Get Mystery Box with random crypto!

ሰበር ዜና በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል አፍዴር ዞን ኤልከሬ ወረዳ የሚንቀሳቀሱ የአልሸባብ አሸባሪ ቡ | ቢቢሲ አማርኛ ዜና

ሰበር ዜና

በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል አፍዴር ዞን ኤልከሬ ወረዳ የሚንቀሳቀሱ የአልሸባብ አሸባሪ ቡድኖች መሪ የነበረው ሼህ መሐመድ ሁሴን ኡስማን ተገደለ

የአልሸባብ አሸባሪ ቡድን በኢትዮጵያ የሽብር ጥቃት ለመሰንዘር ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸውን ግለሰቦች ከኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል በመመልመልና ወደ ሶማሊያ በመውሰድ ቡድኑ በሚቆጣጠራቸው አካባቢዎች በሚገኙ ማሠልጠኛ ጣቢያዎች ሥልጠና በመስጠት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚልክ በተለያዩ ጊዜያት የሚገኙ መረጃዎች ያመለክታሉ።

ከዚህ ጋር በተያያዘ ቡድኑ በኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል አፍዴር ዞን ኤልከሬ ወረዳ ታጣቂዎችን በማደራጀት እንደሚንቀሳቀስ በተገኘው መረጃ መሠረት ከሚያዝያ ወር/2014 ዓ.ም ጀምሮ በተጠቀሰው አካባቢ በተደረገ ተከታታይ ኦፕሬሽን ለሽብር ጥቃት ያሰማራቸው ታጣቂዎችና ከሶማሊያ ያስገቧቸው በርካታ የነፍስ ወከፍ እና የቡድን የጦር መሣሪያዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ይታወቃል።

ይሁን እንጂ በተከታታይ በተደረጉ ኦፕሬሽኖች ከላይ በተጠቀሰው አካባቢ ቡድኑን በበላይነት ሲመራና ሲያደራጅ የነበረው ሼህ መሐመድ ሁሴን ኡስማን በቁጥጥር ሥር ካለመዋሉም በተጨማሪ ሌሎች ቁጥራቸው እስከ ስድሣ (60) የሚደርስ የቡድኑን ታጣቂዎች በመያዝ ሲንቀሳቀስ እንደነበረ ይታወሳል። ነገር ግን ግለሰቡ ሶማሌ ክልል አፍዴር ዞን ኤልከሬ ወረዳ በደው ቀበሌ “ቡላ” በተባለ ተራራማ አካባቢ ከታጣቂዎቹ ጋር ሲንቀሳቀስ ሐምሌ 7/2014 ዓ.ም በሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስ አማካኝነት በተወሰደ ኦፕሬሽን መገደሉን ለመረጃዉ ቅርበት ያላቸዉ ታማኝ ምንጮች መረጃዉን በምስል አስደግፈዉ በመላክ አረጋግጠዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter