Get Mystery Box with random crypto!

በምሥራቅ ሸዋ ዞን በ129 የአሸባሪው ሸኔ አባላት ላይ እርምጃ ተወሰደ! በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ | ቢቢሲ አማርኛ ዜና

በምሥራቅ ሸዋ ዞን በ129 የአሸባሪው ሸኔ አባላት ላይ እርምጃ ተወሰደ!

በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን በአራት ወረዳዎች ላይ በተካሄደ ሕግ የማስከበር ዘመቻ በ129 የአሸባሪው ሸኔ አባላት ላይ እርምጃ መወሰዱ ተገለጸ።

የፌዴራል ፖሊስ እና የኦሮሚያ ልዩ ኃይል በፀረ ሰላም ቡድኖች ላይ እያካሄዱት ባለው ዘመቻ እርምጃ ከተወሰደባቸው በተጨማሪ 17 የሽብር ቡድኑ አባላት በሰላም እጃቸውን መስጠታቸውን የዞኑን ኮሙዩኒኬሽንን ጠቅሶ ኤፍቢሲ ዘግቧል። በተጨማሪም 29 ክላሽንኮቭ ጠመንጃ፣ 10 ሽጉጥ ፣ 200 የብሬን ጥይት፣ 600 የክላሽንኮቭ ጥይት፣ 2 ቦምብ ፣ 56 ሞተር ሳይክል እና ሌሎች የጦር መሳሪያዎች መያዛቸው ተገልጿል።

@Addis_Reporte
@Addis_Reporter