Get Mystery Box with random crypto!

ቢቢሲ አማርኛ ዜና

የቴሌግራም ቻናል አርማ kedirademmatat — ቢቢሲ አማርኛ ዜና
የቴሌግራም ቻናል አርማ kedirademmatat — ቢቢሲ አማርኛ ዜና
የሰርጥ አድራሻ: @kedirademmatat
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.29K
የሰርጥ መግለጫ

@Bbcamharicnews.com

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-20 18:08:10
ካርቱም-በጎሳዎች ግጭት 105 ተገደሉ
በሱዳን ደቡባዊ ግዛት ብሉናይል፣ በመሬት ይገባኛል ውዝግብ የዛሬ ዘጠኝ ቀን በተነሳ የጎሳ ግጭት 105 ሰዎች መገደላቸውንና 291 መቁሰላቸውን የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። ሱዳንን ከኢትዮጵያና ከደቡብ ሱዳን ጋር በሚያዋስነው በዚሁ ግዛት ግጭቱ የተካሄደው በርታና ሀውሳ በተባሉ ጎሳዎች መካከል ነው። ከካርቱም 460 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከምትገኘው ከግዛቲቱ ዋና ከተማ አል ደማዚን የጤና ሚኒስትሩ በስልክ እንደተናገሩት በአካባቢው ጦር ሠራዊት ከተሰማራበት ካለፈው ቅዳሜ አንስቶ ግጭቱ ቀንሷል።የተመድ እንደሚለው በግጭቱ ምክንያት ከ17 ሺህ በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል። ከመካከላቸው 14 ሺዉ አል ደማዚን ውስጥ በሚገኙ ሦስት ትምሕርት ቤቶች ተጠልለዋል።የብሉ ናይሉ ግጭት የተቀሰቀሰው ሃውሳዎች የመሬት አጠቃቀምን በበላይነት የሚቆጣጠር የሲቪል አስተዳደር እንዲሆን ያቀረቡትን ጥያቄ በርታዎች ከተቃወሙ በኋላ ነው።አንድ የበርታ ከፍተኛ መሪ እንዳሉት ግን ግጭቱ የተነሳው ሃውሳዎች የመሬት ይዞታን ደንብ በመጣሳቸው ነው።
508 viewsKedir Adem, 15:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 18:08:09
የአዲስ አበባ ከንቲባ ያለመከሰስ መብታቸው ተነስቶ ለሕግ እንዲቀርቡ ሲል ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ዛሬ ጠየቀ። "የኢትዮጵያ ሕዝብ በገዥው ፓርቲ የሚፈጸሙበት የሰብዓዊ መብት ረገጣዎች፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ቀውሶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፉ በመሄድ ላይ ይገኛሉ" ሲል በመግለጫው የተናገረው ፓርቲው "የከንቲባ አዳነች አበቤ አስተዳደር ከተማዋንም ሆነ አገሪቷን ወደ ቀውስ በፍጥነት እና በጥልቀት እየገፋት ይገኛል" ብሏል።

