Get Mystery Box with random crypto!

በትላንትናው እለት በደረሰ የትራፊክ አደጋ ስምንት ሰዎች ከፍተኛ የአካል ጉዳት ደረሰባቸዉ፡፡ ከአ | ቢቢሲ አማርኛ ዜና

በትላንትናው እለት በደረሰ የትራፊክ አደጋ ስምንት ሰዎች ከፍተኛ የአካል ጉዳት ደረሰባቸዉ፡፡

ከአዲሱ ገበያ ወደ ፒያሳ በማቅናት ላይ የነበረ አይሱዙ የጭነት መኪና መንገድ በመሳቱ ምክንያት ነው አደጋው የደረሰው፡፡በአደጋው ምክንያትም ስምንት ሰዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰ ሲሆን አደጋ የደረሰባቸው ሰዎች ወደ አቤት ጠቅላላ ሆስፒታል ተወስደዋል፡፡

እንደዚሁም በአካባቢው የነበሩ አምስት መኪኖችም ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡
አደጋ ያደረሰው የጭነት መኪናው መንገድ ስቶ ስለነበረ በሁለት የንግድ ሱቆች ላይም የንብረት ጉዳት ማድረሱ ነው የተነገረው፡፡ዜናዉ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ያለዉ መረጃ ይህ ነዉ፡፡

Via Ethio FM
@bbc_amharic1