Get Mystery Box with random crypto!

ቢቢሲ አማርኛ ዜና

የቴሌግራም ቻናል አርማ kedirademmatat — ቢቢሲ አማርኛ ዜና
የቴሌግራም ቻናል አርማ kedirademmatat — ቢቢሲ አማርኛ ዜና
የሰርጥ አድራሻ: @kedirademmatat
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.29K
የሰርጥ መግለጫ

@Bbcamharicnews.com

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-07-17 00:05:07 የቴሌቪዥን የቀጥታ ስርጭት

ይዘት
አፍሪቃ
ደቡብ ሱዳንና ህዝቦቿ ከ11 ዓመት በኋላ
2ከ...ሰዓት በፊት
0 seconds of 0 seconds
 
09:31 ደቂቃ
15.07.2022
ደቡብ ሱዳንና ህዝቦቿ ከ11 ዓመት በኋላ
አዲሲቷን ሀገር መገንባትና ማልማት ህልም ሆኖ ቀረ። ለስልጣን የሚዋጉትን ሁለቱን ተፋላሚ ወገኖች አስታርቆ በሀገሪቱ ሰላም ለማውረድ የተደረጉት ዓለም አቀፍ እና አህጉር አቀፍ ጥረቶች ዳር ደረሱ ሲባል እንደገና ወደ ኋላ እየተመለሱ ሀገሪቱ አሁንም መረጋጋት እንደተሳናት ነው።ስቃዩ እየበረታበት የሄደው ህዝቡም በሁኔታው ተስፋ የቆረጠ ይመስላል።
ደቡብ ሱዳን፣ ከሱዳን ከተገነጠለች ባለፈው ሐምሌ 2 ቀን 2014 ዓ.ም. 11 ዓመት ደፈነች።  እስከ  ጎርጎሮሳዊው 2011 ዓም ድረስ ከሱዳን ነጻ ለመውጣት ሲታገሉ የነበሩት ደቡብ ሱዳናውያን ከሱዳን በመነጠላቸው ቢፈነድቁም ደስታው ግን አልዘለቀም። የተመኙት መረጋጋትና ብልጽግናም አላመጣም።ህዝቡ ነጻነቱን ሳያጣጥም ከሁለት ዓመት በኋላ የተነሳው የርስ በርስ ጦርነት፣ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩትን ለሞት ፣ሚሊዮኖችን ደግሞ ለስደት ዳረገ። አዲሲቷን ሀገር መገንባትና ማልማት  ህልም ሆኖ ቀረ። ለስልጣን የሚዋጉትን ሁለቱን  ተፋላሚ ወገኖች አስታርቆ በሀገሪቱ ሰላም ለማውረድ የተደረጉት ዓለም አቀፍ እና አህጉር አቀፍ ጥረቶች ዳር ደረሱ ሲባል እንደገና ወደ ኋላ እየተመለሱ ሀገሪቱ አሁንም መረጋጋት እንደተሳናት ነው። ስቃዩ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየበረታበት የሄደው ህዝቡም በሁኔታው ተስፋ የቆረጠ ይመስላል።ከመካከላቸው አንዱ ፒተር ካካማንቶ ነው። በሀገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል ይኖር የነበረው ካካማንቶ በጎርጎሮሳዊው 2013 የርስ በርሱ ጦርነት ሲጀመር ከዚያ ሸሽቶ ዋና ከተማይቱ ጁባ ገባ ። በጁባም በአንድ የተፈናቃዮች መጠለያ ሲኖር ዘንድሮ 9 ዓመት አስቆጥሯል። በሀገሪቱ ተስፋ መቁረጡን ይናገራል።
«ተስፋ የሌለ ነው የሚመስለው።ምክንያቱም በደቡብ ሱዳን የደኅንነት ዋስትና ጉዳይ ራስ ምታት ሆኗል። ሰዉ ሰላም ሰላም ሰላም ይላል። ጊዜውም እየሄደ ነው።እስካሁን ድረስ ጥሩ የሚባል ነገር አልሆነም። አሁን የኛ ትውልድ ሀገሪቱን ለቆ ሊወጣ ነው። እኛ አሁን መጪው ትውልድ እንዲመጣ ነው የምንፈልገው።ምንም ጥሩ ነገር የለም።ሰዎች በረሀብ እየተሰቃዩ ነው። በበሽታ በጦርነትም


