Get Mystery Box with random crypto!

የስኬት ሚስጢር

የቴሌግራም ቻናል አርማ keyofsuccesse — የስኬት ሚስጢር
የቴሌግራም ቻናል አርማ keyofsuccesse — የስኬት ሚስጢር
የሰርጥ አድራሻ: @keyofsuccesse
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.15K
የሰርጥ መግለጫ

✍በህይወትዎ ምን ማሳከት ይፈልጋሉ? ቀንዎን በስኬት እና በውጤት ለማሳለፍ።
ውጤታማ የቢዝነስ እና የሽያጭ ሰው ለመሆን።
. የሰራ ፈጠራ ስልጠና
. ለግል ህይወት እና የስብዕና ግንባታ ስልጠና
. የራሰን አቅም በሚገባ ለማወቅ
. ስለ ህልምዎ ፤ ስለ ራዕይዎ ፤ ስለ የህይወት ግብዎ ለማወቅ።
. አነቃቂ እና አስተማሪ የስኬታማ ሰዎች ታሪክ
. በየትኛውም የህይወት ዘርፍ ስኬታማ እና ውጤታማ ለመሆን።

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-01-31 18:52:36 ሚስጢሩ (The secret)

(#documentary_Audio በትርጉም በቅርብ ቤተሰቤ የተሰራ አድምጡት ትወዱታላችሁ። ለህይወት ያላችሁን እይታ ይቀይርላችኋል።

1:32:19
https://t.me/keyOfsuccesse
https://t.me/keyOfsuccesse
293 viewsedited  15:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-31 06:13:42
ጊዜ


ህይወት ጊዜ በሚባል መለኪያ ተሰፍሮ ለሁሉም እኩል ተሰጥቷል። በቀን 24 ሰዓት በሳምንት 7 ቀን በአመት 365 ቀናት ።

እያንዳንዷን ቀን እንደ ባንክ አካውንት አስበው ጊዜን ደግሞ እንደ ከረንሲ ( ገንዘብ) በጊዜ ማንም ደሃ ማንም ሃብታም የለም፤ ለሁሉም እኩል 24 ሰዓት ተሰጥቶታል።

በህይወት የሃብት ልዩነት የሚፈጠረው በጊዜ አጠቃቀም ልዩነት ነው።

ጊዜውን በአግባቡ ለተገቢው ተግባር የተጠቀመ የፈለገውን ና በህይወት አላማው ይኖራል። ጊዜውን በአግባብ ያልተጠቀመ ደግሞ በትችት ና በህይወት ሩጫ ( ሲደክም) ይኖራል።

ሽርፍራፊዋ ሰከንድ ከህወትህ ላይ ተሸርፋ የተሰጠችህ ናት፤ በአግባቡ ተጠቀምባት።

አሁን ማድረግ ለሚገቡህ ነገሮች ሁሉ: በኋላ፣ ነገ፣ ቀጣይ ሳምንት የሚቀጥለው ወር የሚባል ሰበባ ሰበብ አትስጥ ምክንያቱም ምድር ላይ ያለውን እጅግ በጣም ውዱን ጊዜህን እያባከንክ ነው።
ማድረግ ካለህ አሁኑኑ አድርገው።

ማድረግ ከሌለብህ ደግሞ ማድረግ የሌለብህን ነገር በማሰብ እንቁ ሃብትህን አታባክን።

መልካም ቀን
388 views03:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-30 14:36:03 ብቃትን ፍለጋ!

አንድ ጊዜ ፈጣሪ ሰውን ያላካተተ ስብሰባን ጠራና ፍጥረትን ሁሉ ሰብስቦ አንድን ጥያቄ ጠየቃቸው፣ ይላል አንድ ምንጩ ያልታወቀ አፈ-ታሪክ፡፡

ጥያቄው እንዲህ የሚል ነበር፡-

“ለነገሩ ዝግጁ እስኪሆኑ ድረስ አንድን ነገር ከሰው ልጆች ልሰውርባቸው እፈልጋለሁ፡፡ ስለሆነም ያንን ከሰዎች ለመሰወር የምፈልገውን ነገር የት ባስቀምጠው ሰዎች ላያገኙት የሚችሉ ይመስላችኋል?” አላቸው፡፡ ለዚህ ጥያቄ መልስ ለመስጠት ብዙም የደፈረ እንስሳ ማግኘት ከባድ የነበረ ቢሆንም አራት እንስሶች የየግል ሃሳባቸውን ሰነዘሩ፡፡

ንስር እንዲህ አለ፡-

“ከሰዎች ለመሰወር የፈለከውን ነገር ለእኔ ስጠኝና ከፍ ብዬ መብረር ስለምችል ጨረቃ ድረስ ይዤው እወጣና እዚያ አስቀምጠዋለሁ”፡፡ ፈጣሪም መልሶ፣ “አንድ ቀን የሰው ዘር ጨረቃ ላይ የመውጣት ብቃት ስለሚኖረው ማግኘታቸው አይቀርም” አለው፡፡

አሳ እንዲህ አለ፡-

“እንደ ውቂያኖስ ጥልቅ ነገር እንደሌለለና ሰዎች እዚያ ጥልቀት ድረስ እንደማይሄዱ አውቃለሁና እኔ በዋና እዚያ ድረስ መጥለቅ ስለምችል ይዤው ልግባና እዚያ አስቀምጠዋለሁ”፡፡ ፈጣሪም መልሶ፣ የሰው ልጅ ወደጠለቀው ባህር የመግባት አቅም ለማዳበር ብዙ ጊዜ ስከማይፈጅበት ማግኘቱ አይቀርም” ብሎ መለሰ፡፡

