Get Mystery Box with random crypto!

ISLAM IS UNIVERSITY

የቴሌግራም ቻናል አርማ islamisuniverstiy_public_group — ISLAM IS UNIVERSITY I
የቴሌግራም ቻናል አርማ islamisuniverstiy_public_group — ISLAM IS UNIVERSITY
የሰርጥ አድራሻ: @islamisuniverstiy_public_group
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 19.00K
የሰርጥ መግለጫ

⭐️ሰው የሚገነዘብ አእምሮና የሚያፈቅር ልቦና ባለቤት ነው።እነዚህ ሁለቱ ካልተመጣጠኑ ስብእናው አደጋ ውስጥ ነው።የሚያገናዝበው አዕምሮው፣የሚያፈቅረው ልቡ፣የሚንቀሳቀሰው አካሉናወደ ሰማይ የሚወነጨፈው መንፈሱ በውህደት ካልተንቀሳቀሱ ሰውየው ላይ ችግር አለ ማለት ነው
📨የፍቅር እና የጥላቻ ስሜቱ፣የፍላጎት እናየፍርሃት መንፈሱ በአዕምሮ ብስለት ካልተገራ አስቸጋሪ ነው
አስተያየት👇
T.me/Aisuu_bot

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 13

2023-03-14 23:17:49 "ከዬት እንጀምር!"

አሰላሙአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ!..
ብዙ ግዜ መለወጥን እናሰላስል ይሆናል,ነገር ግን አንለወጥም..ማለቴ በዉስጣችን የሆን ሰው በአዕምሯችን እንስላለን።ምን አይነት ሰው መሰላችሁ..አብዝቶ ኢባዳ የሚያደርግ፤ አብዝቶ ቁርአን የሚቀራ፣ አብዝቶ ሱና ሶላቶችን የሚሰግድ እናም ፈርድ ሶላቶችን የሚከታተል፤ ከዚያ በዱንያ ህይወቱ የተረጋጋ እና ሰላም የሆነ ሰዉ ..እያለ ይቀጥላል ሀሳባችን! ...ግን አሁን እኛ ለምን አልሆንም!? ..ይሄንን ጥያቄ ከመመለሳችን በፊት ግን አንድን ሀዲስ እንጥቀስ! ወደ ነብዩ ሰ.ዐ.ወ ዘመን ልመልሳችሁ።በአንድ ቀን አንድ ሰው መጣና ወደ ረሱል ሰ.ዐ.ወ እንዲህ አላቸው:-(አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! የኢስላም ትዕዛዛቶች በዙብኝ አንድ ነገር ንገሩኝ ሌላን ሰው የማልጠይቅበት የሆን ነገር!) አላቸው። ረሱል ሰ.ዐ.ወ እንዲህ አሉት፦[በአላህ አምኛለሁ በልና ከዚያም ቀጥ በል!] አሉት። አሁን ወደራሳችን እንመለስ ልክ እንደዚህ ሰው እኛም የኢስላም ድንጋጌዎች በዝተውብን ይሆናል። በአዕምሯችን ሌላን ሰው አስቀምጠን በዉጩ አለም ግን በሌላ ሰው ተሰርተናል። ነገሩ ምን መሰላችሁ ..ሁሉም ነገር ከአዕምሮ ስለሚመነጭ ነው። አዕምሯችን ያመነበትን ነገር ብቻ ነው በዉጩ አለም የሚያሳየን ለዚህም ነው ረሱል ሰ.ዐ.ወ ለዚህ ሰውዬ አምኛለሁ በል ያሉት! እኛም በመደጋገም"አመንቱ ቢላህ!" እንበል። ከዚያም በዉስጣችን የምናስበውን ሰው ለመሆን አንድ መስፈርት ብቻ ማሟላት ነው።እሱም ቀጥ ማለት ነው። ቀጥ ማለት በኛ አረዳድ መወሰን ማለት ነው። ለመወሰን ደግሞ ከአንድ ነገር ብቻ ሲቀር የሚጎልብን ነገር የለም የእውነት በውስጣችን የምናስበውን ሰው ለመሆን! እሱንም በምላሳችን አምነናል በማለት ጀምረነዋል።..ጀዛኩሙሏህ ኸይረን!

t.me/@mind_islam
tiktok.com/@islamic_mindset1
Youtube.com/@islamic_mindset1
instagram.com/@islamic_mindset_official
82 views20:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-08 06:26:19 Page ➌
የሙስሊም ተቋም መጅሊስ ተስተካክሏል ካልን እንደዚህ የኡማዉ አንገብጋቢ ጉዳይ ፈልፍለዉ አዉጥተዉ የተቀናጀ ስራ ቢሰሩ ለዚህ ዘላቂ መፍትሄ ማምጣት ይችሉ ነበር...መጅሊሱ ከበፊቱ የተሻለ ስራ እንዲሰሩ ይሄንን ብታሳዉቋቸዉ ጥሩ ነዉ ባይ ነኝ



☞ አንዲት ደሴ የማቃት Hiv ያለባት የተሰቃየችዉን ስቃይ ሙሉ በሙሉ አቃለሁ በአካል ትነግረኝ ነበር ግን አልሀምዱሊላህ አዲስ አበባ እንደሷ ኬዝ ያለባት አግብታ የሶስት ልጅ እናት ሁናለች
አሁን ዘመኑ ተሻሽሏል የሚወለዱት ልጆች Hiv አይኖርባቸዉም በሀኪም ክትትል ስለሚወልዱ ..የእሷን ታሪክ ፅፎ ማቅረብ ይቻል ነበር ግን ጊዜ የለም ፅፎ ማዘጋጃ...,በጣም አሳዛኝ አስተማሪ ነዉ እኔን ትነግረኝ ነበር የሰፈሬ ልጅ አብሮ አደጌ ነበረች አብረን ስለአደግን የሚገጥማትን ትነግረኝ ነበር የአሁን ወንዶች መቼም ግማሹ ለትዳር ግማሹ ለስሜት ስጠይቃት የምታሳልፍበት ጥበብ የተለየ ነበር ግን በጣም ተሰቃይታ ነበር ግን ጀሊሉ ጋር የነበራት ቁርኝት የተለየ ነበርና አዲስ አበባ አግብታ ጥሩ ኑሮ እየኖረች ነዉ አልሀምዱላላህ እሷን ያገናኛት አዲስ አበባ የሚኖር ይሄን ኬዝ የሚያቅ አጎቷ ነዉ

Please የትችት ብቻ ሳይሆን የመፍትሄም ሀሳብ አፍላቂ እንሁን ..በፊት ፁሁፍ በማዘጋጅበት ጊዜ ከአቅም በላይ የሆነ  በጣጣጣም ትችት አስተናግድ ነበር ሰዉ የሚሰራን አያስተናግድም
የአሁን ዘመን ትዉልድ የኢንሻ አላህና የአላሁ አክበር ትዉልድ ነዉ....ለዲነል ኢስላም በቻልከዉ ስራ ሲሉት ኢንሻ አላህ ..ከዛ በጀመአ ወይ በመስጊድ ተሰብስቦ የሆነ ነገር ተሰራ ሲባል ተክብር አሏሁ አክበር ብሎ የሚሄድ እንጂ የሚሰራ 0.001% ነዉ ...የሚሰራን የሚተች ደግሞ 99.9% ነዉ፡፡
በፊት አስታዉሳለሁ ታሪክ ሳዘጋጅ ብዙ ቁርአን ሀፊዞች የአንተን ታሪክ ስናነብ ቁርአኑ እየጠፋን ነዉ እያሉኝ በጣም ግራ ገብቶኝ ነበር  እንዴት ቁርአኑ እስከምጥፋት ደረሱ?? ብየ..የአሁን ዘመን ሰዉ ሽንፈቱን የበታችነቱን የኔ
ጥፋት ነዉ ብሎ አያስብም በሰዉ ላይ መለጠፍ ይወዳል እናም የመፍትሄ ሀሳብ እንጂ ሽንፈትን ወደ ሰዉ በማላበክ ጥገኛ ባንሆን መልካም ነዉ...