ይሰቃያሉ። እኔ በግሌ ፍጹም ተስፋ ቆርጫለሁ። ነገሮች ይለወጣሉ ብዬ አላስብም። »
የ10 ልጆች እናት ጃና ኡርጌብ ደግሞ አሁን ምን እንደምደርግ አታውቅም ።ቤተሰቧ ምንም የለውም።
«የምንበላው የለንም ፤ አንዳንድ ጊዜ ከገበያ ባቄላ ገዝቼ ምግብ እሰራለሁ። ግን በየቀኑ አይደለም የማበስለው።የማበስለውም ለልጆቼ ነው። ከዚህ ቀደም ትምሕርት ቤት ይሄዱ ነበር። አሁን ግን ምንም ገንዘብ የለንም»
ተፈናቃዮቹ ከመንግሥት ምንም እርዳታ አያገኙም። ከዚያ ይልቅ ገንዘቡ በመጀመሪያ ባለሥልጣኖች ኪስ ነው የሚገባው።ደቡብ ሱዳን ሙስና እጅግ ከተንሰራፋቸው ሀገራት አንዷ ናት።  በሀገሪቱ አሁን የምግብ ጤና እና ትምሕርት ጉዳይ ትኩረት የሚሰጣቸው አይደሉም። በርካታ የነዳጅ ዘይት ሀብት ያላት ደቡብ ሱዳን መሬቷ ለም ነው። ማንጎ ፣ፓፓያ ፣አናናስና ኦቾሎኒ በብዛት የሚበቅልባት ሀገር ናት።ይሁንና በጦርነቱ ምክንያት መሬቷ ጦም አድሯል።

ደቡብ ሱዳን ከሱዳን ከተገነጠለች በኋላ አስተማማኝ የመንግሥት ስርዓት ለመመስረት ሞክራለች። ይሁንና በሀገሪቱ የተስፋፋው ሙስና ፣ የፖለቲካና አካባቢያዊ ግጭት መቀጠሉ የታለመው ስርዓት እውን እንዳይሆን ማሰናከሉ ይነገራል።በጎርጎሮሳዊው አቆጣጠር ታህሳስ 2013 ነበር በዲንካ ጎሳ አባሉ ፕሬዝዳንት ሳልቪ ኪር ታማኝ ኃይሎችና በኑየሩ ጎሳ በምክትል ፕሬዝዳንት ሪክ ማቻር ታማኞች መካከል ግጭት የተነሳው። ጎሳ ላይ ያተኮረው ግጭትም በፍጥነት በመላ ሀገሪቱ ተዳረሰ።በ10 ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሲገደሉና ሚሊዮኖች ሲፈናቀሉ ሰብዓዊው ቀውስ በረታ ።ከሁለት ዓመት በኋላ በጎርጎሮሳዊው ነሐሴ 2015 ዓ.ም. ኪርና ማቻር የሰላም ስምምነት ከተፈራረሙ በኋላ በሚያዚያ 2016  የአንድነት መንግሥት መሠረቱ።ይሁንና በዚያኑ ዓመት በሐምሌ ወር ጁባ ውስጥ የኪርና የማቻር ኃይሎች አዲስ ውጊያ ሲከፍቱ በቀደመው የርስ በርስ ጦርነት ያልተካፈሉ ታጣቂ ቡድኖች ውጊያው ተቀላቀሉ።የሰላሙ ጥረት እንደገና ተነቃቅቶም በመስከረም 2018 የሰላም ስምምነት ተፈረመ። ይህ ስምምነትም ውጊያው በአመዛኙ ያስቆመ ተብሏል። በዚህ ወቅትም መንግሥትና አብዛኛዎቹ ታጣቂ ተቃዋሚ ኃይሎች አንድ የተባባረ ብሔራዊ ጦር ለማቋቋም፣ የሽግግር መንግሥት በግንቦት 2019 ለመመስረትና በታኅሳስ 2022 ይካሂድ ለተባለው ምርጫ ለመዘጋጀት ተስማምተው ነበር። ይህ ሳይሆን ቀርቶ ምርጫው ለጎርጎሮሳዊው 2023 መጨረሻ ተገፍቶ በየካቲት 2020 ማቻር ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑበት የሽግግር መንግሥት ተመሰረተ።ይሁንና የሰላም ስምምነቱ በስልጣን ክፍፍል አለመግባባት ምክንያት እስካሁን ድረስ  በየጊዜው ከውዝግብና ጠብ አልተላቀቁም። ይህም ሀገሪቱ ነጻ ከወጣችበት ከዛሬ 11 ዓመት ወዲህ እጅግ አስከፊ የምግብ እጥረት ቀውስ ውስጥ ከቷቷል ። ከ11 ሚሊዮን ህዝቧ 7 ሚሊዮኑ እርዳታ ጠባቂ ነው። 

