Get Mystery Box with random crypto!

የስኬት ሚስጢር

የቴሌግራም ቻናል አርማ keyofsuccesse — የስኬት ሚስጢር
የቴሌግራም ቻናል አርማ keyofsuccesse — የስኬት ሚስጢር
የሰርጥ አድራሻ: @keyofsuccesse
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.15K
የሰርጥ መግለጫ

✍በህይወትዎ ምን ማሳከት ይፈልጋሉ? ቀንዎን በስኬት እና በውጤት ለማሳለፍ።
ውጤታማ የቢዝነስ እና የሽያጭ ሰው ለመሆን።
. የሰራ ፈጠራ ስልጠና
. ለግል ህይወት እና የስብዕና ግንባታ ስልጠና
. የራሰን አቅም በሚገባ ለማወቅ
. ስለ ህልምዎ ፤ ስለ ራዕይዎ ፤ ስለ የህይወት ግብዎ ለማወቅ።
. አነቃቂ እና አስተማሪ የስኬታማ ሰዎች ታሪክ
. በየትኛውም የህይወት ዘርፍ ስኬታማ እና ውጤታማ ለመሆን።

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2022-02-26 22:02:00 "10 ትምህርቶች ከ'Rich Dad, Poor Dad' መፅሐፍ!!!"

1. ማዳመጥን ይማሩ!

2. በመጀመሪያ ለራስዎ ዋጋ ይስጡ!

3. ቅንጦትን መጀመሪያ ሳይሆን በስተመጨረሻ ይግዙ!

4. ወጪዎችን ይቀንሱ!

5. የበለጠ ዋጋ ላላቸው ነገሮች ያልሙ!

6. ስሜቶችዎን ይቆጣጠሩ!

7. ለመማር ይስሩ ፣ ለማግኘት አይስሩ!

8. እርስዎ ያልዎትን እውቀት ያህል ነዎት ፣ ብዙ ያንብቡ!

9. የሚያገኙትን ገንዘብ እንደገና ኢንቬስት ያድርጉ!

10. እራስዎን ከእርስዎ በበለጡ ብልህ ሰዎች ይክበቡ!
2.4K views19:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-10 18:14:50 ሃያ አንዱ ማህበራዊ ሕግጋት
ዶ/ር ምህረት ደበበ

1. ይሰለቹሃል አስሬ አትደውል፤ ሰዎች ጋር ከሁለቴ በላይ አይደወልም። ተሰልቺ ትሆናለህ!

2. 'ሼም ነው' የሚከፍለው ሌላ ሰው ነው ብለህ ከፍ ያለ ዋጋ ያለው ምግብና መጠጥ አትዘዝ!

3. አይባልም "... እንዴ እስካሁን አላገባሕም? ለምንድነው እስካሁን ያልወለድሽው? እንዴት ዲግሪሽን እስካሁን ሳትይዢና ሳትይዝ ወዘተ..." አይባልም።

4. ክፈል አብሮህ ላለው ሰው ታክሲ ላይም ሆነ የትም ቦታ አግባብ ነው ብለህ ስታምን ቀድመህ ክፈል። ገና ለገና ይከፍላል ብለህ ከሱ ስትጠብቅ ደምህን እያሯሯጥክ ትሰቃያለህ።

5. ነውር ነው ሰው እየበላም ይሁን በማንኛውም ሰዓት ከሰዎች ጋር ካለህ ጥርስህን አትጎርጉር፣ አፍንጫህንና ሌሎች ያልተገቡ ቦታዎችንም አትነካካ።

6. አታቋርጥ ግዴለህም አብሮህ ያለው ሰው አውርቶ ይጨርስ። ጥልቅ እያልክ አታቋርጥ።ከባሕልም ከስልጣኔም ውጪ ነው።

7. አታብሽቅ ሆን ብለህ የማናደድ ባሕሪ ካለህ ተው። ሰዎች ለመባል የማይወዱትን ተው።ሰዎች ብዙ የማይናገሩትና የተሸከሙት የራሳቸው ብሽቀት ስላለባቸው ለተሻለውና ለሚበረቱበት ሕይወታቸው አድናቆት ስጥ።