አሁንም መፍትሄ አመንጭ እንሁን  ይሄ የHiv ኬዝ ከባድ ኬዝ ነዉ በኢንሻ አላህ የሚታለፍ አይደለም ብዙዎች ሀይማኖታቸዉን እየቀሩ ነዉ.. እንቅፋት ሳንሆን በዚህኳ የመፍትሄ ሀሳብ እናመንጭ

እናንተ Hiv ቢኖርባችሁ ትዳር ብትፈልጉ ምን ታደርጋላችሁ?? አስተያየታችሁን በዚህ bot ጀባ በሉን
T.me/Aisuu_bot  T.me/Aisuu_bot
T.me/Aisuu_bot  T.me/Aisuu_bot

አስተያየት ስትሰጡ ለምን ፁሁፍ አታዘጋጅም --ጠፍተሀል -- ቻናሉ ሰዉ እየቀነሰ ነዉ --ወደ ሚዲያ መቼ ነዉ የምትመለሰዉ ምናምን እንቶ ፈንቶ የሆነ አስተያየት አትፃፉ አልቀበለም..ተወስኗል ወደ ሚዲያም አልመለስም ታሪክም 100% ሁኜ ልንገራችሁ አላዘጋጅም የራሴ የሆነ እኔዉ ብቻ የማቀዉ አሳማኝ ምክንያት አለኝ ...አስተያየት የምትፅፉት ዛሬ ላይ በአነሳሁት ስለ Hiv ኬዝ ላይ ብቻና ብቻ ነዉ፡፡

ስሙኝ ወገን እኛም ቢሆን ተመርምረን እራሳችንን ተመርምረን ብናቅ ጥሩ ነዉ..ቆየትም ቢል ተመርምረን የምናቅ ይኖራል ያልተመረመርንም ይኖራል
አይታወቅም የአላህ ነገር በአመት በሁለት አመት ልዩነት ምን እንደሚፈጠር አናቅም ...ይሄኔ ራስን አዉቆ የህይወት ግብ መቅረፅ ያስፈልጋል በተለይ በትዳር ዙሪያ ላይ

   አሁን አስቸኳይ ጉዳይ ገጥሞናል ስለዚህ Hiv ኬዝ ብቻ እናዉራ ሀሳብ አስተያየታችሁን በዚህ bot ይላኩልኝ ቀጥታ ለኔ ይደርሰኛል
እኔም ይሄን ሀሳብ ላመጣዉ ልጅ እና በሀሳብ እኔን ከሚጋሩ ቤተሰቦች የላካችሁትን አስተያየት እልከዉና ተወያይተን ሀሳብ ላይ  እንደርሳለን

በፊት ትዳር አገናኝም የምትሉም ነበራችሁ አደራ እኔ ማንንም አሁን አምኜ አግባዉ አግቢ ብየ ሀላፊነት አልወስም...እኔ  የምላችሁ ሰዉ የሚወዱትን የሚያፈቅሩትን አያገባም አርባ አራት ነጥብ ለምን አላህ ዱንያ የደስታ ምንጭ አይደለችም አላህ የትንኝ ክንፍ ያህል ቦታ የላትም ብሎ ነግሮን ከዱንያ ደስታን አጋኛለሁ ማለት ራስን ማሞኘት ነዉ፡፡ የሚወዳዱ የሚፋቀሩ  አይጋቡም ፡፡አፍቃሪ ማለት ከመጥፎ እድሉ ዉስጥ ደስታን የሚፈልግ ሰዉ ነዉ፡፡....ማፍቀር አንዱን ትዳርን ከሚከለክሉ ነገሮች ናቸዉ ..አጭተህ የሌላ ሁነህ እንኳ ፍቅሩን ልረሳዉ አችልም ልብህ ሌላ ቦታ ስሜትህ አገባሀት ጋር ሁኖ ልትቸገር ትችላለህ፡፡ አንዳንዴ ልቤን ከአሁን ቡሀላ አልሰጥም የሚሉ አሉ ልብ አንዴ በፍቅር ከተለያየዘ ያ ልብ እንዴት ተብሎ ነዉ ጡሀራ ሁኖ ለሌላ የሚሰጠዉ???
እናም አሁን የፍቅር ዝባዝንኬ አቁሞ ቀጥታ ማግባት ፍቅሩ ከዛ ቡሀላ ይመጣል ፡፡ በፍቅር ተይዘህ ተይዘሽ ያ ንፁህ ልብ ትዳርን ሊፈራ ይችላል የሚሻለዉ አግብቶ አብሮ ሁኖ የትዳር አጋርን መድሀኒት የሚወለዱ ልጆችን ያ የተጎዳን ልብ በልጆች በትዳር አጋር ፍቅር ማከም ብቻ ነዉ፡፡ ማወቅ ያለባችሁ አሁን ትዳር ሲያዝ ሴቶም ወንዱም ያሳለፈዉ ያልተሳካ የፍቅር ጉዞ ይኖረዋል ...ያለፈዉን ለወደፊቱ ችግር እንዳያመጣ አርጎ ዘግቶ
ትዳርን እርስ በርስ በመቀናጀት ህክምና ማድረግ ነዉ፡፡ ዘመኑ ገና 4 -8 ክፍል ያሉ ሴት ተማሪዎች ስለፍቅር በሚያወሩበት ዘመን ወደ ትዳር ወሬ ስጀምር ከአሁን በፊት ፍቅረኛ ነበረሽ ወይ እያልክ አጠይቅ፡፡ የሚሻለዉ ያለፈዉ አልፏል ስለወደፊቱ እናዉራ ብለህ አሁን ላይ የጠፋዉ እንደ ወንድ የሆነ ወንድ እንጂ ተራ ወንድ ነፍ አለ ሀቢቢ ስለሆነም ትዳር አገናኘኝ በፊት ጀምሩ የምትሉ ይሄ ጉዳይ እንዳይነሳ

   ወደ ላይ የተወረወረ ሁሉ ተመልሶ መምጣቱ እንደማይቀር ሁሉ በሰዉ ልጅ የህይወት ሂደትም ዉስጥ መሄድና መመለስ ያለ ነገር ነዉ..ወደ ሰማይ የወረወርከዉ ዲንጋይ ተመልሶ መጥቶ ከምድር ላይ በማረፉ መጨረሻዉ ነዉ ብለህ አትሰብ ብትፈልግ ዳግም አንስተህ ልትወረዉረዉ የምትችለዉ ነገር ነዉና ወደ ላይ መዉጫዉ ሆነ ወደ ታች መዉረጃዉ መንገድ አንድ ነዉ
እናም ህይወት ቋሚ አይደለችም ፍቅር ቋሚ አይደለም ሄድ መለስ ነዉ የሚለዉ እናም ህይወትህን ትዳርህን ማስተካክል የምችለዉ አንተ በእጂህ እንጂ በእድል በቁዘማና በማይለቅ ትዝታ አይደለም፡፡የሞተን ፍቅር ማቀፍ የዛሬን የነገን ህይወት ማበላሸት ነዉ
እናም ትዳር የአንቺ ወይ የእሱ ከዛ አንድ ላይ ስትሆኑ የእናንተ የእጅ ስራ ዉጤት እንጂ አንዴ ሳይሳካ ሲቀር የመጨረሻ ነዉ ብለን አንሰብ ፈጣሪ የተሻለ አለዉና