የአፍሪቃን የውጭ ንግድ አቅርቦት የማሰባጠር ጠቀሜታ  


የአፍሪቃ ሀገራት ከሸቀጦች የውጭ ንግድ ጥገኝነት እንዲላቀቁ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አሳሰበ።ድርጅቱ እንደሚለው ሀገራቱ በሸቀጦች የውጭ ንግድ ላይ ብቻ ከማተኮር የውጭ ገበያ አቅርቦታቸውን ቢያሰባጥሩ የኤኮኖሚ እደገታቸው ሊፋጠን ይችላል።የተመ የንግድና የልማት ጉባኤ በምህጻሩ አንክታድ በቅርቡ ባወጣው የ2022 ዓም የአፍሪቃ ኤኮኖሚ ልማት  ዘገባ መንግሥታት ከግብርና በተጨማሪ በቴክኖሎጂና በፋይናንስ ዘርፍ እንዲወርቱ ተማጽኗል። በዘገባው እንደተጠቀሰው ከ54ቱ የአፍሪቃ ሀገራት የ45 ቱ ኤኮኖሚ ግብርና ማዕድን እና ሌሎች የተፈጥሮ ሀብቶችን መሠረት ያደረገ ነው።ድርጅቱ እንዳለው ከአስርት ዓመታት በላይ ለሆነ ጊዜ ድርጅቱ ይህን ሲያሳስብ ቆይቷል። ሆኖም ተግባራዊ አለማድረጋቸውን ነው ያስታወቀው። ነዳጅ ዘይት፣ጋዝ ማዕድኖች ምግብ እና ጥሬ እቃዎችን ለውች ገበያ የሚያቀርቡት ሀገራቱ ገቢያቸው በእጅጉ ተለዋዋጭ ሆኗል።እንደ ድርጅቱ ዘገባ አንዳንድ የአፍሪቃ ሀገራት ግን  ለውጥ አድርገዋል።እነርሱም ትኩረታቸውን በትርንስፖ ርትና ቱሪዝም ላይ ያደረጉ ናቸው። በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂም ሆነ በፋይናንስ አገልግሎት መስኮች አፍሪቃ ለውጭ ገበያ የምታቀርበው ድርሻው 20 ከመቶ ብቻ ነው።ከመካከላቸው ሞሪሽየስ ተጠቃሽ መሆንዋን ፓውል አኪዎሚ የአንክታድ የአፍሪቃ ክፍል ሃላፊ ለዶቼቬለ ተናግረዋል። 
«የሞሪሽየስ የውጭ ንግድ አቅርቦት አሁን  የተሰባጠረ ነው። ከዚህ ቀደም ግን በልምድ ግብርናን የሸንኮራ አገዳ እና ሻይን መሠረት ያደረገ ነበር።አሁን ግን የባንክና የፋይናንስ አገልግሎቶችን


