም ብስለት ማለት ለነገሮች ጠንቃቃ መሆን"

ጥሩ ሥነ-ምግባርና ሁኔታዎችን እንዴት እንደምናስተናግድ ማወቅ ነው"

"ትክክለኛ ብስለት ማለት አንድ ሰው ሲጎዳህ የተጎዳህበትን ነገር ንቀህ እያወቅህ አንተ ግን መልሰህ አለመበቀልና መተው ማለት ነው።

"ብስለት ማለት ትልልቅ ንግግሮችን መናገር መጀመር ሳይሆን ትንንሽ ነገሮችን ማስተዋል መጀመር ነው።

"በህይወት ውጣ ውረድ ድራማ ሳያቆም ብስለት ይጀምራል።
"ዕድሜ ለብስለት የሚከፈል ትልቅ ዋጋ ነው።

"ብስለት ማለት አለመብሰልን ማወቅና መረዳት ማለት ነው።
"በሳል ፍቅር እንዲህ ይላል ስለምወድህ እፈልግሃለሁ"

"ያልበሰሉ ሰዎች ከሰዎች ጋራ ያላቸው ግንኙነት እስኪበላሽ ድረስ በክርክር ማሸነፍ ያምናሉ።

የበሰሉ ሰዎች ግን በክርክር መሸነፍ ቀርቶ ወርቃማ የሆነው የሰዎች ግንኙነት እንዲጠብቅ ይጠነቀቃሉ።

መልካም ቀን!
236 views06:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 04:02:04 "ቁራጥነት ለለውጥ"
~~~~
ህይወታችን ስንመራ ውሳኔዎች ደጋግመን እናደርጋለን...
አንደኛው ባለንበት ለመቀጠል ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ካለንበት ለቀን እንድንወጣ ነው።
ህይወት ለውጥ ያስፈልጋታል... ከአንደኛው መስመር ወደሌላ መስመር የሚያስኬድ... በለውጥ ጎዳና የሚያስገባ።

ቆራጥነት በምንም መልኩ ለህይወት ለውጥ ያስፈልጋል።

መልካም ቀን!
11 views01:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 07:04:50
#የስኬታማ_ሰዎች_ባህሪያት

#ምኞት
ስኬታማ ሰው ግልጽ የሆኑ ግቦች አሉት። “ሀብታም መሆን” እንደሚለው አይነት ግልጽ ያልሆነ ግብ ይልቅ ፣ “በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ያለኝን አንድ ሱቅ ወደ ሶስት ሱቆች ማስፋፋት የሚል አይነት ውስን ግብ ያስቀምጣል።

#ተነሳሽነት
ስኬታማ ሰዎች በጣም ከሚገለጹበት ባህሪያት አንዱ ተነሳሽነት ነው። ስኬታማ ሰዎች ግባቸውን ለማሳካት ጠንካራ ተነሳሽነት ሊኖራቸው ይገባል። ጠንካራ የተነሳሽነት ስሜት ያለው ስኬታማ ሰው፥ በችሎታው ስለሚተማመንና ግቡን ለማሳካት ስለሚፈልግ ያለ ድካም መስራት ይችላል፨

#ለመማር_ፈቃደኛነት።
ስኬታማ ሰው ሁሉን አውቃለሁ አይልም፨ ከሁሉም ሰውና ከሚያጋጥሙት ሁኔታዎች ሁሉ ለመማር የተከፈተ አእምሮ አለው፨ እያንዳንዱ ተሞክሮ ለማደግ አጋጣሚ እንደሚፈጥር ይረዳል፨ የማያውቀው ነገር እንዳለ ያምናል፥ አዲስ ነገር ለመማር ቦታ እንዳለው ሲገነዘብም እውቀቱን ለማሻሻል ይነሳሳል፨

#ታጋሽነት
ስኬታማ መሆን የምትፈልግ ከሆነ ትዕግስት ሊኖርህ ይገባል፨ ነገሮች ምንም ያህል አሁን እንዲሆኑ ብትፈልግ ሊደረስበት ዋጋ ያለውን ማንኛውም ነገር መጠበቅ ደግሞ ዋጋ አለው፨

#ስርዓት
ስኬት ወጥነት ይፈልጋል፥ ወጥነት እንዲኖር ደግሞ ስርዓት ሊኖር ይገባል፨ ብዙ ስኬታማ ሰዎች ህልማቸውን እውን ለማድረግና በጥረታቸው ውስጥ ወጥነት ያላቸው እንዲሆኑ የዕለት ተዕለት ተግባር ላይ መመስረት አንዱ ቁልፍ እንደሆነ ተገንዝበዋል።

ወጥነት ያለውና ሥርዓታማ በመሆንና ለማደግ ራስህን በመስጠት፣ በስራና በህይወት ውስጥ ብዙ ሽልማቶች እንድታገኝ ያደርግሃል፨ ይህ ሰዎች በሙያቸው ስኬትን ብቻ ሳይሆን ረጅም ዘመን ኖሯቸው እንዲደሰቱ የሚያስችል ቁልፍ ባህሪ ነው።

#ወደ_ሀብት_ጉዞ መጽሐፍ
370 views04:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