Get Mystery Box with random crypto!

የቴሌቪዥን የቀጥታ ስርጭት ይዘት አፍሪቃ ደቡብ ሱዳንና ህዝቦቿ ከ11 ዓመት በኋላ 2ከ...ሰዓት | ቢቢሲ አማርኛ ዜና

የቴሌቪዥን የቀጥታ ስርጭት

ይዘት
አፍሪቃ
ደቡብ ሱዳንና ህዝቦቿ ከ11 ዓመት በኋላ
2ከ...ሰዓት በፊት
0 seconds of 0 seconds
 
09:31 ደቂቃ
15.07.2022
ደቡብ ሱዳንና ህዝቦቿ ከ11 ዓመት በኋላ
አዲሲቷን ሀገር መገንባትና ማልማት ህልም ሆኖ ቀረ። ለስልጣን የሚዋጉትን ሁለቱን ተፋላሚ ወገኖች አስታርቆ በሀገሪቱ ሰላም ለማውረድ የተደረጉት ዓለም አቀፍ እና አህጉር አቀፍ ጥረቶች ዳር ደረሱ ሲባል እንደገና ወደ ኋላ እየተመለሱ ሀገሪቱ አሁንም መረጋጋት እንደተሳናት ነው።ስቃዩ እየበረታበት የሄደው ህዝቡም በሁኔታው ተስፋ የቆረጠ ይመስላል።
ደቡብ ሱዳን፣ ከሱዳን ከተገነጠለች ባለፈው ሐምሌ 2 ቀን 2014 ዓ.ም. 11 ዓመት ደፈነች።  እስከ  ጎርጎሮሳዊው 2011 ዓም ድረስ ከሱዳን ነጻ ለመውጣት ሲታገሉ የነበሩት ደቡብ ሱዳናውያን ከሱዳን በመነጠላቸው ቢፈነድቁም ደስታው ግን አልዘለቀም። የተመኙት መረጋጋትና ብልጽግናም አላመጣም።ህዝቡ ነጻነቱን ሳያጣጥም ከሁለት ዓመት በኋላ የተነሳው የርስ በርስ ጦርነት፣ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩትን ለሞት ፣ሚሊዮኖችን ደግሞ ለስደት ዳረገ። አዲሲቷን ሀገር መገንባትና ማልማት  ህልም ሆኖ ቀረ። ለስልጣን የሚዋጉትን ሁለቱን  ተፋላሚ ወገኖች አስታርቆ በሀገሪቱ ሰላም ለማውረድ የተደረጉት ዓለም አቀፍ እና አህጉር አቀፍ ጥረቶች ዳር ደረሱ ሲባል እንደገና ወደ ኋላ እየተመለሱ ሀገሪቱ አሁንም መረጋጋት እንደተሳናት ነው። ስቃዩ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየበረታበት የሄደው ህዝቡም በሁኔታው ተስፋ የቆረጠ ይመስላል።ከመካከላቸው አንዱ ፒተር ካካማንቶ ነው። በሀገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል ይኖር የነበረው ካካማንቶ በጎርጎሮሳዊው 2013 የርስ በርሱ ጦርነት ሲጀመር ከዚያ ሸሽቶ ዋና ከተማይቱ ጁባ ገባ ። በጁባም በአንድ የተፈናቃዮች መጠለያ ሲኖር ዘንድሮ 9 ዓመት አስቆጥሯል። በሀገሪቱ ተስፋ መቁረጡን ይናገራል።
«ተስፋ የሌለ ነው የሚመስለው።ምክንያቱም በደቡብ ሱዳን የደኅንነት ዋስትና ጉዳይ ራስ ምታት ሆኗል። ሰዉ ሰላም ሰላም ሰላም ይላል። ጊዜውም እየሄደ ነው።እስካሁን ድረስ ጥሩ የሚባል ነገር አልሆነም። አሁን የኛ ትውልድ ሀገሪቱን ለቆ ሊወጣ ነው። እኛ አሁን መጪው ትውልድ እንዲመጣ ነው የምንፈልገው።ምንም ጥሩ ነገር የለም።ሰዎች በረሀብ እየተሰቃዩ ነው። በበሽታ በጦርነትም