ፓርቲው ሰሞኑን የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ለባለ እድለኞች ለመስጠት በወጣው የተጭበረበረ ዕጣ የከተማዋ ከንቲባ "በድርጊቱ መሪ ተዋናይ እንደነበሩ በርካታ መረጃዎች ተገኝቶባቸዋል" ብሏል በመግለጫው፡፡ "በዚህ አውድ፣ ከንቲባዋን ትቶ ሌሎች የአዲስ አበባ አስተዳዳር ባለሥልጣናት እና ሙያተኞች ላይ እርምጃ መወሰዱ የፍትሕ ሥርዓቱን ባዶነት እና አድሎኝነት አጋልጧል" የሚለው ባልደራስ « የከንቲባዋ ያለመከሰስ መብት ተነስቶ ለተነሱባቸው ጥያቄዎች የከንቲባዋ ያለመከሰስ መብት ተነስቶ ለሕግ እንዲቀርቡ፣ የኦሮሚያ ክልል ሕገ መንግሥት በአዲስ አበባ ከተማ ተግባራዊ እንዳይሆን እና የኦሮሚያ ክልል ባንዲራና መዝሙር በአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች እንዳይሰቀል እና እንዳይዘመር" ሲል ጠይቋል።
የከተማው ምክር ቤት አባል የሆኑት ዶክተር ሲሳይ መንግሥቴ ሰሞኑን በተከናወነው የምክር ቤቱ ጉባኤ ላይ "ትምህርት ቤቶች ላይ የኦሮሚያ ባንዲራ ይውለብለብ አይውለብለብ በሚል ችግር ፈጥሯል፣ መዝሙሩ ይዘመር አይዘመር በሥርዓት ነው መወሰን ያለበት" በሚል ላቀረቡት ጥያቄ ከንቲባ አዳነች አቤቤ "የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ለአዲስ አበባ በሚሆን መንገድ የአዲስ አበባ ተማሪዎች ኦሮሚኛን መማር የሚገባቸው በምን መልኩ ነው ለሚለው ካሪኩለም ቀርጿል። ኦሮምኛ መዘመራቸው ይቀጥላል ብለዋል።
443 viewsKedir Adem, 15:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 18:08:09
ዋሽንግተን የዩናይትድ ስቴትስና የአፍሪቃ መሪዎች ጉባኤ