>>>>ግን Hiv ያለባችሁ የእናንተን ኬዝ ስራየ ብየ እስከመጨረሻዉ ድረስ በስልክ በtg የአቅሜን ከአቅሜም ለመስራት ወስኛለሁ ሌሎችም Hiv ያለባቸዉ ታማኝ  group ያላቸዉ ዲነኞች አንድ ወንድሜ እና እህቴ ጋር ለመስራት ስለወሰንኩ በአላህ ፍቃድ በቻልነዉ አቅም እንሰራለን
አደራ በአላህ ስም ይዣችሆለሁ አንብባችሁ እንዳታልፉ አስተያየት ስጡ አደራ ይሄ ሀሳብ ልፓስተዉ ስል በአገራችን ጉዳይ Data ሲቋረጥ ተዉኩት ሙሉ በሙሉ ሰዉም ባይገባ በSafaricom እና በpispon
እየተጠቀመ ስለሆነ ነዉ የፓሰትኩት

እናም አስተያየት ለመስጠት
አስተያየት ለመስጠት
T.me/Aisuu_bot  T.me/Aisuu_bot
T.me/Aisuu_bot  T.me/Aisuu_bot
393 viewsedited  03:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-08 06:26:03 Page ➋
አንዷ ከተማዉ ለጊዜዉ ይቆይ እዚህ ቻናል ልትኖር ስለምትችል  Hiv አለባት ቤተሰብም Hiv እንዳለባት ያቃሉ ትዳር በጣም በብዛት ይመጣል ትምህርት እየተማረች ነዉ ለሚመጣዉ አመት ትመረቃለች..ትዳር ይመጣል ሁሌ አልፈልግም እያለች ትመልሳለች ..ስትነግረኝ አልቅሳ ነዉ የነገረችኝ
ማግባት አልፈልግም እያልኩ እየመለስኩ ነዉ ግን በቃ በጣም ተቸገርኩ...ወንዶች ሲቀርቡኝ እየሸሸሁ ነዉ
በቃ እንጃ ህይወት ከብዶኛል ብላ ነግራኛለች ብሎ አጫወተኝ ..ሚስጥር ስለተደበቀ ነው የዚች ልጅ ሀገር የት እንደሆነ እኔ አቃለሁ በፁሁፍ ሀገሯን መግለፅ ስላልፈለኩ ነው

የሌላ ታሪክ ደግሞ ልንገራችሁ  በልጅነቷ አባት እናቷ በዚሁ ኬዝ ሙተዉ እሷ ቅርብ ቤተሰብ ጋር እየኖረች ነዉ እናም
በቃ ህይወት ፈተና ነዉ የሆነባት ለምን ትዳር እንደመጣ ማግባት አይቻልምና ብላ ይሄዉ ቀን ማታ እያለቀሰች ነዉ እንደዉም ህይወት መረረኝ ጀሊሉ ለኔ ምነዉ ሞት በላከልኝ እስከምትል ድረስ ...የዚችንም ልጅ ሀገር አቀዋለሁ ሚስጥር ለመደበቅ ነው

እናም አሚር ሰይድ እባክህ አንተ እንደተዋቂነትህ የተወሰነ መላ በል...በአንተ ጥረት Hiv ያለባቸዉ ተገናኝተዉ ቢጋቡ አንተ ከአላህ የምታገኘዉ አጅርና የተጋቡትን ሰዎች ደስታ እሰብና አንተ እንደምንም መፍትሄ ስጥ በተለይ ወንድ በተለያየ ስራም ቢዚ ይሆናል ስንት በሆዳቸዉ አፍነው የሚኖሩ ሴቶች አሉ እኔ ብዙ የማቃቸዉ  አለኝ ይሄን ሀሳብ ያመጣዉ ልጅ


እናም ይሄን ፁሁፍ ያነበባችሁ ሁሉ ለኔ ከባድ አማና
ተጥሎብኛል እኔም ለአላህ ብላችሁ ያነበባችሁ ሁሉ አማና አማና አስተያየት ስጡ ለምን ከእናንተ መሀል የትኛዉ የተሻለ ሀሳብ እንደሆነ አይታወቅምና እናም
በተጨማሪም አስተያየት ለመስጠት በዚህ bot ይላኩልኝ

T.me/Aisuu_bot  T.me/Aisuu_bot
T.me/Aisuu_bot  T.me/Aisuu_bot

ግን እኔ በራሴ አንድ ሀሳብ አለኝ
ይሄ ጉዳይ ተደፋፍኖ እንዳያልፍ ማግባት የምትፈልጉ HIV positive የሆናችሁ ይሄ ያማከረኝ ልጅ የHiv positive የሆኑ ብቻ group አለዉ ግን በgroup በእድሜ በሀገር ትዳር ስለሆነ በአስተሳሰብና በኑሮ ደረጃ የተለያዩ ስለሆኑ በእኔ ቻናል ያሉና ሀሳቡን የሚረዱ ካሉ እኔ እዚህ ልጅ ጋር ሁኜ የዚህ case ያለባቸዉ group ከፍተን በጥንቃቄ በSecurity
በሀላሉ ወደ ትዳር እንዲገቡ ለማድረግ አስቢያለሁ፡፡
ደግሞ group ዉስጥ ያሉት በዲን ጠንካራ ሀላል ፈላጊ ናቸዉ እኔ ከዚህ ቻናል ካለ ሀላፊነት እራሴ ወስጄ ከሚፈልጉት ጋር ላገናኛችሁ
በጣም ከባድ ኬዝ ነዉ ግን በቃ የታየኝ ለኔ በዚህ ቻናል ዉስጥ HIV ያለባችሁ ካላችሁ እና የምታቁት ትዳር ፈላጊ ካለ በዚህ bot አሳዉቁኝ
T.me/Aisuu_bot  T.me/Aisuu_bot
T.me/Aisuu_bot  T.me/Aisuu_bot


በተጨማሪ ከኔ የተሻለ ሀሳብ ያላችሁ በተለይ በዚህ ቻናል ላይ ያላችሁ የህክምና ባለሙያ የስነ-ልቦና ባለሙያ ነርሶች ወይም የዩኒቨርስቲ መምህራን ወይም የዩኒቨርስቲ ሜድስን ወይ ፋርማሲ ተማሪዎች ካላችሁ ከልምድ አንፃር ሀሳብ አስተያየት ብታካፍሉኝ በጣም ደስ ይለኛል ..እባካችሁ ይሄ ለብቻ የሚሰራ አይደለም በመወያየት ከአንዱ አንዱ ሀሳብ ተሽሎ ዘላቂ ለዉጥ እናመጣ እንችላለንና

በዚህ bot አስተያየት ይላኩልኝ
T.me/Aisuu_bot  T.me/Aisuu_bot
T.me/Aisuu_bot  T.me/Aisuu_bot

በነገራችን ላይ በአላህ ስም ይዣችሆለሁ ይሄን ፁሁፍ ያነበበ ሁሉ የተወሰነ ቀንም ቢሆን አስቦ ከተለምዶ ወይ የሰማዉ ታሪክ ካለ ወይ የተሻለ ሀሳብ እንዲነግረኝ እፈልጋለሁ

ለማንኛዉም Hiv ያለባችሁ ትዳር የምፈልጉ
☞ስም
☞የምትኖሩበት ከተማ
☞ የትዳር መስፈርታችሁን
በዚህ bot አሳዉቁኝ
T.me/Aisuu_bot  T.me/Aisuu_bot
T.me/Aisuu_bot  T.me/Aisuu_bot

