Get Mystery Box with random crypto!

የስኬት ሚስጢር

የቴሌግራም ቻናል አርማ keyofsuccesse — የስኬት ሚስጢር
የቴሌግራም ቻናል አርማ keyofsuccesse — የስኬት ሚስጢር
የሰርጥ አድራሻ: @keyofsuccesse
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.15K
የሰርጥ መግለጫ

✍በህይወትዎ ምን ማሳከት ይፈልጋሉ? ቀንዎን በስኬት እና በውጤት ለማሳለፍ።
ውጤታማ የቢዝነስ እና የሽያጭ ሰው ለመሆን።
. የሰራ ፈጠራ ስልጠና
. ለግል ህይወት እና የስብዕና ግንባታ ስልጠና
. የራሰን አቅም በሚገባ ለማወቅ
. ስለ ህልምዎ ፤ ስለ ራዕይዎ ፤ ስለ የህይወት ግብዎ ለማወቅ።
. አነቃቂ እና አስተማሪ የስኬታማ ሰዎች ታሪክ
. በየትኛውም የህይወት ዘርፍ ስኬታማ እና ውጤታማ ለመሆን።

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-06-30 07:31:04 " ጥሩ ስብዕናን ለማጎልበት የሚያስፈልጉ ነጥቦች "

1: ድፍረት / Courage
2: መልካም አመለካከት / Positivity
3: ታማኝነት / Integrity
4: ደግነት/ ቅንነት / Kindness
5: ፅናት / perseverance
6 : አክብሮት / Respect
7 : ሀላፊነት / Responsibility
Https://t.me/keyOfsuccesse
817 views04:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-22 21:13:49 ለጊዜያችን ያለን ዋጋ!

ጌዜያችን ላይ ያለን አቋም ምን ያህል ደረጃ ላይ ነው ? አንድ ባልዲ ውሀ ለመሙላት ስንጀምር ከጠብታ ፍሳሾች እንደሆነ ሁሉ እያንዳንዷ ደቂቃ ህይወታችንን ለመሙላት ወሳኝ መሰረት መሆኗን ተገንዝበነዋል?

መልካም ረቡዕ ተመኘን

የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
Https://t.me/keyOfsuccesse
1.3K views18:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-03 19:16:15
.ማገዝ ከሚችሉ ሰዎች ጋር ተወዳጅ፦

አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች በራሳቸው ጥረት ብቻ የሚፈልጉት የስኬት ጫፍ ላይ ለመድረስ ሲታገሉ እንመለከታለን። በተለይ የተሳሳተ አመለካከት ያላቸው ሰዎች የሌሎችን እገዛ መጠየቅ የውድቀት መጀመሪያ መስሎ ይታያቸዋል። በዙሪያ የሚያግዙ ሰዎች መኖር ጥንካሬና ብርታትን ይሰጣል። ስለዚህ የሚያግዝህና ሃሳብህን የምታጋራው አስተዋይ ወዳጅ ይኑሩህ።
2.3K views16:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-13 09:07:52 የተሻለውን ማየት

በህይወት ውስጥ የልብን መሻት ለማግኘት መፍጨርጨር ግድ ነው። ያሰቡትን አግኝቶም ሆነ ሳያገኙ መቆም ግን ድክመት ነው፤ ተገቢ አይደለም። ከግቡ ባሻገር የተሻለውን የበለጠውን ማየትና እሱ ላይ ለመድረስ መገስገስ ያስፈልጋል።

"እኔ የምበላውን ካገኘሁ ይበቃኛል፤ ምን ያለፋኛል?" ማለት የሰነፍ ፣ የንፉግ እና የራስ ወዳድ ሃሳብ ነው። ካንተ አልፎ ለሌላው የሚተርፍ እንዳትሠራ ምን ያግድሃል? ስንፍና ፣ ንፉግነት ወይም ራስ ወዳድነት ካልሆነ በቀር።

የዓለም ሊቃውንት እንዲያ ቢሆኑ ኖሮ ኑሮ ምን ያህል አስቸጋሪ ይሆን ነበር? ቶማስ ኤዲሰን እንዲያ 10ሺህ ጊዜ ባይሞክር ህይወታችን ምን ያህል ጨለማ በዋጠው ነበር።

የእጅ ስልክህ የስንት "ምን ቸገረኝ" ብለው ያልቆሙ እና የተሻለውን ማየት የቻሉ ሰዎች ውጤት ነው።

ወዳጄ ሆይ! ታካች አትሁን። በልፋት ውስጥ ደስታ አለ። እናቶች ሁሉ ልጅ የመውለድ ምጥ ምን ያህል ከባድ መሆኑን እያወቁ ልጅ ይወልዳሉ።

