Get Mystery Box with random crypto!

ISLAM IS UNIVERSITY

የቴሌግራም ቻናል አርማ islamisuniverstiy_public_group — ISLAM IS UNIVERSITY I
የቴሌግራም ቻናል አርማ islamisuniverstiy_public_group — ISLAM IS UNIVERSITY
የሰርጥ አድራሻ: @islamisuniverstiy_public_group
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 19.00K
የሰርጥ መግለጫ

⭐️ሰው የሚገነዘብ አእምሮና የሚያፈቅር ልቦና ባለቤት ነው።እነዚህ ሁለቱ ካልተመጣጠኑ ስብእናው አደጋ ውስጥ ነው።የሚያገናዝበው አዕምሮው፣የሚያፈቅረው ልቡ፣የሚንቀሳቀሰው አካሉናወደ ሰማይ የሚወነጨፈው መንፈሱ በውህደት ካልተንቀሳቀሱ ሰውየው ላይ ችግር አለ ማለት ነው
📨የፍቅር እና የጥላቻ ስሜቱ፣የፍላጎት እናየፍርሃት መንፈሱ በአዕምሮ ብስለት ካልተገራ አስቸጋሪ ነው
አስተያየት👇
T.me/Aisuu_bot

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 11

2023-04-04 13:04:46 https://t.me/arebgendamesjid?livestream=ae91c8bcf0d1ee5306
246 views10:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-03 20:57:58
አሰላሙ አለይኩም ዛሬ አንድ ነገር ላስቸግራችሁ ነዉ
ሙስሊም በጓንታናሞ እስር ቤት የሚለዉ መፅሀፍ የዛሬ አምስት ስድስት አመት በፊት ገበያ ላይ ነበር
እኔም ይህ መፅሀፍ ነበረኝ ግን አበድሬዉ ማን ወስዶ እንዳስቀረብኝ አላቅም ሆነም ቀረ አሁን ላይ ይሄን መፅሀፍ ገበያ ላይ ማግኘት አልቻልኩም፡፡

ደሴ ሁሉም መፅሀፍት መደብር
አዲስ አበባም ኮምቦልቻ ባቲ ሀርቡ ከሚሴ ሀረር አዋሳ አስፈለኩት መፅሀፉ አሁን አይታተምም ገበያ ላይ የለም ሆነ በየአቅጣጫዉ መልሱ፡፡

አሁን ያለዉ አማራጭ ከሙስሊም መፅሀፍ መሸጫ መደብር በፊት አምጥተዉ ያልሸጡት ካለ በአላችሁበት ከተማ አስታዉሳችሁ ፈልጉልኝ በተገኘዉ ዋጋ እገዛለሁ

ወይም የዛሬ አምስት ወይ ስድስት አመት በፊት ገዝታችሁ እቤት ያስቀመጣችሁ ካላችሁ  ለአንድ ወር ብቻ አበድሩኝ ወይም
በተመቻችሁ ዋጋ ሽጡልኝ
መፅሀፉን ፍለጋ 8ወር አለፈኝ
ከመፅሀፉ የሚዘጋጅ ቃል የገባሁት ነበር እናም
አዘጋጅልኝ ብለዉኝ ነዉ...ከዛ መፅሀፍ የሚዘጋጅ በቻናል ይፓሰታል..በሳምንት የሚበተን ወረቀት ላይም የሚዘጋጅ ነዉ ...የሚዘጋጀዉ በጣም ለሙስሊም ትዉልድ የሚጠቅም ራስችንን የምንፈትሽበት ነዉ፡፡መፅሀፉን እናንተ ባላችሁበት ከተማ ብቻ ጠቁሙኝ እኔ ራሴ አመቻችቼ ደሴ አስመጠዋለሁ፡፡ በቻላችሁት አቅም ይሄን መፅሀፍ በመፈለግ ተባበሩኝ በተባለዉ ዋጋ ለመግዛት ዝግጁ ነኝ ብቻ መፅሀፉ ይገኝ
መፅሀፉን በፊት ገዝቶ ያለዉ ካለ ወይም ገበያ ላይ ያገኘልኝ በዚህ Bot
አሳዉቁኝ
T.me/Aisuu_bot  T.me/Aisuu_bot
T.me/Aisuu_bot  T.me/Aisuu_bot
መፅሀፉን ገበያ ላይ ወይም ሰዉ ከሰዉ ተጠያይቆ ያገኘልኝ ወላሂ ባለዉለታየ ነዉ በዚህ bot አሳዉቁኝ