>>> ይሄን ሀሳብ ያነሳዉ  ዲነል ኢስላም ያስተዋወቀን ወንድሜ እሱም ትዳር ፈላጊ ነው ከአገሩ ሙስሊም አላገኘም
☞የእሱ ሀገር ይቆይ ለጊዜዉ ግን ለትዳር ፈላጊዋ እነግራለሁ በቻናል ሚስጥር አይወጣም
☞የራሱ የሆነ ስራ አለዉ
☞በዲኗ ቁርአንና ኪቲብ የቀራች ይመረጣል፡፡
በዚህ Bot አሳዉቁኝ

T.me/Aisuu_bot  T.me/Aisuu_bot
T.me/Aisuu_bot  T.me/Aisuu_bot

ሴቶችም አትፍሩ እኔ አገናኛችሆለሁ ሚስጥር 100% ይጠበቃል

በተጨማሪ ደግሞ ዉጭ ሀገር ያላችሁ  አሜሪካ አዉሮፓም አረብ ሀገርም  አፍሪካም ዉስጥ  ካላችሁ የዚህ case ያለባችሁ ከእዛም የሚፈልግ ስላለ ማገናኘት እችላለሁ ....ብቻ ማንኛዉም ወንድም ሴት Hiv ያለባችሁ ትዳር ማግባት የምፈልጉ እዚህ ቻናል ያላችሁ ወይ የምታቁት ካለ በዚህ bot አሳዉቁኝ
☞ T.me/Aisuu_bot  T.me/Aisuu_bot

ሀሳቤን ጠቅለል ሳረገዉ  አላህን የሚፈሩ Hiv ያለባቸዉ የኢስላም ወንድም እህቶቼ በጣም እየተቸገሩ ነዉ ..የሌሎችም ሀይማኖት ተከታዮች እንደዚሁ በጣም ይቸገራሉ፡፡
በተለያዩ group ሙስሊሞች Hiv ኬዝ ያለባቸዉ ትዳር ሲያገኙ ሀይማኖታቸዉን እየቀየሩ ነዉ

እኛስ የነገን ማን ያዉቃል?? ምን መፍትሄ እናድርግ???  ማሰብ አለብን ..ሀሳቡን አንሸራሽሩት ለጓደኛ ለቤተሰብ ሳይቀር ትምህርት ቤት በተለያዩ ጀመአዎች ስብሰባዎች ሳይቀር

እስኪ ታዋቂ ፀሀፊያን ጋር እባካችሁ አድርሱት ለምሳሌ እኔ እነ ፉአድ ሙና እነ አብደል ሀኪም አሰፋ እነ ነጃት ሀሰን እነ ፋይሰል አሚን  ወዘተ ታዋቂ ፀሀፊያን እና ሰዎች ጋር አድርሱት እና በዚህ ጉዳይ ላይ ቢሰሩና መፍትሄ ሊፈጥሩ ይችላሉ በተለይ ፉአድ ሙናን የምትግባቡት ካላችሁ አስረዱት ለምን እሱ በሚዲያ ላይ ስላለ ተፅእኖ ይፈጥራል
ለፉአድ ሙና በዚህ ጉዳይ group ከፍቶ ይሄን ችግር ቢቀርፍ ጥሩ ነዉ እኔ ይሄ የራሴ ሀሳብ ነዉ
እኔ ለራሴ ተዋዛግቤ የምኖር ሰዉ ነኝ እንደነሱ መፍትሄ ሀሳብ መፍጠር ይከብደኛል እናም ማንም ጋር ስለማልግባባ በራሴ መስመር ብቻ ነዉ የምሄደዉ ግን ሌሎች ፀሀፊዎች አንዳንድ ላይ ተናበዉ አስበዉ ስለሚሰሩ ሀሳቡን አቅርቡላቸዉ ይሄ ግዴታም ጭምር ነው
☞ ወይም Mimber tv ሴቱንም ወንዱንም በማቀላቀል በማዉራት ብዙ ስራ ስለሚሰሩ ጥርት ያለ
ለትዉልድ የሚያስቡ ከሆነ ይሄን በሀሳብ ደረጃ አቅርቡቡላቸዉ በዚህ ላይ ቢሰሩ ..Minber ያልኩት እነሱን ደግፌ ሳይሆን ሰዉ ብዙ ጊዜ የሚጠቅመዉን ስለማያቅ ወደ እነሱ tv ትኩረት ስለሚያደርግ በዛ
እነሱ ሚስጥር ደብቀዉ ቢያገናኙ ብየ ነዉ  አንዳንድ ሚዲያ ብንጠላም ግን ይሄን ቢሰሩ ኸይር ነዉ..ይሄን ያነበባችሁ እንደ አስተያየት ስጧቸዉ
☞Nisiha tv በዚህ ጉዳይ ቢሰሩ ወይም የምትግባቡ ካላችሁ ሙራድ ታደሰን ሀሳቡን ሰጥታችሁት ይሄን ከNiseha tv ከነኡስታዝ ኤልያስ አህመድ ጋር ቢሰራ ዘላቂ መፍትሄ የሚገኝ ይመስለኛል
እናም በቻላችሁ አቅም ሁላችንም የኢስላም ሀላፊነት አለብን ይሄም አንዱ ግዴታችን ነዉ እናም የመፍትሄ ሀሳብ አመንጭ እንሁን ብዙ Hiv ያለባቸዉ ወንድም እህቶች እየተቸገሩ ነዉ...ይሄ በደንብ ቢሰራበት የሌላ ሀይማኖት ተከታይ Hiv ያለባቸዉ ለራሱ ከእኛ አልፈን እንጠቅማቸዉ ይሆናልና ..በጣም አስቡበትና ወደ መፍትሄ እንሸጋገር ተመካክረን
346 views03:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-08 06:25:45
በአላህ ያነበባችሁ ሁሉ አስተያየት ስጡ ለምን የአንዳችሁ መፍትሄ ሀሳብ ሊሆን ይችላልና አደራ
    አሚር ሰይድ

አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካትሁ
አሚር ሰይድ እንዴት ነህ??
ፍቃደኛ ከሆንክ አንድ ነገር ላማክርክ ነበር ማለትም እንደ አስተያየትም ጭምር ነው ለምን የብዙዎች ሙስሊሞች ችግር እኔ በድፍረት ላወያይህ ነዉ

    እኛ ሙስሊም ወንድም እህቶቻቹ የምንችገርበት አንድ ነገር አለ እኔ ለምሳሌ Hiv postive የሆነዉ ትዳርም ወይም እጮኛ ለመያዝ እንቸገራለን፡፡ሴቲቱም Hiv ካለባት ትዳር ለማግኘት በጣም ትቸገራለች ...ምክንያቱም እንደ ነሷራዎች አይደለም እምነታችን  በቻልነው አቅም እንከታተለን ልክ እኛው አይነት ተመሳሳይ አቂዳ ወይም ሸሪዓው አይነት ነገር የሚከተል ሰው ልንፈልግ እንችላለን ያው ትዳር ነውና እናም ያንን ነገር ግን እኛ ማድረግ አንችልም b/c እንደማንኛው ሰው ኢማን አላት ብለክ የምታጨው አይደለም postive ይሁን አትሁን ምታውቀው ነገር የለም ለመጠየቅ ስለምንፈራ ሙስሊም ላታገኝ ትችላለክ ፡፡ ያው ሀሳቤን ትረዳዋለክ ብዬ አስባለው ያው በፁሁፍ ለመግለፅ ትንሽ ይከብዳል መሰለኝ እና አንተ ታሪክ በመፃፍ ታዋቂ ነህ ብዙ ሰዉ ተከታይም አለህ ...አንተን እኔም ስለማምንህ ሌሎች እንደሚያምኑህ አልጠራጠርም  በቻናልህ ላይ ይህ አይነት ኬዝ ያለባቸው ኑረዉ ለሰዉ መንገር ፈርተዉ በሽታቸዉን ደብቀዉ ላያገቡ ይችላሉ...እኛ Hiv positive ያለብን የምንገናኝበት  ጠባብ ነው እና አንተ በዚህ  ኬዝ ላይ ሚስጥራዊ ግሩፕ ከፍተክ ይሄን ነገር ብትቀርፍልን ባይ ነኝ ከሌሎች አንተን አምነሀለሁ አሚር ሰይድ  ይሄን ጉዳይ ለተወሰኑ ታዋቂ ሰዎች ነግሬ መፍትሄ አላገኘሁም ግን አንተ ከሌሎች ትሻላለህ ቶሎ ሀሳብን ተረድተህ መፍትሄ እንደምታመጣ እተማመንብሀለሁ