8. አመስግን ለተደረገልህ ማንኛውም ቅንጣት ነገር አመስግን።

9. ያለስስት አድንቅ ሰዎችን በይፋ አድንቃቸው፣ መልካም ያልሆነ ነገራቸውን ግን በግል አውራቸው።

10. ክፉ አስተያየትህን ቆጥብ ያልሆነ ነገር ብታይ እንኳን አፍህ በበጎ ቃላት ይቀይረው። ወፍሮ ያየኸውን ሰው ኤጭ ተዝረጠረጥክ ከማለት ተቆጠብ።

11. ካልሆኑ ጥያቄዎች ታቀብ ሰዎች የሕክምና ቀጠሮ ሄደው መምጣታቸውን ነግረውህ ይሆናል። የውጤቱን
ምንነት ለማወቅ ግን በጥልቀት አትጠይቅ። በነገሩህ ልክ መልካሙን ተመኝላቸው። በቻልከው መጠን በመረጃና በጥቆማ አግዛቸው እንጂ ድንበር አትዝለል።

12. ስነ-ስርዓት ሰዎች ከስልካቸው ላይ ፎቶ እንድታይ ቢሰጡህ ከፈቀዱልህ ውጪ ሌላ ፎቶ ካላየሁ ብለህ ስልክ አትፈትሽ። ሁሉም ሰው ታልፎ እንዲገባበት የማይፈልገው የራሱ አጥር አለው።

13. ክብር ለሁሉም ከላይ ጫፍ ላለ የሥራ ኃላፊና ከታች ዝቅ ባለ ስራ ላይ ለሚገኘው ሰው እኩል ክብር ስጥ። እንደውም ከላይ ካለው ይልቅ ታች ላለው ሰው የሰጠኸው ክብር ብዙ እውቅና አለው። ለንቀትህ ግን የማንንም አድናቆትና ጭብጨባ አታገኝም።

14. ስልክህን አስቀምጥ ሰዎች በቀጥታ ላንተ እያወሩ ስልክህን የምትነካካ ከሆነ ቀሽምነት ነው። ከሰው
ሰራሹ ይልቅ ራሱ ሰው ትልቅ ዋጋ አለው።

15. አድብ ሰዎች ካልጠየቁህና ካልፈቀዱልህ በስተቀር በራሳቸው ሕይወትና ሥራ ጣልቃ አትግባባቸው።

16. ተቆጠብ ከረጅም ጊዜ በኋላ ያገኘሃቸውን ሰዎች አስጨናቂ ጥያቄ አትጠይቃቸው። ሰዎች ቆይታቸውን እንዲሁም ዕድሜና ደሞዛቸውን ጨምሮ የመናገርና ያለመናገር ብቸኛ ባለመብት ራሳቸው እንደሆኑ እወቅ።

17. መነጽርህን አውልቅ ከሰዎች ጋር በዓይንህ አውራ። ከማንም ጋር በመንገድ ላይ ተገናኝተህ ስታወራ መነጽርህን ከዓይንህ ማንሳት እንዳለብህ አስታውስ። ክብርም ነው!

18. አትሳሳት በድኅነት አስተሳሰብ ሆነህ ስለሀብታሞች ምንነትና ማንነት አታውራ፤ ልጅ ሳይኖርህ ስለልጅና ልጅ ስላላቸው ሰዎች ባሕሪ አትፍረድ።

19. ለስልክ መልዕክት ምላሽ መስጠት በስልክህ የጽሑፍ መልዕክት ሲደርስህ አንብበህ ዝም ማለት ነውር ነው።ተገቢውን ምላሽ በበጎነት ቃል መመለስን ልማድህ አድርገው።

20. ዕቃ መልስ የወሰድከውን ማንኛውም ቁስ ባለቤቱ ሳይጠይቅህ በፊት ቶሎ መልስ።

21. አማራጭ ሐሳቦች ሁሌም አሉ የያዝከውን ሐሳብ ሳትፈራ አውጣው። አንተም ሐሳብህም ትጎለብታላችሁ።
3.1K views15:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-24 09:34:18
ጊዜን መቆጠብ!