T.me/Aisuu_bot  T.me/Aisuu_bot
T.me/Aisuu_bot  T.me/Aisuu_bot
አሚር ሰይድ
465 viewsedited  17:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-03 20:48:05 https://www.youtube.com/live/VDWHMpzyycU?feature=share
428 views17:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-03 13:23:00 https://www.youtube.com/live/sRk_JH2XkfQ?feature=share
666 views10:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 19:15:36 እባካችሁ አሊሞች ሸይሆች  እኛን ወጣቶች በቁርአን በሀዲስ ኮትኩታችሁ ለነገ ትዉልድ ማስተላለፍ ቢያቅታችሁ እንደዚህ ፈሳድ የሆነን በየአመቱ ተከታይ አታድርጉን እባካችሁ ወጣቱን የማይጠቅም የማይጓዳ ጀነሬሽን ባለማድረግ ተባበሩን


የተወሰነ ሰዉ ባይሄድ አሁን ባለቸዉ አቋም የሚቀር የሚቆም አይደለም
ግን አለመሄድ የባለቤቱ ወሳኔ ነዉ...አምና ታስታዉሱ ከሆነ ደሴ በተደረገዉ የጎዳና ኢፍጣር ከአየሁ ቡሀላ
በዛዉ በተደረገ ቀን ከአሁን ቡሁላ ላልሄድ ብየ ምያለሁ....ከዘንድሮ ጀምሬ አደባባይ ኢፍጣር አልሄድም
ይሄን ያነበበ አስተንትኖ ነገሮችን ከግራም ከቀኝም ከሆላም ከፊትም ከሁሉም አቅጣጫ ተመልክቶ በየአመቱ ለወደፊት ለሚካሄድ ኢፍጣር ራሳችሁን ብታገሉ ባይ ነኝ ...የአንድ የሁለት ሰዉ መቅረት ይሄን የአደባባይ ኢፍጣር ለማስቆም አቅም ባይኖረዉም ግን ለወደፊት በየአመቱ ለሚፈጠር ቢድአ ተባባሪ አለመሆን አንድ የሙስሊም ግዴታ ነዉ





ነገር ግን አንዳንድ ደጋግ የአላህ ባሮችና ኢብኑ መስኡድ ኢስላሚክ ሴንተር በየጎዳናዉ የተቸገሩን ማፍጠሪያ የሌላቸዉን በየጎዳናዉ ያስፈጥራሉ እንደዚህ ያሉትን ደጋግ ባሮች ጀመአዎች ለአላህ ብለዉ የሚሰሩን አላህ ንያቸዉን አጅራቸዉን እጥፍ ድርብ ያርግላቸዉ ይሄ መበረታታት ያለበት ነዉ...ነገር ግን የአደባባይ ኢፍጣር ተብሎ ፆታ መለየት እስከሚያቅት  ወንድ ሴት ተደባልቆ ታላቁ በአይኑ የተለየ ይሄን ያህል ሜትር  ክብረ ወሰን በጠስን እያሉ በዲን ስበብ ፈሳድ ባይበዛ ኸይር ነዉ፡፡


ኸይር ፅፌ ከሆነ ከጀሊሉ ነዉ መጥፎ ወይ ስህተት ፅፌ ከሆነ ከሸይጧን ነዉ አዉፍ በሉኝ ስህተት ከሆነም አሳማኝ ምክንያት ከአገኘሁ ስህተት ነዉ ብየ ፁሁፉን ከቻናል እሰርዛለሁ
894 viewsedited  16:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 19:15:20 የጎዳና ላይ ኢፍጣር ደረሰ
        አሚር ሰይድ
     