ዩናይትድ ስቴትስ በመጪው ዓመት ከአፍሪቃ ሀገራት መሪዎች ጋር ጉባኤ ለማካሄድ ማቀዷን አስታወቀች።የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በታህሳስ ወር ሊካሄድ የታቀደው ይኽው ጉባኤ፣ዩናይትድ ስቴትስ አፍሪቃን ለመደገፍ ያላት ቁርጠኝነት ማሳያ ነው ብለዋል። ታህሳስ አጋማሽ ላይ ዋሽግተን ዉስጥ ይካሄዳል የተባለው ጉባኤ ጉባኤ ከምግብ ዋስትና አንስቶ እስከ የአየር ንብረት ለውጥ ድረስ ባሉት ፈታኝ ችግሮች ላይ እንደሚወያይ ባይደን ጠቁመዋል። የዩናይትድ ስቴትስና የአፍሪቃ ግንኙነት አስፈላጊነት፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚጋሯቸው፣ ቅድሚያ በሚሰጧቸው ጉዳዮች ላይ ትብብርን ማጠናከርም ጉባኤው አጽንኦት ከሚሰጣቸው ጉዳዮች ውስጥ መሆኑን ፕሬዝደንቱ አስታውቀዋል።የአሜሪካን ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሃሪስ ማራኬሽ ሞሮኮ ውስጥ በተካሄደው በዩናይትድ ስቴትስ እና አፍሪቃ የንግድ ጉባኤ ላይ ባሰሙት ንግግር ጉባኤው እንደሚካሄድ አንስተው ነበር። ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ የዋሽንግተን አስተዳደር ከፍተኛ ባለሥልጣን እንዳሉት በእቅዱ መሠረት 50 የአፍሪቃ ሀገራት መሪዎች በጉባኤው ላይ ይካፈላሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ባይደን የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ከሆኑ ወዲህ አፍሪቃ አልጎበኙም።የአሁኑ ባይደን ዲፕሎማሲያዊ ጥረት የምዕራቡን ዴሞክራሲ በማስተዋወቅ በአፍሪቃ ብዙ መዋዕለ ንዋይ ከወረተችው ከቻይና ጋር ለመስተካከል የሚደረግ ጥረት ተደርጎ ተወስዷል። ሆኖም ባለሥልጣኑ እንዳሉት የጉባኤው ትኩረት ይሄ አይደለም። «አፍሪቃውያን አጋሮቻችንን ከእኛና ከቻይና እንዲመርጡ አንጠይቃቸውም ሆኖም ዩናይትድ ስቴትስ የተሻለ ሞዴል ታቀርባለች» ብለዋል።
346 viewsKedir Adem, 15:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 18:08:09
በጋምቤላ ከተማ ተደንግጎ የነበረው ሰዓት እላፊ ተነሳ
በጋምቤላ ከተማ ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ሕገወጥ እንቅስቃሴን ለመቆጣጠር በሚል የተደነገገው ሰዓት እላፊ ተነሳ። የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ዛሬ እንዳስታወቀው በከተማው ከምሽቱ 2 ሰዓት እስከ ንጋቱ 11፡30 እንዲፀና የተደነገገው ሰዓት እላፊ ዛሬ ሙሉ በሙሉ ተነስቷል። በሰዓት እላፊው ገደብ መሠረት ከአምቡላንስና ከፀጥታ ኃይል ተሽከርካሪ በስተቀር ማንኛውም ተሽከርካሪና ሰዎች መንቀሳቀስ የሚችሉት ከንጋቱ 11፡30 እስከ ምሽቱ 2 ሰዓት ድረስ ነበር። የጋምቤላ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ኡገቱ አዲንግ ፣ከዚህ ቀደም ኦነግ ሸኔና ጋኽነግ በከፈቱት ጥቃት የከተማይቱ ሰላም መድፍረሱን አስታውሰው በክልሉ አንጻራዊ ያሉት ሰላም ከመጣ በኋላ ተቆርጦ የቀረ የጠላት ኃይል ሲሉ የጠቀሱት ላይ አሰሳ ለማድረግ የሰዓት እላፊ ገደብ መጣሉን ተናግረዋል።ይሁንና «አሁን በከተማይቱ ያለው የፀጥታ ኅይል በቂ በመሆኑ፣ በተለያዩ የልማት ስራዎች የሚሳተፉ ድርጅቶች እንቅስቃሴም በሰዓት እላፊው በመገደቡና የከተማይቱ የአምቡላንስ አገልግሎት በቂ ባለመሆኑ ገደቡ እንዲነሳ ተደርጓል ብለዋል። ክልሉ ሰላም ነው ያሉት ሃላፊው ያም ሆኖ ኅብረተሰቡ እንዲጠነቀቅ አሳስበዋል።
286 viewsKedir Adem, 15:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 18:08:09
ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር የሚደራደር ቡድን መሰየሙን በዚህ ሳምንት ያሳወቀው ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት)«ማናቸውም ንግግር በሰላም ጥረቶች ውስጥ ንቁ ተሳትፎ የነበራቸውን የኬንያውን ፕሬዝዳንት ኡኹሩ ኬንያታን ማካተት አለበት» ብሏል። የህወሓት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ «የድርድሩን ሂደት በሙሉ ለአፍሪቃ ኅብረት መስጠት ለኛ በጣም ሃላፊነት የጎደለው ነው የሚሆነው» ሲሉ ለፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ተናግረዋል። ሁለቱን ወገኖች በተናጠል ሲያነጋግሩ የነበሩት የአፍሪቃ ኅብረት ልዩ ልዑክ የቀድሞው የናይጀሪያ ፕሬዝዳንት ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ ለኢትዮጵያ መንግሥት ቅርበት አላቸው የሚለው ህወሓት ድርድሩ በኬንያታ አስተባባሪነት እንዲካሄድ እንደሚፈልግ ከዚህ ቀደምም አስታውቆ ነበር። የኢትዮጵያ ገዥ ፓርቲ ብልጽግና ግን ማናቸውም ድርድሮች በአፍሪቃ ኅብረት ብቻ ነው ሊመሩ የሚችሉት ብሏል። ከህወሓት ጋር ለሚደረገው ድርድር የመንግሥት ተደራዳሪ ኮሚቴ ሥራ መጀመሩን ባለፈው ሳምንት ተናግሯል።ለትግራዩ ጦርነት ሰላማዊ መፍትሄ ለመፈለግ የሚደረገው ጥረት እንዲሰምር ከሁለቱ ወገኖች ምን ይጠበቃል ?ሃሳባችሁን አካፍሉን ፤ ተወያዩበት
266 viewsKedir Adem, 15:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 18:06:28 የፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫ ኤጀንሲ በታሪኩ ከፍተኛ የተባለዉን ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ!