ከሚደግፉ የኮምፕዩተር ፕሮግራሞችና እና ሉሎች ቴክኖሎጂዎች ጋር አሰባጥረውታል። አሁን አነስተኛ እና መካከለኛ የንግድ ድርጅቶች ከሀገሪቱ አጠቃላይ ዓመታዊ የሀገር ውስጥ ገቢ 40 በመቶውን ይይዛሉ። ይህ የሀገሪቱን ኤኮኖሚ በማሰባጠር ረገድ ትልቅ እርምጃ ነው።»
 በህንድ ውቅያኖስ ላይ የምትገኘው ሞሪሽየስ የውጭ ንግድ አቅርቦትዋን ማሰባጠር የጀመረችው ካለፉት 20 ዓመታት ወዲህ ነው። የሸቀጦች ንግድ ጥገኛ የሆነችውን አፍሪቃን ከኤኮኖሚ ቀውስ ለመዳን ሌሎች የአፍሪቃ ሀገራትም ትኩረታቸውን  ወደ ቴክኖሎጂና ፋይንናስ አገልግሎት እንዲያዞሩ የሚመክሩት አኪዎሚ
346 viewsKedir Adem, 21:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 20:35:05
#ItsMyDam

አይቀሬው የታላቁ ህዳሴ ግድብ የሶስተኛ ዙር የውሃ ሙሌት እና የግብፆቹ ሚዲያዎች የፈጠራ ወሬ !

ሁሌ ጊዜም ሀገራችን የታላቁ ህዳሴውን ግድብ ባፋጠነች እና የውሃ ሙሌቱን በየዓመቱ ባከታተለች ቁጥር የግብፅ ሚዲያዎች እንቅልፍ ይነሳቸዋል።

በቅርቡ የሶስተኛው ሙሌት መጠናቀቅ አይቀሬ መሆኑን ሲያውቁ ከወዲህ ያልተረጋገጠ መረጃ ለህዝብ ማሰራጨቱን አጥብቀው ተያይዘውታል።

አመር አዲብ የተባለ የሚዲያ ሰው በአንድ ቻናል ላይ ቀርቦ " በኢትዮጵያ ኢንደስትሪ ብዙ እምነት የለንም በግድቡ ላይ መሰነጣጠቆች እንዳሉ እና አደጋዎች ሊከሰቱ እንደሚችሉ ይነገራል " ሲል ያልተረጋገጠ መረጃ ሲናገር ተደምጧል።

" የህዳሴውን ግድብ ጉዳይ አብዛኛው ሰው ረስቶታል። የህዳሴው ግድብ ሶስተኛው ሙሌት ሊጠናቀቅ ቀናት ቀርተዋል " ሲልም አክሏል።

የዚህን ሰው ንግግር ሚዲያዎች እየተቀባበሉት እያስጮኹ ነው ፤ በእርግጥ የግብፅ ጋዜጠኞች እና ሚዲያዎች ፣ ምሁራን ከዚህም አለፍ ያሉ ብዙ የፈጠራ ወሬዎችን ሲያስወሩ ዓመታትን ያለፉ በሚሆንም በግንባታው ላይ ያመጡት ለውጥ የለም።

አሁንም ሶስተኛው የታላቁ የህዳሴ ግድብ ሙሌት መጠናቀቅ አይቀሬ መሆኑን ሲያውቁ የሚዲያ ዘመቻውን ተያይዘውታል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
298 viewsKedir Adem, 17:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 20:35:05
የሴቶች 10 ሺህ ሜትር ፍፃሜ ውድድር ዛሬ ይካሄዳል!!