አሰላሙ አለይኩም እንዴት ናችሁ
በፊት በልጅነታችን መድረሳ ቁርአን በምንቀራበት ጊዜ ከኢድ አልፈጥርና ከኢደል አድሀ በላይ ለልጆች የምንወደዉ የሚበላበት የሚጠጣበት
መድረሳ መስጂድ ዉስጥ ነሺዳ ፕሮግራም አዘጋጅተን የምንማማርበት በአል የመዉሊድ በአል ነበር...በልጅነታችን ለብዙ አመታት መዉሊድ በአልን በደስታ እናከብር ነበር...እድሜያችን በሰለ ዲነል ኢስላምን ሰዉ ማወቅ ሲያስተነትን ወደ ቁርአን ሀዲስ ስናዳምጥ ለስልጣን ብለዉ ሳይሆን ለአላህ ለዲነል ኢስላም ብለዉ የሚያቀሩ የሚያስተምሩ ዳኢዎች ኡስታዞች መውሊድ ሀራም መሆኑን በማስረጃ በማስደገፍ ሲነግሩን ትክክል ይሄ ቢድአ ነዉ በመዉሊድ ምክንያት ወደ ተለያየ ሀገር እየተሄደ ፈሳድ ዚና ይበዛል ሺርክ ይሰራል ተብሎ በማስረጃ አስተማሩን ሰሚዕና ወአጦዕና ብለን ብዙ ሰዉ መዉሊድን ቤተሰቦቻችን ሳይቀር ማክበር አቆምን አልሀምዱሊላህ

ዛሬስ?? የጎዳና ላይ ኢፍጣር ተብሎ ከመዉሊድ የማይተናነስ ችግር ይዞ መጥቷል፡፡

መቼም አሁን ላይ ስንት አሊም መሻይሆች ባሉበት ሀገር እንደኔ ያለዉ ጃሂል መናገር መፃፍ አቅሜ ባይፈቅድም ግን እያዩ ማለፉ ብዙም አልተዋጠልኝ ይህ ትዉልድ ለወደፊት በረመዳን አንድ ቀን በየአመት የጎዳና ላይ ኢፍጣር ተብሎ በዲን በኢስላም የሌለ ቢድዓ አይታወቅም እኛም ሙተን የሚቀጥል የዉመል ቂያማ ድረስ ሊደርስ ይችላል መቼም ዲነል ኢስላምን አላህ ይጠበቀዋል ግን
ለብዙ አስርት ወይ መቶ አመታት ሊቀጥል ይችላል...
ግን በኛ ዘመን መጀመር አሳፋሪ መሆኑን ልናዉቅ ይገባል

ብዙ ሰዎች የጎዳና ኢፍጣርን በሁለት ምክንያት ይደግፋሉ
➊ የሙስሊሙን አንድነት ለማጠናከር በሚል
➋ የሌላ ሀይማኖት ተከታዮች መንገዱን አደባባዩን እነሱ ብቻ ለምን ይጠቀማሉ እኛም እንጠቀም አይነት ነዉ፡፡

☞ብዙ ሰዎች አንድነትን ለማጠናከር ሲባል የቱ አንድነት?? ሀብሀብ ተምር በመንገድ ላይ ተበልቶ ነዉ እንዴ ስንት አሊም በተለያዩ የዲነል ኢስላም ነገሮች ያልተስማማበትን በጎዳና ኢፍጣር ላይ አንድነት የሚመጣዉ??? ወይስ የአደም ዘር ወንዱም ሴቶም በአደባባይ ሲያፈጥር ነው እንዴ አንድነት የሚባለዉ??
☞ የሌላ ሀይማኖት ተከታዮች መንገዱን አደባባዩን እደተጠቀሙበት ነዉ የሚሉ አሉ...አዎ ይጠቀሙ እኛ ከእነሱ ይሄን መዉረስ የለብንም ...አላህም በቅዱስ ቁርአኑ በዱንያ እንደሚደሰቱ ነግሮናል እንደፈለጉ ይደሰቱ ይጨፍሩበት... ይልቅ እኛ በእነሱ ከምንቀና ስንት ቁርአን ሀፊዞች ዳኢዎችን ኸይር ስራ የሚሰሩን በንከተል ይሻላል እንጂ ሌሎች ሀይማኖት ተከታዮች እግር በእግር መከታተል ትርፉ ቡሀላ ጥፋት ነዉ፡፡