ሶስቱ ሊቆጠቡ የሚገባቸው ነገሮች (ክፍል አንድ)

ዛሬና በሚቀጥሉት ሁለት ማለዳዎች የምንመለከተው፣ ስኬታማ ሕይወት ለመኖር ወሳኝ የሆኑትን ሶስት መቆጠብ ያለብንን ነገሮች ነው፡፡ ዛሬ የምንመለከተው ጊዜን ስለመቆጠብ ነው፡፡

አንድ ነገር በበቂ ሁኔታ እንዲኖረን ካስፈለገ ወይ የዚያን ነገር የገቢ መጠን መጨመር ነው ወይም ደግሞ የወጪውን መጠን መቀነስ ነው፡፡ ስለ ጊዜ ስናነሳ ምንም ብናደርግ በቀን ውስጥ ያለንን የ24 ሰዓት ጊዜ መጨመር ስለማንችል፣ ያለን አመራጭ ያለንን ጊዜ በበቂ ሁኔታ መጠቀም ነው፡፡

ጊዜ ለመቆጠብ . . .

1. ከዋናው የሕይወታችን ዓላማ አንጻር በእቅድ መኖር፡፡
ጠዋት ተነስተን ሕይወት ያቀበለችንን ሁሉ እያስተናገድን በመኖር ጊዜን በአግባቡ መጠቀም አንችልም፡፡ በአመታት፣ በወራትና በሳምንታት ውስጥ ማከናውን የምንፈልጋቸውን ወሳኝ ነገሮች በማቀድ ቀኖቻችን በእነሱ መምራት አስፈላጊ ነው፡፡

2. ለአስፈላጊው ነገር ቅድሚያ መስጠት፡፡
በየቀኑ ሁለት ነገሮች ለምርጫ ይመጣሉ፣ የምንፈልገው ነገርና የሚያስፈልገን ነገር፡፡ በየቀኑ የምንፈልጋቸውን ነገሮች ቆየት አድርገን በመጀመሪያ አስፈላጊ ለሆኑ ነገሮች ቅድሚያ መስጠት ጥበብ ነው፡፡ ቀናችንን ስናቅድ ለአስፈላጊ ነገሮች ቅድሚያ እንስጥ፡፡

3. ጊዜ አባካኝ ነገሮችን ማራገፍ፡፡
ጊዜ አባካኝ ሰዎች ጋር ማሳለፍ፣ የማሕበራዊ ሚዲያ ሱስ እና የመሳሰሉት ሁኔታዎች ጊዜ አባካኝ ነገሮችስለሆኑ በብልሃትና በሚዛናዊነት ሊያዙ ይባቸዋል፡

ከላይ የተጠቀሱትን ነጥቦች በመለማመድ ጊዜያችሁን ስትቆጥቡ ይህ ልምምድ ከሌላቸው ሰዎች የላቀ ነገርን ማከናወን ትጀምራላችሁ፡፡

ጊዜ ይቆጠብ!