ይሰቃያሉ። እኔ በግሌ ፍጹም ተስፋ ቆርጫለሁ። ነገሮች ይለወጣሉ ብዬ አላስብም። »
የ10 ልጆች እናት ጃና ኡርጌብ ደግሞ አሁን ምን እንደምደርግ አታውቅም ።ቤተሰቧ ምንም የለውም።
«የምንበላው የለንም ፤ አንዳንድ ጊዜ ከገበያ ባቄላ ገዝቼ ምግብ እሰራለሁ። ግን በየቀኑ አይደለም የማበስለው።የማበስለውም ለልጆቼ ነው። ከዚህ ቀደም ትምሕርት ቤት ይሄዱ ነበር። አሁን ግን ምንም ገንዘብ የለንም»
ተፈናቃዮቹ ከመንግሥት ምንም እርዳታ አያገኙም። ከዚያ ይልቅ ገንዘቡ በመጀመሪያ ባለሥልጣኖች ኪስ ነው የሚገባው።ደቡብ ሱዳን ሙስና እጅግ ከተንሰራፋቸው ሀገራት አንዷ ናት።  በሀገሪቱ አሁን የምግብ ጤና እና ትምሕርት ጉዳይ ትኩረት የሚሰጣቸው አይደሉም። በርካታ የነዳጅ ዘይት ሀብት ያላት ደቡብ ሱዳን መሬቷ ለም ነው። ማንጎ ፣ፓፓያ ፣አናናስና ኦቾሎኒ በብዛት የሚበቅልባት ሀገር ናት።ይሁንና በጦርነቱ ምክንያት መሬቷ ጦም አድሯል።

ደቡብ ሱዳን ከሱዳን ከተገነጠለች በኋላ አስተማማኝ የመንግሥት ስርዓት ለመመስረት ሞክራለች። ይሁንና በሀገሪቱ የተስፋፋው ሙስና ፣ የፖለቲካና አካባቢያዊ ግጭት መቀጠሉ የታለመው ስርዓት እውን እንዳይሆን ማሰናከሉ ይነገራል።በጎርጎሮሳዊው አቆጣጠር ታህሳስ 2013 ነበር በዲንካ ጎሳ አባሉ ፕሬዝዳንት ሳልቪ ኪር ታማኝ ኃይሎችና በኑየሩ ጎሳ በምክትል ፕሬዝዳንት ሪክ ማቻር ታማኞች መካከል ግጭት የተነሳው። ጎሳ ላይ ያተኮረው ግጭትም በፍጥነት በመላ ሀገሪቱ ተዳረሰ።በ10 ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሲገደሉና ሚሊዮኖች ሲፈናቀሉ ሰብዓዊው ቀውስ በረታ ።ከሁለት ዓመት በኋላ በጎርጎሮሳዊው ነሐሴ 2015 ዓ.ም. ኪርና ማቻር የሰላም ስምምነት ከተፈራረሙ በኋላ በሚያዚያ 2016  የአንድነት መንግሥት መሠረቱ።ይሁንና በዚያኑ ዓመት በሐምሌ ወር ጁባ ውስጥ የኪርና የማቻር ኃይሎች አዲስ ውጊያ ሲከፍቱ በቀደመው የርስ በርስ ጦርነት ያልተካፈሉ ታጣቂ ቡድኖች ውጊያው ተቀላቀሉ።የሰላሙ ጥረት እንደገና ተነቃቅቶም በመስከረም 2018 የሰላም ስምምነት ተፈረመ። ይህ ስምምነትም ውጊያው በአመዛኙ ያስቆመ ተብሏል። በዚህ ወቅትም መንግሥትና አብዛኛዎቹ ታጣቂ ተቃዋሚ ኃይሎች አንድ የተባባረ ብሔራዊ ጦር ለማቋቋም፣ የሽግግር መንግሥት በግንቦት 2019 ለመመስረትና በታኅሳስ 2022 ይካሂድ ለተባለው ምርጫ ለመዘጋጀት ተስማምተው ነበር። ይህ ሳይሆን ቀርቶ ምርጫው ለጎርጎሮሳዊው 2023 መጨረሻ ተገፍቶ በየካቲት 2020 ማቻር ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑበት የሽግግር መንግሥት ተመሰረተ።ይሁንና የሰላም ስምምነቱ በስልጣን ክፍፍል አለመግባባት ምክንያት እስካሁን ድረስ  በየጊዜው ከውዝግብና ጠብ አልተላቀቁም። ይህም ሀገሪቱ ነጻ ከወጣችበት ከዛሬ 11 ዓመት ወዲህ እጅግ አስከፊ የምግብ እጥረት ቀውስ ውስጥ ከቷቷል ። ከ11 ሚሊዮን ህዝቧ 7 ሚሊዮኑ እርዳታ ጠባቂ ነው። 