በ2013  የሌላ ሀይማኖቶች ሙስሊሙን ለመጨቆን ትንሽ ተንቀሳቅሰዉ ስለነበር በጎዳና ማፍጠሩን እኛም በሀገራችን ይመለከተናል ኸይር ሆነ ጎዳና ላይ ማፍጠሩ
አምና 2014 ተደገመ በየሀገሩ በአደባባይ ተፈጠረ
ዘንድሮ 2015 ደግሞ ይሄዉ ለሶስተኛ ዙር በአደባባይ ይፈጠራል፡፡ እኔ በ2013 በ2014 አብሬ የዚህ አደባባይ ኢፍጣር ተሳታፊ አጅር ያለዉ ይመስል ስራም ሰርቻለሁ ግን ዘንድሮ በዚህ የጎዳና ኢፍጣር አልሳተፍም፡፡ ለምን አምና የጎንደር ሙስሊሞችን አንርሳ በዚህ የጎዳና ኢፍጣር መዘዝ ብዙ ሙስሊም ወንድም እህት እናት አባቶቻችን ተገለዋል ቆስለዋል የአካል ጉዳተኛ ሁነዋል ንብረታቸወ ተዘርፏል ክብራቸዉ ተነክቷል እናም ዘንድሮ የጎዳና ኢፍጣር በነዛ የጎንደር ሙስሊሞች በሞቱት በተጎዱት ላይ በደል መፈፀም ነዉ፡፡ በዚህ በጎዳና ኢፍጣር ላይ በአይኔ ያየሁት ችግር
☞ወንድና ሴት ይቀላቀል ፊት ለፊትም አብሮ ብዙ ሰዉ ያፈጥራል ከአጂ ነቢይ ጋር
☞በዚህ ጊዜ ሴቶች እንደ በአል አርገዉ ነዉ ከቤት የሚወጡት ኑሮ ተወዶ ለራሱ ያልተዉትን ኮስሞቲክስ
ፌር ተቀብተዉ በቃ ለትዳር ፍለጋ ለመጀናጀን ነዉ የሚወጣዉ 70%ሴቱ
☞ በዚህ ጊዜ ዚናም የሚሰራ ሊኖር ይችላል..ወይም በዚህ ቀን ስልክ የሚቀያየረዉ ብዙ ስለሆነ በትዳር ስበብ የዚና መስመር ሊጀምሩ ይችላሉ
☞በtiktok በfacebook በማህበራዊ ሚዲያ የሴቶች የወንዶች ፎቶ ጥልቅለውጥቅ ብሎ ሚዲያ ሲያጨናንቅ አይተናል ..ሴቱ የሚያደርገዉን የሚይዘዉን የሚጨብጠዉን አጥቶ ነበር ሴትነት ትርጉሙ እስከሚጠፋቸዉ
☞ ጎዳና ኢፍጣሩ ሰዉ ሲበተን በዘንድሮ ዘመናይ ዘፋኞች ይቅርታ ሙነሺዶች ለማለት ነዉ በእነሱ ወንድ ሴት ተደባልቆ ሲጨፍሩ አምና የታዘብነዉ ነዉ..አሁን የአምናዉ የአደባባይ ኢፍጣር video በእጄ አለ ...በጣም አሳፋሪ ነዉ ከምር

የሙስሊም አንድነት የሚባለዉ ወንድ ሴት አብሮ በመንገድ ሲያፈጥር ሲጋፋ ነዉ እንዴ?? ጎበዝ

አሁን ይሄ የጎዳና ላይ ኢፍጣር ከመዉሊድ በምን ተለየ????

ዘንድሮ ስንት ሙስሊም በኑሮ ዉድነት በርሀብ በሚፆሞበት በአገሪቱ ወቅታዊ ችግር ምክንያት ስንቶች ከአገራቸዉ ከመኖሪያቸዉ ተፈናቅለዉ መጠለያ ዉስጥ የሚበላ የሚጠጣ ከእርዳታ ብቻ እየተቀበሉ ረመዳን በሚያሳልፉበት ጊዜ እነሱን መርዳት ሲገባን እንዴት በዚህ አደባባይ ኢፍጣር ሰዉ ጠግቦ ላይበላ ፈሳድ ወንጀል ይሰራል???