የፌደራል የሰነዶች ማረጋገጫ ምዝገባ ኤጀንሲ 95 ከመቶ የሚሆነውን የፋይናንስ ስርዓቱን በቴክኖሎጂ መደገፉን ተከትሎ በታሪክ ከፍተኛ የተባለውን ገቢ ማግኘቱን አስታውቋል፡፡በኢንተርኔት ባንኪንግ መክፈል ፣ ለገቢዎች ሚኒስቴር በኢታክስ አማካይነት ቫት ፣ ዊዝሆልዲንግ እንዲሁም ግብር ማሳወቅ ፣ በዳሪስ ሲስተም የገቢ ደረሰኝ እንዲቆረጥ ማድረግ እና የተለያዩ ክፍያዎችን በኢ-ፔይመንት በባንክ በኩል መክፈል መቻሉን ተከትሎ ኤጀንሲው በበጀት ዓመቱ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰብ መቻሉን በፌደራል የሰነዶች ማረጋገጫ ምዝገባ ኤጀንሲ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያው አቶ አብነት ሰለሞን ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡

ኤጀንሲው በ2014 በጀት አመት ከአንድ ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ ያስቻለው አሰራሩን በቴክኖሎጂ በማስደገፉ ነው ያሉት ባለሙያው ፤ ከዚህም ሌላ የሰራተኞች ትርፍ ሰአታቸውን ጨምሮ በሙሉ አቅማቸው እንዲሰሩ መደረጉ አስተዋጾ ነበረው ተብሏል፡፡ከእዚህ በተጨማሪ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ባንኮች ገብተው እንዲሰሩ መደረጉ እና የተሰበሰበ ገንዘብ በእለቱ ወደ ባንክ ገቢ መደረጉ ለአፈጻጸሙ መሳካት ጉልህ ሚና እንደነበረው አቶ አብነት ተናግረዋል፡፡

ተቋሙ በ2014 በጀት አመት ከአገልግሎት 650 ሚሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ አቅዶ ከአንድ ቢሊየን ብር በላይ በመሰብሰብ የእቅዱን 154.66 % ማሳካት እንደቻለ ተገልጿል፡፡በቀጣይም የገንዘብ አሰባሰቡን ስርአት ለማዘመን ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር እየተሰራ በመሆኑ በተያዘው ወር ውስጥ አገልግሎቱ ይጀመራል ተብሏል፡፡

[Bisrat FM]
@bbc_amharic1
254 viewsKedir Adem, 15:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 18:06:28
237 viewsKedir Adem, 15:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 18:06:28
አሜሪካ ለኢትዮጵያ ተጨማሪ የ55 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረገች

ድጋፉ በዓለም አቀፉ የአሜሪካ ተራድዖ ድርጅት በኩል መደረጉም ተገልጿል። የአሜሪካው ዓለምአቀፍ ተራድዖ ድርጅት USAID ተጨማሪው የገንዘብ ድጋፍ ኢትዮጵያ ወቅታዊውን የምግብ አቅርቦት ችግር ለመቋቋም እና ወደፊት ከምግብ ጋር የተያያዙ አደጋዎችን ለመከላከል እና ምላሽ ለመስጠት ተጨማሪ አቅም እንደሚገነባላት አስታውቋል።

የአሜሪካው ተራድዖ ድርጅት የገንዘብ ድጋፉን ከሁለት ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል በተፈጠረው ግጭት ምክንያት ለምግብ እና ውሃ አቅርቦት ችግር ለተጋለጡ አርሶ እና አርብቶ አደሮችን እንዲሁም ቀሪ የማኅበረሰብ ክፍሎች ለመደገፍ እንደሚያውለው አስታውቋል።ፈንዱ የተገኘው የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በፈረንጆቹ ሰኔ ወር መጨረሻ ላይ በጀርመን በቡድን 7 የመሪዎች ጉባዔ ላይ ቃል በገቡት መሠረት ነው።