መልካም ቀን!
3.1K views06:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-23 16:05:05

2.3K views13:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-05 10:00:11
በጎ አስተሳሰብ

በጎ ሃሳቦች የስኬታማ ሕይወት ማስፈንጠሪያ ናቸው። ልበ ሙሉነትና ጉልበትን እየሰጡ በራስ የመተማመን ስሜትን ከፍ የማድረግ ሀይል አላቸው። በጎ አስተሳሰብ የማነቃቂያ ሃሳቦች ማለት አይደሉም።

ከማንነትህና ፣ ከስብዕናህ ጋር ተሰናስለውና በልክ ተሰፍተው ከሁለንተናዊ እንቅስቃሴዎችህና ተግባራቶችህ ጋር ተመጣጥነው በልኬት የሚመዘኑ ናቸው።

ይበልጥ በጎና ቀና አሳቢ በሆንክ ቁጥር ፣ በሁለንተናዊ ሕይወትህ ይበልጥ ደስተኛና ስኬታማ እንድትሆን ማስቻል አለባቸው።

አሉታዊ አስተሳሰቦችን ደግሞ በተቃራኒው መልኩ ልንረዳቸው እንችላለን።

ደካማ ፣ እርባናቢስና ፈሪ እንድትሆን በማድረግ በራስ መተማመንህ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሽቆለቆለ መጥቶ ዜሮ እንዲገባ ያደርጉሃል።

አሉታዊ ሃሳብን ባሰብክ ቁጥር በውስጥህ ያለውን የመለወጥና የቀናነት መንፈስ ከእጅህ እንዲወጣ ታደርጋለህ። በዚህም ተናዳጅና የተከላካይነት ስሜት ይጋባብሃል። በአሉታዊ አስተሳሰብ ውስጥህ መቃኘት ሲጀምር ፍርሀት፣ ተጠራጣሪነትና ሀዘን ውስጥህን እየተፈራረቁ መጎብኘት ይጀምራሉ።

ከጊዜ በኋላ ደግሞ ይህ አሉታዊ አስተሳሰብህ ሙሉ በሙሉ ሰውነትህን ይቆጣጠረውና ራስህን ከመጉዳት አልፎ ከሌሎች ጋር ያለህም የርስ በርስ ግንኙነት እስከማበላሸት ይደርሳል።

ከአሉታዊ አስተሳሰብ በተቃራኒው በጎ(አወንታዊ) አስተሳሰብ በአንጻሩ ለአእምሮ ጤናና ለተሻለ የስራና የመንፈስ አፈጻጸም በርን ይከፍታል።

ስትኖር ደስተኛና ጤናማ ሕይወት እንዲኖርህ ከፈለግክ በጎ አስተሳሰብህን እያዳበርክ አሉታዊ አስተሳሰብህን ተጠራጣሪ ስሜትህን ከአእምሮህ ጠርጎ እያወጣ መሄድ እንዳለብህ ይመከራል።

መልካም ቀን!
3.3K views07:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-19 08:38:27 የዘወትር ማስታወሻ

ውድ እኔ፦

ሰው ሁን። ስህተቱን አምኖ ለተሻለ ማንነቱ የሚጥር ትጉ ሰው ሁን። የራስህን ጉድፍ አጥርተህ ሳትጨርስ የሌላውን ሰው ለማፅዳት አትሞክር። ሌሎችን ለስህተትና ለጥፋት ከመወንጀልህና ጣት ከመቀሰርህ በፊት አንተ እራስህ ከተመሳሳይ ህፀፅ የነጻህ መሆንህን አስቀድመህ ጠይቅ። ከሁሉም በላይ ሰዎች በጎ፣ ጥሩ አሳቢና ቀና አይደሉም ብለህ ከመደምደምህ በፊት በሌሎች እንዲኖር የምትሻው መልካምነት ባንተ ውስጥ ስለመኖሩ ፈትሽ።

በህይወት ትልቁ ስጦታ ሌላውን ሰው መለወጥ ሳይሆን እራስን ለውጦ ለሌሎች የለውጥ ምክንያት ሆኖ መገኘት፤ ከትላንት ተምሮ ዛሬን የተሻለ ሆኖ መገኘት ብሎም በዛሬ ውስጥ የትላንት ማንነትንና የነገን ተስፋ አስታርቆ የመኖር ፅናት ነው።