የአፍሪቃን የውጭ ንግድ አቅርቦት የማሰባጠር ጠቀሜታ  


የአፍሪቃ ሀገራት ከሸቀጦች የውጭ ንግድ ጥገኝነት እንዲላቀቁ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አሳሰበ።ድርጅቱ እንደሚለው ሀገራቱ በሸቀጦች የውጭ ንግድ ላይ ብቻ ከማተኮር የውጭ ገበያ አቅርቦታቸውን ቢያሰባጥሩ የኤኮኖሚ እደገታቸው ሊፋጠን ይችላል።የተመ የንግድና የልማት ጉባኤ በምህጻሩ አንክታድ በቅርቡ ባወጣው የ2022 ዓም የአፍሪቃ ኤኮኖሚ ልማት  ዘገባ መንግሥታት ከግብርና በተጨማሪ በቴክኖሎጂና በፋይናንስ ዘርፍ እንዲወርቱ ተማጽኗል። በዘገባው እንደተጠቀሰው ከ54ቱ የአፍሪቃ ሀገራት የ45 ቱ ኤኮኖሚ ግብርና ማዕድን እና ሌሎች የተፈጥሮ ሀብቶችን መሠረት ያደረገ ነው።ድርጅቱ እንዳለው ከአስርት ዓመታት በላይ ለሆነ ጊዜ ድርጅቱ ይህን ሲያሳስብ ቆይቷል። ሆኖም ተግባራዊ አለማድረጋቸውን ነው ያስታወቀው። ነዳጅ ዘይት፣ጋዝ ማዕድኖች ምግብ እና ጥሬ እቃዎችን ለውች ገበያ የሚያቀርቡት ሀገራቱ ገቢያቸው በእጅጉ ተለዋዋጭ ሆኗል።እንደ ድርጅቱ ዘገባ አንዳንድ የአፍሪቃ ሀገራት ግን  ለውጥ አድርገዋል።እነርሱም ትኩረታቸውን በትርንስፖ ርትና ቱሪዝም ላይ ያደረጉ ናቸው። በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂም ሆነ በፋይናንስ አገልግሎት መስኮች አፍሪቃ ለውጭ ገበያ የምታቀርበው ድርሻው 20 ከመቶ ብቻ ነው።ከመካከላቸው ሞሪሽየስ ተጠቃሽ መሆንዋን ፓውል አኪዎሚ የአንክታድ የአፍሪቃ ክፍል ሃላፊ ለዶቼቬለ ተናግረዋል። 
«የሞሪሽየስ የውጭ ንግድ አቅርቦት አሁን  የተሰባጠረ ነው። ከዚህ ቀደም ግን በልምድ ግብርናን የሸንኮራ አገዳ እና ሻይን መሠረት ያደረገ ነበር።አሁን ግን የባንክና የፋይናንስ አገልግሎቶችን


ከሚደግፉ የኮምፕዩተር ፕሮግራሞችና እና ሉሎች ቴክኖሎጂዎች ጋር አሰባጥረውታል። አሁን አነስተኛ እና መካከለኛ የንግድ ድርጅቶች ከሀገሪቱ አጠቃላይ ዓመታዊ የሀገር ውስጥ ገቢ 40 በመቶውን ይይዛሉ። ይህ የሀገሪቱን ኤኮኖሚ በማሰባጠር ረገድ ትልቅ እርምጃ ነው።»
 በህንድ ውቅያኖስ ላይ የምትገኘው ሞሪሽየስ የውጭ ንግድ አቅርቦትዋን ማሰባጠር የጀመረችው ካለፉት 20 ዓመታት ወዲህ ነው። የሸቀጦች ንግድ ጥገኛ የሆነችውን አፍሪቃን ከኤኮኖሚ ቀውስ ለመዳን ሌሎች የአፍሪቃ ሀገራትም ትኩረታቸውን  ወደ ቴክኖሎጂና ፋይንናስ አገልግሎት እንዲያዞሩ የሚመክሩት አኪዎሚ