@bbc_amharic1
249 viewsKedir Adem, 15:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 18:06:28
በትላንትናው እለት በደረሰ የትራፊክ አደጋ ስምንት ሰዎች ከፍተኛ የአካል ጉዳት ደረሰባቸዉ፡፡

ከአዲሱ ገበያ ወደ ፒያሳ በማቅናት ላይ የነበረ አይሱዙ የጭነት መኪና መንገድ በመሳቱ ምክንያት ነው አደጋው የደረሰው፡፡በአደጋው ምክንያትም ስምንት ሰዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰ ሲሆን አደጋ የደረሰባቸው ሰዎች ወደ አቤት ጠቅላላ ሆስፒታል ተወስደዋል፡፡

እንደዚሁም በአካባቢው የነበሩ አምስት መኪኖችም ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡
አደጋ ያደረሰው የጭነት መኪናው መንገድ ስቶ ስለነበረ በሁለት የንግድ ሱቆች ላይም የንብረት ጉዳት ማድረሱ ነው የተነገረው፡፡ዜናዉ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ያለዉ መረጃ ይህ ነዉ፡፡

Via Ethio FM
@bbc_amharic1
272 viewsKedir Adem, 15:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-17 00:05:07 ውጤታማ ለመሆን የሚያግዙ አሰራሮችንም ጠቁመዋል።
«የቴክኖሎጂውንና የፋይናኑስኑም መስክ ይበልጥ ለማንቀሳቀስ የሚረዱ ተጨማሪ መመሪያና ደንቦች ቢኖሩ ደግሞ ከዚህ የበለጠ ውጤታም ሊሆን ይችላል። ለአነስተኛና መካከለኛ የንግድ ድርጅቶች ተጨማሪ ገንዘብ ማቅረብ ከተቻለ ይህ የብዙ ሀገራትን የልማት እድገቱን ይቀይረዋል።ሸቀጦችን መሰረት ካደረገው ንግድ ይበልጥ ወደ ተሰባጠረው መሻገር ያስችላል።»
በዋጋ ንረት ምክንያት አንዳንድ የአፍሪቃ ሀገራት ከሸቀጦች የውጭ  ንግድ አቅርቦት በጣም ጥሩ ዋጋ ቢያገኙም በአንጻሩ ተጠቃሚዎች ላይ የነዳጅ ዘይት የጋዝ የምግብና የማዳበሪያ ዋጋ በጣም ጨምሯል። በሌላ በኩል መዳብን የመሳሰሉ ማዕድኖች ዋጋ ከከዚህ ቀደሙ አሁን  ቀንሷል። የነዳጅ ዘይት ዋጋም በመጠኑ መቀነስ ጀምሯል። ስለዚህ የውጭ ንግድ አቅርቦትን ማሰባጠር ለኤኮኖሚ እድገት አማራጭ የሌለው መሆኑን አንክታድ በጥብቅ ያሳስባል። 
 

ኂሩት መለሰ 

እሸቴ በቀለ 

ምላሽ
ተዛማጅ ዘገባዎች

12:02 ደቂቃ
አፍሪቃ | 07.08.2021
የሪየክ ማቻርና ወታደራዊ ክንፉ ውዝግብ
ተከታተሉን
ይዘት

ዜና

ኢትዮጵያ

አፍሪቃ

ዓለም

አውሮጳ/ጀርመን

ኤኮኖሚ

ሳይንስ እና ኅብረተሰብ

ጤና እና አካባቢ

ስፖርት

ባህል

ወጣቶች

የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝት

 
ራድዮ

 
2022 Deutsche Welle

 
ለዴስክቶፕ የተዘጋጀ
የግለሰቦች/ድርጅቶች ሰነድ ጥበቃ
የተደራሽነት መግለጫ
Legal notice
458 viewsKedir Adem, 21:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