የሴቶች 10 ሺህ ሜትር ፍፃሜ ውድድር ዛሬ ምሽት 4 ሰዓት ከ20 ላይ ይካሄዳል፡፡ በአሜሪካ ኦሪገን እየተካሄደ በሚገኘው እና ሁለተኛ ቀኑን በያዘው 18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና÷ ኢትዮጵያ በሴቶች 10 ሺህ ሜትር የፍጻሜ ውድድር ታካሂዳለች፡፡

በፍጻሜ ውድድሩም አትሌት ቦስና ሙላቴ፣  አትሌት እጅጋየሁ ታየ እና አትሌት ለተሰንበት ግደይ እንደሚሳተፉ የወጣው መርሐ ግብር ያመላክታል፡፡

በሌላ በኩል ምሽት 5 ሰዓት ከ 5 ላይ በሚካሄድ የሴቶች 1 ሺህ 500 ሜትር የግማሽ ፍጻሜ ውድድር÷ አትሌት ጉዳፍ ፀጋዬ እና አትሌት ፍሬ ወይኒ ኃይሉ ይሳተፋሉ፡፡እንዲሁም ምሽት 2 ሰዓት ከ35 ላይ በሚካሄደው የሴቶች 3ሺህ ሜትር የመሰናክል ማጣሪያ÷ አትሌት ሲምቦ ዓለማየሁ፣ አትሌት መቅደስ አበበ እና አትሌት ወርቅውሃ ጌታቸው እንደሚሳተፉ የአትሌቲክስ ፌደሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

በሌላ መርሐ ግር ደግሞ ሌሊት 10 ሰዓት ከ30 ላይ የወንዶች የ1 ሺህ 500 ሜትር ማጣሪያ የሚካሄድ ሲሆን÷ አትሌት ሳሙኤል አባተ፣ አትሌት ሳሙኤል ተፈራ እና አትሌት ታደሰ ለሚ ይሳተፋሉ፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
265 viewsKedir Adem, 17:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 20:35:05
የ70 ዓመቱ አዛውንት ከቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ በሁለተኛ ዲግሪ ተመረቁ

የ70 ዓመቱ አዛውንት ዓሊ ሳፋ ከቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ በማርኬቲንግ ማኔጅመንት በሁለተኛ ዲግሪ ተመረቁ።

አሊ ሳፋ የዩኒቨርሲቲው የ9ኛ ዙር ተመራቂዎች ልዩ ተሸላሚ ሆነዋል።

“የእድሜዬ መግፋት ከትምህርት ፍላጎቴ አላስቀረኝም” ያሉት ዓሊ ስምንት ልጆችና አራት የልጅ ልጆች አያት መሆናቸውንም ተናግረዋል።

የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከ35 አመት በፊት እንዳገኙ ያስታወሱት አዛውንቱ ፤ ለትምህርት ባላቸው ፍቅር የተነሳ የዕድሜያቸው መግፋት ሳይገድባቸው በ70 ዓመታቸው ዛሬ የሁለተኛ ዲግሪያቸውን ለመቀበል መብቃታቸውን ገልጸዋል።

ልጆችን በማሳደግና በማስተማር ኃላፊነት የተነሳ ከሚወዱት ትምህርት ለዓመታት ርቀው ቢቆዩም ትምህርት ዕድሜ አይገድበውም እንዲሉ ሁኔታዎች በተመቻቹላቸው ጊዜ ለመማር ሳይሰንፉ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከተቀበሉ ከ35 ዓመታት በኋላ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ለመያዝ በቅተዋል። በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ በሙያቸው አገራቸውን ያገለገሉት አዛውንቱ አሊ በጡረታ ላይ ቢሆኑም ትምህርት ቤት ለመሄድ ያገዳቸው ነገር የለም።

በመሆኑም ቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ በመግባት ዕውቀት ገብይተው በማርኬቲንግ ማኔጅመት በሁለተኛ ዲግሪ መመረቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።“ትምህርት ለዚህች ዓለም ችግሮች መፍቻ ቁልፍ መሆኑን የሚናገሩት ዓሊ ሳፋ እውቀት እድሜ አይገደበውም” ብለዋል።በተለይ ልጆች እንዲማሩ ከመገፋፋት ጎን ለጎን ተምሮ አረአያ መሆን ትውልድ ለመቅረጽ ወሳኝ እንደሆነ በመግለጽ ምክራቸውን ለግሰዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
250 viewsKedir Adem, 17:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 20:35:05
በምሥራቅ ሸዋ ዞን በ129 የአሸባሪው ሸኔ አባላት ላይ እርምጃ ተወሰደ!

በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን በአራት ወረዳዎች ላይ በተካሄደ ሕግ የማስከበር ዘመቻ በ129 የአሸባሪው ሸኔ አባላት ላይ እርምጃ መወሰዱ ተገለጸ።

የፌዴራል ፖሊስ እና የኦሮሚያ ልዩ ኃይል በፀረ ሰላም ቡድኖች ላይ እያካሄዱት ባለው ዘመቻ እርምጃ ከተወሰደባቸው በተጨማሪ 17 የሽብር ቡድኑ አባላት በሰላም እጃቸውን መስጠታቸውን የዞኑን ኮሙዩኒኬሽንን ጠቅሶ ኤፍቢሲ ዘግቧል። በተጨማሪም 29 ክላሽንኮቭ ጠመንጃ፣ 10 ሽጉጥ ፣ 200 የብሬን ጥይት፣ 600 የክላሽንኮቭ ጥይት፣ 2 ቦምብ ፣ 56 ሞተር ሳይክል እና ሌሎች የጦር መሳሪያዎች መያዛቸው ተገልጿል።

@Addis_Reporte
@Addis_Reporter
238 viewsKedir Adem, 17:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 20:35:05
ሰበር ዜና

በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል አፍዴር ዞን ኤልከሬ ወረዳ የሚንቀሳቀሱ የአልሸባብ አሸባሪ ቡድኖች መሪ የነበረው ሼህ መሐመድ ሁሴን ኡስማን ተገደለ

የአልሸባብ አሸባሪ ቡድን በኢትዮጵያ የሽብር ጥቃት ለመሰንዘር ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸውን ግለሰቦች ከኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል በመመልመልና ወደ ሶማሊያ በመውሰድ ቡድኑ በሚቆጣጠራቸው አካባቢዎች በሚገኙ ማሠልጠኛ ጣቢያዎች ሥልጠና በመስጠት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚልክ በተለያዩ ጊዜያት የሚገኙ መረጃዎች ያመለክታሉ።

ከዚህ ጋር በተያያዘ ቡድኑ በኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል አፍዴር ዞን ኤልከሬ ወረዳ ታጣቂዎችን በማደራጀት እንደሚንቀሳቀስ በተገኘው መረጃ መሠረት ከሚያዝያ ወር/2014 ዓ.ም ጀምሮ በተጠቀሰው አካባቢ በተደረገ ተከታታይ ኦፕሬሽን ለሽብር ጥቃት ያሰማራቸው ታጣቂዎችና ከሶማሊያ ያስገቧቸው በርካታ የነፍስ ወከፍ እና የቡድን የጦር መሣሪያዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ይታወቃል።

ይሁን እንጂ በተከታታይ በተደረጉ ኦፕሬሽኖች ከላይ በተጠቀሰው አካባቢ ቡድኑን በበላይነት ሲመራና ሲያደራጅ የነበረው ሼህ መሐመድ ሁሴን ኡስማን በቁጥጥር ሥር ካለመዋሉም በተጨማሪ ሌሎች ቁጥራቸው እስከ ስድሣ (60) የሚደርስ የቡድኑን ታጣቂዎች በመያዝ ሲንቀሳቀስ እንደነበረ ይታወሳል። ነገር ግን ግለሰቡ ሶማሌ ክልል አፍዴር ዞን ኤልከሬ ወረዳ በደው ቀበሌ “ቡላ” በተባለ ተራራማ አካባቢ ከታጣቂዎቹ ጋር ሲንቀሳቀስ ሐምሌ 7/2014 ዓ.ም በሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስ አማካኝነት በተወሰደ ኦፕሬሽን መገደሉን ለመረጃዉ ቅርበት ያላቸዉ ታማኝ ምንጮች መረጃዉን በምስል አስደግፈዉ በመላክ አረጋግጠዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
230 viewsKedir Adem, 17:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 20:30:12 ደቡብ ሱዳንና ህዝቦቿ ከ11 ዓመት በኋላ

