Get Mystery Box with random crypto!

የፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫ ኤጀንሲ በታሪኩ ከፍተኛ የተባለዉን ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ! የፌደራል | ቢቢሲ አማርኛ ዜና

የፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫ ኤጀንሲ በታሪኩ ከፍተኛ የተባለዉን ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ!

የፌደራል የሰነዶች ማረጋገጫ ምዝገባ ኤጀንሲ 95 ከመቶ የሚሆነውን የፋይናንስ ስርዓቱን በቴክኖሎጂ መደገፉን ተከትሎ በታሪክ ከፍተኛ የተባለውን ገቢ ማግኘቱን አስታውቋል፡፡በኢንተርኔት ባንኪንግ መክፈል ፣ ለገቢዎች ሚኒስቴር በኢታክስ አማካይነት ቫት ፣ ዊዝሆልዲንግ እንዲሁም ግብር ማሳወቅ ፣ በዳሪስ ሲስተም የገቢ ደረሰኝ እንዲቆረጥ ማድረግ እና የተለያዩ ክፍያዎችን በኢ-ፔይመንት በባንክ በኩል መክፈል መቻሉን ተከትሎ ኤጀንሲው በበጀት ዓመቱ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰብ መቻሉን በፌደራል የሰነዶች ማረጋገጫ ምዝገባ ኤጀንሲ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያው አቶ አብነት ሰለሞን ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡

ኤጀንሲው በ2014 በጀት አመት ከአንድ ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ ያስቻለው አሰራሩን በቴክኖሎጂ በማስደገፉ ነው ያሉት ባለሙያው ፤ ከዚህም ሌላ የሰራተኞች ትርፍ ሰአታቸውን ጨምሮ በሙሉ አቅማቸው እንዲሰሩ መደረጉ አስተዋጾ ነበረው ተብሏል፡፡ከእዚህ በተጨማሪ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ባንኮች ገብተው እንዲሰሩ መደረጉ እና የተሰበሰበ ገንዘብ በእለቱ ወደ ባንክ ገቢ መደረጉ ለአፈጻጸሙ መሳካት ጉልህ ሚና እንደነበረው አቶ አብነት ተናግረዋል፡፡

ተቋሙ በ2014 በጀት አመት ከአገልግሎት 650 ሚሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ አቅዶ ከአንድ ቢሊየን ብር በላይ በመሰብሰብ የእቅዱን 154.66 % ማሳካት እንደቻለ ተገልጿል፡፡በቀጣይም የገንዘብ አሰባሰቡን ስርአት ለማዘመን ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር እየተሰራ በመሆኑ በተያዘው ወር ውስጥ አገልግሎቱ ይጀመራል ተብሏል፡፡

[Bisrat FM]
@bbc_amharic1