በልጁ መወለድ የሚገኘው ደስታ የተሻለ መሆኑን ያምናሉ፤ ያውቃሉም። "ምጥ በልጅ ይረሳል" አይደል የሚባለው።

ስላለህ ነገር ተመስገን ማለት ጥሩና ተገቢ ነው። በምስጋና ውስጥ ድል አለ። ከምስጋናው ባሻገር ግን የተሻለውን ማየትና በእጅ ለማስገባት ሳይስገበገቡ መስራት ያስፈልጋል። ሳይንገበገቡ የሚሠሩ በሚያጋጥማቸው እንቅፋት አያዝኑም፤ አይቆሙም። እንቅፋቱ በጉዞው ውስጥ ሊያጋጥም የሚችል መሆኑን ይቀበላሉ፤ ተገቢውን ጥንቃቄ ያደርጋሉ። ሲያጋጥምም ለመፍትሔው ይሠራሉ።

ዛሬ የትናንት ሥራችን ውጤት ነው። ከትናንት የተሻለ ነገን ለመፍጠር ዛሬ ላይ ማሰብ ፣ መሥራት ፣ መጣር፣ አዲስ ነገር መሞከር ያስፈልጋል። "የተሻለውን ዓይተው የተጓዙ ጥቂቶች ቢሆኑም የሚሻለው አካሄድ እሱ ነው።

ለሀገራችን ፣ ለራሳችን ፣ ለሰው ልጅ የተሻለ ዓለም ለመፍጠር እንጣር፤ ዛሬ አዲስ ቀን ነው።

የተሻለ ልምድ የተሻለ ውጤት!

መልካም ቀን!
5.4K views06:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-12 08:51:11
3.5K views05:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-12 08:51:11 አንተ ደስተኛ እንድትሆን የግድ የምትፈልገው ሁሉ መሳካት የለበትም። ቀንህን ማሳመር ከፈለክ እጅህ ላይ ስላለው ነገር በጎ ነገር አስብ፤ አቅም አለህ፣ ወጣት ነህ፣ ብዙ ነገር መቀየር ትችላለህ ከሁሉ በላይ ደግሞ እየተነፈስክ ነው!

በዚህ አለም አንዳንድ ነገሮች የጎደሉህ ቀን ነው እንደነበሩህ ራሱ የምታውቀው፤ ለምሳሌ ስትታመም ነው ለካ ጤነኛ መሆን ወሳኝ ነገር እንደሆነ የሚገባህ። ወዳጄ የተሰጠህን ተመልከትና ቀንህን አሳምረው!

መልካም ቀን!
3.3K views05:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-06 17:42:06 #ማድረግ_ተለማመድ

√ ጠዋት ከሰው ሁሉ በፊት ከእንቅልፍህ ተነስ
√ ቀንህን በጸሎት ጀምር
√ ውሎህን አቅድ
√ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አድርግ
√ ገላህን ታጠብ
√ የምትወደውን ልብስ ልበስ
√ ስራህን በሙሉ ትኩረት ስራ
√ የዛሬ ስራህን ዛሬ ጨርስ
√ በየቀኑ የንባብ ሰዓት ይኑርህ
√ ሰውነትህ የሚፈልገውን ያህል ብቻ ተመገብ
√ ብዙ ውሃ ጠጣ
√ በየቀኑ የቤተሰብ ሰዓት ይኑርህ
√ ለምታገኛቸው ሁሉ ሰዎች የደስታቸው ምክንያት ሁን
√ በየቀኑ ትንንሽ መልካም ነገሮችን አድርግ
√ ውሎህን ገምግመህ ፈጣሪህን አመስግነህ ተኛ
√ በቂ እንቅልፍ ተኛ

ስኬት እያዳንዷን ቀን በትክክል የመኖር ድምር ውጤት ነው!!

መልካም ምሽት!
3.9K views14:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-03 12:59:36 "ህሊና በሰው የሚገኝ የፈጣሪ ምትክ ነው"

"ዝም ማለት ሁልግዜ እሺ ማለት አይደለም አንዳንዴ ለማይገባው ሰው ማብራራት ሰልችቶኛል ማለት ነው"

"እንደ ጀግና ኑር ከጀግናም ጋር ታገል አንድ ቀን የምትፈልገው ህይወት ብቅ ትል ይሆናል"

"ጨለማን ያላየ መብራት አያደንቅም መውደቅን ያላየ መነሳት አያውቅም"

"ውበት የአምላክ ስጦታ ናት! ከፈት ውበት የአእምሮ ውበት ይበልጣል"!