መልስህን እጠብቃለሁ አሚር ሰይድ ወሰላሙ አለይኩም



ወደራሴ ሀሳብ ስመጣ
ወላሂ ቢላሂ ይሄን አስተያየት ልጁ የላከልኝ ከዛሬ 6 ወር በፊት ነበር  ምን ማድረግ እንዳለብኝ ግራ ገባኝ ..ከዛ አስተያየት ለሰጠኝ ቢያንስ የተወሰነ ቀን ስጠኝና ልሰብበት ነበር መልሴ ...ይሄዉ እሱም ጋር ስንደዋወል ስናወራ ስለሁኔታዉ ሲያጫዉተኝ 6 ወራትን አለፍን

አስባችሁታል እስኪ ራሳችንን   Hiv positive እንዳለብን አርገን እንሰበዉ .
☞ ትዳር ላግባሽ ብሎ ሲጠይቅሽ ወይ በቤተሰብ ቢመጣ ምን ይሰማናል ምን ይሆን መልሳችን??አይከብድም
☞ አባትሽ እናትሽ ዛሬ የማመልሽዉ እምቢ የማትይበት ትዳር መጥቷል ይሄን ያመጣሁልሽን ታገቢያለሽ እምቢ ካልሽ ከአሁን ቡሀላ አባቴ ብለሽ እንዳጠሪኝ ወይ እናቴ ብለሽ እንዳጠሪኝ ያመጣንልሽን ታገቢያለሽ ቢሉሽ እናት አባትሽ አንቺ Hiv አለብሽ
ቤተሰቦችሽ አያቁም
ለእናት አባትሽ ምን ብለሽ ትመልሻለሽ አይከብድም????
☞ ወይም የሰዉ ልጅ ነሽ ፍቅር ቢይዝሽ ያን ልጅ ትወጅዋለሽ ግን የእሱ መሆን አትችይም Hiv አለብሽ እሱን እወድሀለሁ አንተ ጋር መኖር እፈልጋለሁ ግን Hiv አለብኝ ትይዋለሽ?? በጭራሽ አትይዉም ይከብዳል
☞ እኔ እራሴን Hiv positive አድርጌ ልሰብ እስኪ አንተም የምታነበዉ Hiv አለብህ እንበል ትዳር ማግባት ፈለክ ወይም ልጅቷን ወደድካት ከዛም  አወረሀት ብዙ ነገር ተግባባችሁ  Hiv አለብኝ  አንቺስ ብለህ መጠየቅ ትችላለህ???አየህ አትጠይቃትም እኔም እኔ Hiv ቢኖርብኘ  አለብኝ አልልም ለምን ከዚህ ከማይረዳ ማህበረሰባችን አንፃር ይከብዳልና፡፡
☞ቤተሰቦችህ ትዳር መርጬልሀለሁ ይቺን ልጅ አግባ ብለዉ አማከሩህ ይቺን ልጅ የማታገባ ከሆነ እኔና አንተ አባትና ልጅ አይደለህም ብትባል
ልጂቱን ወደሀታል ግን አንተ Hiv አለብህ እንዴት ታደርጋለህ??? አይከብድም

በዚህ መጥፎ ዘመን አንዳንዶች HIV ሲገኝባቸዉ በበቀል የሌለባቸዉን ለማስያዝ የሚያደርጉትን ጥረት እየታዘብን ነዉ...አንዳንዶች Hiv በደማቸዉ ሲገኝ girl frind ይይዙና አላህ በከለከለዉ ዚና አማካኝነት እንደነሱ Hiv አስይዘዉ ሲያገቡ እያየን ነዉ ..ሴቶችም Hiv ሲገኝባቸዉ ወንዱን በማስያዝ ሲጋቡ እያየን ነዉ ግን ይሄ ወንድሜ አላህ የሚጠላዉን የከለከለዉን አልሰራም የሴቶች ህይወት አላበላሽም ግን እንደኔ Hiv ያለባት ዲነኛ  ፈልግልኝ ሲለኝ ወላሂ ከባድ በጣም ከባድ የአእምሮ ስራ ነበር የገጠመኝ...ደግሞ እንደኔ Hiv ያለባቸዉ የተለያዩ ሀገር አሉ group አለ ግን መቼም ትዳር ሲሆን የራስ የስራ ቦታና መስፈርት ይኖራል በዛ ላይ መስፈርት ስላልመጣ እንደሆነ በስልክ ጭምር ስንደዋወል ያሳዉቀኛል፡፡

እንደዚሁ ሀላል ፍላጋ Hiv ያለባቸዉ አዉሮፓም አረብ ሀገርም አፍሪካ ጭምር የብዙ ሰዉ ጥያቄ ነዉ ..አሜሪካ ጀርመን ፈረንሳይ ሱዳን ወዘተ ብዙ ሙስሊሞች አሉ



ከዛ ቡሀላ ያላማከርኩት ሰዉ የለም ስደዉል ምን ስል መፍትሄ አጣሁ..የሚገርማችሁ በሚዲያ የምናቀቸዉ ታዋቂ ኡስታዞችን በሰዉ እንዲጠየቁ አድርጌ ነበር ግን
ምንም መፍትሄ ሀሳብ እንደሌላቸዉ ነዉ ያሳወቁኝ...

መቼም አላህ እድሜዉን ይጨምርለት ምርጥ መካሪየ አስተማሪየ የዲን ወንድሜ በደሀ ፍቅር የምናቀዉ ከድር አህመድ ከሀርቡ ሳማክረዉ አሳማኝ ምርጥ መልስ ሰጠኝ
>>አንድ የማቀዉ Hiv positive ነበር እሱ መድሀኒት ከሚቀበልበት ሆስፒታል የሚሰጠዉን ዶክተር አማክሮ
የሚሆነዉን አግኝቶ አግብቶ እየኖረ ነዉ እናም መድሀኒቱን ከሚቀበልበት ጤና ጣቢያ የሚሰጠዉን ዶክተር ቢያማክር  ጥሩ ነዉ አለኝ ...ምርጥ በላጭ ሀሳብ ነበር ለልጁም ነገርኩት በጣም ትክክል እንደሆነ ነገረኝ..Hiv መድሀኒት ከሚቀበልበት ጤና ጣቢያ ሲያማክር ሙስሊም ሴት እኛ ጋር የሚወስድ የለም አሉት የልጁ ሀገር መግለፁ ለጊዜዉ ይቆይ ፡፡ እሱ የሚኖርበት  ሙስሊም በብዛት የለምና