ሰው ሁን፤ ዛሬን ከትላንት ተሽለህ ነገህን የምትቀርፅበት ብሩህ ቀን ይሁንልህ።

Https://t.me/keyOfsuccesse
2.9K views05:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-14 08:50:35 አስቸኳይ መልዕክት

እባካችሁ ይህንን መልዕክት ለቤተሰብዎና ጓደኛዎ ያስተላልፉ።

ሰሞኑን አንዳንድ ህብረተሰቦች ከማይታወቁ ግለሰቦች ስልክ ጥሪ እየደረሳቸው እንደሆነና ስልክ ቁጥሩም፡፣
Tel: +375602605281
Tel: +37127913091
Tel: +37178565072
Tel: +56322553736
Tel: +37052529259
Tel: +255901130460
ወይም ማንኛውም ቁጥር በ+371,+375,+381የሚጀምሩ እንደሆነ አሳውቀዋል።
እነዚህን ስልክ ቁጥር የሚጠቀሙት ግለሰቦች ሲደውሉ አንዴ ብቻ ከጠራ ብኋላ ይዘጉታል።እርስዎ መልሰው ሲደውሉ የርስዎን Contact List በ 3sec ውስጥ ወደ ራሳቸው ኮፒ በማድረግ እንዲሁ ሞባዬልዎ ላይ ስለ እርስዎ ባንክ ወይም ክሪዴት ካርድ መረጃ በአንዴ በመጥለፍ የማጭበርበር ስራ እየሰሩ ይገኛሉ።ከላይ በተጠቀሱት ስልክ ቁጥር ከተደወለሎት አይመልሱ ፡ወይም መልሰው አይደውሉ።እንዲሁም በማንኛውም ደዋይ #90 or #09 በመስመር እንዲነኩ ከተጠየቁ አይንኩ።ምክንያቱም በቀላሉ ሲማችሁን አክሰስ(በመጠቀም) በናንተ ስም የፈለጉት ወንጀል በመስራት እራሳቸውን ስለሚሸሽጉ ነው።
ይህንን መልዕክት ለቻላችሁ ሰው ፎርዋርድ በማረግ ህዝባችንን ከዚ መሰል ማጭበርበሮች እንታደግ።
ይሃን መልእክት ለ #10 ሰዉ share በማድረግ የሚወዷችዉን ሰዎች ይታደጉ

Https://t.me/keyOfsuccesse
5.9K viewsedited  05:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-30 11:57:36 አስብ !

ሁሌም ሩጫ ላይ ነህ ማለት እያተረፍክ ነው ማለት አይደለም ፤ አንዳንዴ ቆም ብሎ ራስን መጠየቅ መልካም ነው። እያገኘኸው ያለኸው ውጤት የምትፈልገው ነው ወይስ መስተካከል አለበት ?

መስተካከል አለበት ከሆነ በተለየ መንገድ መሥራት የምትችልበትን መንገድ እስቲ ፈልግ ቆም ብለህ አስብ !

መልካም ቀን!
2.6K views08:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-21 10:33:40
ስኬት በእምነት ነው የሚጀምረው። አንድን ነገር አሳካዋለው አደርገዋለው ብለህ ስታምን አይምሮህ የሚያሳካበትን መንገድ ማሳደድ ይጀምራል። በሳይንሱ "Neurological Pathways" ይባላል። ችግሩ አልችልም አይሆንም ካልክ ነው፤ የተሰጠህን አስገራሚ ማሽን ጨለማ ክፍል ውስጥ ቆለፍክበት!

አየህ ወዳጄ አሁን ባለህ እውቀት እንዴት እንደምትችል ማወቅ አይጠበቅብህም ግን እንደምትችል ብቻ ለአይምሮህ ደጋግመህ ንገረው አሳምነው፤ እሱ ተዓምረኛ ነው ከፈጣሪ ጋር ሁሉን እንድትችል መንገዱን ይመራሀል።

መልካም ቀን!

Https://t.me/keyOfsuccesse
2.8K viewsedited  07:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