መልካም ቀን!
3.3K views09:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-02 09:44:59 1. ከሰዎች ጋር ለመስራት ስትፈልግ ሶስት ነገሮቻቸውን ተመልከት፦ ብልህነት (intelligence)፣ ጉልበት (energy) እና ታማኝነት (integrity)፡፡ እና የመጨረሻው ከሌላቸው ስለ መጀመሪያዎቹ ሁለት ስብእናዎች አትጨነቅ!

☞ ምክንያቱም በእውነት (truth)፣ በሐቀኝነት (honesty) እና በስነ-ምግባር (ethics) ልኬቶች ውስጥ የሚሰሩ ሰዎች ማንም ባይመለከታቸው እንኳ ልባቸውን ያዳምጣሉ፣ ትክክለኛውን ነገርም ያደርጋሉ ፡፡

2. ስኬታማ በሆኑና ያልተሳካላቸው ሰዎች መካከል ያለው ልዩነት ስኬታማ ሰዎች በማያስፈልጉ ነገሮች ላይ 'ምንጊዜም 'አይሆንም' (no) ስለሚሉ ነው።

☞ በየቀኑ ወደ እኛ አቅጣጫ ለሚመጡ አስፈላጊ ላልሆኑ ነገሮች ደግመን ደጋግመን 'አይሆንም' (no) ማለት እና አስፈላጊ ለሆኑ ጥቂት ነገሮች ትኩረት በመስጠት 'እሽ' ማለት አለብን።

ይህን መርህ በየትኛውም ነባራዊ ሁኔታ፣ በዕለት ተዕለት የውሳኔ አሰጣጥ መንታ መንገድ ላይ ስትደርስ ልትጠቀምበት ትችላለህ። ይህን ካደረክህይወትህን ማቅለል ትችላለህ።

3. ከአንተ የተሻሉ ሰዎች ጋር ጊዜህን አሳልፍ!
☞ በባህሪያቸው ከአንተ የተሻሉ ጓደኞችን መምረጥ ከቻልክና ከእነሱ ጋር ጊዜህን ካሳለፍክ አንተም ወደዚያ አቅጣጫ መጓዝ ትችላለህ፡፡

ዕድሜህም ሆነ ያለህበት ደረጃ ምንም ይሁን ምን እንደ መሪ፣ የንግድ ሰው ፣ ሠራተኛ እና ሰብዓዊ ፍጡር ከፍ የሚያደርግህን ጥበብ ፣ ልምድ እና ባህርይ የበለጠ ስኬታማ ከሆኑ ሰዎች መማር አስፈላጊ ነው፡፡
.
4. ሀብታም ብትሆን ወይም የገንዘብ ነጻነት ቢኖርህ ልትሰራው የምትችለውን ስራ ለመስራት ወስን!

☞ ይህን ስታደርግ የምትወደውን እና የምትጓጓለትን ነገር መፈለግና ያንን የህይወትህ ዋና ተግባር እንድታደርገው ይረዳሃል።

ይህ ማለት በየቀኑ ልትሰራው የምትጓጓለት ስራ ስላለህ ከአልጋህ ዘለህ ትነሳለህ፣ ምንጊዜም አንድ ነገር ትማራለህ ይህም ደስታን ይሰጥሃል።

5. ዝናን ለመገንባት 20 ዓመት ሊወስድ ይችላል ይህን ለማበላሸት ግን አምስት ደቂቃዎችን ብቻ ይወስዳል ፡፡ ይህን ማስብ ከቻልክ ነገሮችን በተለየ መንገድ ማድረግ ትችላለህ።

☞ የማንኛውም ሰው ዝና ወይም እውቅና በአሸዋ እንደተገነባ ቤት በፍጥነት ሊወድቅ ይችላል። ስለሆነም በህይወት ጉዞህ የምትመራበትን ታማኝነት (integrity) በውስጣዊ የጂፒኤስ ስርዓትህ ውስጥ ሳትገነባ ከቀረህ መውደቅህ የማይቀር ነገር ነው፡፡

መልካም ቀን
2.8K views06:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-27 04:18:10 "ህሊና በሰው የሚገኝ የፈጣሪ ምትክ ነው"

"ዝም ማለት ሁልግዜ እሺ ማለት አይደለም አንዳንዴ ለማይገባው ሰው ማብራራት ሰልችቶኛል ማለት ነው"

"እንደ ጀግና ኑር ከጀግናም ጋር ታገል አንድ ቀን የምትፈልገው ህይወት ብቅ ትል ይሆናል"

"ጨለማን ያላየ መብራት አያደንቅም መውደቅን ያላየ መነሳት አያውቅም"

"ውበት የአምላክ ስጦታ ናት! ከፈት ውበት የአእምሮ ውበት ይበልጣል።

መልካም ቀን!
2.6K views01:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