በስልክ በተደዋዉለን ቁጥር ከአንድ ሰአት በላይ እናወራለን Hiv ኬዝ ያለባቸዉ በጣም ብዙ ሰዉ እንዳሉ ግን ሁሉም እየደበቁ ነዉ እኔም ቤተሰብ ተጨነቀብኝ ቶሎ ማግባት አለብኝ አብረን በአላህ ፍቃድ መፍትሄ እንፈልግ አለኝ
የሚገርማችሁ በስልክ ካጫወተኝ ወላሂ ከወንዱ በላይ ሴቶች በጣም እየተቸገሩ እንደሆነ እምባ የሚያለቅሱ እህቶች እንዳሉ ብዙ ታሪክ አጫዉቶኛል፡፡ እኔስ ወንድ ልጅ ነኝ እቋቋመዋለሁ ግን ሴቶች ያሳዝኑለል ከባድ ጊዜ የሚያሳልፉ አሉ አሚር ብሎ በጣም ብዙ ነገር አጫዉቶኛል

ለHiv positive ብቻ የተከፈቱ ቻናሎች አሉ አንዳንዶች ያስተዋውቁና ከተጋቡ የደላላ ኮምሺን የሚቀበሉ አሉ::በዚህ group የተለያዩ ሀይማኖት አሉ ለትዳር ብለዉ በዚሁ Hiv ኬዝ ስላለባቸዉ ትዳር ስለሚያጡ ብዙዎች ሀይማኖታቸዉን እየቀየሩ ነዉ፡፡
እኔ ደግሞ በነዚህ አይነት ቻናሎች የመጡ ማግባት ይከብዳል ዲን አይኖራቸዉም ሀይማኖታቸዉ ሌላም ቢሆን ለትዳሩ ሲሉ  እስከመቀየር የሚደርሱ አሉ እናም ከነዚህ group ማግባት በጣም ከባድ ነዉ አለኝ

እስኪ ከነገረኝ ታሪኮች ልንገራችሁ
351 viewsedited  03:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-07 14:52:01
#አይ_ዱኒያ
የሳዑዲ ልዑል #ሚሽአል ሲሞት አንድ ትሪሊየን ሁለት መቶ ሚሊዮን ሪያል ለወራሾቹ ትቶ ነበር።
ከስር ያለው ምስል #የልዑል_ሚሻአል ጀናዛ በመካ ሰላተል ጀናዘ ከመሰገዱ በፊት ነበር ምስሉ ምንም ገለፃ ሳያስፈልግ ሁሉን ነገር ይናገራል።
የልዑል ሚሻአል ወራሾች ሁለት ሚስቶች ና ልጆቹ ነበሩ
የሚስቶቹ የአንዷ ድርሻ 75 ቢሊዮን ።
የ9 ሴት ልጆቹ የአንዷ ድርሻ 45.65 ቢሊዮን
የ7ወንዶች ልጆቹ የአንዱ ድርሻ 91.3 ቢሊዮን ነበር። #አጂብ ይህ ሁሉ ብር ለወራሽ ነው የተሰጠው ልዑሉ ከሞቱ በኋላ አንድ ሪያል ከሱ ጋ አልሄደም ።

#ዱንያ እንዲ ናት #ልዑል ሆንክ #ንጉስ ስትሞት #ከከፈን ውጪ ይዘኸው ምትሄደው ነገር የለም

ይህ ለኛ ብዙ ያስተምረናል ዱንያ ምንም ብንለፋላት ትተናት እንሄዳለን ይልቅ የአኼራ ቤታችንን እናሳምር

አላህ በሰጠን ነገር ደስተኛ ና አመስጋኝ እንሁን እሱን በማስታወስ ላይ ዘውታሪ ያድርገን

اللهم أعنا على ذكرك وشكرك وحسن عبادتك...
987 views11:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-07 11:31:39
በግራ በኩል በእናቱ እቅፍ ውስጥ አዲስ የተወለደ ህጻን አለ። ሐኪሙ በቀኝ በኩል ተቀምጦ ሲያለቅስ ይታያል።

  እናት በጠና ታማለች። ልጁን በህይወት ለመዳን ከባድ መስዋዕትነት እንደሚያስከፍል ዶክተሮች ተረድተዋል።
  ልጅ እንዲሰጣት ሁሉን ቻይ የሆነውን አምላክ አላህን ደጋግማ ትማፀናለች። የቀዶ ጥገናው ውጤት ልጁን ማዳን ወይም እናቱን ሆኗል።

ዶክተሩ ለ 7 ሰዓታት ያህል የተቻለውን እያደረገ ሕፃኑን እና እናቱን ለማዳን ጣረ።

በመጨረሻም ዶክተሩ በእናትየው የተጠየቀውን ለማድረግ ወሰነ። ልጇን በእሷ የህይወት ዋጋ ማዳን ነበር። አዎ ልጄ በህይወት ይኑር እኔ ግን ይህን አለም ልልቀቅ አለች። ቢሞግቷትም ልትቀበል አልፈቀደችም።

ህፃኑ ከእናቱ ሆድ ሲወጣ የለቅሶ ድምፅ አሰማ እናት ፈገግ አለችና ዓይኖቿን ለመጨረሻ ጊዜ ጨፈነች ዳግም ላትመለስ ከጌታዋ ጋር ተገናኘች ። ሕይወቷን የሰጠችውን እናቱን ዳግም ላያገኛት ተለያት።

አይ አንቺ እናት!
አላህ በጀነቱ ያኑራት።
1.0K views08:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-07 11:30:11 ዶክተር ዋዲ ፋቲህ ይሰኛል። የሰለመበትን ገጠመኝ እንዲሀ እያዋዛ ይተርክልናል። እንደ አውሮፓውያን የዘመን ቀመር በ1978 አሌክሳንድሪያ በሚገኘው ሙሀረም ቤክ ሆስፒታል ውስጥ ዶክተር ሆኜ አገለግል ነበር። በወቅቱ በድንግል ማርያም ቤተክርስቲያን አንጋፋ ዲያቆን፣ የኮፕቲክ ሰንበት ትምህርት ቤቶች መምህር ነበርኩ።

ከእለታት በአንዱ ቀን ሳንታ ሉቺያ ምግብ ቤት ኩሽና እሳት ተነሳ።  አምቡላንሶች ቁስለኞችን ይዘው ወደ ሆስፒታላችን ከነፉ። ወደኔ ክፍል የገባው ታካሚ በጣም የተጎዳ ሰው ነበር። ምግብ አብሳይ ነው። ሰውነቱ ሙሉ በሙሉ ተቃጥሎ ከስሏል። ያቃስታል የህመም ጩኸት ያሰማል።

ከልምድ አንፃር በ24 ሰአት ውስጥ እንደሚሞት ገምቼ ነበር። ሰውነቱ ውስጥ ያለው ቃጠሎ እንዲፀዳለት pain killers ሰጠሁት። በጣም በተረጋጋ መንፈስ ዶክተር ቆይ አለኝ ለስራ ባልደረቦቼ መድሀኒታቱን እንዳይግቱት ምልክት እየሰጠ። በጀርባው ተንጋሎ ማውራት ጀመረ
"ከአላህ ጋር ጥብቅ ትስስር አለኝ። በጥቂት ሰዓታት ውስጥ እንደምሞት አውቃለሁ። አደራ ራስህን አታድክም መድሃኒቶችንም በከንቱ አታባክን። ሞትን አልፈራም ግና የህመም ስሜት በተሰማኝ ቁጥር ቁርአንን እየቀራሁ አላህን መገናኘት እፈልጋለሁ" አለና ቁርአንን ከፍ ባለ ድምፅ በሚማርክ ዜማ ማንበብ ጀመረ።

በማግስቱ ጠዋት ሆስፒታሉ አልጋ ላይ አላገኘሁትም ነበር። ነርሶቹን ጠየቅኩ ከመሀላቸው አንዱ "ነፍሱ እስክትወጣ ቁርአን እየቀራ ነበር። ውሃና አንድ ሲሪንጅ ብቻ ነው የጠየቀው" አለኝ ምስሉ በምናቤ ተደቀነ።