አንበሳ በተራው እንዲህ አለ፡-

“እንኳን ሰው አብዛኛዎቹ የዱር እንስሶች እንኳ የሚፈሩት ጥቅጥቅ ያለውን ጫካ የምደፍር እኔ ነኝ፡፡ እዚያ ወስጄ ባስቀምጠው ስለማያገኙት ለእኔ ስጠኝ”፡፡ ፈጣሪም፣ “ሰዎች ጫካን መመንጠር ብዙም ስለማይከብዳቸው ቀስ በቀስ ይደርሱበታል” አለ፡፡

ጦጣ በመጨረሻ እንዲህ አለች፡-

“ፈጣሪ ሆይ፣ ከእነዚህ ሁሉ ሃሳብ ሰጪዎች በበለጠ ሁኔታ ከሰው ጋር ቀረብ ብዬ የምኖረው እኔ ስለሆንኩኝ ባህሪያቸው በደንብ አውቀዋለሁ፡፡ ሰዎች አብዛኛውን ነገር ፍለጋ ውጪ ውጪውን ነው የሚሉት፡፡ ውስጣቸው ያለው ነገር ትዝም አይላቸው፡፡ ስለዚህ ውስጣቸው ብታስቀምጠው በቀላሉ አያገኙትም” አለችው፡፡

የጦጣ መልስ ተቀባይነት ስላገኘ ፈጣሪ ለመደበቅ ያሰበውን ነገር በሰው ውስጥ አስቀመጠው ይባላል፡፡ ይህ የተደበቀው ነገር የራሳቸው የሰዎቹ እምቅ ብቃት ነው፡፡ ብዙ ሰዎች በውስጣቸው ፈጣሪ ያስቀመጠው አስገራሚና የታመቀ ብቃት እያላቸው ምንም እንደሌላቸው በከንቱ ጊዜያቸውን ያባክናሉ፡፡

በውስጣችሁ ተዝቆ የማያልቅ እምቅ ብቃት እንዳለ ታውቃላችሁ? ፈልጋችሁ አግኙት! አውጡት! አዳብሩት! ተጠቀሙበት!
https://t.me/keyOfsuccesse
https://t.me/keyOfsuccesse
542 viewsedited  11:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-31 09:10:18
Albent Healing Clay:-
አልቤንት ክሌይ ከእሬት ተክል እና ከእሳተገሞራ ፍንዳታ የሚገኘው በውስጡ ከ50 በላይ ማእድናትን ከያዘው ቤንቶናይን ክሌይ የሚመረት ሲሆን የፊታችንን ሆነ የመላ ሰውነታችን የሞተ ቆዳ በማንሳት ጤናማ እና ብሩህ ገፅታ እንዲኖረን ያደርጋል።

አጠቃቀሙም የአልቤንት ፓውደርን በፕላስቲክ ወይንም ጠርሙስ እቃ ውስጥ በመጨመር በአፕል ሳይደር ቪኔጋር ወይንም ለብ ባለ ውሃ በፕላስቲክ ማማሰያ መበጥበጥ በመቀጠልም በቆዳዎ ላይ በመቀባት እንደቆዳዎ አይነት ከ 5 እስከ 20 ደቂቃ (ደረቅ የፊት ቆዳ ካለዎት ከ 5 እስከ 10 ደቂቃ ወዛም የፊት ቆዳ ካለዎት ከ 15 እስከ 20 ደቂቃ) በማቆየት ለብ ባለ ውሃ መታጠብ
 
ደውለው ይዘዙን ያሉበት ድርስ እናመጣለ       ለማዘዝ: 0935785595


Etcare !  i care!  you care!  we care!

ኑ አብረን የተሻለ ነገን እንገንባ።

ወደ ቻናላችንን ይግቡ
@etcare_Ethiopian_Company
@etcare_Ethiopian_Company
@etcare_Ethiopian_Company

#share

To register መልክት መቀበያችን

@message_bots
@message_bots
@message_bots
359 views06:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-06 03:07:48

239 views00:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-05 05:49:09

367 views02:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-04 19:02:34

404 views16:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-03 16:34:06
275 views13:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-03 05:57:35
ዝም ብለህ ከከፍታ በላይ ብረር

https://t.me/keyOfsuccesse
373 viewsedited  02:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-03 05:57:10
በህይወታችን የሚመጡትን መልካም አጋጣሚዎች በሙሉ መጠቀም በጣም አስፈላጊ ነው። ምክንየቱም ያ ነገር ተመልሶ ወደኛ ላይመጣ ይችላል ወይም ደግሞ ከበፊቱ የበለጠ ዋጋ ሊያስከፍለን ይችላል። ታዲያ ዛሬ ላይ ምን እየገፋን ነው ያለነው? እውነትስ ከዛ የተሻለ ነገር እጃችን ላይ ኖሮ ነው?። አንድን ነገር አልፈልግም ብሎ ለመተው እኮ እኛ ጋር ከዛ የተሻለ አማራጭ እኛጋ ሊኖር ይገባል። ካልሆነ ግን አማራጭ በሌለ ጊዜ የመጣውን መልካም አጋጣሚ አፈፍ አድርጎ ህይወትን ወደተሻለ ደረጃ ማሻገር ያስፈልጋል።

ስኬታማና የዛሬዋን መልካም አጋጣሚ
የምንጠቀምበት ቀን ያድርግልን

https://t.me/keyOfsuccesse
393 viewsedited  02:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