የሚገርመዉ አምና ለጎዳና ኢፍጣሩ ላይ የአህባሽ አመለካከትን የሚያራምዱ አቂዳ ተከታዮች በብዛት መጥተዉ አይቻቸዋለሁ...አህባሾች ለደአዋ ለዲነል ኢስላም ለመመካከር ሲጠሯቸዉ አይመጡም ነገር ግን ለእዚህ ለጎዳና ኢፍጣር መጡ እነሱ የተሻለ ኸይር ነገር የሚሰራ ቢሆን እንደማይመጡ እርግጥ ነዉ ግን ኢፍጣሩ ሲያበቃ ለብቻቸዉ ሁነዉ በራሳቸዉ አመለካከት አቂዳቸዉን በነሽዳ ወንድና ሴት ተደባልቀዉ  ሲያስተላልፉ ነበር ...ለደአዋ ለኢስላም እንወያይ ሲሏቸዉ የማይመጡ እንዴት ለአደባባይ ኢፍጣሩ መጡ???
አንዳንዶች አይታወቅም አዲስ አበባ ከአፍሪካ ወይ ከአለም አንደኛ አደባባይ ኢፍጣር ክብረ ወሰን ለመበጠስ ልትሉ ትችላለሁ እሺ እንደ ተልካሻ ዲነል ኢስላም የማያቀዉ የሚያሳምን የሚመስል መልስ ልታመጡ ትችላላችሁ ግን በአደባባይ ኢፍጣር ነዉ ወይስ በቁርአን ሀፊዞች ቁጥር ብዛት በተዉሂድ ክብረ ወሰን በጠስን ተብሎ ቢወራ አይሻልም???
እሺ አዲስ አበባ እንደዚህ ከተባለ ሌሎች ከተማ ለምን ምክንያት ማድረግ አስፈለገ???
ከምር ግን ሊታሰብበት ይገባል...እኛ ለልጃቻችን ለትዉልድ ይሄን ማዉረስ የለብንም....የኛ ልጆች የልጅ ልጆች ይሄ የአደባባይ ኢፍጣር በነብዩ ሰዐወ በሱሀቦች በአራቱ ኸሊፋ ጊዜ የሌለ መቼ ተጀመረ ሲባል በኛ ዘመን በእኛ ትዉልድ ነዉ ብሎ መነገሩ ታሪክ ላይ መፃፉ አግባብ አይደለም


መዉሊድን ሀራም ነዉ ለማለት ስንት ኡስታዞች ኡለሞች መዉሊድ በዚህ ዘመን የተጀመረ ነዉ ብለዉ እንዳላስተማሩ ዛሬ ገና በ2013 የተጀመረን አንድነት የሚመስል ፈሳድ ለምን መከልከል ተሳናቸዉ???
የዚህ በጎዳና ኢፍጣር ሰበብ የሚፈጠር ወንጀል ማዕሲያ እስከ ቆየበት ዘመን ድረስ የኛ አስተዋፆኦ እንዳለበት ለትዉልድ መጥፎ ነገር እንዳላስተላለፍን ልናወቅ ይገባል


አሁን ላይ አሊሞች መሻይሆች የመስጊድ ኢማሞች  አሊሞችም መሻይሆችን ስልጣንን ላለማጣት ፍራቻ
የመስጊድ ኢማሞችም ይቺኑ የወር ደመወዛቸዉን ላለማጣት ፍርቻ ቢድአ ወንጀል መሆኑን እያወቁ ዝም ብለዋል የሚከለክል ስለሌለ ይሄን ፁሁፍ ያነበበ ሰዉ ቁርአን ሀዲስ አንፃር አስበን ህሊናችንን ዳኛ አድርገን
እኛ ባለመሄድ የዚህ ለወደፊት ብዙ አመታት የሚቀጥል እንደ መዉሊድ ቢድአ የሆነን የዚህ የአደባባይ ኢፍጣር ባንሄድ ጥሩ ነዉ፡፡
ደግሞ ይሄን የሚያካሂደዉ 90% ወጣቱ ነዉ
955 views16:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 19:06:40 https://www.youtube.com/live/jbpLKx75JqM?feature=share
745 views16:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 11:14:14 https://www.youtube.com/live/we-LbK8v3Ak?feature=share
165 views08:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-30 11:33:05 https://www.youtube.com/live/Oi02DzpuUM4?feature=share
563 views08:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-29 20:07:00 https://www.youtube.com/live/KJ3vWPsBCIc?feature=share
575 views17:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