ሞትን እንዴት አይፈራም? በጌታው ላይ ምን የሚሉት መተማመን ነው ያለው? ከእርሱ ጋር መገናኘትን እንዴት ቢናፍቅ ነው? ይህ መጽሐፍ (ቁርአን) ቃላቶቹ የተዳሰሱበትና በአስደማሚ አረፍተ ነገሮች የተዋቀረበት ሚስጥርስ ምንድን ነው? ራሴን ጠየቅኩ። ስለኢስላም ለመረዳት ጣርኩ። አነበብኩ። ከአስራ አምስት አመትበኋላ በ1993 ዓመት አላህ እስልምናን ወፈቀኝ። ቁርአንና ትርጓሜውን ስማር ያ ሰው ከአመታት በፊት የተናገረውን ተረዳሁ። ባስታወስኩት ቁጥር አላህ ሆይ እዘንለት ይቅርም በለው ቀብሩንም የጀነት ጨፌ አድርግለት ስል አላህን እማፀነዋለሁ።

በምላስህ ዳዕዋ ማድረግ ቢከብድህ በተግባርህ ሰዎችን ወደ ኢስላም ተጣራ።
846 views08:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-07 11:29:56
ዶክተር ዋዲ ፋቲህ ይሰኛል። የሰለመበትን ገጠመኝ እንዲሀ እያዋዛ ይተርክልናል።
707 views08:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-07 11:27:31 የፈረንሳይ መኪና ፔጁ የሚለውን ስያሜ ከየት እንደመጣ ታውቃለህን? በእርግጥም ብዙዎቻችን ስያሜውን እናውቀዋለን። ከእኛም መካከል መኪናውን የሚነዳ የኩባንያውን አዳዲስ ሞዴሎች የምንከታተል እንኖራለን። ግና ጉዳዩ የፈረንሳይ መኪና ብራንድ ሳይሆን ከዚያም የበለጠ የመስቀል ዘመቻ ጀብዱ መሆኑን እናስታውስ ላመኑት ይጠቅማልና ማስታወስ።

ማርሻል የጦር አዛዥ ነው። የሙስሊሞችን መሬት የቀማ ክብራቸውን ያዋረደ ነፍሰ በላ። ይህ ወንጀለኛ.. በምዕራባውያን ሚዲያዎች ሃይል እንደ ጀግናም በየሚዲያው የሚለፈፍለት ሰው ነው።

ስለ ኩባንያውና ስለ መኪናው ሁሉንም ነገር እንደምናውቀው ሁሉ ጠላታችንን እንዳናውቀው ትክክለኛ ታሪኩን ሰውረውታል። በፈሪ ዱላ ከመ#ና#ፍቃን ጋር አብሮ ያደረገውን አሰቃቂ ጭፍጨፋ እንደ ጀብድ ይዘምሩለታል።

በእርግጥም እሱ ጨካኝ ወንጀለኛ ነው። ቶማስ ሮበርት ፒጆ ይሰኛል። በ1836 ወደ አልጄሪያ በተደረገው የመስቀል ዘመቻ መሪነቱን ጨብጦ ሴት አዛውንት ሳይል ጨፍጭፏል።

ግንቦት 30 ቀን 1837 ከአልጄሪያ መሪ ልዑል አብዱልቃድር ጋር በአልጄሪያ በተፍናን ወንዝ አቅራቢያ ፈረንሳይን ወክሎ ስምምነቶችን አደረገ። የግዛቱን ሉዓላዊነት ጠብቆ አሚር አብዱልቃድር እንዲያስተዳድር እውቅና ሰጠ። ግና ብዙም ሳይቆይ ይህን ስምምነት ውድቅ አድርጎ ከሁለት አመት ካልበለጠ አጭር የእርቅ ጊዜ በኋላ ጦርነቱ እንደገና ተቀሰቀሰ። በ1840 ፔጁ የአልጄሪያ ጠቅላይ ገዥ ሆኖ ተሰየመ። የሙስሊሞችን ተቃውሞ ለማፈን ጭካኔ የተሞላበት ርምጃዎችን ማድረግ ጀመረ።

በርካታ ኡስታዞችና መሻኢኾችን በአንድ የእስር ቤት ማጎሪያ ተሰብስበው እንዲታሰሩ ትዕዛዝ ሰጠ። የኢስላምን አርማ በቀልባቸው በመሸከማቸው ብቻ የስቃይ ብትር አረፈባቸው። መከራን ከየአይነቱ ቀመሱ። እግራቸውን ሰፊ በሆነ ባልዲ ላይ አስገብተው ሲሚንቶ ይሞሉበታል። መድረቁን ካረጋገጡ በኋላ ከሂሊኮፍተር ላይ ባህር ውስጥ ይወረውሯቸዋል።

ፔጁ የፈረንሳይን ቅኝ ግዛት በአልጄሪያ ማጠናከር እና የአልጄሪያን ሙስሊም ማህበረሰብ በማጥፋት ክርስትናን ተክቶ ውህደትን ማጠናከር አስፈላጊ መሆኑን ያምን ነበር። እነዚህን መርሆች እና ፅንሰ-ሀሳቦች ተግባራዊ ለማድረግም የሙጃሂዶቹንና የአማፂያንን ንብረቶች በመውረስ ለ በአልጄሪያውያን እና በአውሮፓውያን መካከል ለንግድ ልውውጥ ገበያውን መቆጣጠርን ጨምሮ በርካታ አፋኝ ህጎችን አወጣ።

አልጄሪያውያንን በካምፖች ውስጥ በማጎር፣ በመሰብሰብና በመክበብ ለአብዮተኞቹ ምንም አይነት እርዳታ እንዳይሰጡ የማድረግ ዘዴን ቀየሰ። ባላባቶችን የእርሻ ሰብላቸውንና ንብረታቸውን በመንጠቅ “የአረብ ጽሕፈት ቤቶች” እየተባለ የሚጠራውን ተቋም ህጉንና ፖሊሲውን ህዝብ ላይ ተፈፃሚ ለማድረግ መሣሪያ አድርጎ ተጠቀመበት።

ይህ ወንጀለኛ በፓሪስ በኮሌራ በሽታ ህይወቱ አለፈ። ብቻውን በሚኖርበት የእርሻ ሥፍራ አካሉ ለቀናት በስብሶ ውሾች ቦጫጭቀውት ከአስከሬኑ ጥቂት አካል ተገኘ። ሰኔ 10 ቀን 1849 በፓሪስ ከተማ ተቀበረ። ቤተ ክርስቲያን በአልጄሪያና በሞሮኮ ሙስሊሞች ላይ ላደረሰው በደል ቅዱስ ሰው ስትል ሰየመችው። በመ#ግ#ደሉ፣ በማቃጠሉ በማውደሙና በመድ#ፈሩ ክብርና ሞገስ ተችሮት በስሙ ኩባንያ ተቋቋመለት። ወንጀለኛ ሆኖ ኖሮ በውሻ ተቦጫጭቆ ሞተ።