አዲሲቷን ሀገር መገንባትና ማልማት ህልም ሆኖ ቀረ። ለስልጣን የሚዋጉትን ሁለቱን ተፋላሚ ወገኖች አስታርቆ በሀገሪቱ ሰላም ለማውረድ የተደረጉት ዓለም አቀፍ እና አህጉር አቀፍ ጥረቶች ዳር ደረሱ ሲባል እንደገና ወደ ኋላ እየተመለሱ ሀገሪቱ አሁንም መረጋጋት እንደተሳናት ነው።ስቃዩ እየበረታበት የሄደው ህዝቡም በሁኔታው ተስፋ የቆረጠ ይመስላል።https://p.dw.com/p/4EDhl?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
@dwamharicbot
225 viewsKedir Adem, 17:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 20:30:12 የአድማጮች ማኅደር https://p.dw.com/p/4EEwP?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
@dwamharicbot
221 viewsKedir Adem, 17:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 20:30:12 የኦሮሞ አባገዳዎች ህብረት ሰብሳቢ ስለ ኦሮሚያው ግጭት

አባ ገዳ ጂሎ ማንኦ የአገር ሽማግሌ አልቀረ፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ሃዳ ሲንቄዎችም ብሌን ሴቶች ሰብስበን ሳር ይዘን ወጥተን ሁሉንም የሰላም አማራጮች ሞክረናል፡፡ ሲታረቁ ግን አላየንም፡፡ ምናልባት ወደ ፊት ያለቀ አልቆ ያሸነፈም አሸንፎ የቀረ እድለኛ ይኖር ይሆናል” ብለዋል፡፡ https://p.dw.com/p/4EEnU?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
@dwamharicbot
215 viewsKedir Adem, 17:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 20:30:12 የሐምሌ 9 ቀን 2014 ዓ/ም የዓለም ዜና በድምጽ
ርዕሶቹ
በደቡብ ክልል የጌዲኦ ዞን ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ‹‹ በዞኑ ከአደረጃጀት ጥያቄ ጋር በተያያዘ ለዛሬ ቅዳሜ ሊቀሰቀስ ታቅዶ ነበር ›› ያለውን ሁከት ማክሸፉን አስታወቀ ፡፡
ሱዳን ከኢትዮጵያ በምትዋሰንበት የብሉ ናይል ግዛት ባሳለፍነው ሳምንት በጎሳዎች መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት 31 ሰዎች መገደላቸውን የሀገሪቱ የደህንነት አገልግሎት ዛሬ አስታወቀ። በግዛቲቱ በቤርቲ እና ሃውሳ ጎሳዎች መካከል በተቀሰቀሰው በዚሁ ግጭት ከሞቱት በተጨማሪ 39 ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል።
የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ከግብጹ ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲ ሲ ጋር በታላቁ የህዳሴ ግድብ ፣ የምግብ ዋስትና እና በኃይል አቅርቦት ጎዳዮች ላይ መነጋገራቸውን የግብጽ ፕሬዚዳንታዊ ጽ/ቤት አስታወቀ።
ግብጽ በማሊ የምታደርገውን የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ከፊታችን የነሐሴ ወር አጋማሽ ጀምሮ ልታቋርጥ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ።
የእስራኤል ጦር ሃማስ ፈጸመው ላለው የሮኬት ጥቃት አጸፋ በጋዛ ሰርጥ ወታደራዊ ጥቃት መፈጸሙን አስታወቀ።
https://p.dw.com/p/4EEwK?maca=amh-RED-Telegram-dwcom
@dwamharicbot
217 viewsKedir Adem, 17:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