በወቅቱ የነበረውን የጀግናዋን የገዛላን ታሪክ ሳላወሳ ማለፍ አልተቻለኝምና እነሆ አያይዤ ታሪኳን ላውሳ

ፈረንሳይ ኢስላምን ከአፍሪካ ምድር ለማጥፋትና ሙስሊሞችን በግድ ለማጥመቅ በሀገረ አልጄሪያ ጦርነት በከፈተች ጊዜ መሐል ከተማው ውስጥ  ያረጁ፣ እድሜያቸው ከአልጋ ያዋላቸው ሽማግሌዎች፣ ሴቶችና ህፃናት እንጂ ሁሉም ወደ ጂሃዱ ሜዳ ዘምቷል። በአላህ መንገድ ሞቶ ኢስላምን ህያው ሊያደርግ የሞቀ ፍራሹን ትቶ በየጫካው የአላህን ጠላቶች ይፋለም ይዟል። በደሙ ታሪክ ለመስራት የወኔ ነበልባል ልቡን ይደፍቀው ይዟል። አዎ ኢስላም እንዲህ ነው ማቀርቀርና አንገት መድፋትን ሳይሆን መብትን ለማስከበር ነፍጥን አነግቦ መፋለምንም ያዛል።

  የበጋው ወራት አልፎ ሰማይ ሰማያዊነቱን ትቶ እንደሚባዘት ጥጥ የተሰናዳ የሚመስለውን ደመና አዝሏል። ክረምት ገብቷል። ጠላት በስተምስራቅ በኩል ያለውን ጦር ደምስሶ ወደ ከተማው መሐል ጉዞ ማድረግ ጀምሯል። ሴቶች አዛውንቶችና ህፃናት ብቻ ወዳሉበት ከተማ! የሙተሀጂቦቹን ሂጃብ እያወለቁ በጀመዓ መድፈር ጀምረዋል። የከተማውን ወንድ እህት እናቱ፣ ሚስት ወዳጁ መርቀው ሸኝተውት ከተማውን እነሱ በአደራ ተቀብለዋል። ታዲያ በዚህ ወቅት ነበር የሴቶችን ክብር ለማስጠበቅ አዲስ የትግልን መንገድ ገዛላ ቢንት ዐማር የፈለሰፈችው። እንደታፈነ ጢስ ልባቸው ውስጥ ተዳፍኖ የነበረው የጀግንነት ወኔ ቦሎ ይንቦለቦል ነዶም ያነዳቸው ይዟል።

የፈረንሳይ የጦር መኪኖችን ድምፅና የእንስቶችን ጩኸት እንደሰማች በመኖርያ ቤቷ ጣርያ ላይ ወጣችና ሴቶች ሂጃባቸውን ለብሰው ወደ እርሷ ግቢ እንዲመጡ አዘዘች። ተጣራች "እናንተ የአላህ ባርያዎች ሆይ! በሂጃባችሁ ላይ ፅኑ ...   ኑ! ተሰብሰቡና በአንድነት ስለ ሂጃባችን እንዋደቅ። ስለክብራችን እንሙት። ኑ እህቶቼ በሂጃባችን እንከፈን የአላህን ትዕዛዝ ለማስከበር ስለሂጃባችን እንሰዋ እሱም ሊረዳን ቃል ገብቷልና" አለች።

  ብዙ ሴቶች ተሰበሰቡ። ከ7 እስከ 60 ዓመት ዕድሜ ውስጥ የሚገኙ እንስቶች ሂጃባቸውን አጥልቀው በኢስላማዊ አለባበስ ተውበው በዙርያዋ ተሰለፉ። አዎ! ተዳፍኖ የነበረው የጀግንነት ፍም በአርምሞ ያለፉበትን የኃያልነት ጊዜ በልባቸው ውስጥ እያስታወሱ የነዘይነብን የነ ሱመያን ታሪክ እያወሱ የኋሊት ተጉዘው ሴትነታቸው ሳይበግራቸው ታሪክ የሰሩ ጀግኖችን በምናብ መነፅር እያዩ የልባቸው እሳት እየተቆሰቆሰ የውስጠት ስሜታቸው እየጨሰ በወኔና በጀግንነት ቆሙ። ተዋርደው የከረሙበትን ረመጥ ዳግም በኃያልነት ማንነታቸው ተቀጣጥሎ እንዲንቦገቦግ የሚያደርገውን ነዳጅ ከታሪክ ማህደር እየቀሰሙ ትናንት ያሳለፉትን እያንዳንዷን ሁነት መቃኘት ጀመሩ።

  እያንዳንዳቸው የሌላኛቸውን እጅ አጥብቀው በመያዝ እጅ ለእጅ ተሳሰሩ። በገመድ ራሳቸውን ጠፍረው አሰሩ። እንደ አንድ ሰው እንደ አንድ አካል ሁሉንም ሊጋፈጡ ቆረጡ። ነጭ ሽንኩርትን በመጭመቅ በጠርሙሶች ውስጥ አዘጋጅተዋል። የሽንት ቤት ፍሳሽም በአንድ ጎን አስቀምጠዋል። ፊታቸውን በሸክላ ከሰል ለቅልቀዋል። የፈረንሳይ ወታደሮች ቆንጆ ሴቶችን መርጠው ለማውጣት ሲሞክሩ ያን የነጭ ሽንኩርት ጭማቂና የሽንት ቤት ፍሳሽ የሰውነት ገላቸው ላይ እየለቀለቁ ከአጠገባቸው እንዲርቁ እርስ በእርሳቸው እየተጓተቱ ራሳቸውን ከጥቃት ይከላከላሉ።

   ግና የፈረንሳይ የመስቀል ጦረኞች ሴቶችን ለመጠበቅ የወንድነት ድፍረትን የታጠቀችው ይህን አብዮት የምትመራው ገዛላ ቢንት ዐማር መሆኗን ሲያውቁ ከምንጩ ለማድረቅ ይከታተሏት ገቡ። አሳቻ ሰአትን ጠብቆ ባለ ሙሉ ማዕረጉ የኤስ ኤ ኤስ ኦፊሰር ደረቷን በከባድ መሳሪያ ደለቃት። ሰውነቷ ባዶ እስኪሆን ድረስ ለ3 ቀናት ደም ማስታወኳን ቀጠለች። በመጨረሻም ነፍሷ ወደምትወደው ጌታዋ በረረች።

ምስሏን ያነሳው ፈረንሳዊው ፎቶግራፈር በማስታወሻ ደብተሩ ላይ እንዲህ ሲል ፃፈ
"በህይወቴ ቅንጣት ፈርቼ አላውቅ። የዚህችን ሴት ፎቶ ሳነሳ ግን ፍርሀት ብቻም ሳይሆን ድንጋጤም ሰውነቴን ወሮት እጆቼ እየተንቀጠቀጡ ነበር"

አላህ ይቀበላት
767 views08:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-07 09:23:19
በአዕምሯችን ማዕከል ውስጥ የሆነን ሰው ፍፁም ከእንከን የጠራ የሰውነትን ጥግ የተላበሰ እናም የሱን ህይወት በአዕምሯችን የምንቀርፀው ሰው አለ።ይህ ሲሆን ብናውቅም ባናውቅም ማለት ነው! ይህ የህይወት ተምሳሌት ይባላል። ይህ ተምሳሌታችን ብልሹ ሲሆን የህይወት ምሳሌያችን ሙሉ በሙሉ የተበከለ ይሆናል። ታዲያ ያኔ ራሳችንን ከምሁርነት ደረጃ ሳንወርድ ስራችን ተቃራኒ እውነት ይሆናል።በዚህ ሚዛን መሰረት ሙስሊሞችም ነብዩ ሙሀመድን የህይወት ተምሳሌት ሲያደርጉ በቅፅበት ተንቀሳቃሽ ቁርአን መሆናቸው አንቀሬ ይሆናል..ልክ አኢሻ ረ.ዐ ነብዩን ሰ.ዐ.ወ እንደገለፀቻቸው!..
የህይወት ተምሳሌታችን ማን ይሆን!



t.me/@mind_mind
tiktok.com/@islamic_mindset1
Youtube.com/@islamic_mindset1
instagram.com/@islamic_mindset_official
884 views06:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